ሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ lmka Teklehaymanot church

  • Home
  • United Kingdom
  • Liverpool
  • ሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ lmka Teklehaymanot church

ሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ lmka Teklehaymanot church በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዩኬና አየርላንድ ሀገረ ስብከት የሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ

Divine Liturgy: Ascension of our Lord 🙏🏽✝️       #ዕርገት
18/05/2026

Divine Liturgy: Ascension of our Lord 🙏🏽✝️

#ዕርገት

Divine Liturgy: Ascension of our Lord 🙏🏽✝️   #ዕርገት
18/05/2026

Divine Liturgy: Ascension of our Lord 🙏🏽✝️

#ዕርገት

The Translation of the Holy relics of St Teklehaymanot. 🙏🏽✝️
11/05/2026

The Translation of the Holy relics of St Teklehaymanot. 🙏🏽✝️

Passion Week ✝️🙏🏽
07/04/2026

Passion Week ✝️🙏🏽

Hosanna in Liverpool ✝️🙏🏽
05/04/2026

Hosanna in Liverpool ✝️🙏🏽

በዩኬና አየርላንድ የተካሄደውን ሕገወጥ "ሹመት" አስመልክቶ ከምዕመናን ኅብረት የተሰጠ መግለጫ
28/03/2026

በዩኬና አየርላንድ የተካሄደውን ሕገወጥ "ሹመት" አስመልክቶ ከምዕመናን ኅብረት የተሰጠ መግለጫ

ከዩኬና አየርላንድ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የተላለፈ የአቋም መግለጫ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አንድ አምላክ አሜን። “… በእነርሱም ምክንያት የእውነት መንገድ ይሰደባል።” ፪ ጴ...
28/03/2026

ከዩኬና አየርላንድ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የተላለፈ የአቋም መግለጫ

በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አንድ አምላክ አሜን።

“… በእነርሱም ምክንያት የእውነት መንገድ ይሰደባል።” ፪ ጴጥ ፪፥፪

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማዋን ቀኖናዋን እና ትውፊቷን ጠብቃ ልጆቿም በዚህ ጥላ ሥር አንዲኖሩ ስታስተምር ኖራለች፣ ለወደፊቱም ትኖራለችም፤ ሆኖም በውጭ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የተሟላ አገልግሎት እንዲያገኙ፣ በመንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት በኩልም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማድረግ በሚገኙበት ሀገረ መንግሥት የሕግ ማዕቀፍ ጋር የተስማማና የቤተ ክርስቲያናችንን ልእልና፤ ኲላዊነት፤ዓለማአቀፋዊነት እንዲሁም መዋቅራዊ ሰንሰለት የጠበቀ ወጥ ደንብ በማውጣት እና መዋቅራዊ ሰንሰለቱን የጠበቀ የአስተዳደር ሥርዓት ዘርግታ እየመራች ትገኛለች። በውጭ ከሚገኙ አህጉረ ስብከት መካከል ግንባር ቀደሙ የዩኬ እና አየርላንድ ሀገረ ስብከት አንዱ ነው። ሀገረ ስብከቱ እንዳሳለፈው ዘመን እና በሥሩ ካሉት ሊቃውንት ፤ ካህናት ፤ መምህራንና ምእመናን ቁጥር አንጻር የሚጠበቅበትን እንዳልተወጣ የሚታወቅ ነው። በተለይም ነፍሰ ሔር ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካረፉ በኋላ ሀገረስብከቱ ላለፉት 6 አና ከዚያ በላይ ለሆኑ ዓመታት ያለ ሥራ በጥቂት ሰዎች ብቻ እየተመራ፤ የሚጠበቅበትን ተግባር እና ኃላፊነት ሳይወጣ ቀርቷል።

ይህ ያሳሰባቸው ካህናት እና ምእመናን በትጋት አብያተ ከርስቲያናት አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ በማስተባበር ለሚመለከታቸው አካላት ከብፁዕ ወቅዱስ ቅዱስ ፓትርያርክ ጀምሮ በተዋረድ ያሉብንን ችግሮች ለማስረዳት እና መፍትሔ ለማግኘት በአካል ልዑክ በመመደብ እና በደብዳቤ ብዙ ዓመታት ሲጠይቅ ኖሯል። ቅዱስ ሲኖዶስም በቅርቡ አቤቱታችንን ተቀብሎ የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ወደ ዩኬ ሄደው ለችግሮች መፍትሔ ይዘው አንዲመጡ መወሰኑ ይታወቃል።

ይህንንም ውሳኔ በዩኬ ያሉ ካህናት እና ምእመናን በአዎንታ ተቀብለው ሲጠባበቁ ሊቀ ጳጳሱ ግን በለንደን ከተማ ላይ ብቻ ተወስነው ከሦስት ወር በላይ ተቀምጠው ምንም ችግሮችን የመፍታት እርምጃ ሳይወስዱ መቆየታቸው አሳዝኖናል። በቅርቡም የትኛውንም አብያተክርስቲያናት ያላካተተ እና የቃለ ዓዋዲውን አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 6 በመተላለፍ በእውቂያ ላይ ብቻ አና በዙሪያቸው ያሉትን አባቶች ምደባ በማድረግ ደብዳቤ መላካቸው መላውን ካህናት እና ምዕመናንን ያሳዘነ ሆኖ ሳለ ይባስ ብሎም ካህናቱን እና ምእመናኑን በመናቅ የትውውቅ መርሐግብር እናደርጋለን በማለት የፊታችን እሑድ መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጥሪ ማስተላለፋቸው ለቀኖና ቤተ ክርስቲያን እና ለልጆቻቸው ጩኸት ግድ የሌላቸው መሆኑን በግልጽ አሳይተዋል። በዚህም ምክንያት የአብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤያት ምክትል ሊቃነ መናብርት፣ ዋና ፀሐፊዎች እና የሰንበት ት/ቤቶች ተወካዮች በተገኙበት ዓርብ መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም በአብያተ ክርስቲያናት ኅብረት፣ በማኅበሩ ካህናት ዘዩኬ ወአየርላንድ እና ሊቀ ጳጳሱ ከዚህ ቀደም ባቋቋሙት የጥናት ኮሚቴ አስተባባሪነት አጠቃላይ ስብሰባ በማድረግ ጥልቅ ውይይት ካደረገ በኋላ የመላው ዩኬ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥተናል።


1.⁠ ⁠የዩኬና አየርላንድ አብያተ ክርስቲያናት እና መላው ካህናትና ምእመናን ለመዋቅራዊ አንድነት እና ለሲኖዶሳዊ ሉዓላዊነት ያለንን ሙሉ ድጋፍ በመስጠት ምን ጊዜም ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጣቸውን መመሪያዎች፣ ሕጎችና ደንቦች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንቀበላለን።

2. በብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ የቃለ ዓዋዲውን አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 6 በመተላለፍ አድባራቱን ባገለለ መልኩ በድብቅ የተደረገው “የጨረቃ” ሹመት ከቃለ ዓዋዲውና ከሕገ ቤተክርስቲያን አንጻር የሕግ መሠረት የሌለው በመሆኑ ሙሉ በሙሉ አንቀበለውም በየትኛውም አጥቢያ ላይም ተፈጻሚነት አይኖረውም።


3.⁠ ⁠በሊቀ ጳጳሱ እና በካህናት ጉባኤ በአንድነት ከአንድ ዓመት በፊት የተሰየመው እና በሊቀ ጳጳሱ ደብዳቤ ደርሶት አጥኚ ኮሚቴው ያዘጋጀውን ጥናት በየደረጃው አወያይቶ ለተግባራዊነቱ መሥራት ሲገባ ፣ ጥናቱን ሳይቀበሉ በግል የተደረገውን ሂደት የማንቀበለው መሆኑን እየገለጽን ጥናቱ በአስቸኳይ ወደ ሥራ እንዲገባ እንጠይቃለን።

4.⁠ ⁠በዩኬ የምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ለዓመታት እየደረሰባት ከሚገኘው አስተዳደራዊ በደል አኳያ በትዕግሥትና በስክነት ስናካሂደው የቆየነውን ትግል አጠናክረን የምናስቀጥል መሆኑን እንገልጻለን።

5.⁠ ⁠የሁሉንም አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች እና ተወካዮች ሰብስቦ እና አወያይቶ ቅቡልነት ያለው ሀገረ ስብከት ከማቋቋም ይልቅ በቅርብ የሚያውቋቸው ከአንድ ደብር ካህን እና ዲያቆን መርጠው ሀገረ ስብከት መድቤአለው እና ለትውውቅ ተገኙ ብሎ ስብሰባ መጥራቱ የቤተ ክርስቲያንን ችግር ለመፍታት ሳይሆን በቤተክርስቲያን ላይ መሳለቅ ነው፤ በቃለ አዋዲ አንቀፅ ፵ መሰረት የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ተመስርቶ በተገቢው መንገድ ሳይሆን በሕገ ወጥ" የተደረገው ሹመት በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ የማንቀበለው ከመሆኑም በላይ ለዚህ ሂደት አድባራቱ ምንም ዓይነት ትብብር እንደማያደርጉና ሊቀ ጳጳሱ በአስቸኳይ ለውይይት የተዘጋ በራቸውን እንዲከፍቱ እንጠይቃለን።

6. በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ካለው ያልተቋረጠ በደል የተነሳ መላው አድባራት እና ባለ ድርሻ አካላት ሕግንና ሥርዓትን በመጠበቅ የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ሁሉን አቀፍ የሆነ በጥናት ላይ የተመሠረተ ቀጣይ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናስታውቃለን።

7.⁠ ⁠ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ጀምሮ በየደረጃው የምትገኙ አባቶች እና መዋቅሩ በሙሉ ለዘመናት በዩናይትድ ኪንግደም የተንሰራፋውን ብልሹ አሰራር በማስተካከል ቤተ ክርስቲያንን እንድትታደጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅ !

የዩኬና አየርላንድ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት

መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም
ለንደን፤ዩናይትድ ኪንግደም

ግልባጭ
ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
ለውጭ ጉዳይ መምሪያ
ለመንፈሳውያን ማኅበራት በሙሉ
ባሉበት

We had the blessing of visiting the Coptic Orthodox Church, where we shared a wonderful time together in fellowship. It ...
09/03/2026

We had the blessing of visiting the Coptic Orthodox Church, where we shared a wonderful time together in fellowship. It was a meaningful opportunity to strengthen our relationship and discuss how we can continue supporting one another and working together in the future.

ታኅሣሥ ተክለሃይማኖት ✝️🙏🏾        #ተክለሃይማኖት
10/01/2026

ታኅሣሥ ተክለሃይማኖት ✝️🙏🏾

#ተክለሃይማኖት

Address

1 Buckingham Avenu
Liverpool
L173BA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ lmka Teklehaymanot church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ lmka Teklehaymanot church:

Share