Sanctuary Kingdom Community

Sanctuary Kingdom Community this is the place that you get something to chew for your life .

20/11/2024

Blessed is the man whose strength is in thee; in whose heart are the ways of them.
"the happiness and all the blessing is pivot on the journey " when ever we are in the journey it is like moving from one glory to another glory.

18/05/2023

the reformed last days church is in this planet under divine mission .this divine mission fulfilled only by acting and fallowing the upper realm .
king David who was under divine command he fought many battles but one day he starts to be NORMAL as any other kings around him in those days ,he began to count how many soldiers he had to fight the next enemy.he fall down from the ways of the upper realm.no one can fight God's fight by the mind setup of this realm .because he did this count, God stope fighting the enemy and return back to fight king David. when God fight you you will be the reason for what is going to be happen in your family.because of David leadership many died by God.so watch out Leaders !

02/01/2022

አዲስ አመት የተለየ የሚያደርገው የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በተዘጋጀ መልኩ እየተሰራች መሆንዋና በምድር ላይ ነውጦች እየጨመሩ መሄዳቸው ነው ።

በልብዋ እየተሰራችና እየተዘጋጀች የምትሄድ ቤተክርስቲያን ድምጽ አንድና ግዙፍ ነው ያም በሰማይ ያለውን ድምጽ በምድር ላይ ማስተጋባት ነው ።መንፈሱ የሚለውን ሙሽራዋ ታውቀዋለች ፥መንፈሱ ና ሲል ሙሽራውም ና ትላለች ።

በእኛ ዘንድ የምድርን ድምጽ ማስተጋባታችን ቀርቶ የሰማይን ድምጽ ማስተጋባታችን እየጨመረ ይሄዳል

25/04/2019

ሐዋሪያት ወይም ጥበበኞች (ሶፎስ) ናቸው ከእነርሱም አንዳዶቹ ተገድለዋል ።ምንም እንኳን እስከሞት ያህል ብዙ ነገር ቢደርስባቸውም እነርሱ፣ሲሰቀሉ፣ሲገረፉ፣ሲሰደዱ፤ሲገደሉ የዚያን ጊዜ የእግዚአብሄር ጥበብ በስራ ላይ ነበረች ።
ጌታ ሲናገር “የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች።” ብሎዋል ። የስንዴ ፍሬን በጥሩ ሙዚየም ውስጥ በእንክብካቤ በመስተዋት ውስጥ አስቀምጠናት ለብዙ ጊዜ ብንጠብቃት ወደፊት አንድ ወቅት ላይ በእንዲህ አይነት ጊዜ የነበረች ስንዴ ከመባል ውጪ ምንም ሌላ ነገር አይኖራትም እንዲያውም ይህን በማድረጋችን ለስንዴ የተነገረላትን ህይወት እንዳትኖር አድርገናታል።በዘፍጥረት ለስንዴ የተነገረው የትንቢት ቃል ከአንድ ወደ ብዙ እየሄደች ለትውልድ ሁሉ እንድትሆን ነው ለዚህም መሞት አለባት ።ስንዴ ውበትዋ፤ሃይልዋ፤ጉልበትዋ የሚገለጠው ስትሞት ብቻ ነው። ጥበብ በስንዴ ላይ ሲገለጥ በመሞት ነበር የተገለጠው ። ሐዋርያት በእግዚአብሄር ቤት ውስጥ በጊዜ ፣ በጥቅም ሰጪነት ፣ በሥርዓት የመጀመሪያውን ስፍራ እንዲይዙ እግዚአብሄር አድርጓል ስለዚህም እነርሱ አስቀድመው በብዙ መከራ አለፉ እንዲሁም መሞትን በሁሉ አቅጣጫ ሞቱ ።ለራስ ጥቅም፤ለራስ ማንነት ወይም ለእኔነት የሞቱ ናቸው። ሐዋሪያነት በመኖር ማሸነፍ አለ በሚል ህብረተሰብ ውስጥ መሞት የማሸነፊያ መንገድ ነው የሚል ጥበብ የተገለጠበት መድረክ ነው።

04/04/2019

የባቢሎን ጸባይዋ ተሾልቆ ሲታይ አድራሻዋ በጣም ቅርብ ነው።

ዘፍጥ11፡8

1፤ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች።
1. በባቢሎን የተመሰከረለት አንድነት አለ አንድ ቋንቋ አንድ ንግግር ከዚህም የተነሳ የሚሰሩትን የሚከለክላቸው የለም ።ይህን ያለው እግዚአብሄር ነው።አንድነት ምንም እግዚአብሄር ቢመሰክርለት ካልተመረመረ ትልቅ ጥፋትን ያመጣል።

2፤ ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ።
2. ባቢሎን የሜዳ ላይ ኑሮ እንጂ ተራራማ አይደለም ስለዚህም ከእግዚአብሄር የተስፋ ቃል ውጪ የሆነ አኗኗር ያለበት ነው።የእግዚአብሄር የተስፋ ቃል ኑሮ ወደ ተራራማው አገር አወጣችኋለሁ የሚለው ነው።
3. በዚያም ተቀመጡ ፦በባቢሎን እንቅስቃሴ የለም መቀመጥ እንጂ ወደ በለጠ ነገር መዘርጋት የለውም ይህ አይነት ኑሮ የራሱን ሃይማኖት ይፈጥራል።

3፤ እርስ በርሳቸውም። ኑ፥ ጡብ እንሥራ፥ በእሳትም እንተኵሰው ተባባሉ። ጡቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው፤ የምድርም ዝፋት እንደ ጭቃ ሆነችላቸው።
4. ባቢሎን ግንባታ ወይም ቤት የሚሰራው ከአፈር በተገኘ ጡብ ነው ።በድንጋይ አይደለም።ምድራዊና ጊዜያዊነት ያለው እንጂ ዘለቄታዊነት ያለው አይደለም።

4፤ እንዲህም። ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበተንም ስማችንን እናስጠራው አሉ።
5. ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ሰማይ መግቢያ ግንብ ለመስራት የሚሞክር ነው ፤በራስ ጥረት መንፈሳዊውን አለም ሰማይን ለመንተራስ የሚደረግ ፍትጊያ ያለበት ነው።ቤተክርስቲያን ብቻ ናት ራስዋ ወደ ሰማይ የደረሰው።
6. በባቢሎን ግንባታ የሚባልም ነገር አለ ፤ግንባታ ከአንድ ከፍታ ወደሌላ ከፍታ የሚሄድ ነው።
7. የመበታተን የወደፊት እይታ ያለበት ነው።
8. ግንባታው ሁሉ የተያያዘው አንድ ቋንቋና ንግግር ያላቸውን ሰዎች ስም ማስጠሪያ ሃውልት ለማቆም በሚል ትጋት ያለበት ነው።

5፤ እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ።
9. የባቢሎን የግንባታ ይዘት እግዚአብሄርን ለማየት እንዲወርድ ስቦታል።ሆኖም ግን የወረደው ስራውን ለማጥፋትና ለማስተጓጎል ነው።

6፤ እግዚአብሔርም አለ። እነሆ፥ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፥ ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም።
10. የባቢሎንን አንድ ቋንቋና አንድ ወገናዊነት ልቦና ይዘው በመኖራቸው ስራቸው ወደ ፍጻሜ ይገሰግስ ነበር ። እንዲህ አይነቱን ስርአት ያለ እግዚአብሄር ማንም ሊያፈርሰው አይችልም።

7፤ ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።
11. ባቢሎን የተደባለቀ ቋንቋ ሲኖራቸው በዚያ ግራ መጋባት ሰፍሮባቸው ነበር።
12. የባቢሎንን ግንባታ ለማፍረስ እግዚአብሄር “ኑ እንውረድ” ብሎ በዙሃነቱን የተጠቀመበት ስፍራ ነው።

8፤ እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተዉ።
13. ባቢሎን ከክልል ያለፈ ኑሮ እንዲኖሩ ለስደት የተዳረጉ ህዝብ ያሉበት ነው።

9፤ ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፥ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።
14. እግዚአብሄር የባቢሎንን ቋንቋ ደባለቀ ፤እግዚአብሄር ስራቸውን አስተጓጎለ ‘እግዚአብሄር በተነ።

የዚህ አለም ኑሮ የተቃኘው ይህን በሚመስል ባቢሎናዊ አስተዳደር እንደሆነ ጥርጥር የለውም ሆኖም ግን በአትኩረት መጠየቅ የሚገባን ነገር ቢኖር ይህን የሚመስል አይነት ሁኔታ በቤተክርስቲያን ውስጥ የለም ወይ ? የሚለውን ነው መልሱ አለ እንጂ ነው ! ስለሆነም ባቢሎን ኢራቅ ውስጥ ሳይሆን ያለው እኛው ቤት ነው ።ይህን አይነት የባቢሎን ጥምቀት ቤተክርስቲያን ወስዳ ወደ ክርስቶስ ሙላት አትደርስም ስለዚህም አስቀድማ ከባቢሎን ዘዴና ጥበብ መጥራት አለባት።ከሐዋሪያት ጋር አንድ አይነት መንፈስ ካለን በባቢሎን ውድቀት ደስ ይለናል።

“ሰማይ ሆይ፥ ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ፥ በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፥ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና። አንድም ብርቱ መልአክ ትልቅን ወፍጮ የሚመስልን ድንጋይ አንስቶ ወደ ባሕር ወረወረው እንዲህ ሲል። ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ ተገፍታ ትወድቃለች ከእንግዲህም ወዲህ ከቶ አትገኝም።”(ራእይ 18፡20_21)

i walk at the midst of my enemies
23/01/2019

i walk at the midst of my enemies

11/10/2018

Three Characteristics of the Pharisee Spirit:

• v.5: “to be seen of men” – The motivation of the Pharisee spirit is purely carnal. It seeks the praise and recognition of men over God. Its activity is therefore hollow as it purifies only that which can be seen by men (activities) and allows the unseen rubbish to fester. It is an earthly and sensual form of godliness that has no spiritual power (v.1).

• v.2: the trumpet of pride – The Pharisees deliberately drew attention to their good works to receive glory from men. This represents a further distortion of internal motivation and the absence of a pure heart before God.

• v.6 – The Pharisees used to perform their deeds in public for recognition. But God advises us to do ours in private. To “ shut the door” represents the alignment of our hearts with God and to find the Father who is in and responds from the secret place.

Indirizzo

Rome
00126

Sito Web

Notifiche

Lasciando la tua email puoi essere il primo a sapere quando Sanctuary Kingdom Community pubblica notizie e promozioni. Il tuo indirizzo email non verrà utilizzato per nessun altro scopo e potrai annullare l'iscrizione in qualsiasi momento.

Contatta Il Luogo Di Culto

Invia un messaggio a Sanctuary Kingdom Community:

Condividi