22/07/2023
★ቅዱስ ቁርአን ከመፅሀፍ ቅድስ ገልብጧል ለሚለው ትችት የማያዳግም ኢስላማዊ መልስ ★
ክፍል ~1~ ‼
ዶ/ር ዛኪር ናይክ - peace tv amharic
¶ለመጀመሪያ ጊዜ ብሉይ ኪዳን (መፅሀፍ ቅዱስ) #በአረብኛ ቋንቋ የተተረጎመው ነቢዩ ከሙሀመድ (ሰአወ) ህልፈት ወይም ከሞቱ ከ200 አመታት በኋላ ነው ።¶
በመፅሀፈ ኢሳያስ 29:12 "ማንበብና መፃፍ የማይችለውን ነቢይ ይከተላሉ ይላል
ቅዱስ ቁርአን ከመፅሀፍ ቅዱስ ነው የኮረጀው ብለው ሂስ የሚያቀርቡ ሰዎች ያለተረዱት ነገር ቢኖር.......
☞ነቢዩ ሙሀመድ (ሰአወ) ማንበብም ሆነ መፃፍ የማይችሉ ከመሆናቸውም ባሻገር በነበሩበት ዘመን በአረብኛ ቋንቋ የተተረጎመ ብሉይ ኪዳንም አዲስ ኪዳንም መፅሀፍ ቅዱስ በፍፁም አለመኖሩን ትልቁ ማስረጃ ነው ።✔ አእምሮ ላለው ብቻ‼
ሲቀጥል
☞ለመጀመሪያ ጊዜ ብሉይ ኪዳን በአረብኛ ቋንቋ የተተረጎመው (እአአ) በ 900 ዓል #አርፋዲያ በተባለ ሰው ነው።
ይህ ማለት ነቢዩ ሙሀመድ (ሰአወ) ከሞቱ ከ200 አመት በኋላ መሆኑ ነው ።
እዚህ ጋር ልብ አድርጉ☞ ከ 200 አመታት በኋላ‼
☞ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ ኪዳን (ወንጌል) ወደ አረብኛ የተተረጎመው #አርፔኒየስ በተባለ ሰው (እአአ) 1616 ነው።
ይህ ማለት ነቢዩ ሙሀመድ (ሰአወ) ከሞቱ ከ1,000 አመታት በኋላ መሆኑ ነው ።
እዚህም ጋ በደምብ ልብ አድርጉልኝ☞ ከ 1000 አመታት በኋላ‼
☞በእርግጥ ቁርአንና ባይብል ሊያመሳስላቸው የሚችል ጥቂት መልእክቶች ይኖራሉ ...... ይህ ማለት ቅዱስ ቁርአን ቀድሞ ከመጣው ባይብል ኮርጆ ነው ለማለት አያስችልም፣ አያስደፍርምም,,,
ሁለቱም ምንጩ አንድ ከሆነ ከሌላ ከሶስተኛ አካል እንደመጡ ሊጠቁሙ ይችላል ።
☞የአላህ (ሱወ) መልእክት በአንድ አምላክ የማመን መልእክት ነው ።
ቀደም ሲል ከአላህ ለሰው ልጆች የተሰጡ መፅሀፍት በክልል ወይም በጊዜው የተገደቡ ሲሆን,, በሰው ልጅ የተበረዙና የተከለሱ በርካታ ነገሮችን ይዘዋል ።
እንደዛም ሆኖ የተወሰኑ የጋራ የሆኑ መመሳሰሎች ዛሬም ድረስ አሉ ።
ይህንን መነሻ በማድረግ ብቻ ነቢዩ መሀመድ ሰአወ ከመፅሀፍ ቅዱስ ኮረጀዋል ማለት በፍፁም አያስችልም ።
እንዲሁም ደግሞ (አዲስ ኪዳንና ብሉይ ኪዳን) በርካታ መመሳሰሎችም ስላላቸው ኢሳ (አሰ) ከብሉይ ኪዳን ኮርጆ ነው ማለትም አይቻለም ።
የሁለቱም ምንጭ አንድ ነውና ።
☞ለምሳሌ አንድ ተማሪ ከሌላ ተማሪ ፈተና ቢኮርጅ ከማን እንደኮረጀ የመልስ ወረቀቱ ላይ አይፅፍም ።
☞ ነቢዩ ሙሀመድ (ሰአወ) በቁርአን በተገለፀላቸው መሰረት ሙሳ ፣ኢሳ ፣ኢብራሂም (ዐሰ) ከአላህ የተላኩ ነቢያቶች መሆናቸውን በቁርአን (በአላህ ቃል) አስተላልፈዋል,,,,
የሚገባቸውን ክብርም ሰትተዋል ። እንግዲህ ቁርአንን ከመፅሀፍ ቅዱስ ቢኮርጁ ኖሮ ይህንን አያደርጉም ነበር ። ይህም ላለመኮረጁ ሁለተኛው ማስረጃ ነው ።
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
☞ታሪካዊ በሆኑ ጉዳዮች ብቻ በመመርኮዝ መፅሀፍ ቅዱስ ወይም ቁርአን ልክ ናቸው ለማለት አንችልም ። ማን ትክክል እንደሆነ ሳይንሳዊ እውነታዎችን በመመርኮዝ በሚቀጥለው ክፍል እንመለከታለን ።
https://www.facebook.com/profile.php?id=100064506050455 ዶ/ር ዛኪር ናይክ - peace tv amharic
ክፍል ~2~ ይቀጥላል …………
#ሼር✔