Ethiopian Orthodox Tewahedo Page

Ethiopian Orthodox Tewahedo Page የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው።
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
(1)

" "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን !በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ!የሰውን ወገን ለማ...
07/08/2026

" "
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን !

በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ!

የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ!
“ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤
ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡

ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው!

ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔርይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤

የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል
ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣

ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፣

በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤
የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡

ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤

በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት !

ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔርትእዛዝና ፍቅር ነው፣

እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብርኣዞናል ክቅዱሳን ፍጥረታት መካክል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤

ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናክብራታለን፤

ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው!

በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡

በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብርትእዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን ! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡

በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በኣጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡

ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡

በመጨረሻም

በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤

የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

  ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን።ቅዱስ ገብርኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!!የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል  ተራዳኢነት የሰማዕታቱ የቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት ኢየሉጣ የገድ...
26/07/2026

ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

ቅዱስ ገብርኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!!

የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት የሰማዕታቱ የቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት ኢየሉጣ የገድላቸው በረከት ይደርብን የእግዚአብሔር ቸርነት ከሁላችን ጋር ይኑር አሜን።

10/06/2026

እግዚአብሔር መልስ ይሰጣል ።

 #በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመው ግድያና ማሳደድ አልበቃ ብሎ የቤተክርስቲያኗ ተቆርቋሪዎችና አገልጋዮች እየታደኑ እየታሰሩ ከመሆናቸው ሁነት የምንረዳው ሓቅ አሳሪው ከገዳዩ የራቀ አለመሆኑን...
10/06/2026

#በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመው ግድያና ማሳደድ አልበቃ ብሎ የቤተክርስቲያኗ ተቆርቋሪዎችና አገልጋዮች እየታደኑ እየታሰሩ ከመሆናቸው ሁነት የምንረዳው ሓቅ አሳሪው ከገዳዩ የራቀ አለመሆኑን ነው። ገዳዮች መታሰርና ለህግ መቅረብ ሲገባቸው..?? አባቶቻችንን፣ ወንድሞቻችን ባስቸኳይ ይፈቱ ነፃ ናቸው።

  (ከ1985–2018)  🔥🔥🔥 #ለምን?????🔥🔥🔥​በኢትዮጵያ ዘመናዊ የታሪክ ጉዞ ውስጥ ባለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት (ከ1985 እስከ 2018 ዓ.ም. / እ.ኤ.አ. 1992–2026) የተመ...
03/06/2026

(ከ1985–2018)




🔥🔥🔥 #ለምን?????🔥🔥🔥

​በኢትዮጵያ ዘመናዊ የታሪክ ጉዞ ውስጥ ባለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት (ከ1985 እስከ 2018 ዓ.ም. / እ.ኤ.አ. 1992–2026) የተመዘገቡት የፖለቲካ ሽግግሮችና ማኅበራዊ ቀውሶች በርካታ ንጹሐን ዜጎችን ዋጋ አስከፍለዋል። ከእነዚህ ዘግናኝ ክስተቶች መካከል በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን፣ ካህናትና አብያተ ክርስቲያናት ላይ የተፈጸሙት ስልታዊ ጥቃቶችና ጭፍጨፋዎች ግንባር ቀደሞቹን ጥልቅ ጠባሳዎች ጥለው አልፈዋል። ኦርቶዶክሳውያን በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው፣ በቤታቸውና በምስጋና ስፍራቸው ላይ ሳሉ ያለምንም ጥፋታቸው ለይቶ ባጠቃ ሁከት የሰማዕትነት ጽዋን ለመቀበል ተገደዋል። ይህ ጽሑፍ ከ1985 ዓ.ም. የአርባ ጉጉ ፍጅት ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜው የ2018 ዓ.ም. የዝቋላና አርሲ ጥቃቶች ድረስ የተከሰቱትን መጠነ-ሰፊ ጭፍጨፋዎች፣ የደረሱትን ጉዳቶችና ለዚህ ሁሉ ግፍ መነሻ የሆኑትን ሥር የሰደዱ ምክንያቶች በዝርዝር ያትታል።

​1. የጭፍጨፋዎቹ ታሪካዊ ሂደትና የደረሱት ጉዳቶች
​ባለፉት ሠላሳ-አራት ዓመታት ውስጥ በተለያዩ የፖለቲካ ማዕበሎችና አለመረጋጋቶች ማግስት ኦርቶዶክሳውያን ኢላማ የተደረጉባቸው ዋና ዋና ስፍራዎችና የደረሱት ጉዳቶች በሚከተለው መልኩ በታሪክ ተመዝግበዋል

​1. በቦታዎች የተለዩ ጥቃቶችና ጭፍጨፋዎች

👉አርባ ጉጉ እና አርሲ (1984–1985 ዓ.ም. / 1991–1992 እ.ኤ.አ.)

➠የደርግ ሥርዓት መውደቅን ተከትሎ በሽግግሩ ወቅት በአርባ ጉጉ (በወቅቱ በአርሲ ክፍለ ሀገር) በሰፈሩ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የአማራ ተወላጆች ላይ ስልታዊ ጭፍጨፋ ተካሄደ።

➠ ንጹሐን ምዕመናን ከገደል ተጥለዋል፣ በስለትና በዱላ ተገድለዋል፣ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል። ይህ ክስተት በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ በሃይማኖትና ብሔር መደራረብ ምክንያት ከደረሱት የመጀመሪያዎቹ መጠነ-ሰፊ ጥቃቶች አንዱ ነው።

​👉ጅማ (የ1999 ዓ.ም. / 2006 እ.ኤ.አ. የከተባና አካባቢው ጥቃት

➠ በጥቅምት 1999 ዓ.ም. በጅማ ዞን (በተለይም በከተባ፣ አጋሮና አካባቢው) በኦርቶዶክሳውያን ላይ ከፍተኛ ጥቃት ተሰነዘረ።

➠ ከማኅበረ ቅዱሳንና ከቤተ ክርስቲያን ሰነዶች መረዳት እንደሚቻለው፣ ቁጥራቸው ከ20 በላይ የሚሆኑ ምዕመናንና ካህናት ተገድለዋል። ከማንነታቸው ባሻገር የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ መሆናቸው ብቻ ተለይቶ ጥቃት የተፈጸመባቸው ሲሆን፣ ከ6 በላይ አብያተ ክርስቲያናትና በርካታ የምዕመናን መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል።

👉ጅጅጋ (የነሐሴ 2010 ዓ.ም. / 2018 እ.ኤ.አ. ጥቃት)

➠በሶማሌ ክልል በነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋትና በወቅቱ የክልሉ ልዩ ኃይልና "ኬሮ" በተባሉ ወጣቶች አማካኝነት በጅጅጋ ከተማ የሚኖሩ "የደቡብና ደጋው ሕዝብ" (ከክልሉ ውጭ የሆኑ ብሔረሰቦች) እና የኦርቶዶክስ ተከታዮች ኢላማ ተደረጉ።

➠በወቅቱ የጅጅጋ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን ጨምሮ 8 አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል። የጅጅጋው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቴዎስን ጨምሮ ከ7 በላይ ካህናትና መነኮሳት በጭካኔ ተገድለዋል፤ አስከሬናቸውም በክብር እንዳይቀበር ተከልክሎ ነበር።

👉ሲዳማ / ሐዋሳ (የሐምሌ 2011 ዓ.ም. / 2019 እ.ኤ.አ. የ"ኤጄቶ" አመፅ)

➠የሲዳማ የክልልነት ጥያቄን ተከትሎ በተቀሰቀሰው አመፅ፣ የ"ኤጄቶ" ቡድን አባላት በሐዋሳና አካባቢው (በተለይም በይርጋለምና ሻሸመኔ አዋሳኝ አካባቢዎች) የሚኖሩ የኦርቶዶክስ ምዕመናንን አጠቁ።

➠የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ይኖሩባቸው የነበሩ መንደሮች ተቃጥለዋል፣ ምዕመናን ተገድለዋል፣ ንብረታቸውም ተዘርፏል።

👉ምዕራብ ሐረርጌ (የተለያዩ ዓመታት፣ በተለይም 2012 ዓ.ም.)

➠በምዕራብና ምሥራቅ ሐረርጌ (ጭሮ፣ በደኖ፣ ሂርና እና አካባቢው) በተለያዩ ጊዜያት በሚነሱ የብሔርና የፖለቲካ ውጥረቶች ወቅት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት የጥቃት ማዕከል ሆነዋል።

➠ ካህናት ከአገልግሎት ሲመለሱ መታገድና መገደል፣ የምዕመናን እርሻዎችና ቤቶች መቃጠል በስፋት የተመዘገቡ ክስተቶች ናቸው።

​🔥2. በታዋቂ የፖለቲካ ክስተቶች ወቅት የደረሱ ጭፍጨፋዎች

👉በጁሀር መሐመድ "የመንግሥት አካላት ከበቡኝ" ጥሪ ወቅት (ጥቅምት 2012 ዓ.ም. / ኦክቶበር 2019 እ.ኤ.አ.)

​➠የክስተቱ መነሻ አክቲቪስት ጁሀር መሐመድ በማኅበራዊ ገጹ "የመንግሥት የደኅንነት አካላት ሊያጠቁኝ ከበቡኝ" የሚል መልእክት ካስተላለፈ በኋላ በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞችና በሐረሪ ክልል ከፍተኛ አመፅ ተቀሰቀሰ።

​➠በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰው ጉዳት አመፁ ወዲያውኑ መልክ በመቀየር የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችንና የአማራ/ጉራጌ ተወላጆችን ኢላማ አደረገ። በኢሰመኮ ሪፖርት መሠረት በነዚህ ጥቂት ቀናት ውስጥ 86 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ አብዛኞቹ በድንጋይ፣ በዱላና በገጀራ ተጨፍጭፈው የሞቱ የኦርቶዶክስ ምዕመናን ነበሩ። በዶዶላ፣ በባሌ ሮቤ፣ በናዝሬት (አዳማ) እና በሻሸመኔ የተፈጸሙት ግድያዎች እጅግ ዘግናኝ ነበሩ።

👉በድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ሞት ማግስት (ሰኔ/ሐምሌ 2012 ዓ.ም. / ጁላይ 2020 እ.ኤ.አ.)

​➠የክስተቱ መነሻ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ በአዲስ አበባ መገደሉን ተከትሎ የተነሳ መጠነ-ሰፊ ሁከት።

​➠በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰው ጉዳት ሁከቱ በተለይ በሻሸመኔ፣ ባቱ (ዝዋይ)፣ አርሲ ነገሌ፣ ደረባ እና ዶዶላ ከተሞች ውስጥ ቀጥተኛ የሃይማኖትና የብሔር ማጽዳት መልክ ይዞ ነበር።

​➠በሻሸመኔ ከተማ ታዋቂው የኦርቶዶክስ ምዕመን አቶ አየለ በየነ (አባ ቶርቤ በተባለ ቡድን በጭካኔ የተገደሉ) እና በርካታ ወጣቶች ተጨፍጭፈዋል።
​በዝዋይ/ባቱ የቅዱስ ገብርኤልና የቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ተገድለዋል፤ ሆቴሎች፣ ትምህርት ቤቶችና የኦርቶዶክሳውያን ንብረቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።
​የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሪፖርቱ ይህንን ጥቃት "ሰብአዊነት የጎደለውና የተወሰኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን (ኦርቶዶክስና አማራን) ለይቶ ያጠቃ" በማለት ፈርጆታል።

👉በሰሜኑ ጦርነት ወቅት (2013–2015 ዓ.ም. / 2020–2022 እ.ኤ.አ.)

​➠የክስተቱ መነሻ በፌዴራል መንግሥቱና በሕወሃት (TPLF) መካከል የተቀሰቀሰው የእርስ በርስ ጦርነት።

​➠በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰው ጉዳት ጦርነቱ በዋናነት በትግራይ፣ በአማራ (ወሎ፣ ጎንደር፣ ሸዋ) እና በአፋር ክልሎች የተካሄደ በመሆኑ፣ የጉዳቱ ሰለባዎች በብዛት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ነበሩ።

​➠በትግራይ (አክሱም ጽዮን) በኅዳር 2013 ዓ.ም. በአክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን ምዕመናንና ተፈናቃዮች መገደላቸውን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሪፖርቶች አረጋግጠዋል።

​➠በአማራ ክልል (ወሎና ሸዋ) የሕወሃት ኃይሎች ወደ ደቡብ ወሎ (ኮምቦልቻ፣ ደሴ) እና ሰሜን ሸዋ (ሸዋ ሮቢት) በገቡበት ወቅት በርካታ ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ተዘርፈዋል፣ ተደብድበዋል። ካህናትና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል።

​👉3. ከ2015 እስከ 2018 ዓ.ም. (2023–2026 እ.ኤ.አ.) የቀጠሉ ወቅታዊ ጥቃቶች

​ከላይ ከተጠቀሱት ታሪካዊ ክስተቶች በኋላም ቢሆን፣ በተለይ በኦሮሚያ ክልልና በታጠቁ ኃይሎች (የኦነግ ሸኔ/OLA እና ሌሎች ቡድኖች) በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸሙት ግድያዎች መልክ እየቀያየሩ ቀጥለዋል፦

​👉የአርሲ መርቲ እና ሸርካ ጥቃቶች (2016 ዓ.ም.) በቅርብ ጊዜ በአርሲ ዞን ውስጥ በታጠቁ ኃይሎች አማካኝነት በአንድ ሌሊት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆኑ የአንድ ቤተሰብ አባላት፣ ሕፃናትን ጨምሮ፣ በቤታቸው ውስጥ በስለትና በጥይት የተጨፈጨፉበት ክስተት የቅዱስ ሲኖዶስን ከፍተኛ ማውገዝና የኃዘን መግለጫ አስከትሏል።

​👉የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ጥቃት (የካቲት 2016 ዓ.ም.) የታጠቁ ኃይሎች ታሪካዊው የዝቋላ ገዳም ውስጥ በመግባት አራት መነኮሳትንና አባቶችን (አባ ተክለ ማርያም አስራት፣ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን፣ አባ ገብረ ማርያም አሰፋ እና አቶ ኃይለመደኅን ታደሰ) አፍነው በመውሰድ በግፍ ገድለዋቸዋል።

🔥እነዚህ ከ1985 እስከ 2018 ዓ.ም. ድረስ የተመዘገቡት መረጃዎች የሚያሳዩት፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥርዓት ለውጥና አለመረጋጋት በደገሰ ቁጥር፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ምዕመናኖቿ ዋነኛ የጥቃት ሰለባ መሆናቸውን ነው። ጥቃቶቹ በአብዛኛው የብሔር ማንነትንና የሃይማኖት ስብጥርን መሠረት ያደረጉ በመሆናቸው፣ በታሪክ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ማኅበራዊና ሥነ-ልቦናዊ ጠባሳ ጥለው አልፈዋል።

🛑➽2. ኦርቶዶክሳውያን ያለምንም ጥፋታቸው የተገደሉባቸው ምክንያቶች

​ንጹሐን ምዕመናን በገዛ ሀገራቸው ያለምንም ጥፋትና ወንጀል የዚህ ሁሉ ሰቆቃ ሰለባ የሆኑባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች በማኅበራዊ፣ በታሪካዊና በፖለቲካዊ ትንታኔዎች ሲመረመሩ የሚከተሉት መሆናቸው ይገለጻል

​የሃይማኖትና የብሔር ማንነት መደራረብ በኢትዮጵያ በብዙ አካባቢዎች የኦርቶዶክስ እምነት ከተወሰኑ የብሔር ስብስቦች (በተለይም ከአማራ፣ ከጉራጌ ወይም ከደቡብ ሕዝቦች) ጋር ተደራርቦ ይታያል። ጽንፈኛ የብሔር ፖለቲካ አራማጆች ወይም የታጠቁ ቡድኖች ከአንድ ብሔር ጋር ያላቸውን ፖለቲካዊ ቅሬታ ለመወጣት ሲሉ፣ በዚያ አካባቢ የሚገኘውን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመንና ተቋም እንደ ቀጥተኛ ተወካይ አድርገው በመውሰድ ምዕመኑን በብሔሩና በሃይማኖቱ ለይተው ያጠቁታል።

​ቤተ ክርስቲያንን “የቀደመው ሥርዓት ምልክት” አድርጎ የመሳል የተሳሳተ ትርክት፦ ባለፉት አሥርት ዓመታት በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ የተዘረጉ የተዛቡ የታሪክ ትርክቶች Historical Narratives ቤተ ክርስቲያኗን ከቀደሙት የነገሥታት ሥርዓቶችና ከጭቆና መዋቅሮች ጋር ብቻ አያይዘው እንዲስሏት አድርጓል። ይህ ፕሮፓጋንዳ በአክራሪ ኃይሎች ዘንድ ስልታዊ ጥላቻን በመፍጠሩ፣ ንጹሐን ምዕመናንና አገልጋዮች የጥንቱ ሥርዓት ቀጣይ ተደርገው ያለምንም ጥፋታቸው ኢላማ ይሆናሉ።

​ቤተ ክርስቲያንን “የኢትዮጵያ አንድነት ምሰሶ” አድርጎ በመውሰድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሀገሪቱ ምሥረታ፣ ታሪክ፣ ባህልና አንድነት ጋር ያላት ትስስር የጠበቀ ነው። ሀገሪቱን በብሔር መስመር ብቻ የመበተን ዓላማ ያላቸው ኃይሎች፣ ቤተ ክርስቲያኗን ለዚህ ስልታቸው እንደ ትልቅ ዕንቅፋት ያዩታል። በመሆኑም “የሀገርን አንድነት ለማላላት መጀመሪያ ምሰሶዋን ማፍረስ” በሚል እሳቤ አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠልና ምዕመናንን ማሳደድ የፖለቲካ ግባቸው ማሳኪያ ያደርጉታል።

​የመንግሥት የጸጥታ መዋቅር ክፍተትና የተጠያቂነት መጥፋት በየዘመናቱ በነበሩ የሽግግርና የፖለቲካ አለመረጋጋት ወቅቶች የመንግሥት ሕግ የማስከበር አቅም መላላቱ ለጽንፈኞች አመቺ ሁኔታን ፈጥሯል። በአርባ ጉጉ፣ በሻሸመኔ፣ በጅጅጋም ሆነ በአርሲ ጥፋት የፈጸሙ አካላት በአግባቡ ለሕግ አለመቅረባቸውና ተገቢውን ቅጣት አለማግኘታቸው፣ ሌሎች ታጣቂዎችም በተመሳሳይ ሁኔታ ንጹሐንን እንዲጨፈጭፉ ማበረታቻ ሆኗቸዋል።

​የሕዝብ ስብጥር ለውጥና የይገባኛል ጥያቄዎች Demographic Changes በአንዳንድ አካባቢዎች የበላይነት ማግኘት የሚፈልጉ ኃይሎች፣ አናሳ ወይም መጤ አድርገው የሚፈርጇቸውን የኦርቶዶክስ ምዕመናን በኃይል በማፈናቀልና በመግደል፣ የአካባቢውን የስነ-ሕዝብና የሃይማኖት ስብጥር በግዳጅ ለመቀየር ይሞክራሉ።

​ይህ ሁሉ ግፍ ያለምንም ጥፋታቸው ቢደርስባቸውም፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ምዕመናኖቿ የታሪክ ጠባሳውን በትዕግሥት፣ በጸሎትና በሰማዕትነት እያለፉት ይገኛሉ። ንጹሐን በማንነታቸው ብቻ የሚታረዱበት ይህ ዘግናኝ የታሪክ ምዕራፍ፣ የሀገርን ሰላምና ማኅበራዊ ትስስር በእጅጉ የሚጎዳ በመሆኑ ፈጣንና ዘላቂ ፍትሕን ይሻል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአርሲ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያናችን እና በኦርቶዶክሳ...
03/06/2026

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአርሲ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያናችን እና በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።

ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት እንደሚከተለው ነው፦

መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

‹‹ወረሰዩ አብድንቲሆሙ ለአግብርቲከ መብልዐ ለአዕዋፈ ሰማይ፣ ወሥጋሆሙኒ ለጻድቃኒከ ለአራዊተ ገዳም፦ የአገልጋዮችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የቅዱሳንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት።››
(መዝሙረ ዳዊት ፸፰፥፪)

በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤ እና በሙኔሳ ወረዳዎች በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ስለደረሰው አሰቃቂ ጥቃት የሰማነው በተሰበረ ልብ ነው።

የእምነት ነፃነት ተደፍሮ መቶ ዓመታት ያስቆጠረው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በተቃጠለበት፣ እንዲሁም የካራ ኩፍቴና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በተዘረፈበት በዚህ ክፉ ቀን፤ በርካታ ምእመናን በግፍ መሰዋታቸውና በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ቤተ ክርስቲያናችንን በእጅጉ ያሳዘነ ክስተት ነው።

የሰላም፣ የፍቅርና የታሪክ ማህደር የሆነችው ቤተ ክርስቲያን በምድራዊ መከራ ውስጥ ያሉትን ምእመናን በምታጽናናበት በዚህ ወቅት ራሷ በፈተና ውስጥ ሆና ከመቸገሯም በላይ በአርሲ ምድር በተደጋጋሚ የሚስተዋለው በደልና ግፍ በሁላችንም ልቡና ውስጥ "እስከ መቼ?" የሚል የቁጭት እና የኀዘን ጥያቄን ፈጥሯል።

በመሆኑም ይህ መከራ እያበቃ ሳይሆን እየሰፋ በመምጣቱ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን አደራ የተጣለባችሁ የጸጥታ አካላትና በየመዋቅሩ ያላችሁ ሓላፊዎች ከምንም በላይ ታሪክ የሚጠይቃችሁ በሥልጣን ዘመናችሁ ለዜጎች ደኅንነት በምትከፍሉት ዋጋ ነውና ይህንን የጥቃት ሰንሰለት በማስቆምና ወንጀለኞችን ለሕግ በማቅረብ ከታሪክ ባለዕዳነት ትድኑ ዘንድ በቤተ ክርስቲያናችን ስም አበክረን እናሳስባለን።

በየአካባቢው የምትገኙ ምእመናንና መላው ኢትዮጵያውያንም በወንድማማችነት መንፈስ ተጋግዛችሁ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና በጸሎት ከቤተክርስቲያናችን ጎን እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያናችን ለሰላም፣ ለይቅርታና ለሰው ልጆች ክብር ሁል ጊዜ የምትቆም መሆኑን በመግለጽ ይህንን የኀዘን ሰዓት አምላካችን በምሕረቱ ያሳልፍልን፣ የሞቱትን ነፍሶቻቸውን በመንግሥቱ ይቀበልልን፣ የተጎዱትንም በቸርነቱ ያጽናናልን በማለት አባታዊ የኀዘን መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

©️የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት

12/04/2026

! ✨
እንኳን ለዚህ ቅዱስ ቀን በሰላም አደረሳችሁ። የትንሳኤው ብርሃን ልባችሁን በተስፋ፣ ቤታችሁን በፍቅር፣ ሕይወታችሁንም በደስታ ይሙላው። ከቤተሰብና ከወዳጆቻችሁ ጋር የማይረሱ ደስታዎችን እንድትካፈሉ እመኛለሁ።

Happy Easter! 🕊️
May this beautiful and blessed season fill your heart with peace, your home with love, and your life with renewed hope and joy. Wishing you laughter, warmth, and endless blessings as you celebrate with your beloved family and friends.

07/04/2026

ከሰኞ እስከ ቅዳሜ
ኪርያያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን
ኪርላይሶን--- አማኑኤል ጌታ
ኪርላይሶን--- በጥፊ ተመታ
ኪርላይሶን--- አለም ሊታደግ
ኪርላይሶን--- ተነዳ እንደ በግ
ኪርላይሶን--- አዳምን ሊፈውስ
ኪርላይሶን--- ቆመ ከቢላጦስ
#ኪርላይሶን/3/
ኪርላይሶን--- እጁን ቸነከሩት
ኪርላይሶን--- አጥንቱን ቆጠሩት
ኪርላይሶን--- የሾሕ አክሊል ደፍቶ
ኪርላይሶን--- ገዳዩን ረቱት
ኪርላይሶን--- የሁላችን በደል
ኪርላይሶን--- ተሻረ በእርሱ ቁስል
#ኪርላይሶን/3/
ኪርላይሶን--- ኮምጣጤ አጠጡት
ኪርላይሶን--- በገመድ ጐተቱት
ኪርላይሶን--- በወንበዴ ፋንታ
ኪርላይሶን--- ተሰቀለ ጌታ
ኪርላይሶን--- ሁሉም ዘበቱበት
ኪርላይሶን--- በዘላለም ሕይወት

23/03/2026

የሞተ ስደተኛ በሃገሩ አይቀበርም ክፉ ዘመን። የሞተ ዘመድን መቅበር አለመቻል ስሜቱ ከባድ ነው። በሐዘን አብረን የማናዝንበት የተረገመ ዘመን ለመሆኑ ወዴት እየሄድን ነው።
ለዳንኤል ክብረት ትክክለኛ የተሰጠ ምላሽ አድርጉት

Address

London

Telephone

+447474124487

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Orthodox Tewahedo Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Ethiopian Orthodox Tewahedo Page:

Shortcuts

Share