Catholic Eparchy of Emdeber

Catholic Eparchy of Emdeber Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Catholic Eparchy of Emdeber, Catholic Church, Wolkite.

14/09/2026

የአዲስ ዓመት የበዓል ቅዳሴ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በእምድብር ሀገረስብከት ካቴድራል ቤተክርስቲያን 🌼እንኳን ለ2019 ዓ.ም. በሰላም አደረሳችሁ 🌼
11/09/2026

የአዲስ ዓመት የበዓል ቅዳሴ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በእምድብር ሀገረስብከት ካቴድራል ቤተክርስቲያን

🌼እንኳን ለ2019 ዓ.ም. በሰላም አደረሳችሁ 🌼

  በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ፣ በእምድብር ሀገረ ስብከት የምትገኙ ካህናት፣ ደናግል፣ ምዕመናን፣ እንዲሁም በጎ ፈቃድ ያላችሁ ሁላችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፦የጊዜ ባለቤት፣ የዘመን ባለቤት እ...
10/09/2026



በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ፣ በእምድብር ሀገረ ስብከት የምትገኙ ካህናት፣ ደናግል፣ ምዕመናን፣ እንዲሁም በጎ ፈቃድ ያላችሁ ሁላችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፦

የጊዜ ባለቤት፣ የዘመን ባለቤት እግዚአብሔር ነው። ዘመናትን የሚባርክ፣ ዘመናትን የሚቀያይር እርሱ ነው። 2018 ዓመተ ምህረትን በፍቅሩ ጠብቆ፣ ለ2019 ዓመት በሰላም ስላሻገረንና ስላደረሰን የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን።

እግዚአብሔርን ስናመሰግን በደስታና በተስፋ በተሞላ ልብ ሆነን ነው። «ሁሉን ነገር አዲስ አደርጋለሁ» ይላልና እግዚአብሔር።

ዓመታትን ሲያሻግር ሲቀያይር አዲስ ዓመት ብለን ደግሞ ስናከብር፦

ባለፈው ዓመት እግዚአብሔር የሰጠንን በረከት እየቆጠርንና እያመሰገንን፣
በጎደለብንና ባጎደልነው ነገር ደግሞ በዘንድሮው ዓመት እግዚአብሔር ሙሉ እንዲያደርግልን እኛም የጎደለውን ለመሙላት ጥረት እያደረግን፣
በተለይ ደግሞ ከምንም በላይ እግዚአብሔርን የበለጠ የምንፈራበት፣ የምናከብርበት ለእግዚአብሔር የምንታዘዝበት
ወንድሞቻችንን እንደ ራሳችን አድርገን የምንወድበት፣
ፍጥረትን የምንከባከብበት፣
በተሰጠን ኃላፊነት ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂነት እንዳለብን በመረዳት በመታመን፣
መልካሙን ገድል እንደሚጋደሉ መልካም ክርስቲያኖች መልካም ሥራን እየሠራን የምንኖርበት፣

በእምነት የምንጸናበት፣ በፍቅር የምንቆምበት፣ ስለ ሰላምና ስለ እርቅ የምንጸልይበት፣ የምናውጅበትና የምንሰራበት ዘመን እንዲሆን እግዚአብሔር ዕድል ሰጥቶናል።

እንደ ካቶሊካውያን ምዕመናን፣ እንደ ካቶሊካውያን ወገነ ክህነት፣ እንደ ካቶሊካውያን መነኮሳት፣ በሀገረ ስብከታችን እግዚአብሔር የሰጠንን ታላቁን የስብከተ ወንጌል ተልዕኮ በጽድቅና በቅድስና መፈጸም እንድንችል እግዚአብሔር እንዲያግዘን የምንጸልይበትና የበለጠ የምንተጋበት ጊዜ ነው።

«ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፣ ወንጌልንም አስተምሩ፤ በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው» ብሎ ያዘዘውን ቃል በመከተል፦
ወንጌልን በእውነትና በፍቅር በመስበክ፣
ሥርዓተ አምልኮን በክብር፣ ለቅድስናና ለጽድቅ በመፈጸም፣
በመልካም እረኝነት በመምራት፣
በፍቅር ሌሎችን ወንድሞችና እህቶችን በማገልገል፣
የምንተጋበት ዓመት እንዲሆን ቁርጥ ፍቃድ እንድናደርግና በሲኖዶሳዊነት መንፈስ አብረን ወደ ጌታ መንግሥት እንድንጓዝ ሁላችንም የበኩላችንን ጥረት እንድናደርግ እግዚአብሔር አዲስ ዓመት ሰጥቶናልና። ዘመንን የሚባርክ፣ ዘመንን የሚቀድስ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን፣ ሕዝባችንንና ሀገራችንን እንዲባርክ እንጸልያለን።

2019 ዓመት የቅዱስ ሉቃስ ዘመን፦
የበረከት፣የጽድቅ፣የቅድስና፣የእምነት ያድርግልን።

ሁላችንንም በፍቅር አስተሳስሮ፣ በአንድነትና በአብሮነት፣ እንደ ወንድማማቾች በእግዚአብሔር እንደሚያምኑ ሰዎች በመልካም ሥነ ምግባር እንዲያቆመን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ይሁንልን።

የተባረከ፣ የተቀደሰ 2019 ዓመት ለሁላችንም ይሁን። አሜን!

06/09/2026
በጉራጌ ዞን ፤ እንደጋኝ ወረዳ ፤ በሸርኮ ቀበሌ በመጠናቀቅ ላይ ያለው የሾርኮ የንፁህ መጠጥ ወሃ ፤ የግልና አከባቢ ንጽሕና አጠባበቅ ፕሮጀክት የእስካሁን  የፕሮጀክቱ ግማሽ ጊዜ ግምገማ (m...
04/09/2026

በጉራጌ ዞን ፤ እንደጋኝ ወረዳ ፤ በሸርኮ ቀበሌ በመጠናቀቅ ላይ ያለው የሾርኮ የንፁህ መጠጥ ወሃ ፤ የግልና አከባቢ ንጽሕና አጠባበቅ ፕሮጀክት የእስካሁን የፕሮጀክቱ ግማሽ ጊዜ ግምገማ (midterm Evaluation) አፈፃፀም በባለድርሻ አካላት የመስክ ምልከታ ተካሄዷል።

ነሐሴ 28/2018ዓ.ም

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እምድብር ሀገረ-ስብከት በጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ ሸርኮ ቀበሌ በካሪታስ አውስትራሊያ የጳጳሳት ጉባኤ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እየተገነባና በመጠናቀቅ ላይ ያለው ከፍተኛ የንፁህ መጠጥ ወሀ ፕሮጀክት የእስካሁን አፈፃፀምና ያለበት ደረጃ በክልል፣ በዞን ፣ በወረዳና በእምድብር ሀገረ ስብከት ባለድርሻ አካላት የመስክ ምልከታ የተደረገ ሲሆን፤ የፕሮጀክቱ የእስካሁን አፈፃፀም አበረታችና ተስፋ ሰጪ መሆኑን ተገልጿል።

በወረዳው ሸርኮ ቀበሌ የተገነባው ይህ ከፍተኛ ምንጭ የንፁህ መጠጥ ውሀ ፤ የግልና አከባቢ ንጽህና አጠባበቅ ፕሮጀክት #ሸርኮ፣ #ሀረግና #አራቲቾ ቀበሌያት የሚገኙ ከ6 ሺህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎች የንፁህ መጠጥ ውሀ ተጠቃሚ የሚያደርግ ይሆናል።

በመስክ ምልከታው ወቅት እንደተገለፀው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ የእስካሁን አፈፃፀም አበረታች መሆኑንና ቀሪ ስራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ማኅበረሰቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል።

በኢትዮጲያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እምድብር ሀገረ-ስብከት ከካሪታስ አውስትራሊያ የጳጳሳት ጉባዔ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እየተገነባ ያለው ይህ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በዚህኛው ምዕራፍ አንድ የምንጭ ግንባታ ፤ የ100 ሺ ሊትር ዌት ዌል ግንባታ (chamber box) ፤ 90 ፓኔል ያለው የሶላር ግንባታ ፤ 5 ኪ.ሜ የቧንቧ ዝርጋታ ፤ የ2 ቦኖዎች ግንባታ ፣ 100ሺ ሊትር ውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ ግንባታ በመስራት እንዲሁም ለማኅበረሰቡ ተወካይ ለሆኑ አካላቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችንም በመስጠት ለሸርኮ፣ ሀረግ እና አራቲቾ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ለሚገኙ ቁጥራቸው ከ6 ሺ በላይ ለሚሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ይህ ፕሮጀክት አጠቃላይ ሥራውም #ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበለት ሆኖ እስካሁን ባለው የምንጩ ግንባታ፣ የሶላር ተከላ፣ የታንከርና የተወሰኑ ቦኖዎች ግንባታ ስራዎች የተጠናቀቁ ሲሆን፤ ቀሪ ውስን ስራዎቹ በአጭር ጊዜያት ውስጥ ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ በመግለጽ የአካባቢው ማኅበረሰብና የወረዳው መንግስት በፕሮጀክቱ የእስካሁን አፈፃፀም ላይ ያደረጉት ድጋፍና ትብብር ላቅ ያለ በመሆኑ ሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ አድናቆትና ምስጋና አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የእምድብር ሀገረ-ስብከት ለእንደጋኝ ወረዳ ባለውለታ መሆኑን የጠቆሙት የእንደጋኝ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሙሉቀን ገዙ እንደተናገሩት ሀገረ-ስብከቱ የወረዳችን የንፁህ መጠጥ ሽፋን ከነበረበት እጅግ ዝቅተኛ አፈፃፀም እንዲሻሻልና የማህበረሰባችን የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት ችግር እንዲሻሻል በዚክር ከፍተኛ ምንጭ በወረዳው ድንቁላ ከተማን ጨምሮ በርካታ ቀበሌያት ተጠቃሚ ማድረጋቸውን በማስታወስ አሁን ላይ በሸርኮና በተፈካ ቀበሌያት ከፍተኛ ምንጮች ላይ ረጂ አካላትን በማፈላለግና ከፍተኛ ሀብት በመመደብ ለወረዳው ማኅበረሰብ ላደረጉትና አሁንም እያደረጉት ያለውን አስተዋጽኦ በእንደጋኝ ማኅበረሰብ ዘንድ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል ብሏል።

👉ክቡር አቶ ሙራድ አህመድ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሲቪክ ማኅበራት ዳይረክቶሬት ዳይረክተር እንደገለፁት ይህ የሾርኮ ንፁህ ውሃ አቅርቦት ፣ የግልና የአከባቢ ንፅህና አጠባበቅ ፕርጀክት ቤተክርስቲያኗ በጥራትም በጊዜም በሚገርም ሁኔታ እንደሰራች በመግለፅ እንደ ክልላችን የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እምድብር ሀገረ ስብከት ጠቅላይ ጼ/ቤት በተለይም በውሃ ፕሮጀክት እጅግ የሚያስመሰግኑ ሥራዎችን እየሰራች እንደሆነ እኛ በቂ ምስክር ነን በማለት ገልፀዋል።

👉 የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ዳይሬክተር ክቡር አቶ ኪዳነማርያም ወ/ትንሳኤም ለተጠየቁት ጥያቄዎች ማብራሪያ በመስጠትና ለተደረገው ትግግዝ ምስጋና አቅርበዋል።
በእለቱም ባለድርሻ አካላት የንፁህ መጠጥ ውሀ ፕሮጀክቱ የእስካሁን አፈፃፀምና ያለበት ደረጃ ተዘዋውረው በመመልከት በድንቁላ ማዕከል በፕሮጅክቱ አፈፃፀምና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፤ የፕሮጀክቱ የእስካሁን አፈፃፀም አበረታችና ተስፋ ሰጪ መሆኑንም ተመላክቷል።

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የእምድብር ሀገረስብከት ዓመታዊ የካህናት ሱባኤ ከነሃሴ 25-30 በመቂ ሀገረስብከት ጥቁር ወሃ ቅዱስ ዮሐንስ የሱባኤ ማዕከል ተደረገ። ሱባኤው በፀሎት እና...
04/09/2026

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የእምድብር ሀገረስብከት ዓመታዊ የካህናት ሱባኤ ከነሃሴ 25-30 በመቂ ሀገረስብከት ጥቁር ወሃ ቅዱስ ዮሐንስ የሱባኤ ማዕከል ተደረገ። ሱባኤው በፀሎት እና በመስዋዕተ ቅዳሴ ያስጀመሩት ብፁዕ አብነ ሉቃስ ፍቅሬ የእምድብር ሀገረስብከት ጳጳስ ሲሆኑ ሱባኤው መንፈሳዊ ትምህርት በማስተማር የመሩት ክቡር አባ ኤርማኖ ናቸዉ።

ማዕረገ ክህነት ተሰጠ (24-12-2018 ዓም እምድብር)አዲስ ካህን አለን!!!በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በእምድብር ሀገረ ስብከት በቅዱስ እንጦንዮስ ካቴድራል ለክቡር ዲያቆን ሀብተ...
30/08/2026

ማዕረገ ክህነት ተሰጠ (24-12-2018 ዓም እምድብር)

አዲስ ካህን አለን!!!

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በእምድብር ሀገረ ስብከት በቅዱስ እንጦንዮስ ካቴድራል ለክቡር ዲያቆን ሀብተማርያም (አሸናፊ) እና ለክቡር ዲያቆን ኢዮብ (ከበደ) በብፁዕ አቡነ ሉቃስ የሀገረ ስብከታችን ጳጳስ እጅ ማዕረገ ክህነት ተሰጠ።

በቤተ ክርስቲያኒቷ ሥርዓት እና አስተምህሮ መሠረት ላለፋት በርካታ ዓመታት በፍልስፍና በነገር መለኮት፣ በሥርዓተ አምልኮ፣ እንዲሁ በትምህርተ ክርስቶስ ሲዘጋጁ ቆይተው፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ እነሆ በዛሬው ዕለት ማዕረገ ክህነታቸውን ተቀብለዋል፦ ይህም ለቤተክርስትያን ትልቅ ደስታ ነው።

መዓረገ ክህነቱን የሰጡት ብፁዕ አባታችን መሥዋዕተ ቅዳሴውን የመሩ ሲሆን ባሰሙት ቃለ ምዕዳን፤ ክህነት አገልገሎት ነው፤ በዮሐንስ ወንጌል እንደምናገኘው፤ እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሔዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ ፍሬአቹም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኋችሁ፤ ስለዚህ እናንተ ክቡራን ካህናት ሆይ የመረጣችሁ እግዚአብሔር ነው፤ የመረጣችሁን, ፍሬ እንድታፈሩ አደራ የተቀበላችሁት ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህንንም አደራ የምጠብቁት፤ ቤተክርስትያንን በመምራት፤ሕፃናትን በማስተማር፤ ወጣቶችን በመምከር፤ ክህነታዊ ኑሮን በመኖር ነው።

ዲያቆናቱን ለቅብዓተ ክህነት ያቀረቡአቸው የቅዱስ ኤፍሬም ዓቢይ ዘርዓ ክህነት ኃላፊ፥ እንዲሁም ክቡር አባ ግርማይ, ክቡር አባ ዳንኤል እና ክቡር አባ አለማየሁ፤ ሲሆኑ ብፁዕ አቡነ ሉቃስም እነዚህ አባቶች በካህናት ሕንጸት ላይ እየሠሩ ስለሚገኙ፤ ለዚህ ትልቅ አገልግሎታቸው በእምድብር ሀገረ ስብከት ስም አመስግነዋቸዋል።

ክቡር አባ ሀብተማርያም (አባ አሸናፊ) ከጉብርየ ረዳኢተ ክርስቲያን ማርያም ቁምስና እንዲሁም ክቡር አባ ኢዮብ (አባ ከበደ) ከድብረትዬ ቅዱስ ዮሴፍ ቁምስና የተገኙ አባቶች ናቸው። አዲሶቹ ካህናት ባቀረቡት የምስጋና ንግግር ከሁሉ በማስቀደም ለዚህ ቀን ያደረሰን, ያገዘን, የረዳን, እግዚአብሔር አምላካችን የተመሰገነ ይሁን። ብፁዕ አቡነ ሉቃስን ለአባታዊ ምክራቸው፤ ለቡራኬአቸው፤ አመስግነው፤ ከልጅነት ጀምሮ ኮትኩተው, ቀርጸው, አስተምረው፤ እኛን ለቤተክርስትያን ያቀረቡን ቤተሰቦቻቸውን፤ በተለያዩ የሕይወት ጉዞአችን ያገዛችሁን ወዳጆቻችንን ጓደኞቻንን እናመሰግናለን፤ እግዚአብሔር ይስጥልን። በክህነታች ዕለት እዚህ ስለተገኛችሁ ሁላችሁንም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እናመሰግናለን፤ ዛሬ ይህንን ጉዞ ጀመርነው፤ ስለዚህ በጸሎታችሁ እንድታግዙን አደራችሁን።

በተመሳሳይም ብፁዕ አቡነ ሉቃስ እነዚህን ክቡራን ካህናትን ለቤተክርስትያ የሰጡትን ወላጆችን አመስግነው፤ በተለይም የክቡር አባ ሀብተማርያም(አባ አሸናፊ) ወላጆች፦ ክቡር አቶ ተክሉ እና ወይዘሮ አልማዝ የጋብቻቸውን 50ኛ ዓመተ በዓል እያከበሩ ይገኛሉ። በተመሳሳይም የላዛሪስ ገዳም አባት የሆኑት ክቡር አባ አማኑኤልም ከዚሁ ቤተሰብ የተገኙ አባት ናቸው።

ክህነት ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚሰጥ ጥሪ በመሆኑ እና ካህን የሚገኘውም ከምዕመናን ዘንድ በመሆኑ ለዚህ ትልቅ የአገልግሎት ጥሪ አድምጠው ለቤተ ክርስቲያን እንዲያሳውቁም የእምድብር ሀገረስብከት የሐዋርያዊ ጽ/ቤት አስተባባሪ የሆኑት ክቡር አባ ተስፋአምላክ ፍቅሬ አሳስበዋል።

በዕለቱም የእምድብር ቅዱስ እንጦንዮስ ካቴድራል፤ የድብረትዬ ቅዱስ ዮሴፍ እና የጉብርየ ረዳኢተ ክርስትያን ማርያም ወጣት መዝምራን በኅብረት በመሆን በዝማሬ አገልግለዋል።

የጋልዬሮግዳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ታድሶ እንደገና አገልግሎት መስጠት ጀመረ።18/12/2018በብፁዕ አቡነ ሉቃስ በተመራ መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደዚሁም ብፁዕ አቡነ ተስፋሥላሴ፣ የአዲስ አበ...
28/08/2026

የጋልዬሮግዳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ታድሶ እንደገና አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
18/12/2018

በብፁዕ አቡነ ሉቃስ በተመራ መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደዚሁም ብፁዕ አቡነ ተስፋሥላሴ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳሳት፣ እና ብፁዕ አቡነ ሙሴ የቀድሞ የእምድብር ሀገረ ስብከት ጳጳስ፣ ክቡራን የሀገረ ስብከቱ ካህናት፣ ገዳማውያን፣ ገዳማውያት እንደዚሁም የጋልዬሮግዳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ምእመናን እና ከአካባቢ ቁምስናዎች የመጡ ምእመናን በተገኙበት ቤተክርስቲያኑ እድሳቱ አልቆ እንደገና ተባርኮ ሥራ ጀምሯል።

በዚሁ ዕለት የቁምስናው ሁለገብ አዳራሽ እና የካህናት መኖሪያ ግምባታው ተጠናቆ ተባርኮ አገልግሎት ጀምሯል። በዕለቱም ብፁዕ አቡነ ሉቃስ በሰጡት ቃለ ምዕዳን፣ በዚህ አካባቢ ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት የተሠራው ሐዋርያዊ ሥራ ብዙ ውጤት አፍርቶ ብዙ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ልጅነት ጸጋ በጥምቀት ተቀብለው መልካም የሆነ ሐዋርያዊ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል።

በዚህ አካባቢ ከህንድ ሀገር የመጡ የቤታኔ አባቶች እና የቅድስት ሀና ሲስተሮች በትምህርት፣ በጤና፣ በስብከተ ወንጌል ሥራ፣ በማኅበራዊ አገልግሎት የሕዝቡን ሕይወት ለመቀየር ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።

በተመሳሳይም በዕለቱ ሀያ የሚሆኑ የቁምስናው ታዳጊ ሕፃናት የመጀመርያ ቁርባም ከብፁዕ አቡነ ሉቃስ እጅ ተቀብለዋል።

በቦታው ተገኝተው ቡራኬአቸውን የሰጡት ብፁዓን ጳጳሳት፦ ብፁዕ አቡነ ተስፋሥላሴ፣ እና ብፁዕ አቡነ ሙሴ ለሕዝቡ ለእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈው፤ ሕዝቡም በእምነቱ እንዲጸና እና በተስፋ እንዲጠብቁ መክረው አባታዊ ምክራቸውና ቡራኬአቸውን ሰጥተዋል።

በስተመጨረሻም ብፁዓን ጳጳሳቱ በጋልዬሮግዳ የሚገኘውን የቅድስት ሀና እኅቶችን ገዳም እና በጎሩ የሚገኘውን የቤታኒ አባቶች ገዳም ጎብኝተው, ቡራኬ ሰጥተው በመቀጠልም በወሊሶ የቅዱስ ገብርኤል ካቶሊክ ቤተክርስትያን ቁምስና ጎብኝተው ጸሎት አድርሰው, የዕለቱ መርሐግብር ተጠናቀቀ።

የብፁዕ አቡነ ሙሴ የአምሳኛ የክህነት ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ ተከበረ (17/12/2018 ዓ.ም.)"ካህናቲከ ይለብሱ ጽድቀወጻድቃኒከ ትፍሥሕተ ይትፌሥሑበእንተ ዳዊት ገብርከ"            ...
23/08/2026

የብፁዕ አቡነ ሙሴ የአምሳኛ የክህነት ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ ተከበረ (17/12/2018 ዓ.ም.)

"ካህናቲከ ይለብሱ ጽድቀ
ወጻድቃኒከ ትፍሥሕተ ይትፌሥሑ
በእንተ ዳዊት ገብርከ"

ብፁዕ አቡነ ተስፋሥላሴ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የእምድብር ሀገረስብከት ጳጳስ በተገኙበት የብፁዕ አቡነ ሙሴ የእምድብር ሀገረስብከት የቀድሞ ጳጳስ የክህነት የ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ የምስጋና በዓል በከበረ መንፈሳዊ ሥርዓት ተከበረ

በዕለቱ በብፁዕ አቡነ ሙሴ ገ/ጊዮርጊስ በተመራ የምስጋና መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ወቅት ተተኪያቸው ለሆኑት ለብፁዕ አቡነ ሉቃስ በሀገረስብከቱ ላደረጉት እና እያደረጉት ላሉት አስተዋጽዖ ልባዊ ምስጋና አቅርበው በዚህ የምስጋና መሥዋዕተ ቅዳሴ ላይ ምእመናን በጸሎት እንዲያስቧቸውና ጸሎታቸው እንዳይለያቸው አደራ ሰጥተዋል።

ብፁዕ አቡነ ሙሴ እ.ኢ.አ. ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ ለሃያ ሁለት ዓመታት ያክል የእምድብር ሀገረስብከትን ከተረከቡ ጊዜ ጀምሮ ለምእመናን መንፈሳዊ እድገት፣ በቤተ ክርስቲያን ለሚደረጉ ምሥራቃዊ ሥርዓትን በማስተማር፣ በሀገረስብከት ውስጥ ያሉት ቁምስናዎች እና ቤተ ጸሎቶች ይበዙ ዘንድ፥ እንዲሁም ከሐዋርያዊ ሥራዎች በተጨማሪ ብዙ የፍቅር እና ማኅበራዊ ሥራዎች ለአካባቢው ማኅበረሰብ በማበርከት ትልቅ አሻራቸውን ያኖሩ ሲሆን ከ2017 ዓ.ም. ጀምሮ ሀገረስብከቱን ለብፁዕ አቡነ ሉቃስ በማስረከብ ጡረታ ወጥተዋል።

ር.ሊ.ጳ. ሊዮ 14ኛ ለብፁዕ አቡነ ሙሴ የላኩትን የምስጋና እና ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ የእንኳን አደረሰዎ መልእክት የእምድብር ሀገረስብከት ጽ/ቤት ጠቅላይ ጸሐፊ የሆኑት ክቡር አባ ሀብተሥላሴ አንቷን አንብበዋል።

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የእምድብር ሀገረስብከት ጳጳስ ለብፁዕ አቡነ ሙሴ ላበረከቱት አስተዋጽዖ እና ለመልካም አርዓያነታቸው ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል፤ ለብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ተስፋሥላሴም እንኳን ደህና መጡ በማለት አገልግሎታቸውን እንዲባርክ፥ እንዲሁም በዛሬው ዕለት ይህን የክህነት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ የሚያከብሩ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ እና ብፁዕ አቡነ ጸጋዬ ቀነኒም ባሉበት ሁሉ ረጅም እድሜ እና ጤና እንዲሆንላቸውም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ብፁዕ አቡነ ተስፋሥላሴም ለብፁዕ አቡነ ሙሴ የእንኳን አደረሰዎ እና የምስጋና ቃል አስተላልፈዋል።

ብፁዕ አቡነ ሙሴ በሀገረስብከታችን ውስጥ ለሠሩት ሥራዎች፣ ላደረጉት ገድል ሁሉ እግዚአብሔር በሰላም እና በጤንነት እንዲያቆይዎት ያገለገሉት ሀገረስብከት በጸሎት ከጎንዎት ነው፤ መልካም የአምሳኛ የክህነት ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል በሰላም አደረስዎት ብፁዕ ጳጳሳችን አቡነ ሙሴ

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በእምድብር ቅዱስ እንጦንዮስ ካቴድራል የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የፍልሰቷ በዓል በከበረ መንፈሳዊ ስነ ሥርዓት ተክብሮ ዋለ።          ነሐሴ...
22/08/2026

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በእምድብር ቅዱስ እንጦንዮስ ካቴድራል የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የፍልሰቷ በዓል በከበረ መንፈሳዊ ስነ ሥርዓት ተክብሮ ዋለ።

ነሐሴ 16,2018ዓ.መ

ትናንት በዋዜማው የተጀመረው የበዓሉ ስነ ሥርዓት ዛሬም ብፁዓን ጳጳሳት በተገኙበት በሌሊት የማኅሌት ጸሎት ቀጥሎአል፤ መሥዋዕተ ቅዳሴውን የመሩት ብፅዕ አቡነ ሉቃስ ለአንድ ዓመት ለእኛ ርቀው በውጭ ሀገር የቆዩትን ብፁዕ አባታችን አቡነ ሙሴን ከምዕመናን ጋር እንኳን ደኅና መጡ ብለው የተቀቡሏቸው ሲሆን፤ በነገው ዕለትም የክህነት 50ኛ ዓመት የአገልግሎት በዓላቸውን በታላቅ ምስጋና ስናከብር እንዲሁም በሐምሌ ወር የክህነት 50ኛ ዓመት የአገልግሎት በዓላቸውን ያከበሩት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ እና ብፁዕ አቡነ ጸጋዬ በጸሎት ይታሰባሉ፤

በነገው ዕለትም ብፁዕ አቡነ ተስፋሥላሴ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ተተኪ ሊቀ ጳጳስ፤ ሁሉም የሀገረ ስብከቱ ካህናት፤ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ምስጋና የሚከበር ይሆናል፤ በዛሬው ዕለትም ለብፁዕ አቡነ ተስፋሥላሴ በቅዱስ እንጦንዮስ ቤተክርስትያን አቀባበል ይደረጋል፤ በዚያም የማታ ጸሎት የሚያደርሱ ይሆናል።

ብፅዕ አቡነ ሉቃስ ባሰሙት ቃለ ምዕዳን፤ ለ15 ቀናት በሌሊት ተመላልሰን ያደረስነው ጸሎት በከንቱ የሚቀር አይደለም፤ ይልቁንም ለምድራችን በረከት የሚወርድበት፤ እኛም ጸጋን የምናገኝበት፤ የምንባረብክበት፤ የምንፈወስበት ነው፤ የዛሬ በዓል ትልቅ ምሥጢር ያለው በዓል ነው፣ የካቶሊክ ቤተክርስትያንም ስለ እመቤታችን ያላትን አስተምህሮ(ዶግማ) አንዱ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ፍልሰቷ ነው። ለዚህም ትልቅ

ማርያም ዛሬ የምታስተምረን፤ ቅድስና የሚገኘው እሺ ከማለት ነው፤ ከትሕትና ነው፤ የራስ ፍላጎት ከመፈጸም በላይ የእግዚአብሔርን ቃል ማዳመጥ ነው፤ እርሱም ማስቀደም ነው። እንዲሁ ቢመችም ባይመችም ከሰዎች ጎን መሆነን ነው፤ ችግራቸውን መካፈል ነው።

እንዲሁ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰት ለክርስትያኖች ትልቅ ተስፋ ነው። ብለው አባታዊ ምክራቸውና ቡራኬአቸውን ሰጥተዋል።

የእመቤታችን አማላጅነቷ አይለየን አሜን

Address

Wolkite

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Catholic Eparchy of Emdeber posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share