29/03/2022
✅መፅሀፉ ስንክሳር የመጋቢት ፳ ቀን !!!
🚩መጋቢት 20
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን አሜን አሜን አሜን!!!
✅ሐዋርያ ቅዱስ አልዓዛር፦
✏ከቀናት በፊት ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ አልዓዛር አረፈ ብለን ነበር:: ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ::
✏ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር ተቀበለችው::
"አዳም ወዴት ነህ" ያለ (ዘፍ. 3:10) የአዳም ፈጣሪ "አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት" አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ::
✏ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር! አልዓዛር!" ብሎ አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ እንዲህ ታስተምራለች::
(ዮሐ. 11:1-ፍጻሜው)
✏ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በሁዋላ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ (ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ነውና) : ለ40 ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ : በ74 ዓ/ም አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል::
🚩የጌታችን ቸርነቱ : የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን::
🚩ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፦
1.ቅዱስ አልዓዛር ጻድቅ ሐዋርያ (የጌታ ወዳጅ)
2.ቅድስትና ብጽዕት ሰማዕት አስጠራጦኒቃ (ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱዋ)
3.ቅዱሳን ሰማዕታት (የቅ/አስጠራጦኒቃ ማሕበር)
4.እናታችን ቅድስት ጽጌ-ሥላሴ (ኢትዮዽያዊት)
5.ቅዱስ አስቃራን ሰማዕት
6.አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት
🚩ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
3.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
4.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
5.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
6.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
✅ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
አሜን አሜን አሜን!!!