Batu Yehiwot Birhan Church -Ziway

Batu Yehiwot Birhan Church -Ziway Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Batu Yehiwot Birhan Church -Ziway, Religious Center, Batu.

12/09/2024

“እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፤ በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህም ይገዙልሃል፤ አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።”
— ዘዳግም 33፥29.
በ2017 የጠላቶችህን/ሽን ደጅ በኢየሱስም ውርስ/ሺ።

03/05/2022

Yontan mekuria

06/12/2021

God bless all

17/11/2021

እኔማ ምን ልበል ....

06/12/2020

✨✨✨✨✨✨✨
6ቱ ደረቅ ጥያቄዎች.....
✨✨✨✨✨✨✨

አንድ ሰነፍ ልጅ ገና መጀመሪያ ተማሪ ቤት የገባ እለት እንደ ደንቡ ፊደል መቁጠር ጀመረ። ከ"ሀ" እስከ "ፐ" ድረስ አንድ ጊዜ ብቻ የፊደሉን ተራ ወጣና ከሁለተኛው ላይ መምህሩ መልሶ ሲመራው "ሀ" በል ቢለው ተማሪው እንቢ አለ። ቢያባብለው ቢለምነው አሻፈረኝ እንቢ ብሎ እስከጭራሹ እያለቀሰ ሸሽቶ ከተማሪ ቤት ወጥቶ ሄደ።

እያለቀሰ ሲሄድ አንድ ሰው አግኝቶት ምነው ምን አገኘህና እንዲህ ታለቅሳለህ ቢለው መምህሬ "ሀ" በል ቢለኝ እንቢ ብዬ በዚህ ተጣልተን ነው የማለቅሰው አለው። "ሀ" ለማለት ታዲያ ምን የሚያስቸግር ነገር አገኘህበት ብሎ ቢጠይቀው፣ እነዚህ መምህሮች መቼ ጣጣቸው በ"ሀ" ብቻ ያልቃል "ሀ" ስል "ሁ" በል ይሉኛል፣ "ሁ" ስል "ሂ" በል ይሉኛል፤ እንደዚህ እያሉ እስከ "ፐ" ድረስ የተፃፉትን ፊደሎች ሁሉ አንድ ባንድ ሲያስቆጥሩኝ ያለበት ድካም አንድ ጊዜ ቀምሼው አንገፈገፈኝ። ከእንግዲህ ወዲያ ይግደሉኝ እንጂ ምንም ቢሆን "ሀ" ብየ አልጀምርም ብሎ ተማሪው መለሰለትና እንደገና እያለቀሰ ወደ ቤቱ ሂደ።

በዚህ ምድር ትምህርትን እንደሚጠላ ሰው አስፈሪና አደገኛ ነገር ምንም የለም። የማያነብ ደራሲና ጥሬ ዕቃ የጨረሰ ፋብሪካ አንድ ናቸው። የማይማር ሰው የሚኖረው በግምት ነው። በግምት የሚኖር ሰው ደግሞ ጠንቋይ ብቻ ነው። የማያነብ ደራሲ ማንበብ ሲያቆም ድርሰቱ ይቆማል፤ ጥሬ ዕቃ ያለቀበት ፋብሪካም መጨረሻው መቆምና መዘጋት ነው። ጎተራ የሆነው ሆድህ ሲርበው እየመገብከው በእውቀት ማነስ የከሳችውን ነፍስህንማ እንዴት አብልጠህ እትመግብም? ያለዛ ተንሻፈህ ታድጋለህ።

በትምህርት ቤት እያለን መምህሮች አሳይመንት ይሰጣሉ። አርብ የተሰጠ አሳይመንት ሰኞ የሚገባ ከሆነ ጎበዙ በጊዜ ሰርቶ ያጠናቅቃል፤ ሰነፉ ደግሞ ሰኞ በሌሊት ሄዶ የጎበዙን ግጥም አርጎ ገልብጦ ያስገባል። አዎ ምድራዊ አሳይመንቶች የሰውን ላብ በመቅዳት ያለ ልፋትና ጥረት ይኮረጁ ይሆናል። መምህሩንም እናታልልበት ይሆናል። ግን የማይታለለውንና አሳይመንት የሰጠን ጌታ ፊት ምን እንሆን ይሆን?

የምድር መምህራን አሳይመንት መስጠትን የለመዱት ከልዑል ጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ የህይወት አሳይመንት ሰጥቶናል። ደግሞ አሳይመንታችንን ሊሰበስብ ሊቀበለንና ሊያርመው ይመጣል። ዛሬ ተወርዋሪ ኮከብ የሚመስሉ አይኖችህን ተማምነህ የምትኮርጀው፣ ከውልደት እስከ ማርጀት መኮረጅ ህጋዊ መብትህ መስሎህ የኖርከው ይሄንን የህይወት ፈተና ማን ያስኮርጅህ ይሆን? ቢኖር እንኳ ኮርጀህም ከተሳካልህ ጥሩ ነው። ታድያ ለምን የተሰጠህን 6 ደረቅ ጥያቄ መስራት አትጀምርም? ምርጫ፣ አዛምድ ለለመደ ሰው ቢከብደውም ..ምንም ማድረግ አይቻልም ፍለጠው።

አሳይመንቱ ሞዴል አይደለም ፋይናል ነው። የሚታረመው ከዘላለም ህይወት ነው። ወዳጄ እንዳትዘናጋ "F" አለው። እመረቃለው ስትል መጫርም እንዳለው እንዳትዘናጋ።

የሚገርመው በጣም የሰነፍ ሰነፍ መሆናችን ነው። እንዴት ጥያቄውና መልሱ ተነግሮን መስራትና መድፈን ያቅተናል? በቃ ያለ አጤሬራና ያለ ጎግል ምንም መስራት አንችልም ማለት ነው?
ጥያቄው እኮ፦
የተራበ አብልተሃልን?
የተጠማ አጠጥተሃልን?
የታረዘ አልብሰሃልን?
የታመመና የታሠረ ጠይቀሃል?
እንግዳንስ ተቀብለሃልን?

ምድራዊው መምህር በሰጠው የቤት ስራ የፀና አቋም ካለው ህይወት የሚያሻግረው ታሪክ የሚቀይረው ታላቁ መምህር ኢየሱስማ ለሰጠው የቤት ስራ እንዴት አይገደው!
ይህንን አሳይመንትህን በጎግል ሰርች ብታደርግ ከሊቃውንት ብትጠይቅ የሚሞላ ዳሽ ሙላ ስላልሆነ እራስህ የልብህን ወገብ በፍቅር ታጥቀህ ፣ በቸርነት እጆችህ ተዘርግተህ፣ በሩህሩህ እግሮች ተጉዘህ የምታደርገው መልካምነት ነው። እግዚአብሄር ጋር 99.9% የሚባል ነጥብ አያያዝ የለም ነጥብ ማሸጋሸግም የለም ድፍን አርገህ መስራት አለብህ።
ለራስህ ስትል ዛሬ አሳይመንትህን መስራት ጀምር......ካነበብኩት

20/10/2020

ዝዋይ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን

" በማን ትመስሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታስተካክሉኛላችሁ? እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር ታስተያዩኛላችሁ?" (ትንቢተ ኢሳይያስ 46: 5) የዕለቱ ቃል በወንድም ሹሚ ዶሬ
11/10/2020

" በማን ትመስሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታስተካክሉኛላችሁ? እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር ታስተያዩኛላችሁ?"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 46: 5) የዕለቱ ቃል በወንድም ሹሚ ዶሬ

28/09/2020
እሁድ ያገለገሉን እግዚአብሔር ይባርካቸው
27/09/2020

እሁድ ያገለገሉን እግዚአብሔር ይባርካቸው

20/09/2020

እሁድ የዝማሬ አገልግሎት ብርክ በሉልልን ዘመናችሁ ይባረክ

Address

Batu

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Batu Yehiwot Birhan Church -Ziway posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share