ቶጫ ሙሉወንጌል አጥቢያ ቤተ ክርሰትያን

ቶጫ ሙሉወንጌል አጥቢያ ቤተ ክርሰትያን PREACH GOSPEL
ይህንን የወንጌል አገልግሎት በገንዘባችሁ መደገፍ የምትፈልጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቶጫ ቅርንጫፍ አካውንት ቀጥር 1000193287151

12/07/2026

“አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ።”
— 1ኛ ሳሙኤል 2፥3

03/04/2026
ቶጫ ያላችሁ በፍጹም እንዳያመልጣችሁ።
26/03/2026

ቶጫ ያላችሁ በፍጹም እንዳያመልጣችሁ።

 "አብርሃም ሆይ! ይስሐቅን በወለድክ ጊዜ በረከትን አገኘህ፤ ነገር ግን ይስሐቅ በልብህ ላይ ከነገሠ፣ አንተ ለፈጣሪ መስዋዕት መሆንህን ትተህ ለበረከትህ ባሪያ ትሆናለህ። ሰውን እግዚአብሔርን...
22/02/2026



"አብርሃም ሆይ! ይስሐቅን በወለድክ ጊዜ በረከትን አገኘህ፤ ነገር ግን ይስሐቅ በልብህ ላይ ከነገሠ፣ አንተ ለፈጣሪ መስዋዕት መሆንህን ትተህ ለበረከትህ ባሪያ ትሆናለህ። ሰውን እግዚአብሔርን እንዳያገለግል የሚያደርገው ሰይጣን ብቻ አይደለም፤ በአግባቡ ያልያዝነው 'በረከታችንም' ጭምር ነው!"

​እውነተኛ መንፈሳዊነት ስጦታዎቻችንን (ይስሐቆቻችንን) ለእግዚአብሔር መሠዊያ አድርገን እንድንሰጥ እንጂ፣ ስጦታዎቻችን እኛን አስረው ጌታን በትጋት ከመፈለግ እና እርሱን ከማገልገል እንዲያደርጉን መፍቀድ የለብንም። ብዙ ጊዜ ሰውን ከፈጣሪው የሚለየው ችግር ሳይሆን በረከት ነው። በችግር ጊዜ ወደ አምላክ እንጮኻለን፤ በበረከት ጊዜ ግን በረከቱ እኛን አስተኝቶን (አጋድሞን) አምላካችንን እንድንረሳ ያደርገናል።

እውነተኛው መሠዊያ ያለው ልብህ ላይ ነው። በረከትህን (ይስሐቅህን) በመሠዊያው ላይ ካላስቀመጥከው፣ በረከትህ አንተን መሠዊያው ላይ ያጋድምሃል።

Christ Followers የክርስቶስ ተከታዮች

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ለአንድ ወር የሚቆይ ሀገር አቀፍ የጾም እና ጸሎት አወጀችየኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ መሪዎች ዛሬ የካቲት 12 ቀን ...
20/02/2026

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ለአንድ ወር የሚቆይ ሀገር አቀፍ የጾም እና ጸሎት አወጀች

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ መሪዎች ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በመላው ዓለም የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ አማኞች የሚሳተፉበት ለአንድ ወር የሚቆይ የጾም እና ጸሎት አዋጅ ይፋ አድርገዋል።

መግለጫውን የሰጡት አመራሮች፦

የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት መጋቢ ላኮ በዳሶ
ምክትል ፕሬዚዳንት መጋቢ ለወየው ስንሻው
የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ ተመስገን አዋኖ
የሥራ አመራር ቦርድ ጸሐፊ መጋቢ የኋላሸት ቡኩሉ

የጸሎቱ ዝርዝር መረጃ፦

1. መርሐ-ግብሩ ከየካቲት 30 እስከ ሚያዝያ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ አንድ ወር ይቆያል።

2. ዓላማው ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ እና ስለ ሀገር ሰላም የሚጸለይበት ሲሆን፤

*የንስሐ፣
* የምስጋና እና
* የምልጃ ጸሎቶችን ያካተተ ነው።

3. በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የሚገኙ መሪዎች፣ አገልጋዮችና ምዕመናን በሙሉ በጋራ በጸሎት እንዲተጉ ጥሪ ቀርቧል።

የሥራ አመራር ቦርድ ጸሐፊ ፓስተር የኋላሸት ቡኩሉ እንደገለጹት፣ ለጸሎቱ አጋዥ የሚሆኑ ሳምንታዊ የጸሎት ርዕሶች በቤተ ክርስቲያኒቱ ይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ በየጊዜው የሚለቀቁ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን The Ethiopian Full Gospel Believers' Church

27/01/2026

ኢየሱስ ይመጣል!

Endereço

Tocha

Notificações

Seja o primeiro a receber as novidades e deixe-nos enviar-lhe um email quando ቶጫ ሙሉወንጌል አጥቢያ ቤተ ክርሰትያን publica notícias e promoções. O seu endereço de email não será utilizado para qualquer outro propósito, e pode cancelar a subscrição a qualquer momento.

Entre Em Contato Com O Local De Adoração

Envie uma mensagem para ቶጫ ሙሉወንጌል አጥቢያ ቤተ ክርሰትያን:

Atalhos

Compartilhar

Categoria