የወላይታ ሶዶ ኦቶና ደብረ ፅዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ሰንበት ት/ቤት ገጽ

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • የወላይታ ሶዶ ኦቶና ደብረ ፅዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ሰንበት ት/ቤት ገጽ

የወላይታ ሶዶ ኦቶና ደብረ ፅዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ሰንበት ት/ቤት ገጽ የወላይታ ሶዶ ኦቶና ደብረ ፅዮን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ፈለገ_ሕይወት ሰንበት ት/ቤት ገጽ

09/06/2024

ክርስቶስ በስጋው ፍጡር ማለት ምን ማለት ነው?
/ክፍል አንድ/

የተዋህዶን ትርጉም በደንብ ለተረዳ ኦርቶዶክሳዊ ይህ አገላለጽ ሊጸንበት አይችልም፡፡ ተዋህዶ ማለት ሁለት አካላት አንድ አካል፣ ሁለት ባሕርያት አንድ ባሕርይ የሆኑበት ታላቅ ምስጢር ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ስንል፣ ፍጹም ሰው፣ ፍጹም አምላክ፣ ስግው ቃል፣ክሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ የሆነ ማለት ነው፡፡

በተዋህዶ ስጋ የራሱን ገንዘብ ሳይለቅ (በተአቅቦ)፣ የመለኮትን ገንዘብ ገንዘቡ አደረገ፡፡ መለኮትም የራሱን ገንዘብ ሳይለቅ (በተአቅቦ)፣ የስጋን ገንዘብ ገንዘቡ አደረገ፡፡ በመሆኑም ስግው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ፣ አንድ አካል፣ አንድ ባሕርይ ያለው፣ ፍጹም ሰው፣ ፍጹም አምላክ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ሲራብ፣ ሲጠማ፣ ሲደክም፣ ሲተኛ፣ ሲታመም፣ ሲሞት ብናየው፣ አንዲህ የሆነው ማነው ቢሉን አምላካችን ጌታቸን ኢየሱስ ክርስቶስ እንላለን፡፡ በደረቅ ግንባር አይንን ሲፈጥር፣ ውሃን ወደ ወይን ጠጅ ሲቀይር፣ ድውያንን ሲፈውስ፣ ሽባን ሲተረትር፣ ሙት ሲያስነሳ፣ ሞትን ድል አድርጎ ሲነሳ፣ ሲያርግ ያየነው እርሱ ማነው ቢለው ቢጠይቁን አሁንም ደግመን፣ ስግው ቃል፣ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብለን እንመልሳለን፡፡

ንስጥሮስ ይህንኑ ጥያቄ ቢጠየቅ፣ እንዲህ ይመልሳል፡፡ የተራበው፣ የተጠማው፣ የታመመው፣ የሞተው ስጋው ነው፡፡ ድውያንን የፈወሰው፣ ሙታንን ያስነሳው፣ ሞትን ድል ያደረገው ደገሞ መለኮት ነው ይላል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን ሁለት ማነነት ያለው፣ ሁለት ፈቃድ ያለው፣ ሁለት እኔ ባይ አካል ያለው ያደርግና፣ ይህን ያደረገው ስጋው ነው፡፡ ይህን ያደረገው መለኮቱ ነው በማለት ክርስቶስን ከሁለት ይክፍለዋል፡፡

ይህ ንስጥሮሳዊ ኑፋቄ፣ ከ1500 ዓመታት በኋላ ወንድማችንን አክሊል በሚያደርገው የlive ውይይት፣ ኢየሱስ በስጋው መለኮቱን ያመልከዋል? በማለት ጥያቄ ሲቀርብለት ሰምተናል፡፡ ለጊዜው ጥያቄስ መልስ ባይሰጠውም፣ ጠያቂው በማወቅም ይሁን ባለማወቅ፣ ክርስቶስን ስጋው እና መለኮቱ በማለት ክፍሎ ሲናገር ስምተነዋል፡፡ እንዲህ ያለ እምነትና ጥያቄ ንስጥሮሳዊነት ነው፡፡

ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና! የታመመው፣ የሞተው፣ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው፣ ያረገውም አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ‹‹አትፍራ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርኩ እነሆም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፣ የሞትና የሲኦል መክፈቻ አለኝ›› (ራዕ 1፡18) ያለው እርሱ አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

ክርስቶስ በስጋው ፍጡር፣ ማለትና ስጋው ፍጡር ነው ማለት አንድ ነውን?

በፍጹም አንድ አይደለም፡፡ ስጋው ብለን ስንጠራ በተዋህዶ የከበረውን የስግው ቃልን (ኢየሱስ ክርስቶስን) ስጋ ማለታችን ነው፡፡ ይህም ስጋ በተዋህዶ ከብሯልና፣ ከተዋህዶ በኋላ ከመለኮት ነጥለን ስጋው ፍጡር ነው አንልም፡፡ ለመለኮትም እንዲሁ ነው፡፡ ከተዋሆዶ በኋላ መለኮትን ከስጋ ነጥለን፣ ብቻውን ፈጣሪ ነው አንልም፡፡ ክርስቶስ በስጋ ፍጡር ማለት ስህተት የለበትም፡፡

ክርስቶስ በስጋ ፍጡር ስንልስ ምን ማለታችን ነው?

ፊደላት ታላቅ ትርጉም እንዳላቸው የምንረዳው አዚህ ጋር ነው፡፡ ክርስቶስ በስጋ ስንል፣ "በ" ፊደል ተዋህዶን የምታመለክት አያያዥ ቃል ናት፡፡ ክርስቶስ በስጋ ስንል፣ መለኮት በስጋ ማለታችን ነው፡፡ በዚህም መለኮት በተዋሃደው ስጋ ምክኒያት ገንዘብ ያደረገውን የስጋን ገንዘብ እንጠራበታለን፡፡

ፍጡርነት የስጋ ገንዘብ ነው፡፡ ኢፍጡርነት የመለኮት ገንዘብ ነው፡፡ ተዋህዶ፣ እኒህ ሁለት ባህርያት አንድ ባህርይ ሆኑ ብሎ ማመን ነው፡፡ ይህም ማለት፣ ስጋ ፍጡርነቱን ሳይለቅ (በተአቅቦ) ፈጣሪ ሆነ፡፡ መለኮትም፣ ኢፍጡርነቱን (ፈጣሪነቱን) ሳይለቅ (በተአቅቦ)፣ ፍጡር ሆነ ብሎ ማመን ነው፡፡ ፍጡር ሆነ ሲባል፣ ሰው ሆነ ከማለት ጋር አንድ ነው፡፡ ሌላ የተለይ ትርጉም ወይም ማብራሪያ የለውም፡፡ ፍጡር ሆነ ሲባል፣ በተዋህዶ ማለት ነው፡፡ ውላጤን እያሰቡ፣ ወይም አርዮሳዊ ክህደትን እያሰቡ፣ ወይም ኢአማንያን የሚያነሱትን ኑፋቄ እያሰቡ፣ ይህንን የቀና ኦርቶዶክሳዊ እምነትና ትምህርት በሌላ መተርጎም ተገቢ አይደለም፡፡

ይቆየን!

/ይቀጥላል…../

27/11/2023

"እርሱም አውቆ ተከፈተ"

በመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እና በመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ዘመን በክርስትናው ዓለም እስከዛሬ የምንደነቅባቸው እውነቶች ይገኛሉ። ይኼ ታሪክ ታዲያ እስከዛሬም ድረስ የሚያስደንቅ ታሪክ ነው፤የክርስትና መሠረት ከሆኑ ነገሮች አንደኛው የቤተክርስቲያኒቱ ኅብረታዊ አንድነት መሆኑንም የምናውቅበት ነው። ጌታ የመጣበትን ፍጥረተ ዓለምን(ዓለም ላይ ያሉ ሁሉ ፍጥረታት የተፈጠሩት ለፍጥረትታቱ ዓለም ለሆነው ለአዳም ነውና) ማዳን ሥራውን ከጨረሰ በኋላ ወደቀደመ ክብሩ ዐረገ። ባረገ በዓሥረኛው ቀን በትንሣኤው ሃምሳኛው ቀናት ጰራቅሊጦስን ልኮላቸው “ቤተክርስቲያን ልደቷን” አከበረች በዕለተ ጰራቅሊጦስ ቤተክርስቲያን ተወለደች ።

ይህቺ ቤተክርስቲያን የልደቷ ቀን ልጅነት አላገዳትም የወለዳት የመሠረታት “እንደልጅ/እንደሰው” በጥቂቱ ቢያድግም የወለዳት ቤተክርስቲያን ግን በተወለደች ዕለት ነው ቆማ መሄድ የጀመረችው፤ መጀመር ብቻም አይደለም ሳትንደረደር ማራቶን መሮጥ የጀመረችው።

በቀደመችው ቤተክርስቲያን ሩጫ ግን የእንደመሰናክል ሩጫ የሆኑባት እጅግ ብዙ ጊዜያት ነበሩ (ሩጫዋን የመሰናክል ያደረጉባት)። ከነዚህም መካከል የመጀመሪያ ልባቸው የተዘጋ ለክርስቶስ ወንጌልና ለሐዋርያት ስብከት ድፍን የነበሩት ነገሥታት፤በዘመኑ የነበሩ የኦሪት መምህራን፤ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን ናቸው።
ይሄንንም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በገሃድ የምናገኘው ነው።
ሐዋርያቱን እና ወደ መጀመሪያዋ ቤ/ክ የተጨመሩትን ክርስቲያኖችን በማሰር፣በመግረፍ፣በድንጋይ በመውገር እና ከሃገር እንዲወጡ
በማረግ (ክርስትና ከኢየሩሳሌም ውጪ እንዲሰበክ! እርሱ ባወቀ!) በወህኒ በማሰር....ነበር።

ይኼ ጽሑፍ ዓላማው ያደረገው በዚህ የቤተክርስቲያን መከራ ወቅት የነበረን አንድን የወህኒ ቤት “በር” ነው።
የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እንዲህ ብሎ የሚጀምር አንድ ታሪክ አለው “በዚያ ዘመን ንጉሡ ሄሮድስ መከራ ያጸናባቸው ዘንድ ከቤተክርስቲያን አንዳንዶቹ ላይ እጁን ጫነ” ሐዋ 12፡1 ይኼ የሄሮድስ እጅ መጫን እንደ ሐዋርያት ሌላ አንድ እንደ ማትያስ ያለ ሐዋርያ ለመጨመር የተደረገ አይደለም!(ሐዋ 1) እንደ ጳጳሳት ካህናትን ለመሾም የተደረገም እጅ መጫን አይደለም፤ እንደ ቅዱስ ያዕቆብ መልእት ደዌ ያለባቸውም እንዲፈወሱ አይደለም!
ለምንድነው የሚለኝ ቢኖር ቅዱስ ሉቃስ ታሪኩን እንዲህ ነው የሚቀጥለው “የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለ”፤ የሄሮድስ እጅ መጫን ለሞት ነው!
በመስቀል የተጀመረች ቤተክርስቲያን ስትቀጥል የዓለም ነገሥታት ሽልማቷን እና ሕይወቷን ከእንጨት መስቀል በተጨማሪ የብረት ሰይፍም አድርገውት ነበር።
ክርስቶስ መስቀልን እንደቀደሰው ሐዋርያቱ የሚሆኑ ሁሉ የሚሞቱበትን መስቀል በደማቸው ቀድሰውታል!
በቅዱስ ያዕቆብ ላይ የሆነው ታዲያ “አይሁድንም ደስ እንዳሰኛቸው” ባየ ጊዜ ሄሮድስ “ጨምሮ ጴጥሮስን ደግሞ ያዘ” (እንደው የዛሬ ዘመን ሄሮድሶች ማንን ደስ አሰኝተው ይሆን “ደስ የሚላቸው ከሆነማ” እያሉ ቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ መከራ መስቀል የሚያበዙት?፤ደስ ያላቸውስ አይሁዳያን የትኞቹ ይሆኑ? ...ልብ ይስጥልን!)
ንጉሡ ሕዝቡን ደስ ለማሰኘት “በአንዳንዶች” ላይ የጀመረውን እጅ መጫን ቤተክርስቲያን ወደተሠራችበት ዐለት ደረሰ፤ጴጥሮስ ጋር።
ቅዱስ ጴጥሮስን ወደ ወህኒ አጋዘው። በፋሲካ በዓል ዋዜማ ጌታውን የካደ ጰጥሮስ ዛሬ አስቀድሞ በካደው አምላክ ስም ሰብኮ በቂጣ በዓል ወደ እስር ቤት ገባ። በዚህ የፋሲካ በዓል እውነተኛው የመስዋእት በግ መሰዋቱ ለጴጥሮስ ጠቀመው፤ ለክርስቶስ ሞት ተሽሮ የነበረ የፋሲካ ፍርድ ለጴጥሮስ ጸናለት፤ በበዓሉ ምክንያት ጴጥሮስ ወደ ወህኒ ገባ እንጂ ባይሆን ይገድለው ዘንድ አስቦ ነበር።
ጴጥሮስ በወህኒ ይጠበቅ የነበረው በአራት ጭፍራ ወታደር ነው። በእስሩ ዐለቷን ልታጣ ባለች ቤተክርስቲያን “ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት አጥብቃ” ታደርግ ነበር። ይህቺ የዛሬዋ የኛ ቤተክርስቲያን ናት “ለታሰሩት እንማልዳለን”።
የአካልን ጸሎት ራስ ይሰማልና የቤተክርስቲያን ጸሎት ተሰማ በእግዚአብሔር ዘንድ።
ቅዱስ ጴጥሮስ በሁለት ወታደሮች መካከል በሰንሰለት ታስሮ ተኝቶ ስለነበረ፤ጠባቂዎች በደጁ ፊት ሆነው ወህኒውን ይጠብቁ በነበረበት የቤተክርስቲያን ጸሎት መልአክ ሆና ደረሰች ። “እነሆም የጌታ መልአክ ቀረበ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃው”
(ወህኒ ቤት? በሁለት ወታደር መካከል? በሰንሰለት ታስሮ? ጴጥሮስ እንዴት ያለ እንቅልፍ ነበር የተኛው?...የሰላም!...”እንቅልፍን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው”)።
ጴጥሮስ ነቃ ሰንሰለቱም ወደቀ...የወህኒው ጠባቂዎች የሚጠበቁ እንጂ የሚጠብቁ አይመስሉም ነበር ይሄ ሲሆን ተኝተዋል
“ጠባቂ በከንቱ ይደክማል” ።
ጴጥሮስ ከመልአኩ ጋር ሲወጣ በአራት ጭፍራ ይጠበቅ የነበረ ትልቅ በር ታሪክ ያስደንቃል!
መጽሐፉ እንዲህ ይላል “የመጀመሪያውንና የሁለተኛውንም ዘብ አልፈው ወደ ከተማ ወደሚያወጣው ወደ ብረቱ መዝጊያ ደረሱ “እርሱም አውቆ ተከፈተላቸው”።
ይኼ በር መልአኩ እና ቅዱስ ጴጥሮስን በምን አውቆ ይሄን ታኢክ ተጋራ?! የብረት በር እንደሆነ እንጂ በዘመኑ አሁን እንዳሉ በሮች “ሴንሰር” የተገጠመለት በር አልነበረም። ቅዱስ ሉቃስ በደንብ በሩ መልአኩንና ጴጥሮስን እንደለየው “ወደ ብረቱ መዝጊይዝ ደረሱ እርሱም አውቆ ተከፈተላቸው” ብሎ ነግሮናል።
ወደ’ኛ ልብ እንምጣ እስቲ!
አይሁድ ለትምህርቱ ልባቸውን ቢዘጉ የወህኒ በር ወደ ዓለም ሄደው እንዲሰብኩ እነርሱ እንደሆኑ አውቆ ተከፈተ።
የብረት መዝጊያ አውቆ የሚከፈትለት ጸሎት ከወህኒ መዝጊያ ጠብቆ የተከረቸመ የልባችን በር ሊከፍት እንደዚያች ቤተክርስቲያን ያለ ጸሎት ያስፈልገናል።
ስለቤተክርስቲያን ብለው በየወህኒ የታሰሩ በጨለማ የታጎሩ ክርስቲያኖችን አውቆ የሚከፈትላቸውን በር ከቤተክርስቲያን ጋር በጸሎት እንፍጠር።
የምትሰደደው ቤተክርስቲያን የሚፈናቀሉ ክርስቲያኖች ተስፋ የሚሆን ብርሃኑን የሚያሳይ የእግዚአብሔር መልአክ እንዲላክ በጸሎት እንበርታ!
ከብረት መዝጊያዎች አስቀድሞ የኛ የልባችን በር ይከፈት!

ወላይታ ሶዶ ኦቶና ደ/ጽ/ቅ/ ማርያም ቤ/ክ ፈለገ_ሕይወት ሰ/ት/ቤት

13/02/2023
11/02/2023
09/02/2023

Address

W/soddo
S**o
180

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የወላይታ ሶዶ ኦቶና ደብረ ፅዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ሰንበት ት/ቤት ገጽ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to የወላይታ ሶዶ ኦቶና ደብረ ፅዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ሰንበት ት/ቤት ገጽ:

Share

Category