18/08/2026
📖 📖
🔔 አዲስ ኪዳንና ትምህርቱ — የ4 ሳምንት ተከታታይ ትምህርት
ለ9 ሳምንታት በ“መጽሐፍ ቅዱስና ትምህርቱ” ዋና ርዕስ ሥር፣
ክፍል 1 - መግቢያ፣
ክፍል 2 - ብሉይ ኪዳንና ትምህርቱ፣
እንዲሁም Sola Scriptura ላይ ያደረግነውን ጥናት አጠናቀን፣ አሁን ደግሞ ወደ ቀጣዩ ክፍል እንሻገራለን።
📖
"ነገር ግን እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ጕድለት በማግኘቱ እንዲህ ይላቸዋል፤
“ከእስራኤል ቤት ጋር፣
ከይሁዳም ቤት ጋር፣
አዲስ ኪዳን የምገባበት፣
ጊዜ ይመጣል፤ ይላል ጌታ።”
ዕብራውያን 8፥8
ከፊታችን ሐሙስ፣ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት ሐሙሳት የአዲስ ኪዳንን ትምህርት በጥልቀት እንማራለን።
🙏 ጉኑኖና አካባቢው የምትገኙ ቅዱሳን ሁላችሁ፣
ይህ ታላቅ የቃሉ በረከት እንዳያመልጣችሁ በጌታ ፍቅር እንጋብዛችኋለን።
📌 መጽሐፍ ቅዱሳችሁንና ማስታወሻችሁን አትርሱ!
መጽሐፍ ቅዱስን በእጃችን፣
ቃሉን በልባችን! ❤️📖
✨ ኑ፤ አብረን እንማር፣ እንወቅ፣ እንኑር!