ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ስቶክ ኦን ትሬንት - EOTC St Gebreal Stoke On Trent, UK

ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ስቶክ ኦን ትሬንት - EOTC St Gebreal Stoke On Trent, UK በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዩናይትድ ኪንግደምና አየርላንድ ሀገረ ስብከት የስቶክ ኦን ትሬንት ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን

"እውነት እውነት እላችኋለሁ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው" ዮሐንስ 10፥1
02/02/2025

"እውነት እውነት እላችኋለሁ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው" ዮሐንስ 10፥1

የጥምቀት በዓል በዩናይትድ ኪንግደም በርሚንግሃም ከተማ በአንድነት የተከበረ ሲሆን በርካታ የአጥቢያችን ነዋሪዎች በአሉን በአንድነት በሥፍራው ተገኝተው አክብረዋል።እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ...
19/01/2025

የጥምቀት በዓል በዩናይትድ ኪንግደም በርሚንግሃም ከተማ በአንድነት የተከበረ ሲሆን በርካታ የአጥቢያችን ነዋሪዎች በአሉን በአንድነት በሥፍራው ተገኝተው አክብረዋል።እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ !

የከተራ እና የጥምቀት በዓል በዩኬ እና አየርላንድ ሀገረ ስብከት በበርሚንግሃም ከተማ የበርካታ አድባራት ታቦታት በተገኙበት በድምቀት ይከበራል።መላው ምእመናን በዚህ በዓል ላይ ተገኝታችሁ እን...
17/01/2025

የከተራ እና የጥምቀት በዓል በዩኬ እና አየርላንድ ሀገረ ስብከት በበርሚንግሃም ከተማ የበርካታ አድባራት ታቦታት በተገኙበት በድምቀት ይከበራል።መላው ምእመናን በዚህ በዓል ላይ ተገኝታችሁ እንድታከብሩ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።አድራሻ - 1 Hockley Clrcus, Birmingham
Post Code - B18 5PP

Dmk Amanuel EOTC Birmingham L
ማኅበረ ካህናት ዘዩኬ ወአይርላንድ /Mahibere kahinat UK&Ireland/

እንኳን ለአጋዕዝተ ዓለም ሥሉስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁሥላሴ በበረከት ይጎብኙን
15/01/2025

እንኳን ለአጋዕዝተ ዓለም ሥሉስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁሥላሴ በበረከት ይጎብኙን

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
07/01/2025

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

በዓለ ጥምቀትን በእንግሊዝ በርሚንግሃም ከተማ የ፳፻፲፯ ዓ.ም በዓለ ጥምቀት በዩናይትድ ኪንግደም እና አየርላንድ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እና መንፈሳዊ ማኅበራት ጋር በዓሉ በድምቀት ይከበ...
03/01/2025

በዓለ ጥምቀትን በእንግሊዝ በርሚንግሃም ከተማ

የ፳፻፲፯ ዓ.ም በዓለ ጥምቀት በዩናይትድ ኪንግደም እና አየርላንድ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እና መንፈሳዊ ማኅበራት ጋር በዓሉ በድምቀት ይከበራል።

እርስዎም ከበዓሉ በረከት ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል።

TMC - የበዓሉ የሚዲያ አጋር

አዘጋጅ - የዩኬና አየርላንድ አብያተ ክርስቲያናት ከደብረ መድኃኒት አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን

Dmk Amanuel EOTC Birmingham L

ዓመታዊ የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ የንግስ በዓል ጥሪበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የግላስጎ ደብረ ሲና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ዓመታዊው የቅድስት አርሴማ በዓለ ንግስ ጥቅምት 02/2017...
02/10/2024

ዓመታዊ የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ የንግስ በዓል ጥሪ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የግላስጎ ደብረ ሲና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ዓመታዊው የቅድስት አርሴማ በዓለ ንግስ ጥቅምት 02/2017 በዚህ ሀገር አቆጣጠር October 12/2024 ከለሊቱ 8:00 (2Am) ሰዓት ጀምሮ ስለሚኖረን ሁላችንም በሰዓቱ ተገኝተን የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።
በዕለቱም ከሀገር ቤት በሚመጡት በልሳነ ክርስቶስ መምህር ጳውሎስ መልክዓ ሥላሴ ሰፊ የወንጌል አገልግሎት ይሰጣል፡፡

ከግላስጎ ውጪ ከሩቅ ለምትመጡ ምዕመናን የምታድሩበት ማረፊያ ቤት የተዘጋጀ ስለሆነ ከታች ባለው የስልክ ቁጥር በመደወል ማረፊያ ቦታ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

አገልግሎቱ የሚደረግበት ቤ/ክ አድራሻ
50 Old Dalmarnock Rd
Bridgeton, Glasgow
G40 4AU

ለበለጠ መረጃ በእነዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉ
07496724623,
075383658884
እግዚአብሔር አምላካችን ሀገራችን ኢትዮጵያን ይህንም ሀገር ዓለሙን ሁሉ ከፈተና ህዝቦቿንም ከጥፋት ይጠብቅልን። አሜን!

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን የከበረ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤል በዓሉ ነው።ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአማላ...
29/09/2024

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን የከበረ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤል በዓሉ ነው።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአማላጅነቱ ይማረን ረድኤቱም ከእኛ ጋራ ትሁን ለዘለዓለሙ አሜን።

ለምእመናን በሙሉ !
23/09/2024

ለምእመናን በሙሉ !

መልካም አዲስ ዓመት !
11/09/2024

መልካም አዲስ ዓመት !

"ይህ ዓመት ለሕዝባችን፣ ለሀገራችንና ለዓለማችን ሰላም፣ ደስታና መንፈሳዊ እድገት እንዲያመጣ የዘወትር ምኞቴና ጸሎቴ ነው" ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ሊቀ ጳጳስ   ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም (...
10/09/2024

"ይህ ዓመት ለሕዝባችን፣ ለሀገራችንና ለዓለማችን ሰላም፣ ደስታና መንፈሳዊ እድገት እንዲያመጣ የዘወትር ምኞቴና ጸሎቴ ነው" ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ሊቀ ጳጳስ

ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የዩኬ፣ አየርላንድና የሩቅ ምሥራቅ ሀገራት ሊቀ ጳጳስ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ መልእክት አስተላልፈዋል። የብፁዕነታቸው መልእክት ሙሉ ቃል ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

‘‘ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የአምላክህ የእግዚአብሔር ዓይን ሁልጊዜ በእርስዋ ላይ ነው።’’
ኦሪት ዘዳግም ፲፩:፲፪

በዚህ የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ዕለት ሰፊ በሆነው ምሕረቱ ፣ ጥልቅ በሆነው የአባትነት ፍቅሩ ለሰከንዶች በማይቋረጠው ጥበቃውና እንክብካቤው ሳይለየን ከዘመነ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ አሸጋግሮ ለዚህ ቀን ላደረሰን ሁሉን ቻይ ለሆነው ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋናችንን በፊቱ እናቀርባለን። በኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ ፲፩ ቁጥር ፲፪ ላይ ያሉት አምላካዊ ቃላት አልፋና ኦሜጋ የሆነው አምላችን ልዑል እግዚአብሔር በዘመናት ውስጥ ሁሉ ለሕዝቡ ያለውን ፍቅር የሚያስገነዝብና በተለይም በኦርቶዶክሳዊው ቅዱስ ትውፊት የእግዚአብሔር መግቦትና እንክብካቤ በሕይወታችን ዘመን ሙሉ እንደሚሰራና በፍጹም አባትነቱ እንደሚመራን የምንገነዘብበት ክፍል ነው።

በጥንታውያን ቅዱሳን አባቶቻችን ትምህርትና ሕይወት ባማረውና ባሸበረቀው የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜያችን ይህ ክፍል እግዚአብሔር ፍጥረታቱን ፈጥሮ የተወ ሳይሆን ይልቁንም ከፍጥረታቱ ያለተለየ የፍጥረታት ሁሉ መጋቢና ጠባቂ መሆኑን እንመለከትበታለን። አበው እንደተረጎሙትም ‘‘የእግዚአብሔር ዓይን’’ ተብሎ በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ የተጻፈልን ቃል እግዚአብሔር በፍጥረታቱ ላይ የሚያፈሰውን የማያቋርጥ መግቦት፣ ጥበቃ፣ መሪነትና በረከተን የሚያሳይ ነው። ለዚህም ወደር የለሽ መለኮታዊ እንክብካቤ የማያቋርጥ የምስጋና እና የመታዘዝ ሕይወትን በመምራት ራሳችንን በምላሹ ለእርሱ መስጠት ይገባናል።

የ ፳፻፲፯ ዓመተ እግዚእ አዲስ ዓመትን ስንጀምርም፣ ያለፈውን ዓመት እንዴት እንደተጓዝነውና እንዳሳለፍነው በማሰላሰል ልባችንን ለመንፈሳዊ የሕይወት ለውጥና ዕድገት ዝግጁ ማድረግ ይገባናል። ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ የጊዜያችንን አላፊ መሆንና የተሰጠንንም ጊዜ በጥበብ መጥቀም እንዳለብን ካስገነዘበ በኋላ በጥበብ መመላለስ እንደሚገባን ‘‘በልብ ጥበብን እንድማር ቀኝህን እንዲህ አስታውቀን’’ (፹፱:፲፪) በማለት ያስተምረናል። ጥበብን ማወቅ ማለት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ፣ ሀሳብና መንገድ መጓዟን ፣ ፍትሃዊ መሆንን ፣ ምሕረት ማድረግ መውደድንና ይልቁንም እንደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትህትና በምድር ላይ መመላለስና መኖር መቻል ነው።

ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን በእያንዳንዷ ቅጽበት እግዚአብሔርን በማሰብና የእርሱን ከእኛ ጋር መሆኑን ማስተዋል እንደሚገባን ታስተምራለች። የሥርዓተ አምልኮ ማዕከልም ከተሰጠን ከእስትንፋሳችን ጀምሮ ለማያልቀው ከእርሱ ለተቀበልነው ልዩ ልዩ ስጦታዎቹ የማያቋርጥ ምስጋናን ማቅረብና ከእርሱ ያልሆነ ምንም ነገር እንደሌለ ማስገንዘብ ነው። ቅዱስ ዳዊት ‘‘በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ ፣ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል’’ (፷፬፡፲፩) በማለት እንደዘመረው ፈጣሬ ዓለማት ልዑል እግዚአብሔር ዘመናትን የበረከቱን አክሊል ያቀዳቸዋል። እኛም ልጆቹ በጸሎት፣ በመልካም ሥራና እርሱ ለመምሰል በሚደረግ ክርስቲያናዊ ጉዞ እንድንጓዝ ተጠርተናል።

በመሆኑም አሮጌው አልፎ አዲሱን ዓመት ስንቀበል ቅዱስ ጳውሎስ በ ፪ኛ ቆሮንቶስ መልእክቱ ‘‘ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው’’ (፭:፲፯) በማለት የጻፈልንን ቃል ማሰብና እንደ ቃሉ መኖር ይገባናል። ይህ ከእግዚአብሔር የተሰጠን አዲስ ዓመት ምድራዊ ለውጥን ብቻ ሳይሆን ይልቁንም መንፈሳዊ የሕይወት ለውጥ እንድናመጣና ዕድገትንም እንድናሳይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠን አዲስ የንስሐ ጊዜ እንደሆነ እናስብ። ይህ የመንፈሳዊ ሕይወት ለውጥም በቤተክርስቲያናችን ውስጥ በጾም፣ በጸሎትና በቅዱሳት ምሥጢራት አማካኝነት በመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ መሆኑን እናስተውል። በዚህ አዲስ ዓመት በእነዚህ ከእግዚአብሔር በተሰጡን ቅዱሳት ምሥጢራት አማካኝነት በኃጢአት የጎሰቆለውን አሮጌውን እኛነታችንን ትተን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በማያቋርጥ መንፈሳዊ ዕድገት ውስጥ መገኝት ይገባናል።

የተወደዳችሁ አበው አባቶቻችንና የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ፣

ይህንን አዲስ ዓመት ስንጀምር ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ፣ በጸሎት ሕይወታችን በመበርታት፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባሳየን ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ ፍቅር እርስ በእርሳችን በመዋደድ ለቤተክርስቲያናችን ፣ ለሀገራችን ብሎም ለዓለማችን የሰላም ምሳሌዎችና ምንጮች እንሆን ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እማጸናችኋለሁ።

ይህ ዓመት ለሕዝባችን፣ ለሀገራችንና ለዓለማችን ሰላም፣ ደስታ እና መንፈሳዊ ዕድገት እንዲያመጣ የዘወትር ምኞቴና ጸሎቴ ነው።

በዚህ አዲስ ዓመት ዘላለማዊ የሚሆን የሰማይ ቤታችንን ብቻ መመልከት እንችል ዘንድ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና እና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃ፣ ረድኤትና በረከት ይደርብን ! ከዚህ ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ የእግዚአብሔር በረከቱ፣ ፀጋው፣ ፍቅሩ እና ጥበቃው ከእኛ ጋር ይሁን! አሜን።

‘‘የተስፋ አምላክም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ እንድትበዙ በማመናችሁ ደስታና ሰላምን ሁሉ ይሙላባቹሁ ’’
ሮሜ ፲፭: ፲፫

አባ ያዕቆብ
የሩቅ ምሥራቅ፣ እንግሊዝ፣ አየርላንድና አካባቢው ሀገራት ሊቀ ጳጳስ
የዓለም የሰላም አምባሳደር

ለደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ምእመናት በሙሉበደብራችን በተደጋጋሚ የሚታየውን የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት መነሻ በማድረግ የተለያዩ አካላት የሰበካ ጉባኤውን እና ...
05/09/2024

ለደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ምእመናት በሙሉ

በደብራችን በተደጋጋሚ የሚታየውን የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት መነሻ በማድረግ የተለያዩ አካላት የሰበካ ጉባኤውን እና የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነት አደጋ ውስጥ ለማስገባት ሲጥሩ ቆይተዋል።

ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ለማስተካከል እና ቤተ ክርስቲያኑ በሕግና በሥርዓት እንዲመራ ለማድረግ ሰበካ ጉባኤው አስፈላጊውን ጥረት እያደረገ በሚገኝበት በዚህ ሰዓት አንዳንድ የጉባኤ አባላት አቅጣጫውን የሳተ እና ከእውነት የራቁ ሀሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጩ እንደሚገኝ ተረድተናል።

ስለሆነም መላው የደብራችን ምእመናን ከሰበካ ጉባኤው በይፋ ከሚሰጥ መረጃ በቀር በአንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች አማካይነት ከሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ ራሳችሁን እንድትጠብቁ እንዲሁም አባቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው፤ አጥንታቸውን ከስክሰው ያቆዩልን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ዶግማዋና ቀኖናዋ በግለሰቦች ሲጣስ እና ሲፈርስ ዝም ብሎ ከመመልከት ይልቅ ሕግና ሥርዓት እንዲከበር ሁሉም አማኝ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያኑ ጠበቃ እንዲሆን ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት
ነሐሴ 29 ቀን 2016 ዓ.ም
4 September 2024

Address

3 East Wood
Stoke-on-Trent
ST64BU

Telephone

+447904912081

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ስቶክ ኦን ትሬንት - EOTC St Gebreal Stoke On Trent, UK posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share