በኢ/ካቶሊካዊት/ቤ/ን የሶዶ ሀ/ስብከት/ECC-Apostolic Vicariate of Soddo

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • በኢ/ካቶሊካዊት/ቤ/ን የሶዶ ሀ/ስብከት/ECC-Apostolic Vicariate of Soddo

በኢ/ካቶሊካዊት/ቤ/ን የሶዶ ሀ/ስብከት/ECC-Apostolic Vicariate of Soddo "እርሱ የሚላችሁን አድርጉ" ዮሐ 2:5

22/06/2026
በቅዱስ ዮሐንስ ወንድሞች ገዳም የመጨረሻ የምንኩስና መኃላ ተካሄደ።     በአዲስ አበባ ካቶሊካዊ ሰበካ ሰኔ 13/2018 ዓ.ም በቅዱስ ዮሐንስ ወንድሞች ገዳም የቶጎ ዜግነት ያላቸው ክቡር ወ...
20/06/2026

በቅዱስ ዮሐንስ ወንድሞች ገዳም የመጨረሻ የምንኩስና መኃላ ተካሄደ።
በአዲስ አበባ ካቶሊካዊ ሰበካ ሰኔ 13/2018 ዓ.ም በቅዱስ ዮሐንስ ወንድሞች ገዳም የቶጎ ዜግነት ያላቸው ክቡር ወ/ም አልዶ ኢፕፋን የመጨረሻ የምንኩስና መኃላ አደረጉ።
የአዲስ አበባ አገረስብከት ተሰያሚ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ተስፋሥላሴ፣ ካህናት፣ መነኮሳት እና ምዕምናን የተገኙ ሲሆን በዚሁ ቅዱስ ዮሐንስ ወንድሞች ገዳም የመጨረሻ መኃላ የሚደረገው ለ3ኛ ጊዜ ነው።

💙 ሰኔ 14 (June 21) የእናቶች ቀን እንደሆነው ሁሉ የታላላቅ አባቶች ቀን (Father's Day) ነው! 💙በሕይወታችን ውስጥ እኛን በመምራት፣ በመጠበቅና በፍቅር ኮትኩተው ላሳደጉን ውድ...
20/06/2026

💙 ሰኔ 14 (June 21) የእናቶች ቀን እንደሆነው ሁሉ የታላላቅ አባቶች ቀን (Father's Day) ነው! 💙

በሕይወታችን ውስጥ እኛን በመምራት፣ በመጠበቅና በፍቅር ኮትኩተው ላሳደጉን ውድ አባቶቻችን፣ አያቶቻችን፣ የክርስትና አባቶቻችን፣ የሃይማኖት አባቶችና የአባትነት ሚናቸውን ለተወጡልን ውድ ወገኖቻችን በሙሉ የምስጋና እና የእውቅና ቀን ነው!

የአባት ፍቅር ብዙ ጊዜ በቃል ብቻ ሳይሆን በከባድ መስዋዕትነት፣ በጠንካራ ሥራ፣ በጸጥታ ጥንካሬና ለቤተሰብ ባለው ፍጹም ታማኝነት ይገለጻል። የእነርሱ መኖር ለቤታችን ትልቅ ምሶሶ ነው።

"የሰማዩ አባታችን ሆይ፤ ስለ አባቶቻችን ሁሉ እናመሰግንሃለን። በብርታት፣ በጥበብ፣ በትዕግሥትና በጤና ባርካቸው። ቤተሰቦቻቸውን በፍቅርና በእምነት እንዲመሩ ኃይልን ስጣቸው። መስዋዕትነታቸውን ክፈልላቸው፤ በትግላቸውም አጽናናቸው። ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት አባቶቻችን ደግሞ በመንግሥተ ሰማያት የዘላለም ዕረፍትን ስጣቸው። አሜን!" ✨

ሁልጊዜም ለምታደርጉልን ተቆጥሮ ለማያልቅ መስዋዕትነት እናመሰግናለን! በሕይወት ያሉትን አባቶቻችንን ረጅም ዕድሜና ጤና ይስጥልን፤ ያለፉትንም ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን።

⚛️ለዓለማችን ድንቅ አባቶች በሙሉ መልካም የአባቶች ቀን! 🎉💙

#መልካምየአባቶችቀን #የአባትነትክብር #ምስጋና #በረከት #እምነት #ኢትዮጵያ

✨ "ጌታ በፊታችሁ ይቅደም፤ የታወቀውንም ያልታወቀውንም ሰልፋችሁን ይዋጋ!" አሜን🙏✨በሕይወት ጉዟችን ውስጥ አንዳንዴ የምናያቸውና የምናውቃቸው ግልጽ ፈተናዎች ይገጥሙናል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ...
19/06/2026

✨ "ጌታ በፊታችሁ ይቅደም፤ የታወቀውንም ያልታወቀውንም ሰልፋችሁን ይዋጋ!" አሜን🙏✨

በሕይወት ጉዟችን ውስጥ አንዳንዴ የምናያቸውና የምናውቃቸው ግልጽ ፈተናዎች ይገጥሙናል፤ በሌላ በኩል ደግሞ እኛ ሳናውቀውና ሳናስተውለው በስተጀርባ ሕይወታችንንና ቤታችንን የሚፈታተኑ ስውር ውጊያዎች አሉ። ነገር ግን በኃያሉ አምላክ ጥላ ስር ለሚጠለል ሰው ፍርሃት የለም!

እርሱ መንገድ ጠራጊ አምላክ ነው። እኛ ገና ያልረገጥነውን ነገያችንን፣ የወደፊት ሕይወታችንን፣ የልጆቻችንን መስመር እርሱ አስቀድሞ በመባረክ በፊታችን ይዘረጋል።

እኛ የምንጨነቅበትንና በዓይናችን የምናየውን የኑሮ፣ የጤናም ሆነ የሥራ ፈተና ብቻ ሳይሆን፤ ጠላት በስውር ያጠመደውንና እኛ የማናውቀውን ወጥመድ ሁሉ እርሱ በኃይሉ ይሰብረዋል።

ትክክለኛ ሰላምና ጥበቃ የሚጀምረው ከቤት ነው። እግዚአብሔር በቤታችሁና በቤተሰባችሁ ዙሪያ የእሳት ቅጥር ሆኖ ይጠብቃችኋል።

"አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፤ ከእኛ አቅምና እውቀት በላይ በሆኑት የሕይወት ውጣ ውረዶች ሁሉ አንተ በፊታችን ቅደም። በቤታችንና በኑሯችን ላይ የተደቀኑትን የታወቁትንም ሆነ በስውር ያሉትን ሰልፎች ሁሉ አንተ ተዋጋልን። እኛ በሰላም እንድንኖር አንተ ታላቅነቱንና ድልን ስጠን። አሜን!"

#እምነት #የዕለቱጸሎት #አሜን #በረከት #መንፈሳዊሕይወት #ኢትዮጵያ

  በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የሀዋሳ ሀገረስብከት ልበ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ዓመታዊ የልበ እየሱስ ክብረ በዓል  በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል ።በበዓሉም ክቡር አባ ፀጋዬ ...
19/06/2026


በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የሀዋሳ ሀገረስብከት ልበ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ዓመታዊ የልበ እየሱስ ክብረ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል ።

በበዓሉም ክቡር አባ ፀጋዬ ጌታሁን የሀዋሳ ሀገረስብከት የማህበራዊ እና ልማት ኮሚሽን ጽ/ቤት ሃላፊ በበርካታ ካህናት ታጅበው መስዋዕተ ቅዳሴን አሳርገዋል።

ክቡር አባ ፀጋዬ በወንጌል ስብከታቸው የጌታ እየሱስ ልብ የፍቅር ምንጭ ምልክት ነውና እኛም ጌታ እየሱስ አብዝቶ እንደወደደን እኛም ልንወደው እና እርስ በእርሳችን በጌታ ፍቅር እንዋደድ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

በዕለቱም በረካታ የቁማስናው ምዕመናን ወጣት መዘምራን እንዲሁም ከሌሎች ቁምስናዎች የመጡ እንግዶች ልበ እየሱስ ጌታ ሆይ ልባችንን እንደ ልብህ አድስ እያሉ በኡደት በዝማሬ እና በተለያዩ መንፈሳዊ ሥነስርዓቶች አክብረዋል።

ሀዋሳ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ⛪
HCC PRODUCTION 🎬

የብፁዕ አቡነ ኃይለማርያም መድኅን የጋምቤላ ሀገረስብከት ተተኪ ጳጳስ ቅብዐተ ጵጵስና በጋምቤላ ቅዱስ ዮሴፍ  ካቶሊክ ካቴድራል ተካሄደበኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንየጋምቤላ ሀገረስብከት ...
14/06/2026

የብፁዕ አቡነ ኃይለማርያም መድኅን የጋምቤላ ሀገረስብከት ተተኪ ጳጳስ ቅብዐተ ጵጵስና በጋምቤላ ቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ካቴድራል ተካሄደ
በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንየጋምቤላ ሀገረስብከት ተተኪ ጳጳስ ሆነው በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ የተሾሙት የብፁዕ አቡነ ኃይለማርያም መድኅን ቅብዓተ ጵጵስና በብፁዕካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን መሪነት ተደረገ። በመ
ስዋዕተ ቅዳሴው የአዲስ አበባ፣የጋምቤላ፣ የመቂ፣ የጅማ ቦንጋ፣ የሀረር፣ የባህር-ዳር ደሴ፣ የነቀምት፣ የሶዶ እና የሀዋሳ ሀገረስብከት ብፁዓን ጳጳሳት፤የአዲግራት፣ የሆሳዕና፣ የእምድብር እና የባሌ-ሮቤ ሀገረስብከት የብፁዓን ጳጳሳት ተወካዮች፣ የቅድስት መንበር በኢትዮጵያ ተወካይ፣ የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት፣ምክትል ፕሬዝደንት እና ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፤ የሳሌዢያውያንቅዱስ ዮሃንስ ቦስኮ ካህናት እና ወንድሞች ከቅድስት መንበር፣ ከአፍሪካ፣ ከኤርትራ እና ከመላው ኢትዮጵያ፤ ከኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳትጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት፣ የኃይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ ከተለያዩ ሀገረስብከት ጽ/ቤቶች የተወከሉ የሥራ ኃላፊዎች፣ በርካታ ካህናት፣ገዳማውያን እና ገዳማውያት እንዲሁም ከተለያዩ ቁምስናዎች የመጡ የጋምቤላ ሀገረስብከት ምዕመናን ተሳትፈዋል።በብፁዕ ካርዲና
ል አቡነ ብርሃነኢየሱስበካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥርዓት መሰረት ቅብዓተ ጵጵስናውን የመሩ ሲሆን ተተኪ ጳጳሱ ወንጊላዊው ዮሐንስ በጻፈው የጌታችን የኢየሱስክርስቶስ ወንጌል 21፡20 በመረጡት “ተከተለኝ” በሚለው መሪ ቃል እና ስም መሰረት ብፁዕ አቡነ ኃይለማርያም መድኅንብለው ለተተኪ ጳጳስነት ቀብተዋቸዋል።ብፁዕ ካርዲናል አቡ
ነ ብርሃነኢየሱስበዕለቱ ባስተላለፉት መልዕክት ተተኪ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኃይለማርያም “እንኳን ወደ ጋራ የፍቅር ተልዕኮበደህና መጡ” ብለዋል። ብፁዕነታቸው በዚህ መንገዱ አስፈሪ በሚመስል ነገር ግን በፍቅር ለተሞላው ታላቅ አገልግሎት በእግዚአብሔርጸጋ እንዲበረቱ አደራ ብለዋል። ብፁዕ ካርዲናል “አንተ ኖላዊ ነህ” በማለት አዲሱ ተተኪ ጳጳስ በመልካሙ እረኛ ምሳሌ በጎቻቸውንእንዲጠብቁ፣ በሥልጣን ሳይሆን በፍቅር ህዝባቸውን ያለምንም ልዩነት እንዲያገለግሉ ሰበካውን በእግዚአብሔር ጸጋ የወንጌልን ሥራ ለማስቀጠል በተስፋ ሰጥቻለሁ ብለዋል። በመስዋዕተ ቅዳሴው የተገኙ
ት ክብርትፕሬዝደንት ወ/ሮ አለሚቱ ዑሙድ ለኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን፣ እና ለጋምቤላ ሀገረስብከት እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ቤተክርስቲያኗበክልሉ ለምታደርገው አስተዋጽዖ አመስግነዋል። ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ዜጎችን በስነምግባር ለማነጽ፣ በፍትህና ሰላም ስራዎች፣በልማት ስራዎች ያለምንም አድልዖ ከገጠር እስከ ከተማ ለምታደርገው ድጋፍ፣ በትምህርት እና በጤና እንዲሁም በውሃ ሥራዎች ለማህበረሰቡለምታሳየው አብሮነት፣ ወጣቶችን የሚያንፁ ፕሮግራሞችን በመቅረጽ ለትውልድ የሚተርፍ ሚና አበርክተዋል ብለዋል። ክብርት ፕሬዝደንቷአሁንም እነዚህን ታላላቅ ሥራዎች ለማስቀጠል አዲስ ለተሾሙት ተተኪ ጳጳስ መንግስት ከጎናቸው እንደሚሆን አረጋግጠዋል። የቅድስት መንበር በኢትዮጵያ ተወካ
ይብፁዕ ሊቀጳጳስ ብሪያን የርዕሰ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንቼስኮችን ሰላምታ እና ቡራኬ በመስጠት “በዚህ በብዙ ባህሎች፣ ብሔረሰቦች እናበርካታ ቋንቋዎች እንዳሚነገሩ በሚነገርባት በዚህ ምድር ጳጳስ ሆነው ስለተሾሙ እንኳን ደስ አሎት” ብለዋል። ብፁዕነታቸው የጋምቤላ ሰበካ ካህናት፣ገዳማውያን እና ምዕመናንን አዲስ የተሾሙላቸውን ጳጳስ በሐዋርያዊ አገልግሎታቸው እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል። ብፁዕ አቡነ ኃይለማሪያም ለጋምቤላሀገረ
ስብከት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ጳጳስ፣ ለሰበካው ሶስተኛ ጳጳስ እንዲሁም ለሳሌዢያውያን ዮሀንስ ቦስኮ ማህበር ሁለተኛው ኢትዮጵያዊጳጳስ ናቸው።

ሰላም ካቶሊክ ቲቪ Pax Catholic TV

በጋምቤላ አገረስብከት ሰኔ 07/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ቅብዐተ ጵጵስና ለመካፈል ወደ ጋምቤላ ለተጓዙ በጋምቤላ አየር ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ተደረገ።በጋምቤላ አገረስብከት ሰኔ 07/2018 ...
13/06/2026

በጋምቤላ አገረስብከት ሰኔ 07/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ቅብዐተ ጵጵስና ለመካፈል ወደ ጋምቤላ ለተጓዙ በጋምቤላ አየር ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ተደረገ።

በጋምቤላ አገረስብከት ሰኔ 07/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ቅብዐተ ጵጵስና ለመካፈል ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስን ጨምሮ የአዲስአበባ አገረስብከት ረዳት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ተስፋሥላሴ፣ የባሕር ዳር ደሴ አገረስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ልሳነክርስቶስ፣ የአዲስ አበባ አገረስብከት ጳጳስ እንደራሴ ክቡር አባ ተስፋዬ ወልደማርያም፣ የኢትዮጵያ ጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ክቡር አባ ከተማ አስፋው፣ ምክትል ጠቅላይ ፀሐፊ እና የሐዋርያዊ ክፍል ኃላፊ ክቡር አባ አብርሃም፣ የአዲስ አበባ አገረስብከት ሐዋርያዊ ማስተባበርያ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አባ ጴጥሮስ በርጋ፣ በሥርዐተ ጵጵስናው ላይ ለመካፈል ጋምቤላ ገብተዋል።

በጋምቤላ አየር ማረፊያ ሲደርሱም የክልሉን ፕሬዚዳንት ክብርት ወይዘሮ ዓለሚቱ ዑመድ፣ ምክትል ፕሬዚዳት ዶ/ር ጋቱሏክ ሮንና ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፀጥታ አካላት፣ ካህናት፣ ደናግል፣ የጋምቤል ምዕመናን በጋምቤል አየር ማረፊያ በመገኘት ደማቅ አቀባበል አድርገዋል።

የጋምቤላ ክልል ዋና አስተዳዳሪ ወይዘሮ ዓለሚቱ ዑመድ የእንኳ ደህና መጣችሁ ንግግር አድረገዋል።

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ በክልሉ መንግሥት ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል አመስግነው፣ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ከመንግሥት ጎን በመሆን የተለያዩ ልማታዊ ሥራዎችን እየሠራች መሆኑን በመግለፅ በቀጣይም አጋርነቷ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ሰላም ካቶሊክ ቲቪ Pax Catholic TV

በቅድስት መንበር የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ተወካይ ክቡር አባ ጃሮዝላቭ ለሐዋርያዊ ጉብኝት በእምድብር ሀገረስብከት ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝትለሐዋርያዊ ጉብኝት ወ...
13/06/2026

በቅድስት መንበር የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ተወካይ ክቡር አባ ጃሮዝላቭ ለሐዋርያዊ ጉብኝት በእምድብር ሀገረስብከት ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት

ለሐዋርያዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ ባጋጠማቸው መጠነኛ ሕመም ምክንያት በእምድብር ሀገረስብከት ለታቀደው ጉብመገኘት ባይችሉም እንኳን የእርሳቸው ተወካይ የሆኑት ክቡር አባ ጃሮዝላቭ በሰበካው ተገኝተዋል።
ክቡርነታቸው በእምድብር ሲደርሱ በብፁዕ አቡነ ሉቃስ የእምድብር ሀገረስበከት ጳጳስ፣ በካህናት፣ ገዳማውያን፣ ምዕመናን እና የከተማው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ክቡር አባ ጃሮዝላቭ በሰበካው ባደረጉት ቆይታ በእምድብር ካቶሊክ ጽ/ቤት፣ በጠ‍ኤና እና ትምህርት ተቋማት፣ በቁምስናዎች፣ በአጣጥ የእመቤታችን ሉርድ ማርያም ቁምስና እና በአጣጥ ሆስፒታል በመገኘት ለሕሙማን ጸሎት አድርገዋል።

ጉብኝታቸውን በመቀጠልም በወልቂጤ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጉራጌ ሀገረስብከት ጳጳስ ጋር ተገናኝተዋል።

ክቡር አባ ጃሮዝላቭ በእምድብር ለተደረገላቸው ደማቅ መንፈሳዊ አቀባበል ደስታቸውን በመግለጽ ሐዋርያዊ ቡራኬአቸውንና ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ የተላከ መልዕክት እና ቡራኬ አስተላልፈዋል።

Catholic Bishops’ Conference of Ethiopia

Address

Wolaita Soddo
S**o
132

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በኢ/ካቶሊካዊት/ቤ/ን የሶዶ ሀ/ስብከት/ECC-Apostolic Vicariate of Soddo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share