የሐዋርያው አቢይ ማስታወሻ apostle Abiy Notes

የሐዋርያው አቢይ ማስታወሻ apostle Abiy Notes The fear of the Lord is the beginning of knowledge, but fools despise wisdom and instruction. Prover

ከእርሱ ጋር አስነሣን !ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፣6 7ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው ስለእኛ ነው። ክርስቶስ ወደ...
12/04/2026

ከእርሱ ጋር አስነሣን !
ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፣6 7
ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው ስለእኛ ነው። ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው እኛ በሃጢያታችን ምክኒያት ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላላም እንዳንለያይ ነው።
ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፣21 22
ክርስቶስ ኢየሱስ የሞተው እኛ በሃጢያታችን መሞት የነበረበንን ሞት ነው። ክርስቶስ የሞተው በእኛ ምትክ ነው። ክርስቶስ የሞተው ለእኛ ነው።
በመጀመሪያ ሰው የተፈጠረው ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላላም እንዲኖር ነበር። በእግዚአብሔር የተፈጠረው ሃጢያትን የማያውቅ ፍጹም ሰው ነበር።
ሰው ከእግዚአብሔር የተለየው ሃጢያት በሰራ ጊዜ ነበር።
እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና። ዘፍጥረት 2፣16 17
ክርስቶስ የመጣው እኛ ወደፊት እንዳንሞት ከእግዚአብሔርም ጋር ለዘላላም እንዳንለያይ ነው።
ክርስቶስ ሃጢያት ያልተገኘበት ፍጹም ነው። ክርስቶስ መሞት አይገባውም ነበር። ክርስቶስ የሞተው እኛ ሞት ሰለሚገባን ነበር። ክርስቶስ የሞተው እኛን ከሞት ሊያስነሳን በእኛ ምትክ ነው።
ክርስቶስ የሞተው ለእኛ ትንሳኤን ሊሰጠን ነው።
እኛ ከክርስቶስ ጋር አብረነው ካልተነሳን ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።
የክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ "ከእለታት አንድ ቀን ክርስቶስ ከሞት ተነሳ" ብለን ብቻ የምናስታውሰው የክርስቶስ ታሪክ አይደለም። የክርስቶስ ትንሳኤ የእኛም ከሙታን የመነሳት ልምምድ ነው። በክርስቶስ ሞትና ተንሳኤ የምናምን ሁላችን ከሞት ተነስተናል።
ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፣5-7
የትንሳኤ በአል የክርስቶስ ብቻ ሳይሆን የእኛም የትንሳኤ በአል ነው።
መልካም የትንሳኤ በአል
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

09/03/2026

ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ በአቢይ ዋቁማ ዲንሳ for he who comes to God by Abiy Wakuma Dinsa

06/03/2026

Nyd de videoer og den musik, du holder af, upload originalt indhold, og del det hele med venner, familie og verden på YouTube.

እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል። ዕንባቆም 3:18...
18/02/2026

እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።
ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።
ዕንባቆም 3:18-19

ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ሮሜ 5:8
13/02/2026

ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ሮሜ 5:8

26/01/2026

ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥
ኤፌሶን 2:5

20/01/2026

ቀራጮችም ደግሞ ሊጠመቁ መጥተው፦ መምህር ሆይ፥ ምን እናድርግ? አሉት። ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ አትውሰዱ አላቸው። ጭፍሮችም ደግሞ፦ እኛ ደግሞ ምን እናድርግ? ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም፦ በማንም ግፍ አትሥሩ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፥ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ አላቸው። ሉቃስ 3፡12-14

መልካም የልደት በአል። እንኳን ለገና በአል አደረሳችሁ!
06/01/2026

መልካም የልደት በአል። እንኳን ለገና በአል አደረሳችሁ!

Happy Christmas!
25/12/2025

Happy Christmas!

የብልጽግና ወንጌል ምሥጢር ሲገለጥ  በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡16ወንጌል በሃጢያታ...
28/11/2025

የብልጽግና ወንጌል ምሥጢር ሲገለጥ
በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡16
ወንጌል በሃጢያታቸው ምክኒያት ለዘላለም ከእግዚአብሔር የተለያዩትን የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም እንዲኖሩ የሚያስችል ታላቅ የምስራች ነው።
አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1:10-11
ወንጌል ጠላቶች የነበሩትን የሰው ልጆች በማስታረቅ የእግዚአብሔር ወንድና ሴት ልጆች አድርጎ መቀበል የሚያስችል ታላቅ የምስራች ነው።
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ የዮሃንስ ወንጌል 1:12
ወንጌል በሃጢያት ምክኒያት ከሰይጣን የባርነት እስራት ወስጥ ሲሰቃዩ የነበሩትን የሰው ልጆች በሰይጣን ላይ ስልጣን የሚሰጥ የእግዚአብሔር ታላቅ የማዳኛ ሃይል ነው፡፡
እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። ወደ ዕብራውያን 2:14
#የብልጽግናወንጌል #ወንጌል #ኢየሱስ #የምስራች #እግዚአብሔር #የበለጸገ #መልካምዜና

Address

48 Smith Street New Town
Birmingham
B193EN

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሐዋርያው አቢይ ማስታወሻ apostle Abiy Notes posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to የሐዋርያው አቢይ ማስታወሻ apostle Abiy Notes:

Share