16/07/2025
🔵 ቁልቢ ገብርኤል ገዳም አመሠራረት🔵
♦♦ቁልቢ ገብርኤል ከአዲስ አበባ በስተም ሥራቅ 461 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጋራ ሙለታ የሚገኝ ከተመሰረተ ጀምሮ ብዙዎቹን እንቆቅልሸ የፈተ ቤተ ክርስ ቲያን ነው፡፡
♦♦በዘጠነኛው ክፍለ ዘመነ ዮዲት ጉዲት ተነሥታ አብያተ ክርስቲያናትን ስትመዘብር፣ ክርስቲያኖችን ስትገድልና መጻሕፍትን ስትቆ ነጻጽል ንጉሥ አንበሣ ውድም በአኩስም እና በአከባቢዋ የነበሩ ታቦታትንና ንዋያተ ቅዱሳትን በመያዝ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ዝዋይ መጣ፡፡
♦♦ከ40 ዓመታት ስደት በኋላ አንበሣ ውድም ወደ አኵሱም ሲመለስና ንዋያ ቅዱሳት ቆጠራ ሲደረግ ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል በዝዋይ መቅረቱ ታወቀ፡፡
♦♦ከኤርትራ ደብረ ሲና ማርያም የመጡና አባ ሌዊ የተባሉ አባት ታቦቱን ለማምጣት ከን ጉሡ አስፈቅደው ወደ ዝዋይ መጡ፡፡
♦♦አባ ሌዊ ከሰባት ቀን ሱባኤ በኋላ ታቦተ ቅዱስ ገብርኤልን ይዘው ወደ አኵሱም ሲጓዙ ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ “እኔ ወደ ማሳይህ ቦታ ታቦቱን ይዘህ ሂድ” አላቸው፡፡ አባ ሌዊም ታቦቱን ይዘው ተከተሉት፡፡ በመጨረሻም ቁልቢ ደረሱ፡፡
♦♦ለአባ ሌዊም የተፈቀደላቸው ቦታ ይሄ መሆኑን ታቦቱም በኋላ ዘመን ለሕዝቡ ድንቅ ሥራ እንደሚሠራ ቅዱስ ገብርኤል ነግሯቸው ተሰወረ፡፡
♦♦እሳቸውም ስለታቦቱ ታሪክ ታቦቱ በፍታ ላይ ጽፈው አባ ሌዊ በቦታው ለ130 ዓመታት ያህል አገልግለው በንጉሥ ግርማ ሥዩም ዘመነ መንግሥተ ታኅሳስ 14 ቀን ዐርፈዋል፡፡
♦♦ቱርካዊው ግራኝ አሕመድ ወረራ ዘመን ካህናት ንዋያተ ቅዱሳትን ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ለመጋዝ ተነሱ።ሸዋ ሲደርሱ ታቦተ ገብርኤል አልንቀሳቀስም አለ።
♦♦ካህናቱም ስለገብርኤል ታቦት በበፍታ ላይ የተጻውን እና ሸዋ መቀመጡን ይዘውት በነበረው መጽሐፈ ቀሌ ሜንጦስ ሕዳግ ላይ ጻፉት፡፡መጽሐፉን ዝዋይ ደሴት አስቀምጠውት ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡...........................................................
♦♦ይህ እንዲህ እንዳለ በዝዋይ ደሴት በመጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ያለውን የገብርኤልን ታቦት ታሪክ ያነበበ ሰዎች ለሐረር ገዥ ለነበሩት ለራስ መኰነን ነገሯቸው።
♦♦ራስ መኮንን የሰሙት ገብርኤል ታቦት ታሪክ ልባቸውን ተካናና"ገብርኤል ሆይ! ይህን ደም አፋሳሽ የጎሳዎች ግጭት ካስወገድክልኝ፤ በዚህ ደም አፋሳሽ ቦታ በስምክ ቤተክርስትያን አሰራልሀለው!"ብለው ተሳሉ።
" በአፍህ የተናገርኸውን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በፈቃድህ ተስለሃልና ከከንፈርህ የወጣውን ታደርግ ዘንድ ጠብቅ። "
(ኦሪት ዘዳግም 23:23)
♦♦ልዑል ራስ መኮንን ይህን ስለት ሊሳሉ የቻሉት የሐረር አውራጃ አስተዳዳሪ ሆነው ሳሉ የሐረር ጎሳዎች ዘወትር ውጊያ የሚገጥሙበት ብዙ ደም የሚፈስበት አንድ ደም አፋሳሽ ቦታ ስለነበረ ነው።......................................................
♦♦ለወዳጆቹ ፈጣን ሆነው ቅ/ስ ገብርኤል ራስ መኮንን ስለትን ሰምቶ የተለመደ ጎሳዎች ግጭትን አቁሞ በቦታው ሰላም አመጣላቸው።
♦♦ተሳሉት ተፈጸመላቸው ራስ መኮንንም የቅዱስ ገብርኤል ታቦት የት እንዳለ ሲያፈላልጉ ቡልጋ ውስጥ ከአዠጉጉ ካህናተ ሰማይ ጋር አባ ዱባለ የተባሉ ካህን ያስቀመጡት ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል መኖሩ ተነገራቸው፡፡
♦♦ልዑል ራስ መኰንን አባ ዱባለ መልእ ክት ስለላኩባቸው ከሐረር በተላኩ ካህናት አማካኝነት የቅዱስ ገብርኤልን ታቦት ላኩ፡፡
♦♦ልዑል ራስ መኰንን ከነሠራዊቶ ቻቸው ሸንኮራ ድረስ ሄደው ታቦቱን በመቀበል የካቲት 21 ቀን 1884 ዓ.ም ታቦቱ ቁልቢ ገባ፡፡
♦♦የመቃኞው ሥራ በ1883 ዓ.ም