Megabe Sireat qesis michael's Page

Megabe Sireat qesis michael's Page Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Megabe Sireat qesis michael's Page, Religious organisation, London.

We seek to follow the teaching of Jesus Christ, based on the the teachings and values of Ethiopian Orthodox Church, we aim to nurturing the Christian faith, building and supporting Christian Community, developing educational programmes in the Community.

23/12/2024

ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክቶ ከዩናይትድ ኪንግደምና አየርላንድና ማኀበረ ካህናት  የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ ...
10/09/2024

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክቶ ከዩናይትድ ኪንግደምና አየርላንድና ማኀበረ ካህናት የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት።

በዪናይትድ ኪንግደም እና አየርላንድ እንዲሁም በመላው ዓለም የምትገኙ ሊቃውንተ ቤተከርስቲያን፡ መምህራን፣ ካሀናት እና ዲያቆናት ፡ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች።
የተወደዳችሁ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ምዕመናንና ምዕመናት የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሁላችሁም፡

የዪናይትድ ኪንግደም እና አየርላበሠላም ንድ ማኅበረ ካህናት፡ እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገረን አሸጋገራችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

እንኳን ከ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም ወደ
ከ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም በሰላም አሸጋገረን፣ አሸጋገራችሁ።

አንተሰ አንተ ክመ : ወዓመቲከኒ ዘኢይኀልቅ:: “አንተ ግን ያው አንተ ነህ ፤ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም” መዝ ፦ 101(102) ፥ 27

ፈጣሪያችን በቸርነቱ ዓመታትን ያቀዳጃል፡ ዓመታትን እያሳለፈ ዓመትን በየጊዜው ይሰጠናል፤ ይህም ለኛ ለሰዎች ጥቅም ይውል ዘንድ ነው። የአዲስ ዓመት መምጣት ፡ አዲስ ተስፋ የሚሰጠን እና ከተጠቀምንበት የሚያድሰንና እንደገና ሙሉ ሰዎች የሚያደርገን ከአምላክ የሚስጥ ልዪ ስጦታ ነው፣

የዘመናት ባለቤት ቸሩ ፈጣሪያችን ቅዱስ እግዚአብሔር አሮጌውን አሳልፎ አዲስ ዓመት ሲሰጠን በእርቅ፣በይቅርታ እና በንስሐ በመታደስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈፀም ለሕይወታችን ብርታትና ለእምነታችን ጽናት የሚበጅ መንፈሳዊ ጥንካሬ ላይ ለመድረስ የሚያስችለንን መልካም ሥራ ለመሥራት እና መንፈሳዊ ፍሬ ለማፍራት የተሰጠን ሌላ አዲስ እድል መሆኑን እንገነዘባለን ።

ዓመት በራሱ አዲስ አይሆንም፤ የዘመኑ ቁጥርና የወንጌላውያኑ በተራ መፈራረቅ ካልሆነ ወራቱ ሳምንታት ቀናቱ እንዳለፈው ዓመት ነው። በተሰጡን ወራቶች ሳምንታት ቀኖችና ሰዓታት የምናደርጋቸው የምንተገብራቸው ተግባር ናቸው ዓመቱን በእውነት አዲስ የሚያደርጉት፡፡

ዓመቱ በእርግጥ አዲስ ዓመት እንዲሆን አዲስ ሰው መሆንን ይጠይቃል፡፡ ከክፉ ሥራ ወደ መልካም ሥራ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ በሃይማኖታዊ ጉዳይ ቸልተኛ ከመሆን ጠንካራ ተሳታፊ ለመሆን ሥንሰራ ዘመኑ አዲስ ይሆናል። አዲስን ወይን ጠጅ በአሮጌ አቁማዳ ውስጥ እንደማይጨምሩት አዲሱና አሮጌው እንደማይስማሙ ሁሉ ሰውም በአዲስ መንፈስ ካልተቀበለው አዲሱ ዓመት አይጠቅመውም፡፡ ሰው አኗኗሩን ወደ መልካምነት በመለወጥ የሚኖር ከሆነ ሁሉም አዲስ ቀን አዲስ ወር አዲስ ዓመት ይሆንለታል፡፡

ለስም አጠራሩ ምስጋና ይግባውና ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ከርስቶስ በማቴዎስ 9፡16-17 ሲናገር " በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል። በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠበቃሉ "። አዲሱን ዓመት በሥጋ ፈቃድ ከመመላለስ በመንፈስ ፈቃድ እንመላለስ። ገላ 5÷22-26
የተወደዳችሁ የክርስቶስ ቤተሰቦች ዘመናትን የሚሰጥና የሚቆጣጠር እግዚአብሔር ነው፤ ስለሆነም እግዚአብሔር የሚነግረንንና ከእኛ የሚፈልግብንን መስማትና ማድረግ በእጅጉ ይጠበቅብናል፣ አዲሱ ዓመት በሁላችንም ዘንድ ፍሬ ያለው እንዲሆን፣ ለምድራዊ ኑሮአችን የምናጠፋውን ጊዜና የምናሳየውን ጥረት ለመንፈሳዊ ህይወታችን ማደግ ክርስቲያናዊ አኗኗራችን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የምንጓዝ ልንሆን ይገባል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ዘመንን የሚሰጠው ለፍስሐ ዕድሜን ደግሞ ለንስሃ ነውና።

ስለዚህ አዲሱን ዓመት የቀደመውን የክፋት ሃሳብ በመተው፡ ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ የሆነውን አካሄድ በመተው፡ አዲስ ፍጥረት በመሆን፡ አእምሮን ለእግዚአብሔር ቃል በማዘጋጀት፡ አዲሱን ሰው በመልበስ በንስሐ ተመልሰን ሥጋውን በመብላት ደሙን በመጠጣት፡ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቶ በማድረግ፡ በመፈጽምም ልንመላለስበት ይገባል። ይህንን ዕድል የሰጠን ከዚህ ዘመን ያደረሰን ቸሩ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ይመስገን።

የተወደዳችሁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ምዕመናንና ምዕመናት የእግዚአብሔር ቤተስቦች፡ በድጋሚ እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገረን አሸጋገራችሁ።! አዲሱን ዓመት የንስሐ ፣የፍሥሓ የበረከትና የምሕረት ፣ የሰላምና የፍቅር ዓመት ያድርግልን። ከተዋሕዶ ማማ ፣ ከመስቀል ዓላማ ፣ከወንጌል ከተማ ሳያናውጸን። በቤቱ በሃይማኖት በምግባር አጽንቶ ያኑረን። ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ስለ ሕዝበ እግዚአብሔር መልካም የምንሰማበት የምናይበት ዘመን ያድርግልን:: ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅር አይለየን።

ባደረባችሁ ሕመም ምክንያት በየጸበሉ፡ በሐኪም ቤቶችና በየቤቱ በሕመም ላይ የምትገኙ ሁሉ የምሕረት አባት ምሕረቱን ያውርድላችሁ፤ በከባድ ሀዘን ውስጥም ያላችሁትን ቸሩ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር መጽናናትን ይስጣችሁ፤ በየማረሚያ ቤቶችም ያላችሁትን ፍትህን ይስጣችሁ፣ እግዚአብሔር በምሕረቱ ይፍታችሁ፤ በጦርነት፡ በረሃብ፡ በስደት በመፈናቀል በተለያዩ ምክንያቶች ከቤተሰቦቻችሁ ርቃችሁ ለምትገኙ፣ በሙሉ መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆንላችሁ ምኞታችንና ጸሎታችንም ነው።

አዲሱ ዓመት: ዘመነ ማቴዎስ ፤ የሰላም የጤና የፍቅር የበረከት የብልጽግና የደስታ ዘመን ይሁንልን።
የእግዚአብሔር አብ ፍቅር የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት በሁላችን ላይ ለዘለዓለሙ አድሮ እና ፀንቶ ይኑር: አሜን።

ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም
ዩናይትድ ኪንግድም
ሎንዶን።

✝️ ሁለተኛው ሳምንት ቅድስት ይባላል። የዛሬው የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ቅዱስ ያሬድ)✝️ ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ ሀቡ ስብሐተ ለስሙ አክብሩ ሰንበተ ተገ...
16/03/2024

✝️ ሁለተኛው ሳምንት ቅድስት ይባላል።
የዛሬው የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ቅዱስ ያሬድ)

✝️ ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ ሀቡ ስብሐተ ለስሙ አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ ዝግቡ ለክሙ መዝገበ ዘበሰማያት ኅበ ፃፄ ኢያማስኖ ወኢይረክቦ ሰራቂ ድልዋኒክሙ ንበሩ ዘበላዕሉ ጸልዩ ኀበ ሀሎ ክርስቶስ።

✝️ ትርጉም: ለእግዚአብሔር ተገዙ ስሙንም ጥሩ ሥራውንም ለአሕዛብ ንገሯቸው ለስሙም ምስጋናን ስጡ /አቅርቡ/ ሰንበትን አክብሩ እውነትንም አድርጉ ብል የማያበላሸው ሌባም የማያገኘው በሰማያት ያለ መዝገብን ለእናንተ ሰብስቡ፤ ተዘጋጅታችኹም ተቀመጡ ክርስቶስ ወዳለበት ወደላይ አስቡ፡፡

✝️በዛሬው እለት የሚነበበው /የሚጸለየዉ/ የመጽሐፍ ቅዱስ ምእራፍ እና ቁጥር።

✝️ የቅዱስ ዳዊት መዝሙር 95

➕እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ ምስጋና ውበት በፊቱ
ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው፡፡

✝️ ወንጌል ፡ማቴ.6÷16-24

➕በምትጾሙበት ጊዜ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ እነርሱ እንደ ጾሙ ለሰው ይታዩ ዘንድ መልካቸውን ይለውጣሉና÷ እውነት እላችኋለሁ ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡

✝️ 1ኛ ተሰ.4÷1-12

" ➕ይህንም ለማድረግ አትደፋፈሩ፤ በሁሉም ወንድሞቻችሁን አትበድሉ፤ አስቀድሜ እንደ ነገርኋችሁና እንደ አዳኘሁባችሁ÷ በዚህ ሁሉ እግዚአብሔር የሚበቀል ነውና፡፡ እግዚአብሔር ለቅድስና እንጂ ለርኲሰት አልጠራንምና፡፡

✝️ 1ኛጴጥ.1÷13-ፍጻሜ

➕እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ክፉ ምኞት አትከተሉ፡፡ ነገር ግን የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እንዲሁ እናንተም በአካሄዳችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፡፡ “እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ”

✝️ የሐዋርያት ሥራ 10÷17-29

እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንድናነባቸው እና ቃሉ በልቦናችን ተጽፎ በሥራ እንዲገለጽ የቸሩ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሁንልን።

✝️ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር።
አሜን ፡፡

https://youtu.be/u6vIQeuLtKo

https://youtu.be/u6vIQeuLtKo

የዓቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት::

12/10/2023

✝️ለዩናይትድ ኪንግደም እና አየርላንድ ማኅበረ ካህናት አባላት፣ ክቡራን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ካህናት፣ መምህራን፣ ዲያቆናት እንዲሁም ምእመናን ምእመናት በሙሉ።

✝️✝️✝️ መንፈሳዊ ጥሪ ✝️✝️✝️

26/03/2023

Address

London

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Megabe Sireat qesis michael's Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Megabe Sireat qesis michael's Page:

Share