The Church of the Resurrection Power of Jesus in Paris

The Church of the  Resurrection Power of Jesus  in Paris Informations de contact, plan et itinéraire, formulaire de contact, heures d'ouverture, services, évaluations, photos, vidéos et annonces de The Church of the Resurrection Power of Jesus in Paris, Organisation religieuse, 5 Rue de la noue, Bagnolet, Paris.

ቤተክርስትያናችን እሁድ ጁን 2/2019 በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ የተመሰረተች ፔንቴኮስታል (Pentecostal) ቤተክርስትያን ስትሆን ከተለያዩ ሌሎች ቤተክርስትያናት ጋር በወንጌል አብሮ በመስራት የምታምን ናት።
አላማችን
አንድና ብቸኛ በሆነው በኤፌሶን 1፥9-10 በተጠቀሰው አለምን በክርስቶስ መጠቅለል በሚለው የእ/ር ራእይ ውስጥ የክርስቶስ ህይወትና የትንሳኤውን ሃይል መግለጥ ነው። የትንሳኤው ሃይል ቤተክርስትያን-ፈረንሳይ
ቤተክርስትያናችን በሜይ 30/2019 በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ ተመስርታ የመጀመርያው መንፈሳዊ ፕሮግራም እሁድ ጁን 2/2019 ተካሂዶአል። ቤተክርስትያኒቱ ፔንቴኮስታል (Pentecostal) ቤተክርስትያን ስትሆን

ከተለያዩ ሌሎች ቤተክርስትያናት ጋር በወንጌል አብሮ በመስራት የምታምን ናት።

መልእክተኝነታችን (አላማችን)
አንድና ብቸኛ በሆነው በኤፌሶን 1፥9-10 በተጠቀሰው አለምን በክርስቶስ መጠቅለል በሚለው የእ/ር ራእይ ውስጥ የክርስቶስ ህይወትና የትንሳኤውን ሃይል መግለጥ ነው።

ተልእኮ (Mission)

1. አማኞች በእ/ር ቃል የታነጹ እንዲሆኑ መሰረታቸውን የሚያጸኑ ትምህርቶችና ስብከቶችን መስጠት፣
2. ክርስቶስን መምሰል ማእከል ያደረጉ ትምህርቶችንና ስብከቶችን መስጠት፣
3. አማኞች የእ/ርን ፈቃድ አውቀው የህይወታቸው መርህ እንዲያደርጉት ማነጽ፣
4. አማኞች በሚኖሩበት ማህበረሰብ ውስጥ የክርስቶስ ደቀመዝሙር ሆነው ተጽእኖ ፈጣሪ እንዲሆኑ ማነጽ፣
5. አማኞች የክርስትና እሴቶችን:- እምነትን፣ ፍቅርን፣ ጸድቅን፣ ቅድስናን ፣ እ/ር መፍራትን እርስ በእርሳቸው እንዲያሳዩ ማነጽ፣
6. የክርስትና የክብር ህይወት በአማኝ ህይወት ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ እንዲገለጥ ማነጽ፣
7. በመንፈስ ቅዱስ የጸጋ መገለጥ በፈውስ ፣ ሃይልን በማካፈል፣ በነጻ ማውጣት ማገልገል፣
8. ለማያምኑ የክርስቶስን ወንጌል መመስከር፣
የእምነት አቋም
1. መጽሃፍ ቅዱስ 66ቱን የብሉይና የሐዲስ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ የጻፉትና ሙሉ ስልጣን ያለው የህይወታችን መመርያ እንደሆነ እናምናለን፡፡

2. በአንድ አምላክ፣ በሶስት አካል እና በሶስት የመገለጥ ስርዓት እናምናለን፡፡ በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ በስላሴ እናምናለን፡፡

3. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር አንድያ ልጅ መሆኑን ፣ ከድንግል ማርያም መወለዱን ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑን እናምናለን፡፡

4. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ቤዛ ሆኖ በመስቀል ላይ መሞቱን መቀበሩንና በሶስተኛው ቀን በአካል ከሙታን መነሳቱን ወደ አብ ቀኝ ማረጉንና አሁን ለእኛ እንደሚማልድ ደግሞም በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ እንደሚመለስ እናምናለን፡፡

5. ሰው በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠሩን ፣ ሆኖም በሃጢአት በመውደቁ ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣና ፍርድ ያለበት በደለኛ መሆኑን እናምናለን፡፡

6. ሰው ከሃጢአት ሃይልና ቅጣት ሊድን የሚችለው ሃጢአት የሌለበት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ምትክ ሆኖ በፈጸመው የቤዛነት ስራ ብቻ በመሆኑ ሰው በእግዚአብሔር ፀጋ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ እንደሚጸድቅ እናምናለን ፡፡

7. በሃጢአት ምክንያት ወደ ሰው ህይወት በሽታ፣ ጭንቀት ፣ ፍርሃት፣ ሞት፣ ፍሬያማ ያልሆነ ህይወት፣ ተስፋ መቁረጥ እና ሌሎች ከጨለማ አለም የሆኑ ስርአቶች ገብተውበታል፡፡እነዚህ ሁሉ በክርስቶስ የመስቀል ስራ እንደተሻሩና በእምነት በነፃነት መኖር እንደሚቻል እናምናለን፡፡

8. ሰው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ዳግመኛ ሲወለድ አዲስ ፍጥረት እንደሚሆን መንፈስ ቅዱስ በሕይወቱ እንደሚሰራ እናምናለን ፡፡

9. ሰው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ንሰሐ በገባ ጊዜ በክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ መተባበሩን ለመግለጽ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በውሃ ውስጥ በመጥለቅ እንዲጠመቅ እንዲሁም ጌታ እስኪመጣ ሞቱን ለመናገርና ከምዕመናን ጋር ያለውን ሕብረት ለመግለጽ የጌታን እራት እንደሚካፈል እናምናለን::

10. መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ሕይወት ውስጥ እንደሚኖር እናምናለን:: አማኙ በመንፈስ ቅዱስ ሲጠመቅ ሃይልን እንደሚቀበልና በልሳን እንደሚናገር በየጊዜውም በመንፈስ ቅዱስ እንደሚሞላ እናምናለን፡፡

11. በቤተክርስትያን አንድነትና በክርስቶስ አካልነቷ እናምናለን፡፡

12. በክርስቶስ ዳግም ምፅዓትና በትንሳኤ እናምናለን ፣ ይህ አለም እንደሚያልፍና አዲስ ሰማይና ምድር ለአማኝ እንደተዘጋጀ እናምናለን ፡፡

13. የመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታዎች ሁሉ እስከ ክርስቶስ ምፅዓት ድረስ እንደሚሰሩ እናምናለን፡፡

ወንድማችን ኤልያስና እህታችን አዜብን አስመልክቶ የተዘጋጀ እ/ርን የማመስገን/ የመልስ/ ፕሮግራም። እንኩዋን ጌታ በነገር ሁሉ ረዳችሁ።
07/03/2026

ወንድማችን ኤልያስና እህታችን አዜብን አስመልክቶ የተዘጋጀ እ/ርን የማመስገን/ የመልስ/ ፕሮግራም። እንኩዋን ጌታ በነገር ሁሉ ረዳችሁ።

08/02/2026

ፌብሩዋሪ 1/2026 በፈረንሳይ የወንጌላውያን አብያተ ክርስትያናት ህብረት ምስረታ መርሃ ግብር- አምልኮ ክፍል 1

04/02/2026
እሁድ ፌብሩዋሪ 1/2026 በፈረንሳይ የወንጌላውያን አብያተ ክርስትያናት ህብረት ተመስርቶአል። በዚህ መርሃ ግብር ላይ የተሳተፉት፦1. ጵንኤል የክርስቶስ ወንጌል ቤ/ክ2. ሻሎም የኤርትራ ወን...
04/02/2026

እሁድ ፌብሩዋሪ 1/2026 በፈረንሳይ የወንጌላውያን አብያተ ክርስትያናት ህብረት ተመስርቶአል። በዚህ መርሃ ግብር ላይ የተሳተፉት፦

1. ጵንኤል የክርስቶስ ወንጌል ቤ/ክ
2. ሻሎም የኤርትራ ወንጌላውያን ቤ/ክ
3. የትንሳኤው ሃይል ቤ/ክ ናቸው።

በሻሎም የኤርትራ ወንጌላውያን ቤ/ክ አዳራሽ በተደረገው በዚህ መርሃ ግብር ላይ የፀሎት፣ የአምልኮ፣ የእ/ር ቃል፣ ህብረቱን አስመልክቶ ገለፃ፣ የልጆች ዝማሬና ባርኮት ግዜ እንዲሁም የህብረት ግዜ ነበረን።

እለቱ በጋራ በተደረጉ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ላይ የጌታ ህልውና የነገሰበት፣ የምስጋና ግዜ ፣ እንዲሁም ወንጌልን በጋራ ለማገልገል የተነቃቃንበት ግዜ ነበር።

ክብር ሁሉ ለክርስቶስ እየሱስ ይሁን።

የፈረንሳይ አብያተ ክርስትያናት ህብረት የምስረታ መርሃ ግብርእሁድ ፌብሩዋሪ 1/2026 ከ13-18 ሰአት።ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
22/01/2026

የፈረንሳይ አብያተ ክርስትያናት ህብረት የምስረታ መርሃ ግብር
እሁድ ፌብሩዋሪ 1/2026 ከ13-18 ሰአት።
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

26/12/2025

" እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፥ ልዑል ሆይ፥ ለስምህም ዝማሬ ማቅረብ፤"
መዝሙር 92፥1

የመጋቢ ቴዎድሮስ እና እህት ፀዳለ 10ኛ የጋብቻ አመትን አስመልክቶ በቤተክርስትያኒቱ ቅዱሳን የተዘጋጀ ድንቅ የምስጋና መርሃ ግብር የፎቶ ማስታወሻ። ይህንን መርሃ ግብር ያዘጋጃችሁ የትንሳኤው...
06/08/2025

የመጋቢ ቴዎድሮስ እና እህት ፀዳለ 10ኛ የጋብቻ አመትን አስመልክቶ በቤተክርስትያኒቱ ቅዱሳን የተዘጋጀ ድንቅ የምስጋና መርሃ ግብር የፎቶ ማስታወሻ። ይህንን መርሃ ግብር ያዘጋጃችሁ የትንሳኤው ሃይል ቤ/ክ ቅዱሳን ጌታ አብዝቶ ይባርካችሁ። እንደሁልግዜው ፍቅራችሁን፣ መልካምነታችሁን፣ በጎነታችሁን በብዙ ገልጣችኋል።

በእለቱም ግብዣችንን አክብራችሁ የተገኛችሁ በፓሪስ የምትገኙ አብያተ ክርስትያናት መሪዎችና ቅዱሳን ፣ እንዲሁም ወዳጅ ዘመድ ጌታ አብዝቶ ይባርካችሁ፣ እጅግ ደስ ብሎናል። በተለይም የኤልሮኢ ቤ/ክ መሪ ወንድም ነብዩ በቀለ እንዲሁም የሻሎም ቤ/ክ መጋቢ አልአዛር ጴጥሮስ ተገኝታችሁ በፀሎታችሁም ስለባረካችሁን በብዙ ተባረኩ። እንዲሁም ወንድም አላዛር ከጀርመን በዚህ መርሃ ግብር በመገኘት ድንቅ የግዜውን ቃል ስላካፈልከን ጌታ በብዙ ይባርክህ።

26/07/2025

"እግዚአብሔር ታላቅ ነው እጅግም የተመሰገነ ነው፤ ለታላቅነቱም ፍጻሜ የለውም።"
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 145:3
ዘማሪ ያሬድ በቃሉ
13/07/2025

Wonderful time ! Lots of Praise ! Thanksgiving ! Celebrations ! God is Great.
19/07/2025

Wonderful time ! Lots of Praise ! Thanksgiving ! Celebrations ! God is Great.

1ኛ ሳሙኤል 7፥1212 ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አኖረው፤ ስሙንም፡— እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል አቤንኤዘር ብሎ ጠራው።ባለፉት 6 የምህረት አመ...
19/07/2025

1ኛ ሳሙኤል 7፥12
12 ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አኖረው፤ ስሙንም፡— እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል አቤንኤዘር ብሎ ጠራው።

ባለፉት 6 የምህረት አመታት ከእኛ ጋር የነበረ፣ የረዳን እግዚአብሄር ስሙ ይባረክ።

እሁድ ጁን 9/2024 በቤተክርስትያናችን የተደረገ የውሃ ጥምቀት: እህት ህይወት እና እህት ሳራ። ክብር ለጌታ ይሁን።
21/04/2025

እሁድ ጁን 9/2024 በቤተክርስትያናችን የተደረገ የውሃ ጥምቀት: እህት ህይወት እና እህት ሳራ። ክብር ለጌታ ይሁን።

Adresse

5 Rue De La Noue, Bagnolet
Paris
93170

Heures d'ouverture

Mercredi 18:00 - 20:00
Dimanche 15:00 - 18:00

Téléphone

+33643924927

Site Web

Notifications

Soyez le premier à savoir et laissez-nous vous envoyer un courriel lorsque The Church of the Resurrection Power of Jesus in Paris publie des nouvelles et des promotions. Votre adresse e-mail ne sera pas utilisée à d'autres fins, et vous pouvez vous désabonner à tout moment.

Partager