Vatican News - Amharic

Vatican News - Amharic የቫቲካን ዜና አማርኛ

21/04/2026

“የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የአፍሪካ ጉብኝት ልባችንን እንድናድስ ጥሪ የሚያቀርብ ነው”

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአራት የአፍሪካ አገራት ውስጥ በማድረግ ላይ ያሉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ለረጅም ጊዜ በቅኝ ግዛት ቀንበር ውስጥ የቆዩ ሕዝቦች ጥንካሬን በማጉላት የበለጠ ፍትሃዊ፣ የወንድማማችነት እና ርህራሄ የተሞላበት የዛሬን እና የነገን ዓለም ለመገንባት የሚጋብዝ መሆኑን የቫቲካን ሬዲዮ አስተባባሪ ማሲሚሊያኖ ሜኒኬቲ በርዕሠ አንቀጽ ላይ ገልጿል።

“ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በአፍሪካ ውስጥ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ዓይኖቻችንን እንድንከፍት እና ልባችንን እንድናድስ የሚጋብዝ እና የሰው ልጅ እውነተኛ መልኩን እንዲያሳይ የሚያሳስብ ነው።

በእነዚህ ቀናት ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ፥ በየከተሞች ጎዳናዎች ላይ እንደሚሰበሰቡ፣ ከግድግዳዎች በስተጀርባ ያረጁ የቆርቆሮ ጣሪያዎች እና ደካማ ሕንፃዎች ያሏቸው ቤቶች የሚታዩ ቢሆንም ነገር ግን የሰዎች ዓይን በደስታ የተሞላ እና ፈገግታ የሚታይበት ሰላምታ ሲለዋወጡ ይታያል።

ብዙ ሰዎች ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን በዓይን ለማየት ለሰዓታት ሲጠባበቁ፣ ፎቶ በማንሳት የማይረሱ ትዝታዎችን ለማስቀረት ሲጥሩ፣ በመዝሙር እና በጭፈራ ባንዲራዎቻቸውን እና ቅርንጫፎችን ሲያወዛውዙ ታይተዋል።

የቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት ብዙውን ጊዜ ችላ የተባሉ ሰዎች ቁስሎችን እና ተስፋዎቻቸውን በማካተት፣ ወደ ኋላ ሳይመለከቱ የወንድማማችነት እና የእውነተኛ ግንኙነቶች ትስስርን ለመገንባት የሚጋብዝ ነው።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ወቅት ያገኟት አፍሪካ አስደናቂ ጠቀሜታ እና ከፍተኛ አቅም እንዳላት የሚያሳይ ሲሆን፥ በሌላ በኩል ዓለም አቀፍ ኃይሎች ይህን አቅሟን ለመገደብ እና ለመቆጣጠር ሲፈልጉ የቅኝ ግዛት ተጽዕኖ ዓይነቶችን በግልጽ እንደሚቀጥሉ፥ የተፈጥሮ ሃብቶቿ እና የእርሻ መሬቶቿ በመርዛማ ንጥረ ነገሮች የሚወድሙባቸው፣ ግጭቶች፣ ክፍፍል እና ሙስና የሚስፋፉባቸው ቦታዎችን ጨምሮ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ ኃይሎች የሃብቶች መሰረቅ የትውልድን የአሁን እና የወደፊት ዕጣ ፈንታን የሚያጠፉ ናቸው።

ነገር ግን የሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐዋርያዊ ጉብኝት በጦርነት እና በዓመፅ በተጎዳ ዓለማችን ውስጥ የእርስ በርስ ግንኙነቶችን በማመቻቸት እርቅን፣ መግባባትን፣ አንድነትን እና ሰላምን የሚያበረታታ እንደሆነ ተመልክቷል።

ቅዱስነታቸው በካሜሩን ጉብኝታቸው ወቅት፥ ከቀሪው የአገሪቱ ክፍል ጋር እንደገና የተገናኘችው የሰሜን ምዕራብ ካሜሩን ከተማ ባሜንዳ፥ ከመገንጠል ቀውስ ጋር ተያይዞ በተከሰተ ሁከት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋል፤ ለሞት ተዳርገዋል፤ መንገዶች በአብዛኛው ከጥቅም ውጭ ሆነዋል፤ አየር ማረፊያው ለስምንት ዓመታት አገልግሎት ሳይሰጥ ቆይቷል። ይህ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ሥፍራው መጓዝ አካላዊ ግንባታን ብቻ ሳይሆን አዲስ ተስፋን ለማምጣት አግዟል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአፍሪካ አኅጉር ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው የአገራትን ልዩ ልዩ እውነታዎችን በማጉላት፥ አፍሪካ አኅጉር ሳትሆን ነገር ግን አንድ አካል ብቻ አድርጎ የማሰብ ዝንባሌን ተቃርነዋል።

እያንዳንዱ ሰው በልዩነት መካከል ያለውን አንድነት እና የእግዚአብሔር ልጅ የሆነበትን ሰብዓዊ የጋራ ክብርን በማመላከት እና የወንጌልን መልዕክት ለሌሎች ለማድረስ የተጠሩ በርካታ የቤተ ክርስቲያኒቱ ድምጾች መኖራቸውን በመግለጽ፥ ይህን በሚገባ ከተጠቀሙበት ተነሳሽነትን የሚያበረታታ እና የበለጠ ፍትሃዊ፣ የወንድማማችነት እና አጋዥ ማኅበረሰቦችን ለመገንባት እንደሚረዳ ተናግረዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ “የጋራ ኃላፊነት እንዲኖር” በማለት በአፍሪካ አኅጉር ሆነው ለመላው ዓለም ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል። እያንዳንዳችን ወደ ሌሎች ዘድን እንድንቀርብ የሚጋብዝ መሠረታዊ ጥያቄን አንስተዋል። እርስ በርስ እንድንገናኝ፣ ይቅር እንድንባባል፣ እንድንደጋገፍ፣ በኅብረት እንድንራመድ እና የወደፊት ሕይወትን ለመገንባት የሚያስችል የጋራ ኃላፊነትን እንድንወስድ ጋብዘውናል። ብዙውን ጊዜ በመከፋፈል፣ በትእቢት እና በማስፈራራት በተገነባ ዓለም ውስጥ እያንዳንዳችን በዕለታዊ ሕይወታችን ውስጥ ቁርጠኝነታችንን በተግባር እንድንገልጽ የሚጋብዘንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥሪ በድጋሚ አቅርበዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው እውነተኛ ሰብዓዊነትን መልሶ ለማገናኘት፣ የሰዎችን ሰብዓዊ ክብር እና ነጻነት በመጠገን፥ ዕድገታቸው እና ብልጽግናቸው የሚረጋግጥበትን መንገድ በመፈለግ፣ የበላይነት እና የቁጥጥር ፍላጎቶችን ለማስቀረት ከፍተኛ ድጋፍ አድርገዋል” ሲል ርዕሠ አንቀጹ ሃተታውን ደምድሟል።

21/04/2026

“የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የአፍሪካ ጉብኝት ልባችንን እንድናድስ ጥሪ የሚያቀርብ ነው!”

18/04/2026

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለጋራ ጥቅም የቆሙ መሪዎችን እንዲያዘጋጅ አሳሰቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፥ በካሜሩን ለማዕከላዊ አፍሪካ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ አባላት ባደረጉት ንግግር፥ ዩኒቨርሲቲዎች ለራሳቸው ማኅበረሰብ እና ለዓለም የጋራ ጥቅም ለመሥራት ኃላፊነትን የሚወስዱ መሪዎችን እና ባለሙያዎችን በማፍራት ረገድ ያላቸውን ሚና አስረድተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በካሜሩን ከሚገኝ የማዕከላዊ አፍሪካ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ አባላት ባደረጉት ንግግር፥ የአካዳሚው ባለስልጣናት ላደረጉላቸው ደማቅ አቀባበል እና ለትምህርት አገልግሎት ላላቸው የማያቋረጥ ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1989 ዓ. ም. በማዕከላዊ አፍሪካ ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት (ACERAC) የተመሠረተው ተቋሙ፥ “ለቤተ ክርስቲያን እና ለአፍሪካ አኅጉር እውነትን በመፈለግ እንዲሁም ፍትህን እና አንድነትን በማስተዋወቅ ብርሃን ሊሆን ይችላል” ብለዋል።

“ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እውነተኛ የሕይወት እና የምርምር ማዕከል በመሆን ተማሪዎችን እና ፕሮፌሰሮችን በእውቀት ላይ ከተመሠረተ ወንድማማችነት ጋር ለማስተዋወቅ አስፈላጊ ነው” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።

“የወንጌል እና የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዎች ለዓለም አቀፍ የሰው ልጅ ንቃተ ህሊና ዕድገት አስተዋጽኦ ከሚያደርጉት ጋር በመተባበር የእርስ በርስ ግንኙነት ባሕልን ለማበረታታት የታሰበ ነው” ሲሉ አስረድተዋል።

እውነትን ቀዳሚ የዩኒቨርሲቲ ተልዕኮ ማድረግ
“ዩኒቨርሲቲዎች በዛሬው ዓለም ውስጥ ጠቃሚ እና ማዕከላዊ ሚና አላቸው” ያሉት ቅዱስነታቸው፥ ብዙዎች መንፈሳዊ እና ሥነ-ምግባራዊ እሴቶቻቸውን እያጡ ባሉበት እና እራሳቸውን በግለኝነት እና በግብዝነት መደዳ እያስቀመጡ ባሉበት ዩኒቨርሲቲዎች ልዩ የወዳጅነት፣ የትብብር እና የውስጥ አስተንትኖ ቦታዎች በመሆን ጎልተው ይታያሉ” ሲሉ አስረድተዋል።

ከገንዘብ ወይም ከተፈጠሮ ሃብት በላይ ነው
“የአንድ አገር ሃብት በተፈጥሮ እና ቁሳዊ ሃብት ብዛት ብቻ መመዘን የለበትም” ያሉት ቅዱስነታቸው፥ “በእውነት ውስጥ በተመሠረተ ቅን ሕሊና ላይ ካልሆነ በስተቀር የትኛውም ማኅበረሰብ ሊያድግ እንደማይችል ገልጸው፥ “ለእውነት እና ለፍትህ አገልግሎት” የሚለው የመካከለኛው አፍሪካ ካቶሊካዊ ዩኒቨርሲቲ ጭብጥ የሰው ልጅ ሕሊና የእያንዳንዱ ማኅበረሰብ ፍትሃዊ እና የተረጋጋ መሠረት የሚጣልበት መሬት መሆኑን እንደሚያስታውስ አስረድተዋል።

አዳዲስ ነገሮችን መፍራት አይገባም
በዓለማችን ዙሪያ በአንድ ወቅት የማኅበራዊ ሕይወት መሪ የነበሩ የሞራል እሴቶች እየጠፉ መምጣታቸውን ያስታወሱት ቅዱስነታቸው፥ ተቀባይነት እንደሌላቸው ተደርገው ይታዩ የነበሩ አንዳንድ ልምዶችን ማጽደቅ የተለመደ እየሆነ መምጣቱን እና ለዚህ ለውጥ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች እንዲሁም የፖለቲካ ኃይሎች አስተዋጽኦ አድርገዋል” ሲሉ አስረድተዋል።

ይሁን እንጂ ክርስቲያኖች በተለይም የአፍሪካ ካቶሊካዊ ወጣቶች ከፊታቸው የሚመጡ አዳዲስ ክስተቶችን መፍራት እንደሌለባቸው በማሳሰብ፥ ዩኒቨርሲቲው በዲጂታል አብዮት አውድ ውስጥ አዲስ ሰብዓዊነትን መፍጠር እንደሚችል አስገንዝበዋል።

ብዙዎች የማያቋርጥ ፍለጋ በማድረግ የአፍሪካን ማራኪ የተፈጥሮ ሃብት ለማየት ፊታቸውን ወደ አህጉሪቱ በማዞር የሚያደርሱትን አካባቢያዊ እና ማኅበራዊ ውድመቶችን ቅዱስነታቸው ግልጽ በማድረግ፥ ይህም ለእውነት እና ለመላው የሰው ልጅ አገልግሎት በመሆኑ የአኅጉሪቱ ነዋሪዎች የተፈጥሮ ሃብቶቻቸውን ከቅርምት እንዲያተርፉ አሳስበው፥ “ይህ ጠንካራ ትምህርታዊ ጥረት ካለመኖሩ የተነሳ ልዩ ልዩ የብዝበዛ መንገዶችን መላመድ እንደ አዕምሮ ብቃት ማነስ እና የዕድገት ነፃነት ማጣት ተደርጎ ይወሰዳል” ብለዋል።

በባዶነት ከመኖር መቆጠቡ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፥ “የሰው ሠራሽ አስተውሎት ግንኙነቶችን ወደ ተግባራዊ መስተጋብሮች ሊለውጣቸው ይችላል” ብለው፥ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ እውነተኛ ስብዕና ያለው መሆኑን በማስታወስ፥ “ልዩ በሆኑ ሰዎች መመራት ሲጀምሩ ባዶነት እንደሚሰማ እና ግጭት፣ ፍርሃት እና ዓመፅ የሚስፋፉበት መንገድም ይህ እንደሆነ አስረድተዋል።

ከቤተ ክርስቲያን ልብ የተገኙ ናቸው
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የዩኒቨርሲቲዎች ዓላማን ለካሜሩናውያን ወጣት ወንዶች እና ሴቶች ሲያብራሩ የስደት ዝንባሌዎችን እንዲቋቋሙ አሳስበው፥ ይልቁንም ከአገራቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያገኙትን እውቀት ዜጎቻቸውን ለመርዳት እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል።

ቅዱስነታቸው የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲን በተመለከተ የቀድሞው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ፥ “ከቤተ ክርስቲያን ልብ የተወለደ ነው” ማለታቸውን በመጥቀስ፥ እንዲሁም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2017 ዓ. ም. ይፋ ባደረጉት “የእውነት ደስታ” የተሰኘ ሐዋርያዊ ሠነዳቸው፥ “ፕሮፌሰሮችም ሆኑ ተማሪዎችም በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የክርስቶስን ወንጌል ለሁሉም የማወጅ ተልዕኮ ተሳታፊ ናቸው” ያሉትንም ጠቅሰዋል።

16/04/2026

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ “በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ ማንም የተረሳ አይደለም” ሲሉ ገለጹ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በካሜሩን በጀመሩት ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በመዲናዋ ያውንዴ የሚገኘውን የንጉል ዛምባ የሕፃናት ማሳደጊያን ጎብኝተዋል። ችግር ያጋጠማቸው ሕጻናት እራሳቸውን እንደ አፍቃሪ የቤተሰብ አካል አድርገው እንዲመለከቱ መክረው፥ በማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ ሠራተኞችን ለእንክብካቤያቸው አመስግነዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ረቡዕ ሚያዝያ 7/2018 ዓ. ም. በካሜሩን በጀመሩት የመጀመሪያ ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው የንጉል ዛምባ የሕፃናት ማሳደጊያ ቤት ልጆችን እና ሠራተኞችን ጎብኝተዋል።

ለሕጻናቱ ባደረጉት የመጀመሪያ ንግግር አብረው በመሆናቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፥ የሕፃናት ማሳደጊያው እውነተኛ መኖሪያ ቤት እንደሆነ ገልጸዋል። ነገር ግን ከሁሉም በላይ እንደ ልጆቹ የሚቀበላቸው እና በፍቅር የሚቀርባቸው እግዚአብሔር መሆኑንም አስታውሰዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በማዕከሉ ውስጥ የቤተሰብነት ስሜት እንዳለ ገልጸው፥ ሕጻናቱ ተመሳሳይ የሕይወት ችግር ልምዶችን እንደሚጋሩ እና በማዕከሉ ውስጥ እውነተኛ ቤተሰብን እንደሚፈጥሩ በመናገር፥ በወንድማማችነት እና በእህትማማችነት መንፈስ በኢየሱስ ክርስቶስ ዙሪያ በአንድነት መሰብሰብባቸው ጥንካሬን እንደሚሰጣቸው እና የሕይወት ችግሮችን አብረው ለመጋፈጥ እንደሚያስችላቸው አክለዋል።

ወላጅን በሞት ማጣት፣ ብቸኝነት እና ጥርጣሬ ብዙ ሕጻናትን ከሚያጋጠሟቸው ተግዳሮቶች መካከል ጥቂቶቹ እንደሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው፥ እነዚህ ልምዶች የወደፊት ሕይወታቸውን መግለጽ እንደሌለባቸው አሳስበው፥ “ከደረሰባችው ቁስል ለበለጠ መልካም ሕይወት እንደተጠሩ፣ እግዚአብሔር ለሚሰቃዩት ቅርብ እንደሆነ እና እያንዳንዳቸውን በግል እንደሚያውቃቸው አስታውሰዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሕፃናት ልዩ እንክብካቤ እና ልዩ ቦታ መስጠቱን የሚገልጸው የቅዱስ ወንጌል ክፍል በማስታወስ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬም በተመሳሳይ አሳቢነት እና ፍቅር እንደሚመለከታቸው አስረድተዋል።

ማንም ሰው ፈጽሞ አልተረሳም!
ኅብረተሰቡ ያለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት ያስታወሱት ቅዱስነታቸው፥ ብዙውን ጊዜ በግዴለሽነት በሚታወቅ ዓለም ውስጥ እንደ ወላጅ አልባ ሕፃናት ማሳደጊያ ያሉ ቦታዎች ሰዎች እርስ በርስ እንዲተባበር የሚገደዱበት መሆናቸውን ተናግረው፥ “በእግዚአብሔር ታላቅ ቤተሰብ ውስጥ ማንም ሰው እንግዳ ወይም የተረሳ አይደለም” ብለዋል።

በማዕከሉ ውስጥ ሕጻናትን የሚንከባከቡ ሠራተኞችን፣ በጎ ፈቃደኞችን እና ገዳማዊያትን ለቁርጠኝነታቸው እና ተነሳሽነታቸው አመስግነው፥ ሥራቸው ተጨባጭ የፍቅር መግለጫ እንደሆነ እና የእግዚአብሔር ምሕረት ያሚገለጽበት መንገድ እንደሆነ በማስረዳት፥ ሥራቸው ቁሳዊ ድጋፍ ማቅረብ ብቻ ሳይሆን አብረዋቸው ሆነው መመሪያን በመስጠት እና በማረጋጋት የወደፊት ተስፋን መስጠት እንደሆነ አስረድተዋል።

ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ማጠቃለያ ከማቴዎስን ወንጌል በመጥቀስ፥ በጣም ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች እንክብካቤ ማድረግ ክርስቶስን ራሱን ማገልገል እንደሆነ ጠቁመዋል፥ በሕፃናት ማሳደጊያው ውስጥ የሚሠሩት ሰዎች ጥረታቸውን በጽናት እንዲቀጥሉ አበረታተዋል።

በመጨረሻም የማዕከሉ ሕጻናትን እና ሠራተኞችን ለእመቤታችን ድንግል ማርያም እንክብካቤ አደራ ሰጥተው፥ በተለይም በችግር ጊዜ እንድትጠብቃቸው እና እንድትደግፋቸው በጸሎት ተማጽነዋል።

ማንም ሰው የተረሳ አይደለም!

15/04/2026

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ “የእግዚአብሔር ልብ በጦርነት፣ በዓመፅ እና በፍትሕ መጓደል ክፉኛ ቆስሏል” ሲሉ ተናገሩ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአልጄሪያ በሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው የአናባ የአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከልን ጎብኝተዋል። በማዕከሉ ውስጥ በተዘጋጀው ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፥ “የእግዚአብሔር ልብ ትሑት እና በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ሰላምን ከሚፈልጉ ሰዎችን ጋር ነው” ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአልጄሪያ ሐዋርያዊ ጉብኝት ሁለተኛ ቀን ቅዱስ አጎስጢኖስ ጳጳስ ሆኖ ያገለገለበትን ጥንታዊቷ የ “አርኪኦሎጂ” ሥፍራ አናባን ከጎበኙ በኋላ በትናንሽ የድሆች እህቶች ማኅበር በሚተዳደረው የ “ማ ማይሰን” የአረጋውያን ማዕከል ውስጥ እንክብካቤ ከሚደረግላቸው በርካታ አረጋውያን ጋር አጭር ቆይታ አድርገዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ለማዕከሉ ነዋሪዎች ባደረጉት አጭር ንግግር፥ “እግዚአብሔር እዚህ ይኖራል” ሲሉ ተናግረው፥ “ፍቅር እና አገልግሎት ባለበት ቦታ ሁሉ እግዚአብሔር ይኖራል” ሲሉ አስረድተዋል።

የማዕከሉ ተጠሪ ሳላህ ቡኬሜልን ለሰላምታ ንግግራቸው አመስግነው በማዕከሉ ውስጥ የሚኖሩ የአልጄሪያ ሙስሊም አረጋውያን ለእርስ በእርስ እና ለሃይማኖታቸው ያላቸው አክብሮት እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በምላሹም፥ ሰዎች በወንድማማችነት አብረው ለመኖር በሚጥሩበት ቦታ ያለውን ተስፋ እግዚአብሔር በእርግጠኝነት እንደሚያውቅ ተናግረዋል።

“የእግዚአብሔር ልብ በጦርነት፣ በዓመፅ፣ በኢ-ፍትሃዊነት እና በውሸት እጅግ ቆስሏል” ያሉት ቅዱስነታቸው፥ በሰማያት ያለው አባታችን ልብ ከጨካኞች እና ከትዕቢተኞች ጋር አይደለም” ብለው፥ ይልቁንስ መንግሥቱን በአገልግሎት ከሚገነቡት ጋር እግዚአብሔር አለ” ሲሉ ተናግረዋል።

“እናንተም በዕለት ተዕለት አገልግሎታችሁ፣ በጓደኝነታችሁ እና በሕይወታችሁ አብራችሁ ለመኖር እንደምትጥሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልብ ዘወትር ከሕጻናት እና ከትሑታን ጋር በመሆን የፍቅር እና የሰላም መንግሥቱን ዕለት ዕለት ይገነባል” ብለዋል።

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከ2008 እስከ 2021 ዓ. ም. ድረስ የቆስጠንጢኖስ-ሂፖን ጳጳስ ሆነው ያገለገሉት እና አሁን ከትናንሽ የድሆች እህቶች ገዳማውያት ጋር የሚኖሩት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፖል ዴስፋርጅስ ለቅዱስነታቸው ሰላምታ አቅርበውላቸዋል።

ሊቀ ጳጳሱ በሰላምታ ንግግራቸው፥ ገዳማውያቱ እና የማዕከሉ ሠራተኞች በእንክብካቤያቸው እና በሃሳባቸው በየቀኑ ተአምራትን እንደሚያደርጉ ገልጸው፥ ከቀላል የእጅ መጨባበጥ ጀምሮ ሰዎችን አንድ ላይ የሚያቀራርቡ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በበኩላቸው፥ ከሊቀ ጳጳስ ዴስፋርጅስ ለተደረገላቸው አቀባበል እና ከአረጋውያኑ ጎን በመሆን ለሚሰጡት ምስክርነት አመስግነው፥ በሉቃ. 10:21 ላይ የተጻፈውን በመጥቀስ፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “የሰማይ እና የምድር ጌታ አባት ሆይ! ይህን ከጥበበኞች እና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግናለሁ” ማለቱን አስታውሰዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በንግግራቸው ማጠቃለያ፥ ከሞተ የተነሳው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምስል በስጦታነት ያቀረቡትን ገዳማውያትን እና የማዕከሉ ነዋሪዎችን ለምስክርነታቸው አመስግነዋቸዋል።

በአልባኒያዊው ሠዓሊ ዮሴፍ ድሮቦኒኩ የተሳለው መንፈሳዊ ምስሉ ከጥንታዊው የባይዛንታይን ባሕል ጋር የተያያዘ ሲሆን በግሪክ ቋንቋ፥ “ሂዱና አሕዛብን ሁሉ ደቀ መዛሙርት አድርጉ” የሚል መልዕክት የተጻፈበት እንደሆነ ተመልክቷል።

ከጥበብ ሥራው ጋር ተያይዞ የተሰጠው ጽሑፍም፥ “የእኔ ማንነት፣ በጎነት እና አገልግሎት በሙሉ ከሞት በተነሳው በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲበራ፥ የሰው ልብ መጽናናትን እና ተስፋን በሚጠብቅበት ቦታ ሁሉ ምሕረቱ እንዲወርድ” የሚል የግብዣ መልዕክት ያለበት መሆኑ ተመልክቷል።

Indirizzo

Vatican News, Pizza Pia
Rome

Notifiche

Lasciando la tua email puoi essere il primo a sapere quando Vatican News - Amharic pubblica notizie e promozioni. Il tuo indirizzo email non verrà utilizzato per nessun altro scopo e potrai annullare l'iscrizione in qualsiasi momento.

Condividi