ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ - Orthodox Tewahido

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ - Orthodox Tewahido Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ - Orthodox Tewahido, Religious Center, Jerusalem.

5ቱ  #ችንካሮች ትርጉማቸውና ያረፉባቸው ቦታዎችሳዶር፦ ረዳት ወይም አዳኝ ማለት ነው።​አላዶር፦ መጠጊያ ወይም ከለላ ማለት ነው።​ዳናት፦ መድኃኒት ወይም ፈውስ ማለት ነው።​አዴራ፦ መታሰቢያ ...
11/04/2026

5ቱ #ችንካሮች ትርጉማቸውና ያረፉባቸው ቦታዎች
ሳዶር፦ ረዳት ወይም አዳኝ ማለት ነው።
​አላዶር፦ መጠጊያ ወይም ከለላ ማለት ነው።
​ዳናት፦ መድኃኒት ወይም ፈውስ ማለት ነው።
​አዴራ፦ መታሰቢያ ወይም ምልክት ማለት ነው።
​ሮዳስ፦ ብርሃን ማለት ነው።

➜ ያረፉባቸው ቦታዎች፤
#ሳዶር፦ በቀኝ እጁ ላይ ያረፈ
#አላዶር፦ በግራ እጁ ላይ ያረፈ
#ዳናት፦ በሁለቱ እግሮቹ (ተደራርበው በተቸነከሩበት) ላይ ያረፈ
#አዴራ፦ በደረቱ ወይም በልብ አካባቢ ያረፈ
#ሮዳስ፦ በጎኑ (በቀኝ ጎኑ) ላይ ያረፈ
አንዱ ስለሁሉ ሞተ።

05/04/2026

➡️ በሕማማት ክርስቲያኖች ምን ያደርጋሉ ሲባል ራሱን ለሰጣቸው ጌታ ራሳቸውን ይሰጣሉ።

➡️ በዐይናቸው በጎ ነገር ብቻ ከመመልከት ውጭ ለሥጋ የሚሆንን ነገር ባለማየት፤ በጆሮ ለሥጋ የሚሆን ነገር ባለመስማት፤

➡️ እግር ወደሥጋዊ ነገር ባለመሄድ፤ አንደበት ሥጋዊ ነገርን ባለመናገር፤

➡️ ለሰውነታችን የሚገባውን ሥጋዊ ጌጥ ባለማብዛት እንዲሁም ሰውነትን መንከባከብ በምቾት ሥፍራ ላይ መኖር፤ ምግብ አጣፍጦ መመገብ፤ ዋዛ ፈዛዛና ጨዋታ እንዲህ አይነቶችን ሁሉ ትቶ ለኛ ብሎ ራሱን ለህማም ለሞት እራሱን አሳልፎ ለሰጠ ጌታ ራሳችን መስጠትን የምናደርግበት የስጦታ ሳምንት ነው።

➡️ የምንሰግድበት፣ የምንጸልይበት፣ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ቀኑን ሙሉ ሲሰግዱ የሚውሉት በኛ ስግደት ኃጢአታችን ይደመሰስልናል ብለን አይደለም ፤የእኛ ሥራ ያፀድቀናል ብለን አይደለም።ይህን የምናደርገው ራሳችን ለመስጠት ነው❗

➡️ ብለህ ነው መውደቅ መነሣትህ ወይ እኔ ትቢያ ልሁንልህ።
✔ ለኔ ብለህ ተደፋህ ወይ እኔ ልደፋልህ።
✔ ለኔ ብለህ ተገረፍክ ወይ እኔ ልገረፍልህ ብለን ራሳችን ለጌታ ፍቅር የምናሳይበት ሳምንት ነው።

➡️ ሁልጊዜም እናሳያለን ግን እለቱን ለማሰብ ነው እንጂ ክርስቲያን ሁልጊዜም ኑሮው ሁሉ በክርስቶስ ፍቅር የታሰረ ነው እንጂ አመቱን ሙሉ እሱን ትተን ለሳምንት የክርስቶስ የምንሆን አይደለንም።ይበልጥ ደግሞ በዓል ወስነን የምናሳይበት የምንገልጥበት ያች ቀን የማትረሳ መሆኗን የምናሳይበት ጊዜ ነው ማለት ነው።

⭕ በተለየ ሁኔታ በዚህ ሳምንት
✔ባልና ሚስት አብረው አይተኙም
✔የጣፈጠ ምግብ አይበላም።
✔ወይን የሚያሰክር ነገርና መሰል ነገሮችን ባለመጠጣት፤
✔ ሥጋዊ ጨዋታወችን ቀልዶችን፤
✔ ዘፈን ጨዋታ ድልቂያ ተድላ ደስታን ባለማድረግ እናስባለን።

⛔ 318ቱ ሊቃውንት በፍትሐ ነገሥት ሲናገሩ በሕማማት የሚደሰት ሰው በትንሣኤ ሊያለቅስ ይገበዋል ይላሉ።

▬ በዚህ ሳምንት ድግስ የለም።ይሄን ሁሉ አስበን ከጌታ ጋር የምንታመምበት ሳምንት ነው።

✔ ከክርስቶስ ጋር የታመመ ሰው ከክርስቶስ ጋር ይነሣልና።

ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ

➜ የ 2018 ዓ.ም    በቅድስተ ቤተክርስቲያናችን አቆጣጠር ጳጉሜ ሦስት ብቻ ሳትሆን  ሌሎችም ርኅወተ ሰማይ የሚውልባቸው ዕለታት አሉን። እነርሱም ቀመራቸውን ከጳጉሜን 3 እየጀመሩ በ365 ...
03/04/2026

➜ የ 2018 ዓ.ም
በቅድስተ ቤተክርስቲያናችን አቆጣጠር ጳጉሜ ሦስት ብቻ ሳትሆን ሌሎችም ርኅወተ ሰማይ የሚውልባቸው ዕለታት አሉን።

እነርሱም ቀመራቸውን ከጳጉሜን 3 እየጀመሩ በ365 (366) ዕለታት ወይም በአንድ ዓመት ዐውደ ፀሐይ ውስጥ በየ52 ዕለታት ልዩነት የሚውሉ ዕለታት ናቸው።

እነዚህ ዕለታት በጥቅል ቀመራዊ አጠራራቸው "ዕለታት ዘርኅወተ ሰማይ" ይባላሉ።
ዕለታቱም ጳጉሜ 3 ፤ ጥቅምት 20 ፤ ታኅሳስ 12 ፤ የካቲት 4 ፤ መጋቢት 26 ፤ ግንቦት 18 እና ሐምሌ 10 ናቸው።

ስለዚህ ነገ ቅዳሜ መጋቢት 26 የ2018 ዓ.ም 4ኛው የሰማይ መከፈት ቀን ነው።
መልካም የፀሎት ዕለት🙏

የምናሴ ጸሎት 🤲
20/03/2026

የምናሴ ጸሎት 🤲

19/03/2026
‹‹መጋቢት 10››  መስቀለ ኢየሱስበዚችህ ቀን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቲያን መስቀል ለዘመናት ተቀብሮ ከኖረበትቦታ የወጣበት ቀን ነው።ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለ...
18/03/2026

‹‹መጋቢት 10›› መስቀለ ኢየሱስ
በዚችህ ቀን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቲያን መስቀል ለዘመናት ተቀብሮ ከኖረበት
ቦታ የወጣበት ቀን ነው።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለም ፈጥሮ በሚደንቅ ጥበቡ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ዓለምን አድኗል።

አዳም በኃጢአት በወደቀበት ጊዜ ከ5500 ዓመት በኋላ ከልጅ ልጄህ ተወልጄ አድንኃለሁ ባለው መሰረት በቤተልሔም ተወለደ።

ከ33 ዘመናትም በኋሏ በቀራንዮ አደባባይ በመስቀል ተሰቅሎ አዳምና ልጆቹን አዳነ።

ይህም ድኅነት የተፈጸመው በመስቀል ላይ ነውና የጌታችን ክቡር ደሙ የፈሰሰበት ቅዱስ ሥጋው የተቆረሰበትን መስቀል እናከብረዋለን።

በመስቀሉ ላይ ለእኛ ሲል ተገርፏል ተተፍቶበታል ሞቷልም፤ ሞትን ድል ነስቶ ግን እኛን አዳነን።

መስከረም 16 ቀን ደገኛዋ እናት እሌኒ ቅድስት ደመራ ደምራ በደመራው ጢስ አማካኝነት የተቀበረበትን ቦታ አገኘች። መስከረም 17 ቁፋሮ ጀመረች ከ 300 ዘመናት በላይ ቆሻሻ እየተጣለበት ታላቅ ተራራ አህሎ ነበርና እነሆ ቁፋሮ ስድስት ወራት ፈጀባቸው መጋቢት 10 በዛሬዋ ቀንም መስቀሉ ወጣ።

ክርስቶስን ብንወድ መስቀሉን ተሸክመን እንከተለው። የአምላካችን በረከትና ረድኤት ይደርብን🙏

“ሥላሴ” የሚለው ቃል “ሠለሰ” ሦስት አደረገ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሦስትነት ማለት ነው፡፡ቅድስት ሥላሴ ስንል ለሥላሴ ቅድስት ብለን እንቀጽላለን፡፡ ቅድስት ሥላሴ ማለት ...
16/03/2026

“ሥላሴ” የሚለው ቃል “ሠለሰ” ሦስት አደረገ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሦስትነት ማለት ነው፡፡

ቅድስት ሥላሴ ስንል ለሥላሴ ቅድስት ብለን እንቀጽላለን፡፡ ቅድስት ሥላሴ ማለት ልዩ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ይህም ሦስት ሲሆኑ አንድ፣ አንድ ሲሆን ሦስት ስለሚሆኑ ልዩ ሦስትነት ተብሏል፡፡ ሥላሴ የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ያለና የሚኖረውን አምላክ ለመግለጽ የተጠቀመው የአንጾኪያው ቅዱስ ቴዎፍሎስ በ169 ዓ.ም ነው፡፡ በኒቅያ ጉባዔም 318ቱ ሊቃውንት አጽንተውታል፡፡ ሊቃውንቱ በቅዱሳት መጻሕፍት የተመሰከረውን የእግዚአብሔርን ፍጹም አንድነትና ልዩ ሦስትነት ለእኛ በሚረዳ ቋንቋ ገለጡት እንጂ አዲስ ትምህርት አላመጡም፡፡ ምስጢረ ሥላሴ ማለት የአንድነት የሦስትነት ምስጢር ማለት ነው፡፡ ምሥጢር መባሉም በእምነት የተገለጠ፣ ያለ እምነትም የማይመረመር ስለሆነ ነው፡፡

ይኸውም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ሲሆኑ በባሕርይ በሕልውና፣ በመለኮት ደግሞ አንድ ናቸው፡፡ እንደዚህ ባለ ድንቅ ነገር አንድ ሲሆኑ ሦስት፣ ሦስት ሲሆኑ አንድ ይባላሉና፣ ይህም ልዩ ሦስትነት ረቂቅ እና በሰው አእምሮ የማይመረመር ስለሆነ ምስጢር ይባላል፡፡ ስለዚህም አንድ አምላክ፣ ሦስቱ አካላት ብለን እናምናለን፡፡ ሥላሴ ሦስት ናቸው ስንል እንደ አብርሃም፣ እንደ ይስሐቅ እንደ ያዕቆብ የተነጣጠለና በክብርም ሆነ በዘመን የሚበላለጥ የሚቀዳደም ማለታችን አይደለም፡፡ ሦስት ሲሆኑ አንድ ናቸው እንጂ፡፡ አንድ ናቸውም ስንል ከሰው ሁሉ ቀዳሚ ሆኖ እንደተፈጠረው እንደ አዳም ሦስትነትን የሚጠቀልል መቀላቀል ማለታችን አይደለም፡፡ አንድ ሲሆኑ ሦስት ናቸው እንጂ እንዲል ቅዳሴ ማርያም፡፡

የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በሰው ምሳሌ ይገለጻል፡፡ ሰው በነፍሱ ሦስትነት አለው፡፡ ይኸውም ልብነት፣ ቃልነት፣ ሕይወትነት ነው፡፡ በልብነቷ አብ፣ በቃልነቷ ወልድ፣ በሕይወትነቷ መንፈስ ቅዱስ ይመስላሉ፡፡ የነፍስ ልብነቷ፣ ቃልነቷን፣ ሕይወትነቷን ከራሷ ታስገኛለችና፡፡ ቃልና ሕይወት ከአንዷ ልብ ስለተገኙ በከዊን ወይም በመሆን ልዩ እንደሆኑ በመናገርም ይለያሉ፡፡ እንዲሁም አብ ወልድን በቃል አምሳል ወለደው፣ መንፈስ ቅዱስንም በእስትንፋስ አንጻር አሰረጸው፡፡ ነፍስ ስትገኝ በሦስትነቷ በአንድ ጊዜ ተገኘች አንዷ ልብነቷ ቀድሞ ቃልነቷና እስትንፋስነቷ በኋላ አልተገኙም፡፡ ሥላሴም አንዱ ከአንዱ ሳይቀድሙ ተገኝተዋልና፡፡ ይህን ምስጢረ ሥላሴ የተረዱ ገዳማውያን አንድነቱንና ሦስትነቱን አምነው ያመልኩታል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

ደብረ ዘይት
15/03/2026

ደብረ ዘይት

መድኃኔዓለም አዳነን በማይሻር ቃሉእህደስ ይበለንደስ ይበለንእልል በሉአዳነን በማይሻር ቃሉ🙏
06/03/2026

መድኃኔዓለም አዳነን በማይሻር ቃሉ
እህ
ደስ ይበለን
ደስ ይበለን
እልል በሉ
አዳነን በማይሻር ቃሉ🙏

06/03/2026

ሰልስቱን ደቂቅ (አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤልን) በእሳት ከመቃጠል ያዳናቸው የራማው መልአክ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እኛን በዚህ ዓለም የኃጢአት፣ የክህደት እና የጥላቻ እሳት ከመቃጠል ያ...
29/10/2025

ሰልስቱን ደቂቅ (አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤልን) በእሳት ከመቃጠል ያዳናቸው የራማው መልአክ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እኛን በዚህ ዓለም የኃጢአት፣ የክህደት እና የጥላቻ እሳት ከመቃጠል ያድነን🙏

የአብሳሪው መልአክ ምልጃ፣ ፀሎትና ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን🙏

Address

Jerusalem

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ - Orthodox Tewahido posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share