ST Mary Debrewerk Maryam Church Dublin Ireland

ST Mary Debrewerk Maryam Church Dublin Ireland Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ST Mary Debrewerk Maryam Church Dublin Ireland, Religious organisation, KIMMAGE MANOR, Whitehall Road, Kimmage, Dublin.

06/09/2026

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሑዱ አምላክ

እንኳን ለወርሐ ጷጉሜ እና ለ2019 ዓም ለዘመነ ቅዱስ ሉቃስ በጤና አደረሳችሁ!!!

በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ መዝ 64 ÷ 11
በደብሊን ደብረ ወርቅ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ዩምትገኙ ምእመናንና ምእመናት እንደምን ሰነበታችሁ ። ድካማችንን ኃጢአታችንን ሳይቆጥር በይቅርታው ለዚህ ያደረሰን ልዑለ ባሕርይ እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ለእርሱ ይሁን። ወደዚህ ዘመን ሲያሸጋግረን እድሜን ሲሰጠን ዘመኑን ለደስታ እድሜን ለንስሐ ነውና እንጠቀምበት። አምላካችን እግዚአብሔር ቢፈቅድ የፊታችን ቅዳሜ በ12 September 2026 በአዲስ ዓመት ማግስት ቅዳሴ ይኖረናል በምስጋና ዘመነ ሉቃስን እንቀበላለን ለበረከት በቤቱ እንድንገናኝ ይሁን።
መልካም ወርሐ ጷጉሜ እና መልካም አዲስ ዓመት

*አድራሻ* :
Kimmage Manor Roman Catholic Church
Dublin 12.

**** Bus route, 15A From Dublin city
Bus stop no station's 1093, ከወረዱ በኋላ ወደ ግራ በመታጥፍ ያገኙታል::
በተክርስቲያናችንን መደገፍም ሆነ ማንኛውም ክፍያ ለማድረግ ለምትፈልጉ ደግሞ በዚህ የ የባንክ ቁጥር መላክ ወይም መክፈል ትችላላችሁ።
ST MARY ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH
AIB BANK IBAN: IE04AIBK93103916028186

*ደብረ ወርቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን::*

18/08/2026

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
​የተወደዳችሁ ክርስቶስ ቤተሰቦች፤ እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የፆመ ፍልሰታ ፍጻሜ እና ለብርሃነ ዕርገቷ፣ እንዲሁም ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚከበረው ለደብረታቦር በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!
​ይህንንም ታላቅ የፍልሰታ በዓል ምክንያት በማድረግ፤ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም (August 22, 2026) የቅዳሴ ፕሮግራም ስለሚኖረን፤ ሁላችሁም በዕለቱ በቤቱ ተገኝታችሁ የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

*አድራሻ* :
Kimmage Manor Roman Catholic Church
Dublin 12.

**** Bus route, 15A From Dublin city
Bus stop no station's 1093, ከወረዱ በኋላ ወደ ግራ በመታጥፍ ያገኙታል::
በተክርስቲያናችንን መደገፍም ሆነ ማንኛውም ክፍያ ለማድረግ ለምትፈልጉ ደግሞ በዚህ የ የባንክ ቁጥር መላክ ወይም መክፈል ትችላላችሁ።
ST MARY ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH
AIB BANK IBAN: IE04AIBK93103916028186

*ደብረ ወርቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን::*

07/08/2026
ፍልሰታ ለማርያም፡ ሰአ(ዐ)ሊ ለነ ቅድስትመ/ር ጌታቸው በቀለበኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዐት መሠረት ሁሉ እንዲጾማቸው መጀመሪያቸውና መጨረሻቸው ተቀምሮ ጊዜና ወቅት ተወስኖላቸው ...
07/08/2026

ፍልሰታ ለማርያም፡ ሰአ(ዐ)ሊ ለነ ቅድስት
መ/ር ጌታቸው በቀለ

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዐት መሠረት ሁሉ እንዲጾማቸው መጀመሪያቸውና መጨረሻቸው ተቀምሮ ጊዜና ወቅት ተወስኖላቸው የተደነገጉ ሰባት የዐዋጅ አጽዋማት አሉ፡፡ እነዚህንም በሐዋርያት ሲጾሙ የቆዩና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በቀኖና ያጸኗቸው ዲድስቅልያና ሌሎች የቀኖና መጻሕፍት ሥርዐታቸውን የሠሩላቸው ናቸው፡፡ ከእነዚህም አንዱ “ጾመ ፍልሰታ ለማርያም” ሲሆን ከሕጻናት እስከ አረጋውያን የሚጾም ታላቅ ጾም ነው፡፡

ፍልሰታ ማለት ምን ማለት ነው?

“ፍልሰታ” የሚለው ቃል ፈለሰ፣ ተሰደደ (ተገለጠ)፣መከፈት፣ መገለጥ፣ የመዝጊያ የመጋረጃ ከሚለው የግእዝ ሥርወ ቃል የተገኘ ሲሆን፤ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ትንሣኤ ይመለከታል፡፡ “ፍልሰት” የሚለው ቃል ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር መሔድን ያመለክታል፡፡ “ፍልሰታ ለማርያም” ሲባልም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ካረፈች በኋላ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መወሰዷን (ማረጓን)፣ በኋላም ሥጋዋ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱን ለማመልከት የሚነገር ነው፡፡

ጾመ ፍልሰታ ለማርያም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፭ ቀን ያለው ሁለት ሱባዔ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ኾኖ በምእመናን ዘንድ መጾም እንደሚገባው ሥርዓት ሠርተውልናል (ፍትሐ ነገሥት አንቀት ፲፭)፡፡ ይህ ጾምም ‹‹ጾመ ማርያም (የማርያም ጾም)›› ወይም ‹‹ጾመ ፍልሰታ ለማርያም (የማርያም የፍልሰቷ ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ በጾሙም መጨረሻ የቅድስት ድንግል ማርያም ትንሣኤ ይከበራል፡፡

የሚነበቡ መጻሕፍት

በጾመ ፍልሰታ በቤተክርስቲያናችን በየቀኑ በማኅሌቱ፣ በሰዓታቱና በቅዳሴው በሚደርሰው ቃለ እግዚአብሔር ነገረ ማርያም ማለትም የእመቤታችን ከመፀነሷ ጀምሮ እስከ ዕርገቷ ድረስ ያለው ታሪኳ፣ ለአምላክ ማደሪያነት መመረጧ፣ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ክብሯ፣ ርኅርራኄዋ፣ ደግነቷ፣ አማላጅነቷ፣ ሰውን ወዳድነቷ በስፋት ይነገራል፡፡ እመቤታችንን ከሚያወድሱ ድርሳናት መካከልም በተለይ ቅዳሴ ማርያም፤ ውዳሴ ማርያምም በስፋት ይጸለያል፤ ይቀደሳል፤ ይተረጐማል፡፡ በሰንበታት የሚዘመሩ መዝሙራት፤ በየዕለቱ በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በእግዚአብሔር ለተዋሕዶ መመረጧን፣ ዘለዓለማዊ ድንግልናዋን፣ ክብሯን፣ ቅድስናዋን፣ ንጽሕናዋን የሚያወሱ ናቸው፡፡ የእመቤታችን ንጽሕና የነገረ ድህነት፣ የጌታችን ቤዛነት መነሻ፣ መሠረት ነውና፡፡

ሱባኤ በጾመ ፍልሰታ

በጾመ ፍልሰታ በርካታ ምእመናን፣ ካህናት እና ገዳማውያን በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው በየገዳማቱና በየአብያተ ክርስቲያናቱ በዓት አዘጋጅተው፣ ሱባኤ ገብተው፣ ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው አስገዝተው ይጾማሉ፤ ይጸልያሉ፡፡ እንደዚሁም ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ይቀበላሉ፡፡ ይህ ጾም ለእመቤታችን ያለንን ፍቅርም የምንገልጽበት ወቅት ነው፡፡ በተለይ ኦርቶዶክሳውያን ሕፃናት በአብዛኛው ትምህርተ ወንጌል የሚማሩት፤ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የሚቀበሉት በዚህ በጾመ ፍልሰታ ነው፡፡ ሁላችንም በጾመ ፍልሰታ ሳምንታት በጌታችን፣ በእመቤታችንና በቅዱሳን ሐዋርያት ስም በቤተ ክርስቲያን ተሰባስበን ቅዱሳት መጻሕፍትን ከመማር ባሻገር ብንጾም፣ ብንጸልይ፣ ብናስቀድስ፤ እንደዚሁም ሥጋውን ደሙን ብንቀበል በበረከት ላይ በረከትን፤ በጸጋ ላይ ጸጋን እናገኛለን፡፡

ሰአ(ዐ)ሊ ለነ ቅድስት

በቤተክርስቲያናችን በጾመ ፍልሰታ በተለየ መልኩ ከሚነበቡ፣ ከሚተረጎሙ ቅዱሳት መጻሕፍት አንዱ “ውዳሴ ማርያም” ነው፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ከደግነቱ የተነሳ እመቤታችን ተገልጣለት ውዳሴ ማርያምን ደርሶ አመስግኗታል፡፡ ምስጋናውም በሰባቱ ዕለታት የተከፈለ ፷፬ ምዕራፎች ያሉት ነው፡፡ ፷፬ መሆኑም እመቤታችን በዚህ ምድር በሥጋ የኖረችበትን ዘመን ያጠይቃል፡፡ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ደግሞ በእያንዳንዱ ምዕራፍ መጨረሻ “ሰአ(ዐ)ሊ ለነ ቅድስት” (ቅድስት ሆይ ለምኝልን) የሚለውን ጨምሮበታል፡፡ ሰዐሊ ለነ ቅድስት ተብሎ በዐይኑ ‘ዐ’ ሲጻፍ አዕምሮውን ለብዎውን (ማስተዋሉን) ሳይብን አሳድሪብን ማለት ነው፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት ተብሎ በአልፋው ‘አ’ ሲጻፍ ለምኝልን ማለት ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቅድስት ቤተክርስቲያን “ሰአ(ዐ)ሊ ለነ ቅድስት” እያለች እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ትለምንልን ዘንድ በጸሎትና በምልጃ ታሳስባለች፡፡

እንደማጠቃለያ

ኦርቶዶክሳውያን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ዕረፍትና ትንሣኤ በማሰብ ከልጇ ከወዳጇ ጸጋና በረከት ለማግኘት በየዓመቱ ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን፤ የምንችል ደግሞ ንስሐ ገብተን አስቀድሰን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን እንቀበላለን፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር “ሥጋዬን የሚበላ፤ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው” በማለት እንደተናገረ በጾመ ፍልሰታ አረጋውያንና ሕፃናት ብቻ ሳይኾኑ፤ መላው ኦርቶዶክሳውያን ንስሐ ገብተን፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን በመቀበል መንግሥቱን ለመውረስ መዘጋጀት ይኖርብናል /ዮሐ. ፮፥፶፬/፡፡


የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣
የቅዱሳን ሐዋርያት ጸጋና በረከት አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ዋቤ መጻሕፍት

✍️ ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ
✍️ ነገረ ማርያም ትርጓሜ
✍️ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ፣
✍️ መልክአ ማርያም

04/08/2026

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

​እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የፆመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ!

​ፆሙ የፊታችን ዓርብ ነሐሴ ፩ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም (August 7, 2026) የሚጀመር ሲሆን፤ እግዚአብሔር አምላክ ቢፈቅድና ቢወድ ቅዳሜ ነሐሴ ፪ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም (August 8, 2026) የ ቅዳሴ ፕሮግራም ስለሚኖረን፣ ሁላችንም በቤተ መቅደሱ ተገኝተን የበረከቱ ተሳታፊዎች ያደርገን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።
​አሜን።

አድራሻ :
Kimmage Manor Roman Catholic Church
Dublin 12.

**** Bus route, 15A From Dublin city
Bus stop no station's 1093, ከወረዱ በኋላ ወደ ግራ በመታጥፍ ያገኙታል::
በተክርስቲያናችንን መደገፍም ሆነ ማንኛውም ክፍያ ለማድረግ ለምትፈልጉ ደግሞ በዚህ የ የባንክ ቁጥር መላክ ወይም መክፈል ትችላላችሁ።
ST MARY ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH
AIB BANK IBAN: IE04AIBK93103916028186

ደብረ ወርቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን::

24/07/2026

የደብሊን ደብረወርቅ ምዕመናንና ምዕመናት እንደምን ሰነበታችሁ
እግዚአብሔር አምላካችን ቢፈቅድ የፊታችን ቅዳሜ July 25/07/2026 ቅዳሴ ስላለን የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ቅድስት ቤተክርስቲያን መልእክቷን ታስተላልፋለች
ለበረከት በቤቱ ይሰብስበን!

*አድራሻ* :
Kimmage Manor Roman Catholic Church
Dublin 12.

**** Bus route, 15A From Dublin city
Bus stop no station's 1093, ከወረዱ በኋላ ወደ ግራ በመታጥፍ ያገኙታል::
በተክርስቲያናችንን መደገፍም ሆነ ማንኛውም ክፍያ ለማድረግ ለምትፈልጉ ደግሞ በዚህ የ የባንክ ቁጥር መላክ ወይም መክፈል ትችላላችሁ።
ST MARY ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH
AIB BANK IBAN: IE04AIBK93103916028186

*ደብረ ወርቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን::*

ቅድስት ሥላሴ በአብርሃም ቤትእንኳን ለቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል (ሐምሌ ፯) በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ !!!በመ/ር ጌታቸው በቀለ አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ አብርሃም ቤት ገብተው አብ...
14/07/2026

ቅድስት ሥላሴ በአብርሃም ቤት
እንኳን ለቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል (ሐምሌ ፯)
በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ !!!

በመ/ር ጌታቸው በቀለ

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ አብርሃም ቤት ገብተው አብርሃምን የባረኩበት፣ በቤቱም የተስተናገዱበት፣ ሣራ ይስሐቅን እንደምትወልድ ያበሠሩበት ዕለት ነው፤ ሐምሌ ፯ ቀን፡፡ ይህ የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ በደማቅ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፡፡ታሪኩን ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት አድርገን እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡

ቅድስት ሥላሴ

ሥላሴ ማለት የግእዝ ቃል ሲሆን ሦስት፤ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ “ሥላሴ” የሚለው ቃል ሠለሰ፤ ሦስት አደረገ› ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲኾን ትርጉሙ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ (፲፱፻፵፰)፡፡ መጽሐፍ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፡፡ ገጽ ፮፻፷፱/፡፡

በምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት እንደምንረዳው ሥላሴ አንድም ሦስትም ናቸው፡፡ ሥላሴ ስንልም አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ማለታችን ነው፡፡ እግዚአብሔር በስም፣ በግብር፣ በአካል ሦስት ናቸው፡፡ የስም ሦስትነት፡- አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡ የግብር ሦስትነት፡- አብ አባት፣ ወልድ ልጅ መንፈስ ቅዱስ ሰራፂ፡፡ የአካል ሦስትነት፡- አብ የራሱ የሆነ ፍጹም ገጽ መልክ አለው፤ ወልድ የራሱ የሆነ ፍጹም ገጽ መልክ አለው፤ መንፈስ ቅዱስ የራሱ የሆነ ፍጹም ገጽ መልክ አለው፡፡ የእግዚአብሔር አንድነት በአገዛዝ፣ በሥልጣን፣ ይህን ዓለም በመፍጠርና በማሳለፍ፣ በህልውና፣በመለኮት በፈቃድ በመሳሰሉት ሁሉ አንድ ነው፡፡ / መ/ር ብርሃኑ ጎበና (፲፱፻፹፭)፡፡ ዓምደ ሃይማኖት፡፡ ገጽ 40/፡፡

ሥላሴ “ቅድስት” ተብለው በሴት አንቀጽ መጠራታቸው ሴት(እናት) ፈጭታ ጋግራ ቤተሰቦቿን እንደምትመግበው ሥላሴም በዝናም አብቅለው በፀሐይ አብስለው ፍጥረቱን ሁሉ ስለሚመግቡ “ቅድስት ሥላሴ” እያልን እንጠራቸዋለን፡፡

ቅድስት ሥላሴ በአብርሃም ቤት

አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የወረደውን፣ የመጣ የሔደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ሰይጣን ለተንኮል አያርፍምና ይህንን መልካም ግብሩን ለማሰናክል አሰበ፡፡ አስቦም አልቀረ፤ የተጐዳ ሰው መስሎ ከጐዳና ቆሞ አብርሃም እንግዳ መቀበል እንደ ተወ፤ እርሱ ሊበላ ሊጠጣ ከቤቱ ቢሔድ ራሱን ፈንክቶ፣ ደሙን አፍሶ፣ አጥንቱን ከስክሶ፣ ልብሱን ገፎ እንደ መለሰው ወደ አብርሃም ቤት ለሚሔዱ ሰዎች ይናገር ጀመር፡፡ በዚህ የተነሣም እንግዳ ወደ አብርሃም ቤት አይመጣም ነበር፡፡

አብርሃምም ማዕደ እግዚአብሔርን ያለ እንግዳ አልመገብም ብሎ ሦስት ቀን ሳይመገብ ጾሙን አደረ፡፡ በሦስተኛው ቀን ይህን ደግነቱን እግዚአብሔር ተመልክቶ በኦሪት ዘፍጥረት ፲፰፥፩-፲፱ ተጽፎ እንደምናገኘው በቀትር ጊዜ አብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በሦስት ሰዎች አምሳል አንድም በሥላሴ (በሦስትነት) በመምሬ አድባር ዛፍ ተገልጦለታል፡፡ አብርሃምም ሦስት ሰዎች ቆመው ባየ ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ወደ እነርሱ ሮጠ፡፡ ወደ ምድርም ሰገደና “አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ኾነ ባርያህን አትለፈኝ?” ብሎ ተማጸነ፡፡ በመቀጠል አብርሃም “ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ፤ እግራችሁን ታጠቡ፤ ከዚህችም ዛፍ በታች ዕረፉ፡፡ ቍራሽ እንጀራም ላምጣላችሁ፤ ልባችሁንም ደግፉ፡፡ ከዚያም በኋላ ትሔዳላችሁ፡፡ ስለዚህ ወደ ባርያችሁ መጥታችኋልና” ሲላቸው እነርሱም “እንዳልህ አድርግ” ብለውታል (ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ፣ ፬፥፴፪)፡፡ የኦሪት ዘፍጥረት አንድምታ ትርጓሜ እንደሚያስረዳው አብርሃም ሥላሴን “ጌቶቼ ከቤት ገብታችሁ ዕረፉ” ሲላቸው “ደክሞናልና አዝለህ አስገባን” አሉት፡፡ እርሱም እሺ ብሎ አንዱን አዝሎ ቢገባ ሁለቱ በግብር አምላካዊ (በአምላካዊ ጥበብ) ከቤቱ ገቡ፡፡

አብርሃምም ወደ ሣራ ዘንድ ፈጥኖ ሔደና “ሦስት መሥፈሪያ ዱቄት ፈጥነሽ አዘጋጂ፤ ለውሺውም፤ እንጎቻም አድርጊ” አላት፤ እርሷም እንዳዘዛት አደረገች፡፡ አብርሃምም ወይፈን አርዶ አወራርዶ አዘገጅቶላቸው ተመግበዋል፡፡ ከዚያም የታረደውና የተወራረደውም ወይፈንም ተነሥቶ በድንኳኑ ደጃፍ “ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ፤ ለአብ ምስጋና ይገባል፤ ለወልድ ምስጋና ይገባል፤ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል” ብሎ እግዚአብሔርን አመስገኗል፡፡

ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ጠርቶ ‹‹ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት?›› አለው፡፡ አብርሃምም ከድንኳኑ ውስጥ እንዳለች ነገረው፡፡ እግዚአብሔርም ‹‹የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለሁ፤ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች›› ብሎ ለአብርሃም አበሠረው፡፡ ሣራ ይህንን ቃል በሰማች ጊዜ ባለቤቷም አርጅቶ፤ እርሷም የሴቶች ግዳጅ ትቷት ነበርና መውለዷን በመጠራጠሯ ሳቀች፡፡ እግዚአብሔርም ምሥጢሩን በአጽንዖት ለማስረዳትና አስረግጦ ለመንገር አብርሃምን ‹‹ሣራ ለምን ትስቃለች? በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን?›› አለው፡፡ ሣራም ስለፈራች ‹‹አልሳቅሁም›› አለች፡፡ እግዚአብሔርም መሳቋን እንዳወቀባት ከነገራት በኋላ በድጋሜ በዓመቱ ወደ አብርሃም ቤት እንደሚመጣና ሣራ ወንድ ልጅ (ይስሐቅን) እንደምትወልድ አብሥሯቸዋል፡፡ ከዚህ ትምህርት ብዙ ነገሮች እንማራለን፡፡ ለአብነትም ያህል የተወሰኑትን እንመልከት፡-

አንድነትና ሦስትነት

“በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ኾነ ባሪያህን አትለፈኝ?” የሚለው ኃይለ ቃል አንድነቱን፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ ብሎ ሦስትነታቸውን ምሥጢር ይገልጻል፡፡ ሣራ ዳቦ ያዘጋጀችበት ሦስቱ መሥፈሪያ የሦስትነቱ፤ ዳቦው አንድ መኾኑ ደግሞ የአንድነቱ ምሳሌ ነው፡፡ ሥላሴ አብርሃም ያዘጋጀውን እንስሳ ተመገቡ ተብሎ መነገሩም በሰው አምሳል ስለ ተገለጡና ለአብርሃም የበሉ መስለው ስለ ታዩት ነው እንጂ ለሥላሴ መብል መጠጥ አይስማማቸውም (አይነገርላቸውም)፡፡ ከዚህ በተለየ ምሥጢር ሥላሴ “ሣራ ለምን ትስቃለች? በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን?” ብለው ከጠየቁበት ኃይለ ቃል መካከል “ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን?” የሚለውን እመቤታችንን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እንደምትወልድ ሲያበሥራት ‹‹ወንድ ሳላውቅ ይህ እንዴት ሊኾን ይችላል?›› /ሉቃ. ፩፥፴፯/ ብላ በጠየቀችው ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ደግሞ መናገሩ የእግዚአብሔር ቃል በዘመን ብዛት የማይለወጥ ሕያውና እውነተኛ መኾኑን ያጠይቃል፡፡

የአብርሃም ድንኳን

“በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት፡፡ ዐይኑንም አነሣና እነሆ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፡፡ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፡፡ ወደ ምድርም ሰገደ፡፡ እንዲህም አለ አቤቱ በፊትህስ ሞገስን አግኝቼ እንደሆነ ባርያህን አትለፈኝ” /ዘፍ.፲፰፥፲፭/፡፡

አብርሃም በዚህ ምድር ቤት አልነበረውም፤ የሚኖረው በድንኳን ነበርና በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ ሥላሴ በሰው አምሳል ተገለጡለት፡፡ በግንባሩ ተደፍቶ የአምልኮት ስግደት ሰገደላቸው፤ በአክብሮትም ተቀበላቸው፡፡ ወደ ድንኳኑ እንዲገቡም ተማጸናቸው፡፡ አስተናገዳቸውም፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህች የአብርሃም ድንኳን ትመሰላለች፤ ምክንያቱም ሥሉስ ቅዱስ በማኅፀኗ አድረዋልና ስለዚህ ማኅደረ ሥሉስ ቅዱስ ትባላለች፡፡ ሥላሴን በማኅፀኗ ተቀብላ በትሕትና አስተናግዳለችና፡፡ አብ አጸናት፣ ወልድ ተፀነሰባት፣ መንፈስ ቅዱስ ጋረዳት፡፡/ወላዲተ አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ፤ ገጽ 30/፡፡

በአብርሃም ድንኳን አላፊ አግዳሚው ይመግብበት፣ ያርፍበት እንደ ነበረ ዅሉ በእመቤታችንም አማላጅነትም መንገደኞች ማረፍያ፤ እንግዶች መጠለያ፤ ስደተኞች ተስፋ ያገኛሉና፡፡ ከዅሉም በላይ የነፈስ የሥጋ መድኀኒት፤ የዘለዓለም ማረፍያ፤ እውነተኛ መብልና መጠጥ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የወለደች እርሷ ናትና በአብርሃም ድንኳን ትመሰላለች፡፡ ቀትር በኾነ ጊዜ ማለትም በስድስት ሰዓት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደ ገቡ ሁሉ፣ አምስት ሺሕ አምስት መቶው ዓመት ተፈጽሞ በስድስተኛው ሺሕ ዓመት እግዚአብሔር አብ ለአጽንዖ፤ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፤ እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋን ለመልበስ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አድረዋልና እመቤታችን በአብርሃም ድንኳን ትመሰላለች፡፡

እንደ ማጠቃለያ

ሐምሌ ፯ ቀን እግዚአብሔር አምላክ በአብርሃም ቤት ተገኝቶ አብርሃምና ሣራ ካረጁ በኋላ ልጅ እንደሚወልዱ የተበሰረበት፤ ይስሐቅንም እንደሚወልድ የተነገረበት ዕለት ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ሰው መኾን የተናገረበት ዕለት ከመኾኑ ሌላ የአብርሃምን ዘሩን እንደሚያበዛለትና አሕዛብ ሁሉ በእርሱ እንደሚከብሩ ማለትም ከአብርሃም ዘር በተገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ አሕዛብ እንደሚቀደሱ፤ ይህንን ምሥጢርም እግዚአብሔር ከወዳጁ ከአብርሃም እንደማይሠውር ቃል ኪዳን የገባበት ቀን ነው፡፡

በዓላት የሰው ልጅ በእግዚአብሔር የተደረገለትን የቸርነት ሥራ በማሰብ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት ያደረጉትን ተጋድሎና ተአምራት በመስማትና በማሰማት የተደረገውን ድንቅ ነገር በመዘከር በደስታ የሚከበሩ ዕለታት ናቸው፡፡ “በቃለ አሜን ወበትፍስሕት ድምፁ እለ ይገብሩ በዓለ፡- በዓለ የሚያደርጉ ሰዎች የደስታና የምስጋና ቃል አለው” እንዳለ ቅዱስ ዳዊት /መዝ.፵፩፥፭/፡፡

ዛሬም ሀብት ንብረት ያለን ምእመናን በትሩፋት ሥራ በመሠማራት እንግዶችን በመቀበል፣ ለተራቡ በማብላት፣ በመመጽወት እና በመሳሰለው ተግባር ከኖርን ለተቸገሩ በመራራት፣ በቀና አስተሳሰብ ከተጓዝን እግዚአብሔር ይባርከናል፤ ይቀድሰናል፡፡ ሐምሌ ፯ ቀንም ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተው ቸርነታቸውና ፍቅራቸውን የገለጹበት፣ አብርሃምን የባረኩትና ልጅ እንደሚወልድ፣ መጻዒው ሕይወቱን የነገሩት ዕለት ስለሆነ በዓሉን ስናዘክር ሥላሴን እናመሰግናለን፡፡ ቸርነታቸው፣ ፍቅራቸው እንዳይለየን እንማጸናለን፡፡

የቅድስት ሥላሴ ቸርነት አይለየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

ዋቤ መጻሕፍት
✍️ መጽሐፍ ቅዱስ
✍️ ቅዳሴ ማርያም
✍️ መጽሐፍ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ
✍️ ዓምደ ሃይማኖት
✍️ ወላዲተ አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ
✍️ መለከት መጽሔት

07/07/2026

የደብሊን ደብረወርቅ ምዕመናንና ምዕመናት እንደምን ሰነበታችሁ እንኳን ለ 2018 ዖመ ሐዋርያት የፍዓሜ ቀንና ለቅዱስ ጼጥሮስ ጳውሎስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

እግዚአብሔር አምላካችን ቢፈቅድ ቅዳሜ July 11/07/2026 ቅዳሴ ስላለን የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ቅድስት ቤተክርስቲያን መልእክቷን ታስተላልፋለች
ለበረከት በቤቱ ይሰብስበን!

*አድራሻ* :
Kimmage Manor Roman Catholic Church
Dublin 12.

**** Bus route, 15A From Dublin city
Bus stop no station's 1093, ከወረዱ በኋላ ወደ ግራ በመታጥፍ ያገኙታል::
በተክርስቲያናችንን መደገፍም ሆነ ማንኛውም ክፍያ ለማድረግ ለምትፈልጉ ደግሞ በዚህ የ የባንክ ቁጥር መላክ ወይም መክፈል ትችላላችሁ።
ST MARY ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH
AIB BANK IBAN: IE04AIBK93103916028186

*ደብረ ወርቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን::*

Address

KIMMAGE MANOR, Whitehall Road, Kimmage
Dublin
D12WP44

Telephone

+353894246159

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ST Mary Debrewerk Maryam Church Dublin Ireland posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ST Mary Debrewerk Maryam Church Dublin Ireland:

Shortcuts

Share