14/10/2025
ህዝባችን የመረዳዳት ዕሴትን እያጎለበተ ይገኛል።
፡ ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም ሰሞኑን በማህበራዊ ገፃችን በለጠፍነው የእርዳታ ጥሪ መሠረት ህዝባችን የመረዳዳት ዕሴትን እያጎለበተ ይገኛል።
ታዳጊ ኢያሱ ጌቱ ባጋጠመው የልብ ህመም ምክንያት እናቱ ወ/ሮ አማረች ማሞ አሊ ያለ አባት ያሳደግኩት ልጄ በልብ ህመም ህይወቱ ሊያልፍብኝ ነውና እርዱኝ የሚል ወገናዊ ጥሪ ማስተላለፉን ተከትሎ ደጋግ ልብ ያላቸው ሰዎች ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።
በዚህም መሠረት የተለያዩ ዞናዊ ልማቶችን በመደገፍ እና በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ የሚታወቁት ወንድማችን ኢንጂነር መላኩ አርጋሞ ከአዲስ አበባ 30,000.00 ብር በመለገስ ከፈጣሪ እገዛ ጋር ተባብረን ይህንን ታዳጊ እናድነው የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳኜ ሂዶ፣ የዞኑ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ኡሜ ቸኮልን ጨምሮ በሶስቱም መዋቅር የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች የተጣበበ የስራ ጊዜያቸውን ሰውተው በየጊዜው ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።
ከአመራሮቹ በተጨማሪም በቡርጂ እና ከቡርጂ ውጪ የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለእርዳታ እጃቸውን እየዘረጉ የወገን አለኝታነታቸውን በተግባር እያሳዩ ነው።
ህዝባችን ከዚህ በፊት በተባባረ አንድነትና ፍቅር ገንዘቡን፣ ጊዜውን ሰጥቶ ፀሎት እና ዱኣ በማድረግ የብዙ ሰዎችን ህይወት መታደግ የቻለ በለመልካም ዕሴት ኩሩ ህዝብ ነው።
የተቸገሩ ወገኖችን በራስ አቅም እየተረዳዱ የችግር ቀንበራቸውን እየሰበረ የሚገኘው ህዝባችን ይህንን መልካም ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል እያልን እስከ አሁን ድረስ ካለው ላይ እያካፈለ የንፁህ ሰብዓዊነት ተግባር ለፈፀመ ልበ ቀና የህብረተሰብ ክፍል ሁሉ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው።
የተጀመረውን በጎ ሥራ መተባበር ለምትፈልጉ በባለቤቱ በተከፈተው የባንክ አካውንት ቁጥር መደገፍ ትችላላችሁ::
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) 1000080088877 አማረች ማሞ አሊ
የእናቱ ስልክ ቁጥር፡ 0948565550 ወ/ሮ አማረች ማሞ አሊ