ቅኔ ቲዩብ - kene tube

ቅኔ ቲዩብ - kene tube Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቅኔ ቲዩብ - kene tube, London.

​"በዝማሬ ወደ ፊቱ እንምጣ!" በዚህ ገጽ መንፈስን የሚያድሱ፣ ለነፍስ ምግብ የሚሆኑና ሕይወትን የሚለውጡ የወንጌል ዝማሬዎችን ወደ እናንተ እናደርሳለን።
​ዓላማችን፦ በዝማሬ እግዚአብሔርን ማመስገንና ምዕመናንን በመንፈሳዊ ሕይወት ማነጽ ነው።
በየሳምንቱ የሚለቀቁ አዳዲስ መንፈስን የሚያድሱ ዝማሬዎችና የአምልኮ ጊዜያት እንዲደርሷችሁ የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe በማድረግ የቅኔ ቲዩብ ቤተሰብ ይሁኑ

የምረቃ ግብዣ መልዕክት የክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች መሥራችና ፕሬዝዳንት የሆኑት ነቢይ ኢዩ ጩፋ በሥነ-መለኮት (Theology) የማስተርስ ዲግሪያቸውን ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም....
17/06/2026

የምረቃ ግብዣ መልዕክት
የክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች መሥራችና ፕሬዝዳንት የሆኑት ነቢይ ኢዩ ጩፋ በሥነ-መለኮት (Theology) የማስተርስ ዲግሪያቸውን ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. እንደሚቀበሉ በታላቅ ደስታ እናሳውቃለን።

ይህ የማስተርስ ምረቃ በመጀመሪያ በ2017 ዓ.ም. መግቢያ ላይ የታቀደ ቢሆንም፣ በእናታቸው ህልፈት ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ለኮሌጁ ጥያቄ በማቅረባቸው ፈቃድ እንደተሰጣቸው የኮሌጁ ምክትል ፕሮፌሰር ገልጸዋል።

በተጨማሪም ነቢይ ኢዩ ጩፋ የዶክትሬት (PhD) ጥናታቸውን በትጋት እየቀጠሉ ሲሆን፣ ለማጠናቀቅም በመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደደረሱ ፕሮፌሰሩ አስታውቀዋል። በመሆኑም በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን እንደሚቀበሉ በይፋ ተረጋግጧል።
ስለዚህ በመጪው ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. በሚካሄደው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በመገኘት፣ ከነቢይ ኢዩ ጩፋ ጋር በመሆን ለእግዚአብሔር ምስጋና እንድታቀርቡ ሲሉ በአክብሮት ግብዣቸውን አቅርበዋል።ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን፤ የጀመረውን ያጠናቅቃል።
**በአክብሮት፣** ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች ጽሕፈት ቤት

Graduation Invitation Message
The Office of Christ Army International Church is pleased to announce with great joy that Prophet Eyu Chufa, Founder and President of Christ Army International Church, will receive his Master's Degree in Theology on June 21, 2026 (Sene 14, 2018 E.C.).
Although this Master's graduation was originally scheduled for the beginning of 2017 E.C., it was postponed for a period of time due to the passing of his beloved mother. According to the College's Vice President, Prophet Eyu Chufa formally requested an extension, which was graciously approved by the institution.
Furthermore, the Vice President stated that Prophet Eyu Chufa has continued his PhD studies with diligence and dedication and has now reached the final stage of completion. It has also been officially confirmed that he is expected to receive his Doctoral Degree (PhD) within the coming months.
Therefore, Prophet Eyu Chufa cordially invites you to attend the graduation ceremony to be held on June 21, 2026 (Sene 14, 2018 E.C.), and to join him in giving thanks and glory to God for this significant achievement.
“To God be the glory; He who began the good work is faithful to complete it.”
Respectfully,
Office of Christ Army International Church

ባለፈው ሳምንት አጋጣሚ ሆኖ በታክሲ (ራይድ) ውስጥ እየተጓዝኩ ሳለ በለሆሳስ እዘምር ነበር። ሹፌሩ ዘወር ብሎ “ጴንጤ ነህ?” አለኝ። “አዎ” አልኩት…በረዥሙ ተነፈሰና እንዲህ አለኝ፦> “እኔ...
13/06/2026

ባለፈው ሳምንት አጋጣሚ ሆኖ በታክሲ (ራይድ) ውስጥ እየተጓዝኩ ሳለ በለሆሳስ እዘምር ነበር። ሹፌሩ ዘወር ብሎ “ጴንጤ ነህ?” አለኝ። “አዎ” አልኩት…በረዥሙ ተነፈሰና እንዲህ አለኝ፦

> “እኔም ጴንጤ ነበርኩ.... ረጅም ፀጥታ .."እና " አልኩት .ነበርኩ ማለት ? ......‘ሙሉ ወንጌል’ ቤተክርስቲያን እያለሁ በልሳን እጸልይ፣ በትጋትም አገለግል ነበር። ነገር ግን የሆነ ነገር አጋጠመኝና እንደ ቀልድ ከቸርች ቀረሁ። አንድ ቀን፣ ሁለት ቀን እያለ ሲሄድ ዞር ብሎ ያየኝ፣ ያስታወሰኝና የፈለገኝ አንድም እረኛ ወይም መጋቢ አልነበረም እኔም መሄዱን ረሳሁኝ መፀለዩን ረሳሁኝ ... አሁንማ ሃይማኖት የለኝም ወደሚል ደረጃ ደርሻለሁ…”

እየተጓዝን ስለ ዘመኑ ነቢያት ሀሰተኝነት ፣ ስለ እረኞቻችን መዛልና ስለ እኛ መበተን ብዙ ተጨዋወትን ያጠመቁትን መጋቢዎች ስም ጠቅሶ ነገረኝ ንግግሩ ውስጥ ሀዘን አለ የመገፋት የመረሳት ያለመፈለግ ስሜት ..🥹እኔም መውረጃዬ ደርሼ ስወርድ፣ ያ ሹፌር ብቻውን እንዳልሆነና በየሰፈሩ ያሉ የሱ ቢጤዎች ስፍር ቁጥር የሌላቸው መሆኑን እያሰብኩ ልቤ በሃዘን ተሞላ....🥹🥹

“ለምን ቸርች አትሄዱም?” ብሎ ከመፍረድ በፊት፣ ከእያንዳንዱ ከቀረ ሰው በስተጀርባ በሰው የማይታወቅ ትልቅ ስብራት አለ። ትላንት በመቅደስ ውስጥ በትጋት ሲያገለግሉ የነበሩ ዲያቆናት፣ በልሳን የሚጸልዩ፣ ጉባኤውን በዝማሬ የናኙ የጸሎት መሪዎች ዛሬ በሰው በደል አሊያም በመሪዎች መሃል በተፈጠረ «በተራ ግጭት» ምክንያት ብቻ ከመጋረጃው በስተጀርባ ወድቀው ቀርተዋል ተረስተዋል 🥹

ሌላው ደግሞ በኃጢአት ወጥመድ ውስጥ ወድቆ፣ የሚኮንነው እንጂ የሚምረውና የሚያግዘው እጅ በማጣቱ ቀስ በቀስ ተረሳ🥹
📆አንድ ቀን፣ ሁለት ቀን፣ ሦስት ቀን... እያለ ቀናቶች ወደ ዓመታት ተቀየሩ። መጋቢዎችና የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች ጥቅል ቁጥሩን እንጂ የጠፋውን ነፍስ ረሱት። ቤተክርስቲያን በመድረክ ላይ በምታሳየው ድምቀት መሃል፣ በስተጀርባ ግን ማንም ዞር ብሎ ያላያቸው በጣም ብዙ የከበሩ ምዕመኖቿን እያጣች ነው💔
ጨከን ብለን እናውራ ካልን ትልቅ አስራት ከፋይ ካልሆንክ ምእመን መሆንህን ሁሉ ሊዘነጉት ይችላሉ ...

ነገር ግን የሰው መረሳትና የእረኞች ስንፍና በእግዚአብሔር መረሳት እኮ አይደለም። ሰዎች ሊረሱህ ይችላሉ፤ ያጠመቀችህ ቤተክርስቲያን ልትዘነጋህ ትችላለች። መጽሐፍ ቅዱስ ግን በትንቢተ ኢሳይያስ 63፥16 ላይ እንዲህ ይላል፦
> **"አብርሃም ባያውቀን፥ እስራኤልም ባይገነዘበን፥ አቤቱ፥ አንተ አባታችን ነህ፤ ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን ነው።"**
>
መንፈሳዊው ማህበረሰብ (አብርሃምና እስራኤል) ባያውቁህና ባይረዱህ እንኳ፣ እርሱ ግን አሁንም አባትህ ነው። ሰብአዊው መዋቅር ቢረሳህም፣ ሰማያዊው አባት ግን አሁንም ስምህን በእጁ መዳፍ ላይ ቀርጾታል።

**ስለዚህ ግድ የላችሁም ዛሬ ተነሱ!**
ትላንት ያገለገላችሁበት ያ ቅዱስ ቅንዓት፣ ያ የጸሎትና የዝማሬ መንፈስ አሁንም በውስጣችሁ አለ። በሰዎች ስህተት ምክንያት የቅዱሳንን ህብረት አታጥፉ። መፍትሔው ከእግዚአብሔርና ከቅዱሳን ህብረት መራቅ አይደለም። መሪዎች ቢረሱንም፣ የማይረሳንና "አባታችን" የምንለው አምላክ ስላለን፣ በእርሱ ታምነን ከእነ ችግሩና ጉድለቱ ዳግም ወደ ህብረቱ እንመለስ።

**ተነሱ፤ የእግዚአብሔር መዝገብ ፈጽሞ አልረሳችሁም!**

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ዘወትር እሁድ ቅዱስ መጽሐፋቸውን በመያዝ በቤተክርስቲያን በመገኘት የአምልኮ ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ 🙏
13/06/2026

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ዘወትር እሁድ ቅዱስ መጽሐፋቸውን በመያዝ በቤተክርስቲያን በመገኘት የአምልኮ ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ 🙏

የሙሉወንጌል 'ለ' መዘምራን የአምልኮ ቡድን 50ኛ ዓመት ክብር በዓል ግንቦት 9   በቀጠና ሁለት ሙሉወንጌል  በደማቅ ሁኔታ ተከበረፕሮግራሙ  ከሙሉወንጌል ወጣት ተተኪ መዘምራን ጋር በአምልኮ...
18/05/2026

የሙሉወንጌል 'ለ' መዘምራን የአምልኮ ቡድን 50ኛ ዓመት ክብር በዓል ግንቦት 9 በቀጠና ሁለት ሙሉወንጌል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

ፕሮግራሙ ከሙሉወንጌል ወጣት ተተኪ መዘምራን ጋር በአምልኮ ተጀምሯል።

በመቀጠልም ፓስተር መርዕድ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን 1ኛ ጢሞቲዎስ 1፡12 ን ጠቅሰው "እግዚአብሔር የአምልኮ ቡድኑን ጠራ፣ ቅባቱን አፈሰሰባቸው ፣ ታማኝ አድርጎ ቆጥሮ በቤቱም ሾማቸው፣ ለዚህ ክብርም አበቃቸው" ሲሉ ተናግረዋል::

በጥቁር አንበሳ መሰናዶ ትምህርት ቤት በብዙ ዋጋ መክፈል የተጀመረው የሙሉንጌል ለ መዘምራን የ50 ዓመታት ጉዞ የሚያሳይ አጭር ዶክመንተሪም ቀርቧል።

በመቀጠልም ፓስተር ምህረት ከበደ መዝመር 117 ላይ ተመርኩዘው 'ሀሌሉያ' በሚል ርዕስ የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዋል።

በዕለቱ "ብቻውን መራው" የተሰኘ የአምልኮ ቡድኑ ከአመሰራረቱ ጀምሮ የተጓዘበትን ታሪክ የሚያወሳ መፅሀፍም ተመርቆ ለንባብ ቀርቧል።

በመጨረሻም ከሙሉወንጌል 'ለ' መዘምራን ጋር በአምልኮ መርሀግብሩ ተጠናቋል።

በሶስና እያሱ

 -  እትናስ ይሳል ጥበብ ቤቷን ሰርታበታለች፣ እንትናስ ይጻፍ በመጻፍ ተክኗል፣ እትናስ ይስበክ ስብከት ስጦታው ነው ይባላል። ሙዚቃን ዕንቁ ይጫወት ሙዚቃን መጫወት ያወቅበታል ብቻ ሳይሆን፣ ...
09/04/2026

-

እትናስ ይሳል ጥበብ ቤቷን ሰርታበታለች፣ እንትናስ ይጻፍ በመጻፍ ተክኗል፣ እትናስ ይስበክ ስብከት ስጦታው ነው ይባላል። ሙዚቃን ዕንቁ ይጫወት ሙዚቃን መጫወት ያወቅበታል ብቻ ሳይሆን፣ ሙዚቃ ራሷ ዕንቁ ይጫወተኝ የምትል ይመስለኛል። በሙዚቃ አቅጣጫ የተገለጠ እጅግ አስደናቂ ስራን ከሰሩ እና በቤተክርስቲያን የዝማሬና የሙዚቃ አገልግሎት የራሳቸውን አሻራ ካሳረፉ ሙዚቀኞች አንደኛው ዕንቁ ግርማ ነው። እጅግ በጣም የምንወዳቸው በርካታ አልበሞችና ዝማሬዎች አሻራውን አሳርፏል። ዕንቁ የሰራቸውን ስራዎች በሙሉ ለመዘርዘር ብዙ ነገር ማገለበጥና እርሱን አግኝቶ መጠየቅ ያስፈልናል። በሙሉ አልበም ደረጃ የተለያዩ ዝማሬዎች ላይ በማቀናበርና እንዲሁም በሚክሲንግ ተሳትፏል። ከሰራቸው ስራዎች በጥቂቱ ለአብነት ያህል እንመልከት።

በሙሉ አልበም ደረጃ፤ የዘማሪት ምህረት ኢተፋ ቁ 3 አልበም፣ የሐረር አማኑኤል አልበሞች ላይ፣
የናዝሬት አማኑኤል አልበም ላይ፣ የዘማሪት ሶፊያ ሽባባው ቁ 2 አልበም ተጠቃሽ ናቸው።

ዝማሬን ካቀናበረላቸው ዘማሪያን በጥቂቱ የዘማሪ ሳሚ ተስፋ ሚካኤል፤ የዘማሪ ተከስተ ጌትነት፣ የዘማሪ አውታሩ ከበደ፣ የዘማሪ ዮሴፍ አያሌው፣ ዘማሪት ምህረት ኢተፋ፤ አልበሞች ላይ የተለያዩ ኮሌክሽኖች ላይ እጅግ የተወደዱ ስራዎችን ሰርቷል። ሙዚቃን ማቀናበር ብቻ ሳይሆን እጅግ በርካታን ዝማሬዎችን እና አልበሞችን Mix አድርጓል።

በእርሱ በኃላ በመጡት ብዙ ሙዚቀኞች ላይ የራሱን መልካም ተጽዕኖ አሳርፏል። በብዙ ሙዚቀኞች ዘንድ ጭምር ስራዎቹ እጅግ ተወዳጅ ናቸው። ዕንቁ በሙዚቃ አቅጣጫ ለክርስቶስ አካል ቤተ ክርስቲያን ስላበረከትከው መልካም አስተዋጽኦ እግዚአብሔር ይባርክህ። ስላገለገልከን እናመሰግናለን። ገና ብዙ ስራዎችን ከአንተ እንጠብቃለን።

ዘሪሁን ግርማ

በመካከላችን ያሉ ጤና-ቢሶችንም አስታግሱልን!እንዲህ አይነቱን 'አሳፋሪ' መጋቢ ደግሞ አደብ ብታስገዙልን መልካም ነው። ቤተ ክርስቲያን መድሃኒት ናትና ብዙ አይነት ሰው ለመታከም ይመጣል። መጥ...
09/04/2026

በመካከላችን ያሉ ጤና-ቢሶችንም አስታግሱልን!

እንዲህ አይነቱን 'አሳፋሪ' መጋቢ ደግሞ አደብ ብታስገዙልን መልካም ነው። ቤተ ክርስቲያን መድሃኒት ናትና ብዙ አይነት ሰው ለመታከም ይመጣል። መጥቶም መጋቢው በሚሰጠው አገልገሎት በወንጌል ይለወጣል፥ ሌላ ሰው ይሆናል። አንዳንዱም ከእስራቱ ለመፈታት ጊዜ ይፈጅበታል። ከዚህ የተነሳ ፈውሱ በሂደት ይሆናል። ታዲያ መጋቢው በዚህ ሁሉ ውስጥ ስለሚመግበው ሰው አብሮ እያማጠና እየጸለየ ለተሰጠው መንጋ መንፈሳዊ ጤንነት ይደክማል እንጂ በሚዲያ ተጋበዝኩ ብሎ "ከእኛ ቸርች ሌዚ*ቢያን አለች" ብሎ ለሚዲያ ፍጆታ አይለፍፍም።

የዚህ ቄስ እብደት በግልጽ የሚስረዳን ነገር ቢኖር፦

አንድም፦ መጋቢያዊ ሃላፊነቱ የታሰሩትን በአምላክ ረድኤት በተሰጠው አገልግሎት ነጻ ማውጣት ሆኖ እያለ በተቃራኒው የመጋቢያዊ አሃላፊንቱን ድክመት በአደባባይ መለፈፉ፥ የመጋቢ ትልቅ quality የሆነውን ሚስጥር ጠባቂነት አሽቀንጥሮ መጣሉን ያሳያል። ወደ አንድ መጋቢ ብዙ አይነት ሰው እርዳታን ፈልጎ ይመጣል። የእርሱ ድርሻ የሰዎችን ድካም ስምቶ ሲያበቃ አብሮ ሊጸልይ፣ ካሉበት እስራት እንዲወጡ ሊመክር ሲገባ በመጋቢያዊ አገልግሎቱ የገጠመውን ሁሉ በአደባባይ የሚያወራ ከሆነ በእንዲህና በእንዲያ ድካም ውስጥ ነኝ እባክህ እርዳኝ ብሎ ማን እርሱ ጋር ይመጣል? ደግሞስ የሚያገለግልበት ቤ/ክ መጋቢያዊ አገልግሎቱን እንዲህ abuse ሲያደርግ ዝም ማለትስ ተገቢ ነው? ከዚህ በላይ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት የሚጎዳ ድርጊት አለ ወይ?

ሁለትም፦ የወንጌላዊያንን ማህበረሰብ ስም ለማጠልሸት ከሚሰራ ሰው ሚዲያ ላይ ቀርቦ የጥላቻ ግብአት መሆኑና

ሶስትም፦ የወንጌላዊያኑን ማህበረሰብ ስም በሚያጠለሽ አቀራረብ ቃለ ምልልስ ማድረጉ የሚያሳፍ ነገር ነው።

ከጀርባችን እየተወጋን ያለነው በእንደዚህ አይነት አገልጋዮች ነውና እንዲህ አይነቱን ጤና-ቢስ ቄስ አደብ አስገዙልን!

  ሐዋርያ ዘላለም ጌታቸው ዶ/ር•  ይሄንን ጽሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲንሸራሸር ያየሁት የአንድ አርቲስት ነኝ ያለ ሰው የልቤ ህይወት በተሰኝው ሾው ላይ በገነት...
08/04/2026


ሐዋርያ ዘላለም ጌታቸው ዶ/ር
• ይሄንን ጽሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲንሸራሸር ያየሁት የአንድ አርቲስት ነኝ ያለ ሰው የልቤ ህይወት በተሰኝው ሾው ላይ በገነት ንጋቱ አዘጋጅነት የቀረበው አንተነ ተኸርቁ ከተስኝ ገለስብ ጋር የነበረው ቃለ መጠይቅ ላይ በትዳር ችግር ውስጥ ገብቶ በችግሩ ሊረዳኝ የመጣ ፓስተር በተመሳሳይ ፆታ ገንኙነት ልምምድ ውስጥ ያለ ፓስተር መሆኑን በአደባባይ ሲናገር ሰምተናል።
• የመጀመሪያ ይህንን ጉዳይ የወንጌል አማኝ ማህበረሰብ ስም ለማጠልሸት የሃይማኖቱን መልክ ለማጥቆር የተሄደበት አስተሳሰብ እና አመለካከት እንዳለበት እረዳለው።
• ይሄ ማለት ማንኛውም ነገር የሚጠራው የወል ስም ሁሉንም የሚያካትት እና በተለይ በዛ ስያሜ የሚታወቀውን ማህበረሰብ የሚወክል ሆኖ የሚገኙ ለምሳሌ አንድ ጳጳስ ብዬ ብናገር ጳጳስ የሚለው ቃል የግለሰብ ስያሜ ወይም ከግለሰብ ስያሜ ጋር የተያያዘ ሳይሆን ጳጳስ የሚለው ስያሜ በአንድ ሃይማኖት ውስጥ የሚታወቅ የተጠራው ስያሜ በቀጥታ ድርጅታዊ ሃይማኖታዊ መልክ እንጂ ግለሰባዊ መልክ ሊኖረው አይችልም።
• ስለዚህ ይሄ ሰው የተናገራቸው ጉዳዮች አንድም ሃይማኖት ወይንም ወንጌል አማኙን በሚወክል የወል ስም ላይ የተንጠለጠለ ስለሆነ ማንኛውንም የወንጌል አማኝ የሚወክል መሪን ይወክላል።
• ህዝብ ውስጥ የሚገባው መረዳትም ሆነ እውቀት የሃይማኖት መሪዎች የሚል እንጂ የአንድ ግለሰብ ሰህተት ወይንም የሀጥያት ህይወትን አይወክልም። ስለዚህ ባለቤት አልባው የወንጌል አማኝ ማህበረሰብ ይህንን እውነት ሊጋፈጥ ወይንም በፊት ለፊት ሊቃወምና ሊጠየቅ ይገባል።
• በውስጥ ጉዳያችን ላይ ሃይላችሁን ጉልበታችሁን ለማሳየት የምትሞክሩ የወንጌል አማኝ አክቲቪስቶች እና ተናጋሪዎች እውነተኛውን የወንጌል አማኝ ተሟጋችነት ልታሳዩ ነው የሚገባችሁ። የወንጌል አማኝ ባለቤት የሌለው ስለሆነ ብቻ በሚነሱ አጀንዳዎች ነብይ እከሌ ሳይባል ነብያት ተብሎ ሲጠራ ፓስተር እከሌ ሳይባል ፓስተር ተብሎ ሲጠራ ፓስተሮችን ሁሉ የሚወክል እንጂ አንድን ስህተት ልምምድ ያለውን ፓስተር የሚወክል አይደለም።
• ይሄንን እያነበበ ያለ ይሄንን ሚዲያ እየተከታተለ ያለ ምዕመንህ ፓስተር የሚለውን ስም የሚያውቀው በአንተ በእረኛው ነው። እና አንድ ፓስተር እንዲ አረገኝ ወይንም እንዲሆንኩ ብሎ አንድ ሰው ሲናገር ምዕመንህ አንተ ነህ ትዝ የምትለው አንተም ልትሆን ትችላለህ ብሎ ነው የሚያስበው።
• ስለዚህ የወንጌል አማኝ መሪዎች እረኞች በሙሉ ሁሉ ይሄንን አካሄድ እስከመቼ በዝምታ ባለቤት አልባነትን እንደምናይ አይገባኝም። እንዲህ አይነት ክሶችም በየአደባባዩ የእግዚአብሔርን መንግስት ለወንጌል እንቅፋት እንደሚሆን መረዳት እንዴት እንዳቃተን አላውቅም።
• አንዳንድ ነብያት ተብሎ ነብያት የሚባሉ ግለሰቦች የሉም። ነብይ የሚባል የወንጌል አማኝም ሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሰ የአገልግሎት ጸጋ እና ቢሮዎች ስለዚህ ስም በማጥፋት እምነታችንን በማጠልሸት ላይ የተመሰረተ የውስጡም ይሁን የውጭ አካሄድ ከዚህ በኋላ ባለቤት ሊኖረው እና እንዲህ ያሉ ጉዳዮች ሊቆም ይገባዋል የሚል አቋም አለኝ።
• ሃገራዊ ባለቤትነት እንዳለው ህዝብና ማህበረሰብ ለእንደዚህ
አይነት ጉዳዮች ንቁ ልንሆን እና መብታችንን እንደ ወንጌል አማኞች ልናስከብር ይገባል ብዬ አምናለሁ። ይሄንን እውነት ስናገር የወንጌል አማኙን የባለቤትነት መንፈስ አልባ፣ የመሪ አልባ
፣ የጠያቂነትና የተጠያቂነት አልባ መሆኑን እያስታወስኩኝ መሪዎች እንዲህ አይነት ስራ ላይ ቢያተኩሩ ከው

  ‼️ በወ/ሮ  ገነት ንጋቱ እና  በአቶ  አንተነህ ተኸርቁ መካከል  በተደረገው  ቃለ መጠይቅ  ላይ  ለእምነቱ  ተከታዮች  ካላቸው  ጥላቻ  በመነሳት  የወንጌል  አማኞችን  መንፈሳዊ  ገ...
08/04/2026

‼️


በወ/ሮ ገነት ንጋቱ እና በአቶ አንተነህ ተኸርቁ መካከል በተደረገው ቃለ መጠይቅ ላይ ለእምነቱ ተከታዮች ካላቸው ጥላቻ በመነሳት የወንጌል አማኞችን መንፈሳዊ ገጽታ የሚያበላሽ ምልልስ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው ጉዳይ በእርግጥ ጉዳዩ እውነት ከሆነ የተጠቀሰው አገልጋይን ማንነት በስም መጥቀስ የሚያስፈልግ ሲሆን ይህ ባልሆነበት በደፈናው ሰዎች ለእምነቱና ለተከታዮች ያላቸው ገጽታ እንዲበላሽ ሆን ተብሎ የተሰራጨ ስለሆነ ካውንስሉ በህግ እንዲጠየቁ ክስ የመሰረተባቸው ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ በልዩ ልዩ መድረኮች የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችንና መድረኮችን በመጠቀም ሙያዊ ስነ ምግባርን ባልተከተለ መንገድ የወንጌል አማኝ እምነት ተከታዮችን ገጽታ ለማበላሸት የሚሰሩ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ካውንስሉ አሳስቧል ።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
የወንጌል አማኞች ድምጽ !

Address

London

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቅኔ ቲዩብ - kene tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share