22/05/2021
የማርቆስ ወንጌል 10:46-52
[46]ወደ ኢያሪኮም መጡ። ከደቀ መዛሙርቱና ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጣ የጤሜዎስ ልጅ ዕውሩ በርጤሜዎስ እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር።
[47]የናዝሬቱ ኢየሱስም እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ። የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ማረኝ እያለ ይጮኽ ጀመር።
[48]ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን። የዳዊት ልጅ ሆይ፥ ማረኝ እያለ አብዝቶ ጮኸ።
[49]ኢየሱስም ቆመና። ጥሩት አለ። ዕውሩንም። አይዞህ፥ ተነሣ፥ ይጠራሃል ብለው ጠሩት።
[50]እርሱም እየዘለለ ተነሣና ልብሱን ጥሎ ወደ ኢየሱስ መጣ።
[51]ኢየሱስም መልሶ። ምን ላደርግልህ ትወዳለህ? አለው። ዕውሩም። መምህር ሆይ፥ አይ ዘንድ አለው።
[52]ኢየሱስም። ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል አለው። ወዲያውም አየ በመንገድም ተከተለው።የበርጤሚዎስ ሁለት ችግሮች 1/ኛ አካለ ጎደሎነቱ (ዓይነስውርነበር)ከዚህ የተነሳ በሰው እርዳታ የሚኖር ሰው ነበር ራሱን የማይችል ሸክም ነበር 2ኛ/መጠቀሚያ ነበር ይህ ማለት የሚረዱት ቤተሰቦቹ ይሁኑ ወይም ሌሎች ሰዎች በሱ አካለጎዶሎነት(ችግር) ይጠቀሙ ነበር። ለምኖ ካመጣው ገንዘብ ይካፈሉ ነበር ምናልባትም አብላጫውን ይወሰዱ ነበር ። አንድ መልዕክት አለኝ ዛሬ በዬትኛውም መንገድ በእናንተ ለሚጠቀሙ ሁሉ ኢየሱስ ከተያዛችሁበት ችግር መከራ ውስንነት አለመቻል ወዘተ ነፃ አውጥቶ መሉ ሰው ያደርጋችኋል ። ከዚህ በኋላ በእናንተ ድህነት ችግር በእርዳታ ስም ቢዝነስ አይሠራም። የሐዋርያት ሥራ 16:16,19
[16]ወደ ጸሎት ስፍራም ስንሄድ፥ የምዋርተኝነት መንፈስ የነበረባት ለጌቶችዋም እየጠነቈለች ብዙ ትርፍ ታመጣ የነበረች አንዲት ገረድ አገኘችን።
[19]ጌቶችዋም የትርፋቸው ተስፋ እንደ ወጣ ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ወደ ገበያ በሹማምት ፊት ጐተቱአቸው፤ ከላይ ያየነው በሰዎች የተፈጥሮ ችግር ሊጠቀሙ ስለሚችሉ ሰዎች ነው ያየነው በዘመናችን በስፋት እያየን ስላለ ይህ ምንም ምስክር የሚያሻው ጉዳይ አይደለም። እርግጥ ነው ህይወታቸውን ኑሮአቸውን መስዋዕት ያደረጉም አሉ። በሐዋ 16 16 እና 19 ላይ ያለው ደግሞ በመንፈስ አስሮ መጠቀሚያ ስለማድረግ ነው። በተለይ ይህ በአገራችን የተለመደ ነው በተለያየ ድግምት አስሮ በሰዎች መነገድ ማትረፍ መበልጸግ የብዙዎች የዕብደት ምክንያት ከጥንቆላ ጋር የተያያዘ ነው።ሰው ጨካኝ ነው አይደለም በሩቅ ሰው በቅርብ ቤተሰቡ ሳይቀር ይህን ትብታብ በማድረግ አንዱን አስሮ አድህይቶ ሌላው ሲበለጽግ ይታያል። አሁን ቅዱሳን በዚህ ነገር ነቅተን ተግተን እንፀልይ በቃ እንበል የታሰሩ ይፈቱ ነፃ ይውጡ። በአንድም በሌላም በስውርም በግልፅ መንፈሳዊ ተፅዕኖ ውስጥ ያሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፃ ውጡ!!!! እስራታችሁ ይፈታ ።የተብታቢዎች የትርፋቸው ተሰፋ ይመታ!!! ፀልዩ የማንም መጠቀሚያ ላለመሆን ወደ ጌታ አብዝታችሁ ጩሁ! ምናልባት ጥቅማቸውን አንዳያጡ ዝም ሊያሰኙዋችሁ ይሞክሩ ይሆኑ ይሆናል፤ እናንተ ግን ኖ! አይሆንም አንደበርጤሚዎስ እምቢ በሉ። ዛሬ የእናንተ ቀን ነው! ነፃ ሰው ሙሉ ሰው የምትሆኑበት፤ ታውቃላችሁ፦ ከመናፍስት አሠራር ነው ነፃ የወጣሁት( ምስክርነቴን በመዳን ቀን ቲቪ አሌክሳንደር ለታ ብላችሁ በዩ ቲዩብ ብትገቡ ማየት ትችላላችሁ) ። አና ነፃ ከወጣሁ በኋላ ጠላት በግልፅም በስውርም ተፅዕኖ ያደርግብኝ ነበር። ።የመናፍስቱ ዓለም አገልጋይ እንድሆን ከቤተሰቦቼ አካባቢ ተሰርቶብኝ ነበር፦ ሆኖም የጌታ ከሆንሁ አገልጋይም ከሆንሁ ከሃያ ዓመት በኋላ ነው ከብርቱ ፀሎት የተነሳ ይህ ሰውር እጅ የተሰበረው። ዛሬ ለኔ የጠቀመኝን አንድ ምክር ልምከራችሁ በኑሮአቸሁ በቢዝነሳችሁ በአገልግሎታችሁ በባህሪያችሁ ወዘተ ነፃነት የማይሰማችሁ አሜን አትበሉ! የአርባ ቀን ዕድሌ ነው አትበሉ! እምቢ በሉ! ወደ እግዚአብሔር ጩሁ!!! እግዚአብሔር ሊያድናችሁ ሊታደጋችሁ ይወርዳል። ለማንም መጠቀሚያ አትሁኑ ጉልበታችሁንም በከንቱ አታስበሉ፥ እባካችሁ አብዝታችሁ ጩሁና ነፃ ውጡ ። በሌላ መልዕክት እስክንገናኝ ደህና ሁኑ። ከጠቀማችሁ እናንተ ጋር ብቻ አታስቀሩ ሼር አድርጉ።