ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Orthodox Tewahdo

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Orthodox Tewahdo ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ዜናዎች እና ታሪኮች ይቀርቡበታል ::

 ዑራኤል ማለት ትርጉሙ «የብርሃን ጌታ» «የአምላክ ብርሃን » ማለት ነው። ኢዮር፣ ራማ እና ኤረር የተባሉ ሦስት የመላእክት ከተሞች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ ...
29/04/2026


ዑራኤል ማለት ትርጉሙ «የብርሃን ጌታ» «የአምላክ ብርሃን » ማለት ነው። ኢዮር፣ ራማ እና ኤረር የተባሉ ሦስት የመላእክት ከተሞች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ በነገድ 100 በአለቃ 10 አድርጎ በሦስቱ ሰማያት አስፍሯቸዋል፡፡ ኢዮርን በ4፣ ራማን በ3፣ ኤረርንም በ3 ከፍሎ ነው በዓሥሩ ከተማ ያሰፈራቸው፡፡

በዚህም መሠረት ኢዮርን ላይና ታች አድርጎ በ4 ከተማ ከፍሏታል፡፡ በእርሷ ያሉትን መላእክትን በ40 ነገድ 4 አለቃ አድርጎ ከፈላቸው፡፡ የመጀመሪያው ነገድ ‹‹አጋእዝት›› ይባላሉ፡፡ አለቃቸው ሣጥናኤል ነበር፤ እርሱም የመላእክትን ሁሉ ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳርግ ነበር፡፡ ከክብሩ ሲዋረድ ቅዱስ ሚካኤል በምትኩ ተሹሞበታል፡፡ ሁለተኛው ነገድ ‹‹ኪሩቤል›› ይባላሉ፡፡ እነርሱም መንበረ ሥላሴን ይሸከማሉ፡፡ የቀሳውስት አምሳል ናቸው፡፡ አለቆቻቸው ገጸ ሰብና ገጸ አንበሳ ናቸው፡፡ በሦስተኛው ከተማ በኢዮር ያሉት ሱራፌል ይባላሉ፡፡ የዲያቆናት አምሳል ናቸው፡፡ በትንቢተ ኢሳይያስ በምዕራፍ 6 ላይ የተገለጹትና ኢሳያስን ከለምጹ እንዲፈወስ ያደረጉት ናቸው፡፡ አለቆቻቸው ገጸ ላህምና ገጸ ንስር ናቸው፡፡

(በነገራችን ላይ ‹‹ከሩቤል›› ወይም ‹‹ሱራፌል›› የሚባሉ የግለሰብ መጠሪያ ስሞች ስህተት ናቸው፡፡ አንደኛ እነዚህ ስሞች የብዙ መላእክት መጠሪያን የሚወክሉ ናቸው፡፡ ለአንዱ ሲሆን ‹‹ኪሩብ፣ ሱራፊ›› ይባላል፡፡ ‹ኪሩቤል› ወይም ‹ሱራፌል› ማለት ግን የብዙ ቁጥራቸው መጠሪያ ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ የቅዱሳን መላእክትን ስም እንዳለ በቁሙ ወስዶ ለግል መጠሪያ ስም ማዋል ተገቢ አይደለም፡፡ ‹‹ወለተ ሚካኤል፣ ክብፈ ገብርኤል….›› እየተባሉ ይሰየማሉ እንጂ ቀጥታ ‹ሚካኤል›፣ ‹ገብርኤል› እያሉ ሰዎችን መሰየም ስህተት ነው፡፡ 4ኛው ከተማ በኢዮር ያሉት ኃይላት ይባላሉ፡፡ የእሳት ሰይፍ ይዘው በሥሉስ ቅዱስ ፊት የሚቆሙ ናቸው፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወት የዛሉና የደከሙ ክርስቲያኖችን የሚያበረታቱ ናቸው፡፡ አለቃቸውም ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡)

ዳግመኛም እግዚአብሔር በራማ ያሉትን መላእክት በ30 ነገድ በ3 አለቃ አድርጎ ከፈላቸው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ‹‹አርባብ›› ይባላሉ፡፡ የሥላሴ እልፍኝ አስከልካዮች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔርን መንበር በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ሁለተኞቹ በራማ ከተማ ያሉት ‹‹መናብርት›› ይባላሉ፡፡ ለእግዚአብሔርን እጅግ ቅርብ የሆኑ ናቸው፡፡ የመብረቅ ጋሻቸውን የእሳት ጦራቸውን ይዘው የሥላሴ ጋሻ ጃግሬዎች ሆነው በተጠንቀቅ ይቆማሉ፡፡ የሰውን ችግር ለእግዚአብሔር ያቀርባሉ፡፡ መዝ 88፡6፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡

ሦስተኞቹ በራማ ከተማ ያሉት ‹‹ሥልጣናት›› ይባላሉ፡፡ መላውን ፍጥረት ለመጠበቅ ሥልጣን የተሰጣቸውና የምጽአት ዕለት አዋጅ ነጋሪዎች ናቸው፡፡ ዳን 12፡1፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ሱርያል ነው፡፡

ዳግመኛም እግዚአብሔር በኤረር ያሉትን መላእክት በ30 ነገድ በ3 አለቃ አድርጎ ከፈላቸው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ‹‹መኳንንት›› ይባላሉ፡፡ የሥላሴ የእሳት ባለ ቀስት ናቸው፡፡ የሰው ልጅ ልዩ ጠባቂዎች ናቸው፤ በተለይ በአደጋ ጊዜ ሎጥን እንዳዳኑት ፈጥነው ይደርሳሉ፡፡ በዕለተ ምጽዓት የሰውን ሁሉ ዐፅም ሰብስበው ለትንሣኤ ዘጉባኤ ያበቃሉ፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ሰዳካኤል ነው፡፡ ሁለተኛዎቹ ‹‹ሊቃናት›› ይባላሉ፡፡ የሥላሴ የእሳት ፈረሶች ናቸው፡፡ በእሳት ፈረስ ይመላለሳሉ፡፡ እነዚህም 24ቱ ካህናተ ሰማይ ሲሆኑ አለቃቸው ቅዱስ ሰላታኤል ነው፡፡

በኤረር ከተማ የሰፈሩት ሦስተኛዎቹ ‹‹መላእክት›› ይባላሉ፡፡ ፍጥረትን ሁሉ የሚጠብቁ ናቸው፡፡ አለቃቸው ቅዱስ አናንኤል ነው፡፡ በእነዚህ የማይጠበቅ ፍጥረት የለም፡፡ ከአዝርእት ጀምሮ ሁሉን ይጠብቃሉ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ‹‹በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ 7 መላእክትን አየሁ›› (ራዕ 8፡2) እንዳለ ሊቃነ መላእክት በቁጥር 7 ናቸው፡፡ እነርሱም፡- ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ሩፋኤል፣ ቅዱስ ራጉኤል፣ ቅዱስ ዑራኤል፣ ቅዱስ ፋኑኤል እና ቅዱስ አፍኒን ናቸው፡፡
‹‹ዑራኤል›› የሚለው ስም ‹ዑር› እና ‹ኤል› ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው፡፡ ‹‹ዑራኤል›› ማለት ትርጉሙ ‹‹የብርሃን ጌታ፣ የአምላክ ብርሃን›› ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው፡፡ በመሆኑም መጽሐፈ ሄኖክ እንደሚገልጸው መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል፡፡ ምሥጢረ ሰማይንና ሰማያዊውን ዕውቀት ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራው ይኸው ገናና መልአክ ነው፡፡ መጽሐፈ ሄኖክ 28፡13፡፡

መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሆኖ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨው ይኸው ገናና መልአክ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡

ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን አጠጥቶ ሰማያዊውን ምሥጢር የገለጠለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ ዕውቀት ተሠውሮበት ለነበረው ለኢትዮጵያዊው ሊቅ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በእመቤታችን ትእዛዝ ጽዋ ጥበብን አጠጥቶ ሰማያዊውን ምሥጢር የገለጠለት ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ ‹‹ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ፡፡›› መጽሐፈ ዕዝራ 2፡1፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር የሕይወትና የይቅርታ ዝናም በምድራችን ላይ ያዘንብ ዘንድ እንዲሁም የእርሻችንን አዝመራ በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ ለምግብነት እንዲበቃ ከፈጣሪ ዘንድ ምሕረትን የሚለምን መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡

ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በመልአኩ አማላጂነት እጅግ ብዙ ድርሰቶችን የደረሱት መልአኩ ጽዋ ሕይወትን ካጠጣቸው በኋላ ነው፡፡ በመጀመሪያም አባ ጊዮርጊስ የተወለዱት በቅዱስ ዑራኤል አብሳሪነት ነው፡፡ በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የተመሠረቱ አብዛኞቹ ቅዱሳት ገዳማት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው፡፡ ድርሳኑ ላይ የማይጠቅሳቸው የሀገራችን የከበሩ ቅዱሳት ገዳማትና ቅዱሳን ነገሥታት የሉም፡፡
የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክን ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ስትሰደድ መንገድ እየመራ ወደ ግብጽ እና ወደ አገራችን ኢትዮጵያ ያመጣቸው ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ እመቤታችንን ከተወደደ ልጇ ጋር በደመና ጭኖ መላ ኢትዮጵያን ካስጎበኛት በኋላ ቅድስት አገራችንን ለእመቤታችን የዓሥራት አገር እንድትሆን ያደረገው መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡

መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል በዓመት 3 ዓበይት በዓላት አሉት፡፡ ጥር 22 በዓለ ሲመቱ ነው፡፡ መጋቢት 27 የጌታችንን ክቡር የሆነ ወርቀ ደሙን ለዓለም የረጨበት ነው፡፡ ሐምሌ 22 ቀን ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበትና ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል የዕውቀትን ጽዋ ያጠጣበት ዕለት ነው፡፡

የሊቀ መላእክት የቅዱስ ዑራኤል ጥበቃው አይለየን! በጸሎቱ ይማረን

እና

፡-
ቅዱስ ዑራኤል ለነቢዩ ዕዝራ ጽዋዓ ልቡና ያጠጣዉ ጥበብና ማስተዋልን የሰጠዉ የጠፉትን ቅዱሳት መጻህፍትን በቃሉ አጥንቶ እንደገና እንዲጽፋቸዉ የረዳዉ መልአክ ነዉ
( ) ቅዱስ ዑራኤል ቅድስት ማርያም ልጅዋን ህጻኑን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ ለስደት በተነሳች ጊዜ ከምድረ እስራኤል ወደግብጽ ከዚያም ወደ ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራ ያመጣት መልአክ ነው።
( )

ለዕዝራ ሱቱኤል፤ ለቅዱስ ያሬድ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እና ለሌሎችም ቅዱሳን ጽዋ ልቦና አጠጥቷቸዋል፡፡ ወደ ሔኖክም እየመጣ የተሰወሩትን ምስጢር እና ያያቸውን ራእዮች ይተረጉምለት ነበር፡፡ በድርሳኑ እንደ ተገለጸው በረዳትነቱ በአማላጅነቱ ብዙ ደጋጎችን ረድቷል፡፡

የክርስቶስንም ደም በብርሃን ጽዋዕ ተቀብሎ የኢትያጵያን ምድር የረጨ ሲኾን ሥላሴን በቅዳሴ በውዳሴ ከሚያመሰግኑና ለሰው ልጆች ለምሕረት ለብሥራት ከሚላኩ መላእክት አንዱ ነው፡፡

ያደረገው ተአምር ይህ ነው። ዘወትር ሌት ከቀን የሚጮህ ጋኔን የሚጥለው በሲዶና አገር የሚኖር አንድ ሰው ነበር፡፡ በዚችው አገር ውስጥ የይቅርታ የምሕረት መላአክ የሆነ የመላእክት አለቃ በቅዱስ ዑራኤል ስም የተሠራች ቤተ ክርስቲያን ነበረች፡፡
ይህ ሰው የመላእክት አለቃ በሆነ በቅዱስ ዑራኤል በዓል ጥር 22 ቀን ካህናት በማኅሌት ጊዜ በፍቅርና በሰላም ሲዘምሩና ሲያሸበሽቡ ሳለ ከዚችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገባ፡፡ ያን ጊዜ በዉስጧ ቀይ ሰው መልኩ ከደም ግባቱ ጋር እጅግ ያማረ ከሰው ሁሉ ይልቅ የሚበልጥ በመካከላቸው ቁሞ ከእያንዳንዱ ፊት የሚወርደው ላብ በመሐረም ሲጠርግ አየ፡፡ ያን ጊዜ ከእግሩ በታች ተንፈራገጠ ጋኔኑም ጥቁር ከላዩ የእንጨት ቅርፊትን የመሰለ ሁኖ ወጣ፡፡
ጋኔኑም እሱን ትቶ ሸሸ ዑራኤልም ሽሽቱን አይቶ ፈጥነህ ወደኔ ና ቢለው ፈርቶ ሽሽቱን ቀጠለ ያን ጊዜ አንገቱን አንቆ በያዘው በትር መስቀል ስለደበደበው ጩኾ አለቀሰ፡፡
መልአኩም ሁለተኛ ታሠቃየው ዘንድ ወደዚህ ሰው ትመለሳለህን? ቢለው ከእንግዲህስ ወዲህ ወደሱ ብመለስ የአምላክህ መለኮታዊ ሰይፍ ከሁለት ይከፋፍለኝ ሲል በፊቱ ማለና እንዲሄድ ለቀቀው፡፡ ያም ሰው ያየውንና የሰማውን ሁሉ ለሰዎች ተናገረ፡፡ ያዩና የሰሙ ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ የቅዱስ ዑራኤልንም ተአምራት አደነቁ፡፡
ለእግዚአብሔርና ለእናቱ ለድንግል ማርያም ምሥጋና ይሁን ለኛም ምሕረትና ይቅርታ ይደረግልን፡፡
የመላእክት አለቃ የሆነ የቅዱስ ዑራኤል ረድኤቱ እና ልመናው ከመላው ህዝበ ክርስቲያኑ ጋር ይሁን፡፡ አሜን።



የበዓሉ መታሰቢያ ኅዳር 21 ለእዝራ ሱቱኤል ጽዋ ልቦና ያጠጣበት፡፡ ቀን በዓለ ሢመቱ። ቀን ከፈጣሪው ቃል ኪዳን የተቀበለበት፡፡
ዑራኤል ድንግል ማርያም በአካለ ሥጋ እያለች ወደ ሰማይ አሳርጓታል፡፡
ዑራኤል እመብርሃን በስደቷ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መርቶ አምጥቷታል፡፡
ዑራኤል ሆይ ይህች የበዓለ ሢመት ዕለት የተመረጠች እለት ናት፡፡ ከድንግል እረፍት በኃላ ቃል ኪዳን የተቀበልክባት ቀን ናት፡፡
ዑራኤል ሆይ በምእመን መስቀል ላይ የተሾምክ ታማኝ አገልጋይ ካሕን ነህና አሳሳች ከሚሆን ከሰይጣን አገዛዝ ነፃ አውጥተህ ማኅበራዊ አንድነታችንን ለሁል ጊዜ ጠብቅ የሃይማኖት ጥመኞችንም ታጠጣ ዘንድ የእጅህን ጽዋ ላክልን፡፡
ዑራኤል ሆይ ለነበልባላዊ አካለ ቆምህና ለእሳታዊ ሥነ መልክእህ ሰላም እላለሁ፡፡ ዑራኤል ሆይ ለዕዝራ ሱቱኤል ምሥጢር የሚገልጽ ትንቢትን የሚያናግር ጽዋ ልቡናን ለመጋት እንደ ተቻኮልክ ሁሉ በውስጥ በአፍአ የከበርክ መልአክ ነህና የአንደበቴን ምስጋና ለመቀበል ፈቃደኛ በመሆን ከኅዘኔ ታረጋጋኝ ዘንድ በሩጫ በችኮላ ፈጥነህ ወደኔ ና፡፡
ከመዓርና ከወተት ይልቅ ለሚጥመው ሰም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፡፡
ዑራኤል ሆይ ክፍልህ በደመ ወልደ እግዚአብሔር የተነከረ የታለለ ነውና ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ትሆን ዘንድ ግሩም የሚሆን እግዚአብሔር ሥልጣን በክብር ከፍ ከፍ አደረገህ፡፡
ዑራኤል ሆይ ችግረኞችን ለሚመለከቱ ዓይኖችህና የቅዱሳን ጸሎት ሰምተው ወደ እግዚአብሔር ለሚያቀርቡ አዕዛኖችህ ሰላም እላለሁ፡፡
ዑራኤል ሆይ ቀይሓን እሳታውያን ለሆኑ ጉንጮችህና ከዚያ ዓለም ሽቶ ልዩ መዓዛ ላላቸው አእናፎችህም ሰላም እላለሁ፡፡


Follow 👉👉 ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Orthodox Tewahdo

✥➕✥ ✥➕✥✥"ከከበሩ መላእክት አንዱ ዑራኤል ነው፤ እርሱም በብርሃናትና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ ነው።" (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥2)❶  :- "ዑራኤል" ማለት በዕብራይስጥ "የብርሃን ጌታ" ወይም ...
29/04/2026

✥➕✥ ✥➕✥

✥"ከከበሩ መላእክት አንዱ ዑራኤል ነው፤ እርሱም በብርሃናትና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ ነው።" (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥2)

❶ :- "ዑራኤል" ማለት በዕብራይስጥ "የብርሃን ጌታ" ወይም "የእግዚአብሔር ብርሃን" ወይም እግዚአብሔር ብርሃኔ ነው" (God is my light) ማለት ነው። ስሙ እንደሚገልጸው በጨለማ ለተዋጡ ምስጢርን ገላጭና የዕውቀት ብርሃንን የሚያበራ መልአክ ነው።

❷ :- የጽዋው ምስጢር ቅዱስ ዑራኤል ለነቢዩ ዕዝራ ሰማያዊ ምስጢርን ለመግለጥና መጻሕፍትን እንዲጽፍ የዕውቀት ብርሃንን የየሰጠበት ክፍል እንዲህ ይላል፦ "አፌንም ከፈትሁ፤ እነሆም ጽዋን አጠጡኝ፤ ያም ጽዋ እንደ ውኃ የሞላ ነው፤ መልኩ ግን እንደ እሳት የሚነድድ ነው፤ ያንንም ጠጣሁ፤ በጠጣሁም ጊዜ ልቤ ዕውቀትን አወጣ፤ በደረቴም ውስጥ ጥበብ አደረ፤ ነፍሴም ትውስታን ጠበቀች። አፌንም ተከፈተ ከእንግዲህም ወዲህ እውቀትም አልተወሰደብኝም" (ዕዝራ ሱቱኤል 13፥38-41)

❸ :- ለነቢዩ ዕዝራ የዓለምን ምስጢር፣ የዘመናትን ፍጻሜና መለኮታዊ ጥበብን የገለጠለት መልአክ ነው። መልአኩ ለዕዝራ ለጠየቀው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጠው የሰው ልጅ አእምሮ የአምላክን ጥልቅ ምስጢር መመርመር እንደማይችል ያስረዳበት ክፍል "ያን ጊዜም መልአኩ ዑራኤል መለሰልኝ እንዲህም አለኝ፦ 'እግዚአብሔር የፈጠራቸውን ሦስት ነገሮች ብነግርህ ከእነርሱ አንዱን ልታውቅ ትችላለህን?'" (ዕዝራ ሱቱኤል 2፥10)

❹ ፦ ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የፈሰሰውን ቅዱስ ደም በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በዓለም ዙሪያ (በተለይም በኢትዮጵያ ገዳማትና ቅዱሳት መካናት) ላይ የረጨ መልአክ ተደርጎ ይታወቃል። ይህም ለሀገሪቱ በረከትና ቅድስና ምክንያት ሆኗል።

❺ ፦ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን ይዛ ወደ ግብፅና ኢትዮጵያ በተሰደደች ጊዜ መንገድ መሪና ረዳት ሆኖ አገልግሏል። ለቅዱሳን አባቶች በየሄዱበት (እንደ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ያሉትን) እየተገለጠ ይመራል ምስጢራትንና መንፈሳዊ ጥበብንም ያስተምራል። በረከቱና የዕውቀት ብርሃኑ ትብራልን!

✥"መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ፥ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል።" (መዝሙረ ዳዊት 104:4) አምላከ ቅዱስ ዑራኤል ይመስገን!

follow 👉 ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Orthodox Tewahdo
Share share share 🙏

የት ሀገር ነው? Comment 👇👇Follow 👉 ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Orthodox Tewahdo
29/04/2026

የት ሀገር ነው?
Comment 👇👇
Follow 👉 ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Orthodox Tewahdo

Follow  ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Orthodox Tewahdo Share share share 🙏
25/04/2026

Follow ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Orthodox Tewahdo
Share share share 🙏

+ ከሁሉ በኋላ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ታየኝ..  እንደ ጭንጋፍ ነበርኩቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ምእመናን ስለ ጌታ ትንሣኤ ማስረጃ እያቀረበ ነው:: በዚያን ዘመን ለጌታ ትንሣኤ ማስረጃ ስትጠቅ...
25/04/2026

+ ከሁሉ በኋላ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ታየኝ.. እንደ ጭንጋፍ ነበርኩ

ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ምእመናን ስለ ጌታ ትንሣኤ ማስረጃ እያቀረበ ነው:: በዚያን ዘመን ለጌታ ትንሣኤ ማስረጃ ስትጠቅስ በማቴዎስ ወንጌል እንዲህ ይላል ብለህ እንዳትጠቅስ ገና ወንጌላት አልተጻፉም:: ቢጻፉም ማቴዎስ በሕይወት እያለ በቃሉ መመስከር ሲችል ጽሑፉን ማስረጃ ማድረግ አያስፈልግህም:: ስለዚህ ለመነሣቱ ማስረጃዎች ከተነሣ በኋላ ያዩት ሰዎች ነበሩ:: በሕይወት ያሉትን የዓይን ምስክሮችን መጥቀስ ይቻላል:: የዓይን እማኞች ምስክርነት ከጽሑፍ በላይ የታሪክ ማስረጃ ነው:: ስለዚህ ጳውሎስ ስለ ጌታ ትንሣኤ "እነ እገሌ አይተውታል" እያለ መዘርዘርን መረጠ::

ጌታ ከተነሣ በኋላ እንደ ቀድሞው ለሁሉ አልታየም:: እርሱን ለማየት የተገባቸው ጥቂት ወደ ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ነበሩ:: በማኅበር ያዩት አሉ:: በግል ያዩት አሉ::
ያዩት ነገር ወንጌል የሆነላቸው ብፁዓን ዓይኖች ያሏቸው እንዴት የታደሉ ናቸው? የተሰቀለውን ተነሥቶ ያዩት! ዳግም በሚመጣበት አካል የተገለጠላቸው ምንኛ የታደሉ ናቸው? ከመድኃኔ ዓለም አፍ ተቀብለው ኪዳን ያደረሱ! የጌታን ቅዳሴ ተቀብለው ያስቀደሱ! የትንሣኤው ማግስት ምስክሮች እንዴት ዕድለኞች ናቸው? ቢሞቱም እንኳን መነሣታቸውን በጌታ ትንሣኤ አይተው ደስ ብሎአቸው ያንቀላፉ እነርሱ ምንኛ የታደሉ ናቸው?

ቅዱስ ጳውሎስ በወንጌል ከተጠቀሱት ከነ ኬፋ በተጨማሪ ለይቶ ጌታ ለማን ለማን እንደታየ ገለጸ:: ለያዕቆብ ታየ ብሎ የእልፍዮስን ልጅ ለይቶ ጠቀሰው:: የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፍት እንደሚሉት ይህ ሐዋርያ ከሌሎች በተለየ የጌታን ትንሣኤ ሳላይ እህል አልቀምስም ብሎ የተሳለና አክፍሎትን የጀመረ ነበርና ጌታ ለይቶ ክብሩን አሳይቶታል:: ከዚያም ለዐሥራ ሁለቱ ታየ ብሎ የጌታን ድኅረ ትንሣኤ አስተርእዮ ዘረዘረ:: እኔ ማለትን የማይወደው ትሑት ቅዱስ ጳውሎስ "ከሁሉ በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ አለ::

ጭንጋፍ ምንድር ነው? ጭንጋፍ (ጸዕጻዕ/ ተውራድ) ለፅንስ የሚነገር ቃል ነው:: መወለድ ያለበትን ጊዜ ያልጠበቀ ያለ ጊዜው የተወለደ ፅንስ ነው:: በመጠኑ ከሌላው ጊዜውን ከጠበቀ ፅንስ የሚያንስ ሲሆን ዕድገቱን በተገቢው ጊዜ ከሚወለድ ልጅ ጋር ለማስተካከል ሲባል በሙቀት ማቆያ ክፍል እንዲቆይ ይደረጋል:: ይህ ፅንስ ሲወለድ በሕመም ውስጥ ሆኖ ተሰቃይቶ ተጨንቆ ነው::

ቅዱስ ጳውሎስ ራሱን ለመግለጽ የተጠቀመበት ይህ አንድ ቃል የሕይወት ታሪኩን ጠቅልሎ የያዘ ድንቅ ቃል ነበር::
ቅዱስ ጳውሎስ ምንም እንኳን የቤተ ክርስቲያን ብርሃን የሆነ ሐዋርያ ቢሆንም እንደ ዓሥራ ሁለቱ ሐዋርያት በጊዜው የተጠራ አልነበረም:: እርሱ ከሐዋርያት ጋር አብሮ በዳግም ልደት የተወለደ ሳይሆን ያለ ጊዜው ክርስቶስ ባረገ በስምንተኛው ዓመት የተጠራ ነበረና ራሱን ካለ ጊዜው ከተወለደው ፅንስ ጋር አመሳስሎ እንደ ጭንጋፍ የምሆን ብሎ ጠራ::

ጭንጋፍ ሲወለድ በመጠኑ ከሌላው ፅንስ ያነሰ ይሆናል::
ቅዱስ ጳውሎስም ራሱን ጭንጋፍ ካለ በኋላ "እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስላሳደድሁ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ" ብሎ አብራርቶታል:: (1ቆሮ 15:9)

ልጅ ጭንጋፍ ሆኖ ሲወለድ በሥቃይ ነው:: ጤና ያጣል ይታመማል:: እናቲቱም ትታወካለች በድብታ በጭንቀት ትቸገራለች:: ባለሙያዎቹ እንደሚሉት እናት ያለ ጊዜው ከተወለደ ልጅዋ ጋር እናታዊ ትስስር ለመፍጠርና የእናትነት ፍቅርዋን ለመሥጠት ባልጠበቀችው ጊዜ የመጣ በመሆኑ ምክንያት ለጥቂት ጊዜ ትቸገራለች:: በአጭሩ ጭንጋፍ ሆኖ ሲወለድ እሱም ይሰቃያል እናቱንም ያስጨንቃል:: ወዲያው እንደሌላ ሕፃን በሰው እጅ አይታቀፍም:: ከተፈጥሮአዊ እስከ ሰው ሠራሽ እንደየጊዜው እየዘመነ በሔደው የልጅ ሙቀት መስጫ መንገድ እየታገዘ የሰውነት አካሎቹ በአግባቡ መሥራት እስከሚችሉና በሽታ መቋቋም እስከሚችል ይቆያል::

ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ጭንጋፍ ነበርኩ ያለው ለዚህ ነው:: በዳግም ልደት የተወለደው በደማስቆ መንገድ ወድቆ ሊቋቋመው ባልቻለው ብርሃን ተመትቶ ነበር:: "ሳውል ሳውል ስለምን ታሳድደኛለህ?" የሚል ድምፅ ሲሰማ ፅንስ ነውና ዓይኑን እንኳን መግለጥ አልቻለም ነበር::
ከተወለደ በኋላም ወዲያው ወደ ቤተ ክርስቲያን እቅፍ ወደ ሐዋርያት ማኅበር አልገባም:: እንደ ጭንጋፍ የምሆን እንዳለ ሙቀት ያስፈልገው ነበርና የሰው እጅ ሳያቅፈው ሦስት ዓመት በሱባኤ ቆይቶ በመንፈስ ቅዱስ ተማወቀ::

"ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም፥ ከእኔም በፊት ሐዋርያት ወደ ነበሩት ወደ ኢየሩሳሌም አልወጣሁም፥ ነገር ግን ወደ ዓረብ አገር ሄድሁ እንደ ገናም ወደ ደማስቆ ተመለስሁ። ከሦስት ዓመት በኁዋላ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣሁ" ብሎ ስለ መንፈሳዊ ኃይል መልበሱ ይናገራል:: (ገላ 1:15-18)

ጭንጋፍ ሆኖ የተወለደ ልጅ የሚገጥመው ችግር ከወላጆቹ ጋር በሥነ ልቡና ለመተሳሰር መቸገሩ ነው::
ቅዱስ ጳውሎስን ለማመንና እንደ ልጅ ለመቀበል የቤተ ክርስቲያን ማኅበርም ተቸግራ ነበር::
"ሳውልም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከደቀ መዛሙርት ጋር ይተባበር ዘንድ ሞከረ፤ ሁሉም ደቀ መዝሙር እንደ ሆነ ስላላመኑ ፈሩት" ሐዋ 9:26 ስለዚህ ሐዋርያው እንደ ጭንጋፍ ነኝ አለ::

ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ጌታ መነሣት ምስክሮች ብሎ ሌሎችን ከዘረዘረ በኋላ "ከሁሉ በኋላ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ታየኝ" ብሎ ተናገረ:: ክርስቶስ ተነሥቶአል ወይ ብለው ሲጠይቁህ አዎ ተነሥቶአል እነ እገሌ አይተውታል ብለህ ዘርዝረህ
"ከሁሉ በኁዋላ ለእኔም ታየኝ" ብለህ መናገር መቻል እንዴት መታደል ነው!?

ወዳጄ ክርስቶስ መነሣቱን ታምናለህ:: ልክ ነህ ለብዙዎች ታይቶአል:: አንተስ ከሁሉ በኁዋላ ለእኔም ታየኝ ማለት ትችል ይሆን? ጌታ ከተነሣ በኁዋላ ላለፉት ሁለት ሺህ ዓመታት ለብዙዎች ታይቶአል:: ብዙዎቹ ቅዱሳን አይተውታል:: ቅዱስ እስጢፋኖስ አይቶታል : ቅድስት አርሴማ አይታዋለች : አቡነ ተክለ ሃይማኖት አይተውታል : አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ተመልክተውታል:: አባ ጳኩሚስ በዕንባ ተመልክቶታል : ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ አይታዋለች::

ሁሉም ቅዱሳን ብዕር ቢሠጣቸው ከዕንባ ጋር
"ከሁሉ በኁዋላ ለእኔም ታየኝ" ብለው የትንሣኤውን ማስረጃ ዝርዝር ይቀጥላሉ:: ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በበረሃ ሲጸልይ አይቶት ነበርና ሰው ባገኘ ቁጥር
ወቅቱ የፋሲካ ሰሞን ባይሆንም እንኳን በፈገግታ ተሞልቶ
"ክርስቶስ ተነሥቶአል!" ብሎ ያበሥርና ሰላምታ ይሠጥ ነበር::

ጌታ ሆይ ለእኔ ለኃጢአተኛው የምትታየኝ መቼ ይሆን? ቸርነትህን አይቻለሁ! ፍቅርህን አይቻለሁ! ብሩሕ ገጽህን የማየው መቼ ይሆን? መች እደርሳለሁ የአምላኬንስ ፊት መቼ አየዋለሁ? እኔም እንደ ቅዱሳንህ "ከሁሉ በኁዋላ ለእኔ ታየኝ" ብዬ የተቀመጠውን ብዕር አንሥቼ የምጽፈው መቼ ይሆን? አቤቱ ፊትህን እሻለሁ! አቤቱ ፊትህን ከእኔ አትመልስ! አቤቱ ፊትህን እሻለሁ!

"ኢየሱስ ክርስቶስ በግዕ ዘቀራንዮ
ለላሕይከ ንትሜነይ ከመ ንርአዮ"
"የቀራንዮው በግ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ውበትህን ልናየው እንመኛለን"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ማዕዶት 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!

Follow👉 ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Orthodox Tewahdo
share share share..

የኢትዮጵያ አንድነት ገዳማት ኅብረት ጉባኤ ተካሄደ። EOTCMK TV ሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓ.ምበአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቦሌ ቡልቡላ ምዕራፈ  ቅዱሳን ቅዱስ ሚካኤል እና አቡነ ተክለሃይ...
25/04/2026

የኢትዮጵያ አንድነት ገዳማት ኅብረት ጉባኤ ተካሄደ።

EOTCMK TV ሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቦሌ ቡልቡላ ምዕራፈ ቅዱሳን ቅዱስ ሚካኤል እና አቡነ ተክለሃይማኖት የእናቶች አንድነት ገዳም የኢትዮጵያ አንድነት ገዳማት ኅብረት ጉባኤ ሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ተካሂዷል።

በጉባኤው ላይ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተው ትምህርተ ወንጌል ፤አባታዊ መመሪያና ቡራኬ ሰጥተዋል።

የገዳማት ኅብረቱ ዋና ዓላማ ገዳማውያን በሥርዓት እንዲተዳደሩ ብሎም የገዳማውያን ሥርዓት እንዲጠበቅ እና ሐሰተኞች ገዳማዊነትን መጠቀሚያ እንዳያደርጉ ለማስቻል መሆኑ ተገልጿል።

ሌሎች በርካታ ገዳማውያን ላይ ያሉ ፈተናዎች መፍትሄ እንዲያገኙ ኅብረቱ እየሠራ ይገኛል ተብሏል።

ይህንን ተግባር እና ዓላማ በቅዱስ ሲኖዶስ እንዲደገፍም ገዳማውያኑ ጥሪ አቅርበዋል።

የኅብረቱ ጉባኤ በገዳማውያን አባቶች ለ9 ያህል ጊዜ በተለያዩ ገዳማት ተካሂዷል።

የእናቶች ኅብረት ጉባኤ ደግሞ ለሶስተኛ ጊዜ በቦሌ ቡልቡላ ምዕራፈ ቅዱሳን ቅዱስ ሚካኤል እና አቡነ ተክለ ሃይማኖት የእናቶች አንድነት ገዳም ተካሂዷል ።

በጉባኤው የዘጠኝ አመት የኅብረቱ ጉዞ በዶክመንተሪ ፊልም ለብፁዓን አባቶችእና ለተሳታፊ መነኮሳት ቀርቧል።

ከሰዓት በኃላ በቀጠለው ጉባኤ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የምሥራቅና የሰሜን አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ድርጅት ተገኝተው ትምህርተ ወንጌልእና አባታዊ ቡራኬ በመስጠት ኅብረቱን አበረታተዋል ።

ዘገባው የኢኦቴቤ ቴቪ ነው
Follow 👉 ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Orthodox Tewahdo

በደራሼ ወረዳ ቤተ ክህነት የአልጋዬ ቅዱስ ባለ ወልድ አዲስ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ተመረቀ፤ 400 አዲስ አማንያንም ተጠመቁ።፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠"እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ...
25/04/2026

በደራሼ ወረዳ ቤተ ክህነት የአልጋዬ ቅዱስ ባለ ወልድ አዲስ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ተመረቀ፤ 400 አዲስ አማንያንም ተጠመቁ።
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

"እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው።" (ማቴዎስ ፳፰፥፲፱-፳)

በጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት፣ በደራሼ ወረዳ ቤተ ክህነት የሚገኘው የአልጋዬ ቅዱስ ባለ ወልድ አዲስ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በድምቀት ተከናወነ። በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ዕለት የአዲሱን ሕንጻ መመረቅ ይበልጥ ልዩ ያደረገው በአንድ ቀን 400 የሚሆኑ ኢ-አማንያን የሥላሴን ልጅነት በመቀበል ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መቀላቀላቸው ነው።

በምረቃውና በጥምቀት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ገሪማ ጌታነህ፣ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ መጋቤ ሰናያት ያዕቆብ ደስታ እንዲሁም የሀገረ ስብአቱ የየሥራ ክፍል ኃላፊዎችና በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።

በዕለቱ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው በማመናቸው በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት የተቀበሉት ወገኖች ቁጥር 400 ሲሆን፣ 250 ወንዶች እና 150 ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።

ይህ መንፈሳዊ ተግባር በወንጌል ብርሃንነት ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚገቡ ምዕመናን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የሚያሳይ ታላቅ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል።

የሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ መመረቅ ለአካባቢው ማኅበረሰብ መንፈሳዊ አገልግሎትን በቅርበት ለማግኘት ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን ይታመናል።

መረጃዉ :- የ ነቅዓ ጽድቅ ጋሞና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚዲያ- ነዉ።

በኮንሶ ዞንም ብፁአን አበዉ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋሪያዊ አገልግሎቱን ይቀጥላሉ። ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን።
Follow የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
Share share share 🙏🙏
🙏

የት ቤተክርስቲያን ነው?Comment 👇👇👇
25/04/2026

የት ቤተክርስቲያን ነው?
Comment 👇👇👇

25/04/2026
25/04/2026

ድንቅነው ለኛ 🙏
Share አድርጉት የኦርቶዶክስ ልጆች ለሁሉም ይድረስ.
#ቤተክርስቲያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Orthodox Tewahdo

Follow 👉 ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Orthodox Tewahdo ለቅዱስ እስጢፋኖስ ወዳጆች እንዲደርስ ሁላችሁም Share 🙏
24/04/2026

Follow 👉 ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Orthodox Tewahdo
ለቅዱስ እስጢፋኖስ ወዳጆች እንዲደርስ ሁላችሁም Share 🙏

Address

London
WC1

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Orthodox Tewahdo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share