SCS - Soddo Catholic Secretariat

SCS - Soddo Catholic Secretariat Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from SCS - Soddo Catholic Secretariat, Catholic Church, Ethiopia, Wolaita Soddo, Sodo.

የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት 2🌼19ከ ብጹዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ በኢትዮጲያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የሶዶ ሀገረስብከት ጳጳስ 🌼🙏🏽
10/09/2026

የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት 2🌼19
ከ ብጹዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ በኢትዮጲያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የሶዶ ሀገረስብከት ጳጳስ 🌼🙏🏽

🙏🏽
06/09/2026

🙏🏽

30/08/2026

✝️ «ብርሃናችሁ ይብራ!» (ማቴ 5:16)

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሶዶ ሀገረስብከት ለተከታታይ ሶስት ቀናት (ከነሐሴ 21 - 23)
ሲካሄድ የቆየው የወጣቶች ፌስቲቫል በታላቅ ድምቀት ተጠናቀቀ !!!

**oDiocese

✝️ «ብርሃናችሁ  ይብራ!» (ማቴ 5:16)በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሶዶ ሀገረስብከት ለተከታታይ ሶስት ቀናት (ከነሐሴ 21 - 23) ሲካሄድ የቆየው የወጣቶች ፌስቲቫል በታላቅ የ...
30/08/2026

✝️ «ብርሃናችሁ ይብራ!» (ማቴ 5:16)

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሶዶ ሀገረስብከት ለተከታታይ ሶስት ቀናት (ከነሐሴ 21 - 23)
ሲካሄድ የቆየው የወጣቶች ፌስቲቫል በታላቅ የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎትና በረከት ተጠናቀቀ።

ከ1,200 በላይ ወጣቶች በተሳተፉበት በዚህ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ 📖 ቃለ-እግዚአብሄርን ክቡር አባ አለማየሁ ፎላ ያካፈሉ ሲሆን «ካቶሊካዊነታችንን እንመስክር» በማለት ጥልቅ መልዕክትን አስተላልፈዋል።

መስዋዕተ ቅዳሴውን የመሩት ብፁዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ የሶዶ ሀገረ ስብከት ጳጳስ በመዝጊያው ላይ የሚከተለውን አባታዊ መልዕክት ለወጣቶች አስተላልፈዋል፦

ወጣቶች ሆይ ከፌስቲቫሉ ያገኛችሁትን ትምህርት በፎቶና ቪዲዮ ከማስቀረት ባለፈ በልባችሁና በሕይወታችሁ እንዲቀር ጣሩ፤ ሕይወታችሁ ምስክር ይሁን። የወንበር ወጣቶች ባለመሆን ፤ የመፍትሄና የአገልግሎት ሰው ሁኑ ፣ ቤተክርስቲያን የናንተን ፈጠራ፣ ድፍረትና ተስፋ ትፈልጋለች ስለዚህ ወደ ቁምስናችሁ ስትመለሱ እምነታችሁን አትደብቁ፤መስክሩ እራሳችሁንም ሁኑ።

ይህን እንድታደርጉ ሀይል የሚሰጣችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አንብቡ፤ በቅዱስ ቁርባን ስግደት ተጠናከሩ፤ ንስሀንም አትዘንጉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ያስተላለፉትን መልዕክት በማስታወስ እኔም እንዲህ እላችኃለሁ ቴክኖሎጂንና ሰው-ሠራሽ አስተውሎትን (AI) ለበጎ ነገር ተጠቀሙበት፤ በዲጂታሉ ዓለም የክርስቶስ ምስክሮች ሁኑ።

በመጨረሻም እንደ ቅዱስ ፍራንቺስኮስ “ጌታ ሆይ ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” በማለት ራሳችሁን ጠይቁ፤ ጌታ የሚመልስላችሁንም መልስ የሕይወት ጥሪ አድርጋችሁ ያዙ። በማለት ጥልቅ መልዕክትን አስተላልፈዋል።

#በስተመጨረሻም ፌስቲቫሉ በላቀ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላደረጉት ለሀገረ ስብከቱ የወጣቶች አስተባባሪ ለክቡር አባ አበበ ሜጋ፣ ለሐዋርያዊ አስተባባሪ ለክቡር አባ ማቴዎስ ተገኝ፣ ወጣቶችን በእግዚአብሔር ቃል ሲያንጹ ለቆዩት ለክቡር አባ አለማየሁ ፎላ እና አባ ታዴዎስ አያኖ ፣ በመስዋዕተ ቅዳሴ ላገለገሉ ክቡራን አባቶች፣ ለሲስተሮችና ደናግላን ፣በዝማሬ ላገለገሉት ዘማሪ ቢንያም አፈወርቅና ለፊሶን አባላት፣ ኢያሱ ኮላሶ፣ አማኑኤል አርጃ፣ ለአስተባባሪዎችና ንቁ ተሳትፎ ላደረጉት ወጣቶች በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቅርበዋል።

**oDiocese

27/08/2026

‎ ⛪️ታላቅ የወጣቶች ፌስቲቫል!!

‎በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሶዶ ሀገረስብከት በርካታ የሀገረስብከቱ ወጣቶች የተሳተፉበት ታላቅ የወጣቶች ፌስቲቫል "ብርሃናችሁ ይብራ" በሚል መሪ ቃል በዑደት ፣መቁጠሪያ ፀሎት እና በቅዱስ ቁርባን ስግደት ዛሬ ተጀመረ።

ፌስቲቫሉ እስከ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ መንፈሳዊ መርሀግብሮች ይቀጥላል።

‎ይህ የወጣቶች ፌሲቲቫል በሀገረስብከት ደረጃ በየአመቱ የሚዘጋጅ ሲሆን በመርሀግብሩ
‎🙏🏽 መንፈሳዊ ትምህርት በተጋባዥ ካህናት
‎🙏🏽 መዝሙር በተጋባዥ ዘማሪያን
‎🙏🏽 ጸሎት እና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ዝግጅቶች ያካትታል።

27/08/2026

‎ ታላቅ የወጣቶች ፌስቲቫል!!

‎በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሶዶ ሀገረስብከት በርካታ የሀገረስብከቱ ወጣቶች የተሳተፉበት ታላቅ የወጣቶች ፌስቲቫል "ብርሃናችሁ ይብራ" በሚል መሪ ቃል በዑደት ፣መቁጠሪያ ፀሎት እና በቅዱስ ቁርባን ስግደት ዛሬ ተጀመረ።

ፌስቲቫሉ እስከ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ መንፈሳዊ መርሀግብሮች ይቀጥላል።

‎ይህ የወጣቶች ፌሲቲቫል በሀገረስብከት ደረጃ በየአመቱ የሚዘጋጅ ሲሆን በመርሀግብሩ
‎🙏🏽 መንፈሳዊ ትምህርት በተጋባዥ ካህናት
‎🙏🏽 መዝሙር በተጋባዥ ዘማሪያን
‎🙏🏽 ጸሎት እና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ዝግጅቶች ያካትታል።

እንኳን ደስ አለን! 🎉🎊በ2018 ዓ.ም (2025/26) የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በታዋቂዎቹና ጥራት ባላቸው ትምህርትቤቶቻችን   እና   ካቶሊክ ትምህርት ቤት ለተመዘገበው ደማቅና የላቀ ውጤ...
27/08/2026

እንኳን ደስ አለን! 🎉🎊

በ2018 ዓ.ም (2025/26) የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በታዋቂዎቹና ጥራት ባላቸው ትምህርትቤቶቻችን እና ካቶሊክ ትምህርት ቤት ለተመዘገበው ደማቅና የላቀ ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ!

🎯 አባ ፓስካል ካቶሊክ ትምህርት ቤት ለፈተና ከተቀመጡ 69 ተማሪዎች መካከል ሙሉ በሙሉ(100%) በማሳለፍ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሁሉንም ተማሪዎች ያሳለፈና ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚገቡ ተማሪዎችን በማፍራት ውጤታማነትቱን አስቀጥሏል።

የውጤት ዝርዝር:

ከ 500 በላይ: 10 ተማሪዎች

ከ 400 በላይ: 49 ተማሪዎች እንዲሁም

ከ 350 በላይ: 10 ተማሪዎች አምጥተው አልፈዋል።

🎯 ሌላኛው ትጉ ተቋማችን ዶን ቦስኮ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካስፈተናቸው 121 ተማሪዎች ውስጥ:

104 ተማሪዎች በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን

17 ተማሪዎች ደግሞ ወደ ማሻሻያ (Remedial) ትምህርት የሚያስገባ ውጤት አስመዝግበዋል።

#ለዚህ ታላቅና አኩሪ ስኬት የበቁትን ተማሪዎቻችንን እና ትምህርት ቤቶቻችንን በሙሉ አቅማቸው ሲደግፉ ለነበሩ፡

🙏🏽 ለውድ መምህራኖቻችን፣

🙏🏽 ለተከበራችሁ ወላጆች፣

🙏🏽 ለመላው የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ፣ እና

🙏🏽 ለሁሉም ባለድርሻ አካላት

ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ እና እገዛ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

🎉🎉በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!

 ! 🤝Catholic Caritas Ethiopia Branch Office of Soddo (CCE-S) successfully hosted the inception workshop for our 2027–202...
24/08/2026

! 🤝

Catholic Caritas Ethiopia Branch Office of Soddo (CCE-S) successfully hosted the inception workshop for our 2027–2029 Participatory Strategic Plan.

The event was graced by the presence of His Excellency Bishop Dejene Hidoto, Vicar Apostolic of Soddo, Reverend Fathers, CCE-Soddo staff, and sub-branch representatives.

Bishop Dejene Hidoto opened the event with heartfelt prayers. Dr. Netsanet Demissie B. Executive Director welcomed attendees and explained the workshop’s purpose. Mr. Ashenafi Melaku (MEAL Coordinator) presented a robust framework for our three-year plan, covering key areas like:

🎯 Strategic Assignment & Alignment
🎯Ambition & Purpose
🎯Planning Methodology & Evidence Tools
🎯Governance & Critical Success Factors
🎯Roadmap & Key Deliverables

Engaging discussions followed, with Bishop Dejene Hidoto offering valuable recommendations and thanking everyone for their commitment. The program was concluded with a prayer.
This workshop sets a positive tone for our future development.

#በኢትዮጲያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሶዶ ሀገረ ስብከት የካቶሊክ ካሪታስ ኢትዮጵያ ሶዶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2027–2029 አሳታፊ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ የመክፈቻ ውይይት በስኬት አከናውኗል።

በዝግጅቱ ላይ ብፁዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ የሶዶ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ፣ ክቡራን አባቶች፣ የካሪታስ ሶዶ ሰራተኞች እና የንዑስ ቅርንጫፍ ቢሮ ተወካዮች ተገኝተዋል።
ብፁዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ መርሃ ግብሩን በጸሎት የከፈቱ ሲሆን፣ ዶ/ር ነፃነት ደምሴ የጽ/ቤቱ አስተባባሪ ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈው የውይይቱን ዓላማ አብራርተዋል። በመቀጠልም አቶ አሸናፊ መላኩ (የMEAL አስትባባሪ) ለሦስት ዓመቱ ዕቅድ የሚያገለግል ማዕቀፍ አቅርበዋል። ማዕቀፉ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ያካተተ ነበር፡-
🎯ስትራቴጂካዊ ተልዕኮ እና ቅንጅት
🎯 ምኞት እና ዓላማ
🎯የዕቅድ ዝግጅት ዘዴ እና የመረጃ መሣሪያዎች
🎯አስተዳደር እና ለስኬት ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች
🎯የትግበራ መንገድ እና ዋና ዋና ውጤቶች

ከአቀረቡ በኋላ ፍሬያማ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ብፁዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ ጠቃሚ አስተያየቶችንና መመሪያዎችን በመስጠት አዘጋጆቹንና ተሳታፊዎችን ስላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።
በመጨረሻም መርሃ ግብሩ በጸሎት ተጠናቋል።

የ SPREAD (Strengthening Integrated Peace, Resilience and Disaster Risk Reduction for Cross-Border Communities in the Kar...
19/08/2026

የ SPREAD (Strengthening Integrated Peace, Resilience and Disaster Risk Reduction for Cross-Border Communities in the Karamoja Cluster) ፕሮጀክት አጭር ዘጋቢ ቪዲዮ (Documentary).🎥🎥

በካቶሊክ ካሪታስ ኢትዮጵያ/ሶዶ እና ዳን ቸርች ኤይድ (DCA) አስተባባሪነት፣ በአውሮፓ ህብረት (EU) የገንዘብ ድጋፍ የሚተገበረውን የ SPREAD ፕሮጀክት የሥራ እንቅስቃሴ የሚያሳይ አጭር ዘጋቢ ቪዲዮ ይዘንላችሁ ቀርበናል።

ፕሮጀክቱ በደቡብ ኦሞ አርብቶ አደር አካባቢዎች ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት እና የማህበራዊ ትስስርን (Social Cohesion) ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።

🙏ለዚህ ትልቅ ስራ የገንዘብ ድጋፍ ላደረገልን ለአውሮፓ ህብረት (EU) እንዲሁም ላደረጉት የላቀ አስተዋጽኦ እናድንቅ ስራ ለ DCA ሰራተኞች፣ ለካቶሊክ ካሪታስ ኢትዮጵያ/ሶዶ የኦሞራቴ ንዑስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ ለስራችን ስኬት አብረውን እየሰሩ ላሉ የመንግስት አካላት እና ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ምስጋናችንን እናቀርባለን።

#ፋና #ኢትዮጵያ

Address

Ethiopia, Wolaita Soddo
S**o

Opening Hours

Monday 08:00 - 18:00
Tuesday 08:00 - 18:00
Wednesday 08:00 - 18:00
Thursday 08:00 - 18:00
Friday 08:00 - 18:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SCS - Soddo Catholic Secretariat posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to SCS - Soddo Catholic Secretariat:

Shortcuts

Share