Apostolic Wedding

Apostolic Wedding This page is the member of Apostolic Church of Ethiopia and Apostolic Ethiopia. Its purpose is to promote and appreciate Holy Christian Weddings

በእግዚአብሔር ዓላማ ጋብቻ የሚመሰረተው በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት ጥምረት ነው (ዘፍ.2፡22)፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ፡- “እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፡፡” (ዘፍ.1፡27) “ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው፣ ….ሁለቱም አንድ ስጋ ይሆናሉ፣…አንድ ስጋ ናቸው እንጂ ወደፊት ሁለት አይደሉም፡፡ እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው፡፡” (ማቴ.19፡4-7) ይላል፡፡
ስለዚህ የእግዚአብሔር ዓላማ አንድ ወንድና አንዲት ሴት በጋብቻ ተጣምረው ሳይለያዩ እንዲኖሩ ነው፡፡
በእግዚአብሔር ዓላማ ባል ከእግዚአብሔር የተቀበላትን ሚስት እንደገዛ ራሱ አጥንትና ስጋ

እንዲቆጥራት ነው (ዘፍ.2፡23)፡፡ በምድር ላይ የመጀመሪያው ባል አዳም ነበር፡፡ የመጀመሪያዋም ሚስት ሔዋን ነበረች፡፡ “እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሰራት፣ ወደ አዳምም አመጣት፡፡ አዳምም አለ፡- ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፣ ስጋም ከስጋዬ ናት፣ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል፡፡” የአዳም አባባል የእግዚአብሔርን ዓላማ መሰረት ያደረገ ነበር፡፡ ባሎች ሁሉ ይህን የእግዚአብሔር ዓላማ አንዲያሟሉ፡- “እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደ ገዛ ስጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል፡፡ የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፡፡ ማንም የገዛ ስጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና”(አፌ.5፡28-29) ተብለው በቃሉ ታዝዘዋል፡፡
የእግዚአብሔር ዓላማ ሰው ሚስት ሲያገባ አባቱንና እናቱን እንዲተውና ከሚስቱ ጋር እንዲጣበቅ ነው (ዘፍ.2፡24)፡፡ ይህም አባትና እናት ለልጆቻቸው ጋብቻ እንቅፋት ሆነው መለያየትን እንዳይፈጥሩ እግዚአብሔር ያቀደው ዓላማ ነው፡፡

26/02/2026
26/02/2026
26/12/2025

Address

Woliso

Opening Hours

Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

251114663000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Apostolic Wedding posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Apostolic Wedding:

Share