ሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ሚዲያ - North Wollo Diocese Media

  • Home
  • Ethiopia
  • Woldia
  • ሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ሚዲያ - North Wollo Diocese Media

ሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ሚዲያ - North Wollo Diocese Media በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የሚከናወኑ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኗ የልማት ሥራዎችን ለእናንተ እናደርሳለን።

አድባራት ዘመኑን የዋጁ አገልጋዮችንና ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው ያወቁ ምእመናንን ለማፍራት በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ አሳሰቡ፡፡ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ...
06/08/2026

አድባራት ዘመኑን የዋጁ አገልጋዮችንና ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው ያወቁ ምእመናንን ለማፍራት በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ አሳሰቡ፡፡

ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ)

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የወልድያ ከተማ ቤተ ክህነት አስተዳደር 45ኛ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤውን ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም አከናውኗል።

ጉባኤው በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ኬሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መሪነት የተካሄደ ሲሆን የተጠናቀቀው ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ቀርቦ ተሳታፊዎች ተወያይተውበታል።

ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት የሥራ መመሪያና ቃለምእዳን ባሳለፍነው ዓመት በርካታ ችግሮች ቢገጥሙንም አድባራት ችግሮችን ተቋቁመው ያከናወኗቸው ተግባራትና የተመዘገበው ስኬት የሚያስመሰግንና የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በ2019 ዓ.ም በትኩረት ሊከናወኑ ይገባል ባሏቸው የቤተክርስቲያን አገልግሎቶች ዙሪያ አባታዊ መመሪያ ያስተላለፉ ሲሆን የአብነት ትምህርት ቤቶችን በመከታተል፣ በመደገፍና በማሰልጠን ዘመኑን የዋጁ አገልጋዮችን ማፍራት፤ የሰንበት ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋትና አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት በአግባቡ በመተግበር አውቀው የሚያመልኩ ምእመናንን መፍጠር እንደሚገባ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

ቤተክርስቲያኗ የተገበረችውን የአሥር ዓመት መሪ እቅድ በአድባራት ተግባራዊ ለማድረግ መደበኛ አገልጋዮችን ሊቀጥሩ እንደሚገባ ያሳሰቡት ብፁዕነታቸው ከምእመናን ተሰብስቦ በአድባራት የሚቀረው ገቢ በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉን መቆጣጠርና መከታተል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የከተማ ቤተክህነት አስተዳደሩ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጋር የምክክር ጉባኤ በማዘጋጀት በቤተክርስቲያኗ አጠቃላይ አገልግሎቶች ላይ ውይይት ለማድረግ በእቅድ እንዲይዙ አሳስበዋል፡፡

በጉባኤው የሀገረ ስብከቱ የልዩ ልዩ ክፍል ኀላፊዎች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎችና የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት የተሳተፉ ሲሆን በተጠናቀቀው የአገልግሎት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ አድባራት የተዘጋጀላቸውን የዕውቅና ሽልማት በብፁዕነታቸው ቡራኬ ተቀብለዋል።

───
~ “ ” ~
~ ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ~
───

የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ፦
ቴሌግራም~ https://t.me/NWDnews
ዩቲዩብ~ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia
ድረገጽ~ https://eotc-nw.org
ፌስቡክ~ https://www.facebook.com/EOTCNWD
Tiktok~ https://www.tiktok.com/.north?_t=ZM-8ukkHRXMOYg&_r=1

የራያ ቆቦ ወረዳ ቤተክህነት በተጠናቀቀው የአገልግሎት ዓመት ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ማዲያ)...
05/08/2026

የራያ ቆቦ ወረዳ ቤተክህነት በተጠናቀቀው የአገልግሎት ዓመት ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ማዲያ)

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የራያ ቆቦ ወረዳ ቤተክህነት 45ኛ ዓመታዊ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤውን ዛሬ አካሂዷል።

ጉባኤው በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ኬሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባታዊ መሪነት በቆቦ ከተማ ተካሂዷል።

የወረዳ ቤተክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት ተስፋሚካኤል ፈለቀ የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም ሪፖርትና የቀጣይ ዓመት እቅድ አቅርበዋል።

ወረዳ ቤተክህነቱ በተጠናቀቀው የአገልግሎት ዓመት ለገዳማት፣ ለአብነት ትምህርት ቤቶችና ለግለሰቦች 5 ሚሊዮን ሁለት መቶ ሽህ ብር የሚገመት ሰብዓዊ ድጋፍ ማደረጉን በሪፖርቱ ገልጿል።

ከአፈጻጸም ሪፖርቱ በተጨማሪ በቀጣይ ዓመት ወረዳ ቤተክህነቱ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን የሚያከናወናቸው ተግባራት በመሪ እቅዱ 16 ግቦች መሠረት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሊቀ ጳጳስ ወረዳ ቤተክህነቱ፣ ገዳማትና አድባራት ትኩረት ሰጥተው በሚያከናውኗቸው ተግባራት ዙሪያ አባታዊ የሥራ መመሪያ አስተላልፈዋል።

የሰንበት ትምህርት ቤቶችን ማቋቋምና ማጠናከር፣ የሰበካ ጉባኤያት ምርጫና የአገልግሎት ዘመን፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችን ማጠናከርና የምስጢራተ ቤተክርስቲያን አፈጻጸም፣ የገንዘብ አስተዳደር፣ የበዓላት አከባበርና ሌሎች ትኩረት የሚደረግባቸው ተግባራትን በዝርዝር አስገንዝበዋል።

አድባራት የትርጓሜ መጻሕፍት ሊቃውንትንና የነገረ መለኮት ምሩቃንን በመቅጠር ለምእመናን ትምህርተ ሃይማኖትን በእድሜ፣ በጾታና በእውቀት ደረጃቸው እንዲያስተምሩ አሳስበዋል።

ለአብነት ትምህርት ቤቶች ግብዓት በማሟላትና ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን በመስጠት ቤተክርስቲያኗን ሊመሩ የሚችሉ ኹለገብ ሊቃውንትን ማፍራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በአጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤው የሀገረ ስብከት ልዑካን፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎችና የሰበካ ጉባኤያት ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ አድባራት ወረዳ ቤተክህነቱ ያዘጋጀላቸውን ሽልማት ከብፁዕነታቸው ተረክበዋል።

───
~ “ ” ~
~ ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ~
───

የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ፦
ቴሌግራም~ https://t.me/NWDnews
ዩቲዩብ~ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia
ድረገጽ~ https://eotc-nw.org
ፌስቡክ~ https://www.facebook.com/EOTCNWD
Tiktok~ https://www.tiktok.com/.north?_t=ZM-8ukkHRXMOYg&_r=1

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት መቄት ወረዳ ቤተ ክህነት አስፋ ገነተጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፈለገ አእምሮ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ አስተባባሪነትና በመን...
29/07/2026

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት መቄት ወረዳ ቤተ ክህነት አስፋ ገነተጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፈለገ አእምሮ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት
በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ አስተባባሪነትና በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ከሃያ ዓመታት በፊት የተመሠረተና በደጋግ ኢትዮጵያውያን ቀና ትብብር እየተገነባ የሚገኝ የልኅቀት ተቋም ነው፡፡

በ6 ጉባኤ ቤቶች ከ85 በላይ ደቀመዛሙርት ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖላቸው ለምንም ሳይጨነቁ ትምህርት ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ ተደርጎ በመማር ላይ ናቸው፡፡

ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው B+G+7 ሕንጻ ሲጠናቀቅ የመቀበል አቅሙ ከ500 በላይ ያደርሰዋል፡፡
───
~ “ ” ~
~ ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ~
───
የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ፦
ቴሌግራም~ https://t.me/NWDnews
ዩቲዩብ~ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia
ድረገጽ~ https://eotc-nw.org
ፌስቡክ~ https://www.facebook.com/EOTCNWD
Tiktok~ https://www.tiktok.com/.north?_t=ZM-8ukkHRXMOYg&_r=1

"በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎትን በማስፋፋት፣ ልማትና መልካም አስተዳደርን የተሟላ በማድረግ ችግሩም መፍትሒውም ያለው በታችኛው መዋቅር ነው" ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሊቀ ጳጳስሐምሌ 20...
27/07/2026

"በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎትን በማስፋፋት፣ ልማትና መልካም አስተዳደርን የተሟላ በማድረግ ችግሩም መፍትሒውም ያለው በታችኛው መዋቅር ነው" ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሊቀ ጳጳስ

ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ)

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ኬሚሴ ሀገረ ስብከት 13ኛ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤውን ዛሬ አካሂዷል።

ጉባኤው በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ አባታዊ መሪነት የተካሄደ ሲሆን በተጠናቀቀው የአገልግሎት ዓመት በሀገረ ስብከቱ እስከ አጥቢያ አብያተክርስቲያን ድረስ የተከናወኑ ተግባራትን ሪፖርት የእቅድና ልማት ዋና ክፍል ኃላፊው አቅርበዋል።

ለቤተ ክርስቲያን ኹለንተናዊ አገልግሎት፣ የሰንበት ት/ቤቶች
ሥርዓተ ትምህርት፣ የጊዜ አጠቃቀም፣ የሰው ኀይል አደረጃጀት፣ የንብረት አያያዝ፣ የገንዘብ አጠቃቀምና መረጃዎችን በጥራትና በኀላፊነት ለመያዝ የሚረዳ በዲያቆን አቤል አሰፋ የበለጸገ ሶፎትዌር/software/ትውውቅ መደረጉን የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የጉባኤው ተሳታፊዎች ተጠናክረው መቀጠል ያለባቸውና በቀጣይ ሊታረሙ ይገባል ያሏቸውን አስተያየቶችና ጥያቄዎች አንስተው በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ገነት ደጀን ተስፋዬ ማብራሪያ ተሰጥቶባዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎና የኬማሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት ቃለምእዳን ቤተ ክርስቲያን እየገጠማት ካለው ችግር ለማላቀቅ፣ ልማትን ለማስፋፋትና የመልካም አስተዳደርን የተሟላ ለማድረግ ችግሩም መፍትሒውም ያለው ከታች መሆኑን ጠቅሰው የሰበካ ጉባኤ አባላት ምርጫ እውቀት፣ ቅንነትና ታዛዥነት ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ብለዋል።

የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን ውጤታማ ለማድረግ ከተለመደው አካሄድ በመውጣት በእድሜ ደረጃና በጾታ ለይቶ ለማሰልጠን የሚረዳ ሰነድ በማዘጋጀት በትርጓሜ መጻሕፍትና በነገረ መለኮት መምህራን ተገቢውን ትምህርት መስጠት እንደሚገባ በአጽንኦት አሳስበዋል።

የቤተክርስቲያንን ዶግማ፣ ሥርዓት፣ ትውፊትና ታሪክ በወጉ የተረዱ ሊቃውንትን ማፍራት እንድችሉ የአብነት ትምህርት ቤቶቻችን ላይ በትኩረት መሥራትም ይጠበቃል ብለዋል ብፁዕነታቸው።

በመጨረሻም መሪ እቅዱ በትክክል እንዲተገበር በዘርፉ እውቀትና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ሊኖሩን ይገባል ያሉት ብፁዕነታቸው ሁሉም ሕጻናት በሰንበት ትምህርት ቤቶች ገብተው እንድማሩ አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል።

───
~ “ ” ~
~ ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ~
───

የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ፦
ቴሌግራም~ https://t.me/NWDnews
ዩቲዩብ~ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia
ድረገጽ~ https://eotc-nw.org
ፌስቡክ~ https://www.facebook.com/EOTCNWD
Tiktok~ https://www.tiktok.com/.north?_t=ZM-8ukkHRXMOYg&_r=1

የኬሚሴ ሀገረ ስብከት 13ኛ ዓመታዊ ጠቅላላ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ)የኬሚሴ ሀገረ ስብከት 13ኛውን አጠቃላይ የሰበ...
27/07/2026

የኬሚሴ ሀገረ ስብከት 13ኛ ዓመታዊ ጠቅላላ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ)

የኬሚሴ ሀገረ ስብከት 13ኛውን አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤውን ዛሬ በኬሚሴ ከተማ እያካሄደ ነው።

በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ኬሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባታዊ መሪነት ጉባኤው በጸሎተ ወንጌል ተከፍቷል።

በአጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ሲሆን ጠንካራ አፈጻጸሞች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፤ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ደግሞ በቀጣይ በጀት ዓመት እቅድ ተካትተው እንዲከናወኑ ተሳታፊዎች ሐሳብ ሰጥተዋል።

የቀጣይ ዓመት ልዩ ትኩረት የሚሹ ተብለው ከተነሡት ሐሳቦች መካከል ከመንፈሳዊ አገልግሎቱ ባሻገር የራስ አገዝ ልማትን ማስፋፋት፣ የአብነትና የሰንበት ት/ቤቶችን ማጠናከር፣ የአብያተክርስቲያናት ይዞታ ሕጋዊ ማረጋገጫ እንዲኖራቸው ማድረግና የአዳዲስ አብያተክርስቲያናት መትከያ ቦታን ከሚመለከተው አካል ጋር በመወያየት መረከብ የሚሉት ይገኙበታል።

በጠቅላላ ጉባኤው የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ልዑካን፣ የኬሚሴ ሀገረ ስብከት የክፍል ኃላፊዎች፣ የወረዳ ቤተ ክህነት የክፍል ኃላፊዎች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ነው።
───
~ “ ” ~
~ ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ~
───
የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ፦
ቴሌግራም~ https://t.me/NWDnews
ዩቲዩብ~ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia
ድረገጽ~ https://eotc-nw.org
ፌስቡክ~ https://www.facebook.com/EOTCNWD
Tiktok~ https://www.tiktok.com/.north?_t=ZM-8ukkHRXMOYg&_r=1

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሊቀ ጳጳስ ከኬሚሴ ከተማ አስተዳደር የመንግሥራ ሥራ ኀላፊዎች ጋር በልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረጉ።ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ...
26/07/2026

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሊቀ ጳጳስ ከኬሚሴ ከተማ አስተዳደር የመንግሥራ ሥራ ኀላፊዎች ጋር በልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረጉ።

ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ)

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ኬሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከኬሚሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች ጋር በልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በኬሚሴ ከተማ የሚገኙ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ሕጋዊ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫን በተመለከተ፣ በባቲና በኬሚሴ ከተሞች ተጨማሪ የማምለኪያና የዘላቂ ማረፊያ ቦታ ጥያቄ፣ ሊቃነ ጳጳሳት ምእመናንን በቅርበት ለማገልገል የመንበረ ጵጵስና መስሪያ ቦታ፣ የወረዳ ቤተ ክህነት ቢሮ መስሪያ ቦታና የደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን መግቢያና መውጫ መንገድን በተመለከተ ተወያይተዋል።

የኬሚሴ ከተማ ከንቲባ የተከበሩ አቶ ሸሪፍ ቃሲምና አስተዳደራቸው ለብፁዕነታቸው ያላቸውን ክብር ገለጸው ወደ ኬሚሴ ከተማ በመምጣቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
ከንቲባው አክለውም ከዚህ በፊት ተጠይቀው በሒደት ላይ ያሉና አዲስ የተነሱ ጥያቄዎችን ካቤኔያቸውን በማነጋገር መልስ ለመስጠት ቃል ገብተዋል ሲል የሀገረ ስብከቱ የሕዝብ ግንኙነት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።

───
~ “ ” ~
~ ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ~

───

የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ፦
ቴሌግራም~ https://t.me/NWDnews
ዩቲዩብ~ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia
ድረገጽ~ https://eotc-nw.org
ፌስቡክ~ https://www.facebook.com/EOTCNWD
Tiktok~ https://www.tiktok.com/.north?_t=ZM-8ukkHRXMOYg&_r=1

በዓለ ቅዱስ ገብርኤል በኬሚሴ******************ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ)ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት የገናናው መልአክ ቅዱስ ገ...
26/07/2026

በዓለ ቅዱስ ገብርኤል በኬሚሴ
******************
ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ)

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት የገናናው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በኬሚሴ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤልና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተከብሯል።

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ በእምነታቸው የጸኑትን ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን በመከራቸው መካከል እየተራዳ የእሳቱን ነበልባል እንደክረምት ውኃ ያቀዘቀዘበት፤ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን የታመኑትንም እስከ ሰማዕትነት ፍጻሜ ድረስ የሚያጸና መሆኑን የምንዘክርበት ዓመታዊ በዓሉ በድምቀት ተከብሯል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ኬሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ትናንት በዋዜማው ኬሚሴ ከተማ ሲገቡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎቸ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች መዘምራንና ምእመናን ደማቅ አቀባበል አድርገውላዋል።

ብፁዕነታቸው ትናንት ከዋዜማው ጀምሮ ትምህርት፣ አባታዊ ቡራኬና ቃለምእዳን በማስተላለፍ፣ በሊቃውንቱ ወረብና በሰንበት ትምህርት ቤቶች አባላት ዝማሬ በዓሉ በድምቀት መከበሩን የኬሚሴ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።

───
~ “ ” ~
~ ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ~
───

የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ፦
ቴሌግራም~ https://t.me/NWDnews
ዩቲዩብ~ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia
ድረገጽ~ https://eotc-nw.org
ፌስቡክ~ https://www.facebook.com/EOTCNWD
Tiktok~ https://www.tiktok.com/.north?_t=ZM-8ukkHRXMOYg&_r=1

ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ በእምነታቸው የጸኑትን ቅዱስ ቂርቆስንና ቅድስት ኢየሉጣን በመከራቸው መካከል እየተራዳ የእሳቱን ...
26/07/2026

ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ በእምነታቸው የጸኑትን ቅዱስ ቂርቆስንና ቅድስት ኢየሉጣን በመከራቸው መካከል እየተራዳ የእሳቱን ነበልባል እንደክረምት ውኃ ላቀዘቀዘበት፤ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን የታመኑትንም እስከ ሰማዕትነት ፍጻሜ ድረስ የሚያጸና መሆኑን ለምንዘክርበት ታላቅ በዓል እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

___
~ “ ” ~
~ ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ~
____
የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ፦
ቴሌግራም~ https://t.me/NWDnews
ዩቲዩብ~ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia
ድረገጽ~ https://eotc-nw.org
ፌስቡክ~ https://www.facebook.com/EOTCNWD
Tiktok~ https://www.tiktok.com/.north?_t=ZM-8ukkHRXMOYg&_r=1

መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮችን በማስመል...
25/07/2026

መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮችን በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።

ሓምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም.

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት እንደሚከተለው ነው፦

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

"ገባሬ ሣህል እግዚአብሔር፥ ወይፈትህ ለኩሉ ግፉዓን፦
እግዚአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።"
(መዝሙር ፻፪፥፮)

ከሁሉ በማስቀደም በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም የምትኖሩ ኦርቶዶክሳውያን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንን ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት በከፍተኛ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ለሚከበረው፤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ በእምነታቸው የጸኑትን ቅዱስ ቂርቆስንና ቅድስት ኢየሉጣን በመከራቸው መካከል እየተራዳ የእሳቱን ነበልባል እንደክረምት ውኃ ላቀዘቀዘበት፤ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን የታመኑትንም እስከ ሰማዕትነት ፍጻሜ ድረስ የሚያጸና መሆኑን ለምንዘክርበት ታላቅ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ የወንጌልን ብርሃን በማብራት፣ የሰላምን መንገድ በማስተማር፣ ፍትሕን በማጽናት፣ የተጨነቁትንም በማጽናናት፣ ሕዝብንና ሀገርን እየደገፈች የኖረች ናት።

በዚህ ቅዱስ ተልእኮ ውስጥም መናንያን መነኮሳት እና መነኮሳይያት ዓለምንና ከዓለም የሚገኘውን ጊዜያዊ ክብር፣ ጥቅም፣ ምቾትና የመሳሰሉትን በፈቃዳቸው ትተው፤ በየገዳማቱ በበአታቸው በጾም፣ በጸሎት ተወስነው፤ ሕይወታቸውን በትሕትና ለእግዚአብሔር በመስጠት፤ ስለ ራሳቸው ብቻ ሳይሆን ስለ ሀገር፣ ስለ ሕዝብ፣ ስለ ሰላምና ስለ ዓለም ደኅንነት በመዓልትና በሌሊት የሚጸልዩ የምድራችን በረከቶች ናቸው።

መስቀልን በተሸከሙ፣ ጸሎትን መከታ ባደረጉ፣ ለፍጥረት ሁሉ ምሕረትን በሚለምኑ፣ ራሳቸውን ለመከላከልም ምንም ዓይነት ቁሳዊ ዝግጅት በሌላቸው በእነዚህ መናንያን ላይ እጅን ማንሣት በእግዚአብሔር ዘንድ የተከለከለ፣ በታሪክ ፊትም የሚያሳፍር ድርጊት ነው።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!

በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በቦረና ወረዳ በግዮን አባይ ገዳመ አስቄጥስ ቅድስት አርሴማ፣ አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች አንድነት ገዳም ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት በተፈጸመው ጥቃት የመናንያን መነኮሳይያት ሕይወት በግፍ መጥፋቱን፤ በርካቶች መቁሰላቸውን፤ በገዳሙና በንዋየ ቅድሳቱ ውድመት መድረሱን ከሀገረ ስብከቱ መግለጫ በከፍተኛ ሐዘን የሰማን ሲሆን፤ በተመሳሳይም በዚሁ ዕለት በሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት የአምልኮ ሥፍራ በኃይል መፍረሱና በምእመናን ላይ ጥቃት መድረሱ የሚያሳዝንና በፍጹም ተቀባይነት የሌለው የተወገዘ ተግባር ነው።

በመሆኑም የጸሎት፣ የትምህርት፣ የሰላምና የመንፈሳዊ እሴት ማዕከል የሆኑትን ገዳማት መጠበቅ የአንድ ሃይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ ክብርን፣ የሕግ የበላይነትንና የሀገር ሰላምን የማስጠበቅ ሓላፊነት ያላቸው በየደረጃው የሚገኙ ባለሥልጣናትና የሕግ አስከባሪ አካላት ጭምር እንደመሆኑ አሰቃቂ ጥቃት የፈጸሙት ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ፤ ሌሎች ገዳማትና አድባራት ደኅንነታቸው እንዲጠበቅልን፤ ለተጎዱትም ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግልን ዛሬም አበክረን እንጠይቃለን ።

በመጨረሻም ሕዝበ ክርስቲያንና መላው ኢትዮጵያውያን የጥቃት ሰለባ ከሆኑት ወገኖች ጋር በመንፈሳዊም ሆነ በሰብአዊ ድጋፍ አብራችሁ እንድትቆሙ ከአደራ ጭምር እያሳሰብን፤ በጽድቅ የሚፈርደው እግዚአብሔር አምላካችን ለተበደሉት ፍትሕን፣ ለቆሰሉት ፈውስን፣ በግፍ ሕይወታቸውን ለተነጠቁት ዕረፍተ ነፍስን፣ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ፍጹም ሰላምን ይስጥልን እያልን አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

© የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት

Address

Woldia

Telephone

+251946203517

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ሚዲያ - North Wollo Diocese Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ሚዲያ - North Wollo Diocese Media:

Shortcuts

Share