ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቃል ይጥላል ፡ ትርጉም ያነሳል Long Live To Orthodox Tewahdo! Let's come together with unity to "Tewahdo" and let's share and spread the words of God to the world!

May God bless you all!

19/02/2023

የዐቢይ ፆም የመጀመሪያው ሳምንት



አንዲት ቤተክርስቲያን ፥ አንድ ሲኖዶስ ፥ አንድ መንበር ።

ጾም ማለት ፤
፨ ከእህልና ከውኃ እንዲሁም ከሥጋ ፈቃድ ጾሙ እስኪፈጸም ድረስ መተው ማለት ነው።
፨ ጾም ማለት በጾም ወቅት ሥጋ ነክ ምግቦችንም ሆነ ወተትን፤ ቅቤን የመሳሰሉትን የምግብ እና የመጠጥ ዓይነቶችን ጥሉላትነት በሌላቸው ምግቦች መለወጥ ብቻ ሳይሆን የምንወደውን የሥጋ ፍላጎት ስለ እግዚአብሔር ብለን መተው ማለት ነው። ራስን መግዛት በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ሁሉ አንድ ሰው የሥጋ ፍላጎቱን ወይም የዓለም ምኞቱን ትቶ እግዚአብሔርን እያሰበ የሚጾም ከሆነ በፈጣሪው ዘንድ ጾሙ ተቀባይነት አለው።

፨ ጾም ለእግዚአብሔር ያለንን ታዛዥነት የምንገልጽበት የፍቅር መገለጫ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ዐቢይ ጾም ስንጾምም፤
፠ ዐይናችን ትጹም (ክፉ ከማየት)፤
፠ ጆሮም ትጹም (ክፉ ከመስማት ወይም ሰውን ከማማት እንታቀብ)፤
፠ አፋችን ትጹም (ከመሳደብ ሆነ ክፉ ከማውራት)፤
፠ እጅም ትጹም (ከመስረቅም ሆነ ሰውን ከመደብደብ)፤
፠ አግርም ትጹም (ወደ ኀጢአት ቦታዎች ከመሄድ)

….. ሁላችንም በተሰበረ ልብ ሆነን እንጹም።

ማለት ታላቅ ጾም ማለት ነው። ታላቅ ጾም የተሰኘበት ምክንያት ለ55 ቀናት መጾሙና ከሌሎች አጽዋማት ጋር ሲነጻጸር በቊጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ፍጥረታትን የፈጠረ አምላክ፤ ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ሲል ከዙፋኑ ወርዶ ከእመቤታችን ተወልዶ፤ መጾም ሳይገባው ለእኛ አርአያ ለመሆን ሲል በገዳመ ቆሮንጦስ የጾመው ጾም ነው።

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ወይም ጾመ ሕርቃል በተጨማሪም ሙሴኒ በመባል ይታወቃል፤ ለምን እንደተባለ በዝርዝር ስንመከለከታቸው፤

፩ኛ. ዘወረደ ይባላል፤

‹‹ ፤

፡፡››
‹‹ ››፡፡
«ዘወረደ» ማለትም በቀጥታ፣ ቃል በቃል ሲተረጐም «የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም በምሥጢሩ አምላክ፥ ወልደ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም፥ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን፤ በፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና መውረዱን፥ ከድንግል ማርያም መወለዱን፥ የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ይህ እንዲታወስበት፣ እንዲወሳበት የዐቢይ ጾም የመጀመሪያውን ሳምንትን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው ላይ ‹‹ዘወረደ›› ብሎ ሰይሞታል፡፡ /ዮሐ.3፥13፣ ጾመ ድጓ፡፡/

፪ኛ. ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡

የዐቢይ ጾም የመዠመሪያ ሳምንት ሌላ መጠሪያ ስሙ ‹‹ጾመ ሕርቃል›› ነው፡፡ ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ በስሙ ተሰየመ? በ614 ዓ.ም. ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ንግሥቲቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ካህናትን አሸክሞ፥ ሌላውን ንዋያተ ቅድሳት ዘርፎ፥ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ፥ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ፥ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲያኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፤ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርግ? አላቸው፤ እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን ፩ ሱባኤ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉ ያለበትን አጥቶ ሲቸገር ኪርዮስ መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቊስጥንጥንያ ተመለሰ፤ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ፤ ይህንን ለማሰብ፥ ለማስታወስ የምንጾመው ሲሆን፤ ዛሬም እኛ በመስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን እያልን፥ ለሕርቃል በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳትን፥ መንፈሳዊ ኃይልን እንዲበዛልን እንጾመዋለን፡፡ በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡

፫ኛ. ሙሴኒ
የመጀመሪያው ሳምንት ሙሴኒ የተባለበት ምክንያትም፤ በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ የሰኞ ዕዝል «ከመዝ ይቤ ሙሴ ፀዓቱ እምትእይንት (ሙሴ ከከተማ መውጣቱ እንደዚህ ነው አለ») ስለሚል እንደዚሁም የዚሁ ዕለት ማለት የሰኞ አቡን «ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሰናይት» እያለ የሙሴን ታሪክ ስለሚጠቃቅስ ሳምንቱ ሙሴኒ ተባለ፡፡ ነቢያትም አርባ አርባ ቀን ጾመው ካለፉ በኋላ የሙሴ ሕግና ትንቢተ ነቢያት ፈጻሚ የሆነው አምላካችን እንደ እነሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት መጾሙን የሚያስታውስ ነው፡፡ /ዘፀ.24፥18፤ 1ኛ.ነገ.19፥8፤ ማቴ.4፥1-4/፡፡

ይህ ታላቅ ጾም ሌሎች ስያሜዎችም አሉት ፡፡

አንዲት ቤተክርስቲያን ፥
አንድ ሲኖዶስ ፥
አንድ መንበር ።
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

06/02/2023

"ይቅርታ"

ከሠራተኞችህ አንዱ ከአንተ መቶ ቅንጣት ወርቆችን ተበደረ እንበል፡፡ ሌላ ሰው ደግሞ ከዚህ ሠራተኛህ የተበደረው ጥቂት ብር ነበረው፡፡ ከዚህ ሠራተኛህ የተበደረው ያ ሰውም ወደ አንተ መጥቶ ቸርነትን እንድታደርግለት ለመነህ፡፡ አንተም ሠራተኛህን ጠርተህ፡- “የዚህን ሰው ዕዳ ተውለት፤ ከእኔ ከተበደርከው ዕዳህም እቀንስልሃለሁ” ብትለውና ይህ ሠራተኛህ ከዚያ በኋላ በዚያ ሰው ላይ ቢጨክንና ቢከፋ ይህን ሠራተኛ ከእጅህ ሊያድነው የሚችል ሰው አለን? እጅግ እንደ ነቀፈህ አድርገህ ቆጥረህ ብዙ ግርፋትን አትገርፈውምን? [እንዲህ ብታደርግ] እጅግ ፍትሐዊ ነው፡፡ እግዚአብሔርም የሚያደርገው እንደዚህ ነው፤ በዚያች ዕለተ ምጽአት ላይ እንዲህ ይልሃልና፡- “አንተ ክፉና ተንኰለኛ ባሪያ ያንን ሰው ይቅር ብትለው ይቅርታው የአንተ ነበርን? ለእርሱ እንድታደርግለት የታዘዝከው ከእኔ የተበደርከውን ነበር፡፡ ያልኩህ ‘ዕዳዉን ብትተውለት እኔም እተውልሃለሁ’ ነው፡፡ በእውነት እንዲህ ይህን ኹኔታ ጨምሬ ባልነግርህም እንኳን ስለ እግዚአብሔር ብለህ ዕዳዉን ትተውለት ዘንድ በተገባህ ነበር፡፡ ነገር ግን እንደ ወዳጅ ኾኜ ውለታን ጠየቅሁህ እንጂ እንደ ጌታ አላዘዝኩህም፡፡ የጠየቅሁህ የእኔ ከኾነው ነው፤ ይህን ካደረግህም እጅግ በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍስን እንደምሰጥህ ቃል ገብቼልህ ነበር፡፡ ነገር ግን ምንም ልትሻሻል አልቻልክም፡፡”

ከዚህም በላይ ሰዎች እንደዚህ ሲያደርጉ የሚቀንሱት የዕዳ መጠን ሠራተኞቻቸው ላበደሩአቸው ሌሎች ሰዎች የቀነሱትን ያህል ነው፡፡ ለምሳሌ እንበልና አንድ ሠራተኛ ከአሠሪው መቶ ቅንጣት ወርቅን ይበደራል፡፡ ሌላው ሰው ደግሞ ከዚህ ሠራተኛ ዐሥር ቅንጣት ይበደራል፡፡ ሠራተኛው ዐሥር ቅንጣት ላበደረው ብድሩን ቢተዉለት አሠሪው ግን መቶ ቅንጣቱን አይተውለትም፤ የሚተውለት ዐሥር ቅንጣቱን ብቻ ነው፤ ሌላዉን እንዲመልስለት ይፈልጋል፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን እንደዚህ አይደለም፡፡ አንተ ለባልንጀራህ ጥቂቱን ስትተውለት እግዚአብሔር ደግሞ ዕዳህን ኹሉ ይተውልሃል፡፡ ይህስ [መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ] የት ይገኛል? [ጌታችን] ስለ ጸሎት ባስተማረው ትምህርት ውስጥ አለ፡፡ “ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና” እንዲል (ማቴ.6፡14)፡፡ በ“መቶ ዲናር” እና በ“እልፍ መክሊት” መካከል ያለው ልዩነት ያህል ለሰው ይቅር የምንለው ዕዳና ከእግዚአብሔር ይቅር የሚባልልን ዕዳም አይነጻጸርም (ማቴ.18፡24፣28)!
እንግዲህ መቶ ዲናርን ዕዳ ይቅር ብሎ እልፍ መክሊትን የሚቀበል ኾኖ ሳለ ይህቺን ጥቂት ዕዳስ እንኳን ይቅር ሳይል ጸሎቱን በራሱ ላይ የሚያደርስ ይህ ሰው የማይገባው ቅጣት እንደ ምን ያለ ቅጣት ነው? ምክንያቱም “እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን” ብለህ እየጸለይክ ሳለ አንተ ግን ከዚያ በኋላ ይቅር የማትል ከኾነ እግዚአብሔር ምሕረቱን ወይም ቸርነቱን ኹሉ እንዲያርቅብህ ካልኾነ በቀር ሌላ ምንም እየለመንከው አይደለም፡፡ “እኔ ይቅር በለኝ ብቻ ነው እንጂ የበደሉኝን ይቅር እንደምል በደሌን ይቅር በለኝ ብዬ አልጸልይም” የሚል ሰው ደግሞ አለ፡፡ ታዲያ ይኼ ምንድን ነው? አንተ እንዲህ ብለህ ባትጸልይም እግዚአብሔር ግን እንዲህ አያደርግም፤ ይቅር የሚልህ አንተ ይቅር ስትል ነው፡፡ ይህም ከዚያ በኋላ እንዲህ ብሎ ግልጽ አድርጎታል፡- “ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ የሰማዩ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም” (ማቴ.6፡15)፡፡ ስለዚህ ጸሎቱን ሙሉ ባትደግመው ወይም ዕለት ዕለት እንደዚያ ብለህ ስትጸልይ ፈርተህ ከባልንጀራህ ጋር እንድትታረቅ ብሎ እንድትጸልው ባዘዘህ መንገድ ሳይኾን ቈርጠህ ብትደግመው እንኳን ደገኛ መንገድ ነው ብለህ አታስብ፡፡
“ብዙ ጊዜ ለምኜዋለሁ፤ ተማጽኜዋለሁ፤ ማልጄዋለሁ፤ ሊታረቀኝ ግን አልቻለም” ብለህ አትንገረኝ፡፡ እስክትታረቀው ድረስ በፍጹም አታቁም፡፡ ጌታችን ሲናገር፡- “መባህን ትተህ ኺድ፤ ወንድምህንም ለምነው” አይደለምና፡፡ ያለው፡- “ኺድ፤ ታረቅ” ነው (ማቴ.5፡24)፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን ብዙ ጊዜ ለምነኸው ቢኾንም እስክታሳምነው ድረስ ግን ይህን ማድረግህን አታቋርጥ፡፡ እግዚአብሔር ዕለት ዕለት ይለምነናል፤ እኛ ግን አንሰማውም፡፡ ኾኖም [አልሰሙኝም ብሎ] መለመኑን አላቋረጠም፡፡ ታዲያ አንተ ባልንጀራህን ለመለመን ትታጀራለህን? እንዲህ የምታደርግ ከኾነስ ልትድን የምትችለው እንዴት ነው?

የይቅርታ ልብ ይስጠን።

03/12/2022

እውነት ነው የምላችሁ አንብብ እና የሰላም እንቅልፍ ተኙው

አስታዋሽ አምላኬ ሆይ

በተደነቀ ዝምታ የምትኖር አስታዋሽ ፈጣሪ ሆይ አመሰግንሃለሁ፡፡ አንተ በዝምታህ ውስጥ መልስ አለህና አከብርሃለሁ፡፡

እንደማይሰማ ዝም ብትልም፣ እንደማይሰጥ ብትዘገይም፣ እንደማይገደው ብታልፍም ዓላማ አለህና ተመስገን፡፡ የቀኑን ምልክት በማየት አለባበሴን ባስተካክልም፣ የዘመኑ ምልክት ግን ሳይገባኝ በአንደበቴ ጠፍቻለሁና አድነኝ፡፡ ዓለም ስትንጫጫ ዝም ማለትን አስተምረኝ፡፡

እውነት ስናገር ሰዎች ይከፋቸዋል፣ ሐሰት ስናገር ፍቅርህ ያዝንብኛል፡፡ እባክህ የአንተ ወገንተኛ አድርገኝ፡፡ ያንተ ወገን በሁለት ወገን እንደተሳለው ቃልህ ለማንም አይመችም፡፡

መተማመን በጠፋበትና ቋንቋ በተደባለቀበት ዘመን የልቤና የአንደበቴ ጠባቂ ሁን፡፡ በሰነፎች ዘመን ጠቢብ አድርገኝ፡፡

ውዴ ሆይ፡ የሚያልፍ ዘመን የማያልፍ ንግግር እንዳያናግረኝ እባክህ ተቆጣጠረኝ፡፡

ሰዎች እንደ እኔ ካላሰቡ ከሚሉ ግትሮች ጠብቀኝ፣ እኔም ሰዎች እንደ እኔ ካላሰቡ በሚል የሕይወት ጠንቅ ውስጥ እንዳልገባ ያዘኝ፡፡

ሥጋዬን አላምነውምና መንፈስህ ይምራኝ፡፡ የገዛ ፍቅሬ እንጂ ሌሎችን መጥላት ከማንም ጋር እንዳያፋቅረኝ ተጠንቀቅልኝ፡፡ ያምራል ብዬ ከተናገርኩት ይከፋል ብዬ የተውኩት እንደሚሻል አሳየኝ፡፡

ዘላለም የሚጸናው የአሁኑ ሳይሆን ያንተ ሥርዓት መሆኑን ግለጥልኝ፡፡ ለስሜቴ የሚስማማኝን እየመረጥኩ ቃልህን እንዳልታዘዝ እማጸንሃለሁ፡፡

ተስፋህ ተስፋ ያደረኳቸውን ነገሮች ሁሉ ይውረሰው፡፡ ሰዎች እንዲያምኑኝና ፍትሐዊ ነው እንዲሉኝ የማደርገውን ጥረት ከእኔ አርቀው፡፡

አንተ ትበቃኛለህና ልቤን በጥላህ አኑረው፡፡ በማስፈልግበት ሰዓት እንዳልተኛ እርዳኝ፡፡ ሰው ሁሉ የመፍራት ሥልጣኑን ተጠቅሞ ሲፈራ እኔን በዓለት ላይ አቁመኝ፡፡

ሰዎች ሲያዘምሙ ሳይ ነቢይ እንዳልሆን ጠብ ቀኝ፡፡ ካንተም ይልቅ ቸር እንዳልሆንኩ አስረ ዳኝ፡፡ እገሌ በደለ እንጂ እኔ በደልኩ የማይልን አገርና ትውልድ ፈውስ፡፡ የመካሰስ ወራትን በይቅር ነፋስ ለውጥ፡፡

በአገራችን ሁሉም ሊቅ ነውና የሚማር መንፈስን ስጠኝ፡፡ የሰዎች ርእስ ያልሆኑትን የተረሱትን አንተ አስታውስ፡፡

ኃያላን ሲጣሉ እኛ እንዳንደቅ አውጣን፡፡ በደግ ቀን ያልጸለዩት በክፉ ቀን አይረዳምና በጸሎት አትጋኝ፡፡

አስቤ እንድናገር ሊቃውንት ነግረውኛል፡፡ ነገር ግን አንተ በእኔ ቦታ ብትሆን ለሰውዬው የምትናገረውን እንድናገር እርዳኝ፡፡

የጥያቄዎች ሁሉ መልስ «አምላኬ በእኔ ቦታ ቢሆን ምን ያደርግ ነበር?» የሚለው መሆኑን አብራልኝ፡፡

ጣዕም ባለው ስምህ ለዘላለሙ አሜን።

የማይሾሙህ ንጉሤ

ከከበሩት በላይ ከብረህ የምትኖር የማይ ሾሙህ ንጉሤ፣ የማያበድሩህ ብልጥግናዬ ሆይ አመሰግንሃለሁ፡፡ ዓመታት ዘመናት ብዙ ወዳጆቼን ሲለውጡ እኔም በብዙዎች ስለወጥ አንተ ግን ያው አንተ ነህና አመሰግንሃለሁ፡፡

ልብስ የሸፈነውን ጓዳዬን፣ ጥርስ የሸፈነውን ልቤን ላንተ እገልጣለሁ፡፡ ልትረዳኝ አቅምና ፈቃድ ላለህ ላንተ መሸነፌን አወራለሁ፡፡ አንተ እንደ ሰው አልፎ ሂያጅ አይደለህምና እመካብሃለሁ፡፡

ሰው ሁሉ ራሱንና አካባቢውን በሚያ ዳምጥበት ዘመን ቃሌ አይሰማምና እባክህ አንተ ስማኝ፡፡

ፍቅርና መልካምነት የራቀኝ የትዝታ ሰው ሆኛለሁና ዘመኔን እንደ ቀድሞው አድስ፡፡ ሰው በተሰለቻቸበት ዘመን የማይጠገብ ፍቅር ስጠኝ፡፡ ክፉን በክፉ ሳልመልስ በመልካም ማሸነፍን አድለኝ፡፡

በፀፀት የትላንትናውን፣ በንዴት የዛሬን ከመመልከት በእምነት የወደፊቱን እንዳይ እባክህ እርዳኝ፡፡ በማየው ተወስኛለሁና የተስፋ አገሬን አጉላልኝ፡፡

ሰው በሰው ሆኖ ሲጠቃቀም እኔ ግን ካንተ በቀር የምጠራው የለምና ድረስልኝ፡፡ ሰዎችን በፍጹም ልቤ እንድወዳቸው እርዳኝ፡፡ ሰዎችም እኔን በመውደድ እንዳይፈተኑ አግዛቸው፡፡ ቃላት ቆርጣሚ አማርኛ ሰንጣቂ ከመሆን እውነት ቀማሽ አድርገኝ፡፡ ሰዎች ቋንቋን ያዳምጣሉ፣ አንተ ግን አሳቤን ተረዳልኝ፡፡

ሁሉም ወደ ራሱ አሳብ ሲያዘነብል እኔን ግን በአሳብህ ማርከኝ፡፡ ባልንጀርነትና ትዳር ባቢሎን ሲሆን ለእኔ ግን ቋንቋዬ ሁንልኝ፡፡ የሰው አንደበት ያቆስላል፣ የሚያዩት የሚሰሙት አያስደስትምና ለእኔስ ወደ አንተ መቅረብ ይሻለኛል፡፡

ንጹሕ ምንጭ እንደሚደፈርስ የብዙ በጎ ሰዎች አእምሮ ደፍርሷልና እባክህ አድነኝ፡፡

ከልብ የሚያመልኩህ ሳይበላሹብህ ውሰዳቸው፡፡ የሃይማኖት ቃላችንን ማንም ሊሰማው ጠልቷልና ደግ ዘመን አምጣልን፡፡ ራሴን በቃልህ እንጂ በደከመው ወንድሜ እንዳልመዝን እርዳኝ፡፡ በሚያስጠጋው ስምህ ለዘላለሙ አሜን።
በምስጋና ተውበህ

በክብር ደምቀህ፣ በምስጋና ተውበህ፣ በአእላፋት ተከበህ፣ በኪሩቤል ጀርባ ነግሠህ የምትኖር የማትወሰን፣ ለሁሉ ወሰን የሰጠኸው አምላኬ ሆይ አመሰግንሃለሁ፡፡

ለዚህ ሁሉ ፍጥረተ ዓለም ምክንያቱ አንተ ነህ፣ አንተ ግን ምክንያት ሳትሻ ትኖራለህና አከብርሃለሁ፡፡

እንደ ወደድኸኝ ልወድህ አልችልም፣ እንዴት እንደወደድከኝ እንኳ የፍቅርህን ልክ ማወቅ ተስኖኛልና እባክህ አግዘኝ፡፡

ባምነው መንግሥተ ሰማያት እገባለሁ፣ ብክደው ገሀነመ እሳት እወርዳለሁ ብዬ ሳይሆን ወዶኛል ሞቶልኛል ብዬ እንድከተልህ እርዳኝ፡፡

አቅሜን አላውቅምና በፍቅር አቅሜን አሳውቀኝ፡፡ በመሰበር መማር አይረሳም፣ እኔን ግን በመውደድህ አስተምረኝ፡፡

ሰው ሁሉ ለመከራው አያቅድም፡፡ መከራ ግን በሰው ላይ ያቅዳልና ይሆናል ብዬ መጠበቅንም አስተምረኝ፡፡

የምወዳቸው ያለ ችግር እንዲሆኑ የማደርገውን ጥረት ከእኔ አርቀው፣ አይሳካምና፡፡ ለማንም ካንተ በላይ ደግ እንዳልሆንኩ አሳውቀኝ፡፡ የማልፍበትን የኑሮ ገጽ ሁሉ «ይህም ሕይወት ነው» እንድል አሰልጥነኝ፡፡

ፀጥታ ረብሻ ሲሆን አጽናኝ፡፡ ማንም እንዳይደርስብኝ የከለልኩት የፀጥታ ሰዓቴን ለተጨነቁት ማዋልን አድለኝ፡፡

ራስን በማዳመጥ ሳይሆን ሌሎችን በመርዳት ያለውን ደስታ ግለጥልኝ፡፡

የማላደርገውን እንዳልናገር፣ የተናገርኩትን እንድፈጽም፣ ከሁሉ በላይ ተስፋ ሰጪ ሰው እንድሆን እለምንሃለሁ፡፡ ሰውን የሚያህል ፍጡር በማይፈጸም «እሽ» እንደ ዶሮ እንዳላባርር ማስተዋል ስጠኝ፡፡

«አይሆንም» በጊዜው ጥሩ መልስ መሆኑንም ግለጥልኝ፡፡

ጌታዬ ሆይ ምንም ባስቸግርህ ለፍላጎቴ አሳልፈህ አትስጠኝ፡፡ ከሚያፀፅት ሕሊና አድነኝ፡፡

ሥጋዬ የበላይ ሆኖብኛልና አንተ ግዛኝ፡፡ ላንተ ከመገዛት ውጪ ሌላ አሳብ የለኝም፡፡ ለመታዘዝ ግን ፍላጎት እንጂ አቅም የለኝምና ጸጋህንና የጸጋ ስጦታህን ላክልኝ፡፡

አውቄህ እንዳላወቀህ ከመሆን አድነኝ፡፡ ለዚህ የእንግድነት ኑሮ እንዳልረሳህ ከራሴ ጠብቀኝ፡፡ ምናልባት ነገ ብትመጣ ከነኃጢአቴ እንዳታገኘኝ ነጩን ሸማህን አልብሰኝ፡፡

ወደ ፍጡራን ብጠጋም ጽድቃቸው ለራሳቸውም አልበቃቸውም፣ አንተው በሚተርፈው ጽድቅህ አጽድቀኝ፡፡

በማይታበለው እውነትህ ለዘላለሙ አሜን፡፡

የነገ ሰው ይበለን

24/11/2022

🌿❤️ ዛሬ የነቢያት ፃም (የገና ፃም) ተጀምራል።

በዚህ ፃም ሰለተራቡ፣ስለ ተጠሙ፣ ስለታረዙና ስለተሰደዱ ሰዎች ስለሃገራችንም
ሰላም አበክረን የምናስብበት ወቅት ነው።

ለጥቂት ደቂቃ በዚህ ህይወት ያሉትን ወገኖች እናስባቸው መልካም የፃም ወራት
ይሁንላችሁ የንስሀ ፍሬ የምናፈራበት ለስጋ እና ደሙ የምንበቃበት ያድርግልን አሜን 🤲❤️🤲

The first day a week Sunday a beautiful  day thanks GOD
03/07/2022

The first day a week Sunday a beautiful day thanks GOD

06/04/2022

# ይድረስ_ለሴቶች_እህቶቼ_አንብቡት
ወንዶችም አንብባችሁ ለእህቶቻችን ሼር ሼር ሼር በማድረግ አጋሩ
አዲስ ተች ስልክ የገዛችውን ልጅ አባቷ ሲያያት . . . . . .››
አባት ፡ “”ስልኩን ስትገዢ በመጀመሪያ ያደረግሽው ምንድነው ? “” ብሎ ጠየቃት፡፡
ልጅ ፡ “”በመጀመሪያ ያደረኩት . . . ስክሪኑ እንዳይጫጫር መከላከያ ስቲከር ለጠፍኩበት . . . “”

አባት ፡ “” እንደዚ እንድታደርጊው የገፋፋሽ ሰው እለ ?””
ልጅ ፡ “” የለም ! ! ! “”
አባት ፡“”ያመረቱትን እንደ ማንቋሸሽ አይሆንም ግን . .””
ልጅ ፡“”ኧረ አባዬ ! እንደውም የሚመክሩን እንድንለጥፍበት ነው !”
አባት ፡ “” የሸፈንሽው ግን ርካሽ ስለሆነ ወይም ስለሚያስጠላ ነው ??? “”
ልጅ ፡ “”” በነገራችን ላይ የሸፈንኩት . . . እንዳይበላሽብኝ እና ብዙ ግዜ
እንዲያገለግለኝ ስለምፈልግ ነው ! “”
አባት ፡ “”” ስትሸፍኝው . . . ውበቱን አልቀነሰውም “”
ልጅ ፡ “”” እንደውም በጣም አምሮበታል በዛ ላይ እንዳይበላሽ
ይከላከልልኛል “”
አባት ፡ በአባትነት ዓይን እያያት “”” አንድ ጥያቄ ብጠይቅሽስ. . .
ከስልክሽ የሚበልጠውን ገላሽን እንድትሸፍኝው . . . እሺ ትይኛለሽ ወይ ??? ``
ሁሌም አባታችን እግዚአብሔር ይጠይቀናል በሰው ላይ አድሮ . . . . ብቻ በብዙ
ነገር ራሳችንን እንድንሸፍን ይጠይቀናል !
☞የምናስተውል ካለን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል"፤
፨ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን
ይሸፍኑ (1 ኛ ጢሞ 2፥9)
፠ በሚሞት ስጋችሁ ሐጢያት አይንገስ
ብልቶቻችሁን የፅድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ (ሮሜ
6፥12-14)
፠ ከሴት ጋር አለመገናኘት መልካም ነው ካልተቻለ ዝሙትን ለመከላከል በአንድ
ይፅና ከዚህ ውጭ ጉዞ ወደ እሳት ነው (1ኛ ቆሮ 7፥1)
፠ ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱ
ያፈርሰዋል ቤተ መቅደሱም እናንተው ናችሁ (1ኛ ቆሮ 3፥17)
፠ የወንድ ልብስ የለበሰች ሴት በአምላክ ዘንድ የተጠላች ናት (ዘዳ 22፥5; ዘፀ
39፥28)
፠ ፀጉሯን ሳትሸፍን የምትፀልይ ሴት እራሷን ያዋረደች ናት(1ኛ ቆሮ 11፥5)
እንድናስተውል እና እንደ እግዚአብሔር ቃል እንድንኖር እግዚአብሔር ይርዳን
አሜን (ለምታውቁት ሰው እና መንፈሳዊ ግሩፕ ትልኩ ዘንድ በእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም አበክሬ እጠይቃችኋለሁ አደራ)

13/03/2022

ምኹራብ (የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት)

ምኩራብ:- ማለት ቤተ ፀሎት( የፀሎት ቤት)ማለት ነው።
ኢየሱስም በሰንበት ቀን ከ አይሁድ ምኹራብ በገባ ጊዜ ሙኹራቡን ገበያ አድርገውት ሲገበያዩበት አገኛቸው። ይህን ሲያደርጉ ባያቸው ጊዜ ቤቴ የፀሎት ቤት ነው ተብሎ የተፃፈውን አላነበባችሁም ት.ኢሳ 26:7 እናተ ግን ገበያ አደረጋችሁት በማለት በተናቸው እቃቸውንም ገለበጠባቸው። በጎቹንም በሮቹንም በገመድ እየገረፈ አባረራቸው። ዮሐ.ወንጌል 2 : 17 ደቀ መዛሙርቱም የቤትህ ቅናት በላኝ የሚለው ትንቢት ለካ አሁን ተፈፀመ በማለት አስተዋሉ። መዝ 68:9

የሰንበት መዝሙር ከፆመ ድጓ

ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ የሀይማኖት ቃልን አስተማረ ከመስዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ የሰው ልጅ የሰንበት ጌታዋ ነው።የአባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት ቤቴስ የፀሎት ቤት ይባላል እያለ የሀይማኖትን ቃል አስተማራቸው።ወደ ምኩራባቸውም ገብቶ ዝም ይሉ ዘንድ ገሰፃቸው እነርሱም ትምሕርቱን የቃሉን ግርማና የአነጋገሩን ጣዕምና የአንደበቱን ቅልጥፍና አደነቁ።

ምስባክ

እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩክ ወድቀ ላእሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ
መዝ 68:9
ትርጉም

የቤትህ ቅንዐት በልታኛለችና
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቋልና
ነፍሴን በፆም አስመረርኋት

ወንጌል
ዮሐንስ ወንጌል ም 2፥12-ፍፃሜ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

05/03/2022

እየጦሙ አለመጦም

ተወዳጆች ሆይ! እየጦሙ የጦምን ፍሬ ፃማ የማያገኙበት ሁኔታ እንዳለ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያላችሁኝ እንደሆነም፦

➛ ከምግበ ሥጋ ተከልክለን ከምግበ ኃጢአት ያልተከለከልን እንደ ሆነ፣
➛ ከጥሉላት ርቀን ነዳያንን ያልጎበኘን እንደ ሆነ፣
➛ ወይን ከመጠጣት ታቅበን በክፉ መሻት ከመስከር ያልራቅን እንደ ሆነ፣
➛ ጀምበር እስክትጠልቅ ድረስ ከእህል ከውኃ ርቀን በዓይናችን መልካም ያልሆኑ

ትዕይንቶችን ከማየት ያልጦምን እንደሆነ ነው ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እመልስላችኋለሁ፡፡ ስለዚህ እየጦሙ እንዲህ አለመጦም እንዳለ ዕወቁ፤ ተረዱም፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ

አምላከ ቅዱሳን እየጦሙ ካለመጦም ይሰውረን!

07/01/2022
04/11/2021

"መንፈሳዊ ጥበብን የምትወድ ነፍስ ዘወትር እግዚአብሔርን ታመሰግናለች፡፡ ሰው ሆይ! ሰዎች ክፉ ነገር ሲያደርሱብህ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያን ጊዜም ክፉው መልካም ይኾንልሃል፡፡

"እንዴት?" ብለህ የጠየቅኸኝ እንደኾነም፦ "በደል የሚፈፅመው ክፉ ነገር የሚቀበለው ሳይኾን ክፉ ነገር የሚያደርሰው ሰው ነውና" ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እመልስልሃለሁ፡፡

ስለዚህ ዘወትር እግዚአብሔርን አመስግን፡፡ ብትታመምም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ሀብት ንብረት ብታጣም አመስግን፤ በሐሰት ቢከሱህም አመስግን፡፡ እንደ ነገርኩህ ተጎጂዎቹ ክፉ ተቀባዮች ሳይኾኑ ክፉ አድራሾች ናቸውና፡፡"

20/08/2021

፨፨፨፨ ፍቅር ይበልጣል ፨፨፨፨
-----------------💖💖------------------

ባልና ሚስት በሚኖሩበት አንድ ቤት ውስጥ ከመሸ በራቸው ይንኳኳል ። ሚስት ለመክፈት ትሄዳለች ከዛም ባየችው ነገር በጣም ተገረማለች ። ሶስት ነጫጭ ሽበት ያለባቸው የሚያማምሩ ባለግርማ ሞገስ ሽማግሌዎች ነበሩ ። አቤት ግቡ ምን ፈልጋቹ ነው አለቻቸው ፈራ ተባ ባለ የአነጋገር ድምፀት ። ሶስታችንም አንገባም አንዳችን ነን የምንገባው እራሳችን እናስተዋውቅሽ አሉና ራሳቸውን ማስተዋወቅ ጀመሩ ። 1ኛው ስኬት እባላለው እኔ ቤትሽ ከገባሁ አሳብሽ ሁሉ ይሳካል አላት ፣

2ተኛው ገንዘብ እባላለው እኔ ቤትሽ ከገባሁ ችግር የሚባል አይኖርም አላት ፣

3ተኛው ፦ ፍቅር እባላለው ፍቅር ማብራሪያ የለውም አላት ። ከዛ ሚስት ባለቤቴን ላማክር ብላ ወድ ውስጥ ገባችና ልክ ለባለቤቷ ስትነግረው በነገሩ ተደንቆ እንዲህ አለ ። በእውነቱ ይሄ እድል ሊያመልጠን አይገባም ገንዘብን የሚያክል ነገር ደጅ ቆሞ መወያየት ግፍ ነው ሰርቼ ከሰው በታች የሆንኩት ገንዘብ ሰለሌለኝ ነው እና ፈጠን በይ ገንዘብን ወደቤታችን እንዲገባ ንገሪው አላት ሚስትየውም በሀሳቡ ተስማምታ ገንዘብን ልትጠራው ስትል ልጇ እንዲ አላት እማዬ ገንዘብ ገብቶ አባዬ እንደለመደው ማታ ማታ ከሚደበድብሽ ፍቅር ገብቶ ሰላምሽን ብታገኚ አይሻልም ? አላት ።

እሷም በልጇ ሀሳብ ተደስታ ባልየውን ፍቅር ካልገባ ብላ ሞገተቹ በመጨረሻም ፍቅር እንዲገባ ወስነው ወደ ሽማግሌዎች ሄዱና ፍቅር የተባልከው ሰው ወደቤታችን ግባ ይሉታል ።እሱም ተከትሏቸው ይገባል ባልና ሚስቱም። ዞር ብለው ሲያዩ 3ቱም።ሰዎች ቤት ገብተው ቆመዋል ባልየው ደንግጦ እኛ በቤታችን እንዲገባ ያልነው ፍቅርን እኮ ነው አለ ከሽማግሌዎቹም አንዱ ዞር አለና ልክ ብለሀል ።

ነገር ግን ፍቅር ካለ ስኬት አለ ፍቅር ካለ ገንዘብ አለ ። በማለት 3ቱም ወደቤታቸው ገቡ ፍቅር የሆነው ፈጣሪ ወደቤታችን ሲገባ መልካም የሆኑ በሙሉ አብረው ይገባሉ ።

💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖.... ክርስቶስ የሞተለት ዓላማ ፍቅር ነው.... ፍቅር የህይወታችን ህልውና ነው.... ፍቅር ከሁሉም ይበልጣል "፤ ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። "
(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4: 8)

07/08/2021

እውነተኛ ወዳጅ፥ ወዳጅ መኾኑ የሚታወቀው ጓደኛውን መገሠጽ ሲችል ነው፡፡

ኹላችንም በየጊዜው ኃጢአት እንሠራለን፡፡ አብዛኞቻችን ደግሞ ኃጢአታችንን እንዳላየነው ኾነን ለማለፍ እንጥራለን፡፡ ለራሳችን ይቅርታ እንቸራለን፡፡ ወይም ምንም እንዳላጠፋ ሰው ለመምሰል እንሞክራለን፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሰዓት እውነታውን በትክክል እናይ ዘንድ ዓይናችንን የሚከፍት እውነተኛ ወዳጅ ያስፈልገናል፡፡

አንተ ሆይ! እስኪ ራስህን መርምር፡፡ ጓደኛህ እውነታውን እንዲያይ ታደርጋለህ? ጓደኛህ ኃጢአት ሠርቶ ሲያበቃ ለራሱ ይቅርታ ሲያደርግ ይቅርታው ያደረገው ይቅርታ ትክክለኛ እንዳልኾነ እንዲያውቅ ታደርጓለህን? እንዲህ እውነታውን ስትነግረው ምናልባት ጓደኛህ አለአግባብ ሊቈጣህ ይችላል፡፡ ታዲያ ሲቈጣህ ለመታገሥ ዝግጁ ነህን? ወይስ ከዚህ በተቃራኒ የጓደኛህን ኃጢአት አይተህ እንዳላየህ ነው የምትኾነው?

ጓደኛ ስንመርጥ ከእኛ ጋር እውነተኛ ወዳጅ ሊኾን የሚገባውን መኾን አለበት፤ ስንቈጣው እንኳን ቁጣችንን ታግሦ ስናጠፋ የሚያርመን ሊኾን ይገባል፡፡ እንደዚህ ካልኾነ ጓደኝነት ጥልቀት አይኖረውምና፤ ጓደኞች ነን መባባላችን ጥቅም የለውምና፡፡

ልናውቀው የሚገባን ነገር ግን አለ፡፡ ጓደኛችን በሚያጠፋበት ሰዓት ተግሣጽ አስመስለን እንዲሁ ክብሩን በሚነካ መልኩ ልንናገረው አይገባንም፡፡ ተግሣጻችን ኹልጊዜ እውነቱን ብቻ እንጂ የተጋነነና ሌላውን መልካምነቱን የሚክድ መኾን የለበትም፡፡ ጥፋቱን ስንነግረው ኹልጊዜ በቀና ልብ እንደምንነግረው እርግጠኛ እንዲኾን ማድረግ አለብን፡፡ ይህን የምናደርገው ከፍቅራችን የተነሣ እንጂ ከቅናት ወይም ከንቀት እንዳልኾነ እንዲያውቅ ማድረግ አለብን፡፡ እውነተኛ ወዳጅነት ማለት ይህ ነውና፡

Address

London
N41QW

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኦርቶዶክስ ተዋህዶ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ኦርቶዶክስ ተዋህዶ:

Share