09/10/2020
ቀን ሁለት በሶዶ ባፕቲስት ቤተክርስትያን በተዘጋጀው የአምስቱ ብቻዎች [Five solas] ኮንፈራንስ
ጠዋት
መዝሙር :- እግዚአብሔር በክርስቶስ ስለዋለንን አመሰግንነው
የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜ - ሳይመን ዶይለ
በእምነት ብቻ [sola fide]
ሮሜ 3:18-4:12
መግቢያ
- በእምነት ብቻ የሚለው አስተምህሮ ተደላድሎ ያለ አይደለም። አሁንም በጥቃት ላይ ነው።
- እምነት ብቻ ማለት ለደኅንነት በክርስቶስ ብቻ ማመንና መደገፍ ነው።
- ኃጢአተኛ የሚጸድቀው በእምነት ብቻ ነው።
መዝ 36:9, 119:96
- ከእምነት ተከትሎ የሚመጣው 'ብቻ' የሚለው ቃል ሌላ ተጨማሪ ነገር እንደሌለ የሚያሳይ ቁልፍ ቃል ነው።
- እምነት በራሱ ጽድቅ ማስገኛ ሥራ አይደለም።
- እምነት ሕግን የመጠበቅ ታማኝነት አይደለም።
ገላ 2:15-15, 2ቆሮ 5:20-21
- ከእምነት ብቻ ጋር ተያይዞ ሳይነሳ የማይቀረው : የክርስቶስ ጽድቅ ለእኛ መቆጠሩ [imputation]
ሮሜ 3:23-26, 2ቆሮ 5:20-21
ሁለተኛ ክፍለጊዜ :- ሳይመን ዶይለ
መዝሙር :- ስለ እግዚአብሔር ቃል አዜምን : ለቃሉ ፍቅራችንን ገለጥን
ትግበራ
- ወንጌሉ ያለ መስፈርት ለሁሉም የቀረበ ነው።
ማቴ 11:28-30, ኢሳ 55:1
- የድነት እርግጠኝነት በእምነት ብቻ የሚሆን ነው።
ዮሐ 3:36, 2ጴጥ 1:3-11
- በአጠቃላይ ሕይወታችን ጥንካሬ የሚሆነው በእምነት ብቻ ነው።
መሳ 16:15-22,ዕባ 2:4, 1ቆሮ 1:30-31
ከሰዓት
መዝሙር :- በእግዚአብሔር ተመርጠን : በክርስቶስ ስለተደረገልን አዜምን
የመጀመሪያ ክፍለጊዜ :- ጌዲዮን አግዘው
በክርስቶስ ብቻ :- ከአዲሱ ኪዳን ተስፋ አንጻር
ዕብ 10:19-25
- በእግዚአብሔር ፊት የምቆምበት መሠረት ምንድር ነው ? ከቆሞኩስ የምፀናው በምንድርነው ?
- በክርስቶስ ብቻ ነው!!!
ኤር 31:31 , 31:14
* እውነተኛ ካህን, ንጉሥ የአዲሱ ኪዳን ተስፋ ነው።
- ይህ የተሟላው በክርስቶስ ብቻ ነው!!
* ዕብ 10:22
- የአዲሱ ኪዳን ተስፋ ፍጻሜ በኃይልና በሥልጣን በክርስቶስ ተፈጽሟል። ስለዚህ ክርስቶስ ብቻ በቂ ነው።
መዝሙር :- እግዚአብሔር ስለገለጠልን ፍቅር አመሰገንን ደስ ተሰኘን
ሁለተኛው ክፍለጊዜ :- ጌዲዮን አግዘው
በክርስቶስ ብቻ :- ከሰው ልጅ የመፈጠር ዓላማ አንጻር
መዝ 8
* ኃጢአት የሰው ልጅን ከሰውነት አጉድሏል
መዝ 106:20
* ክርስቶስ ወደ ቀደመው ማንነት መልሷል። ስለዚህ ክርስቶስ ብቻውን በቂ ነው።
ጌዲና ሳይመን ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ!!
መርሃ ግብሩ ነገም የሚቀጥል ይሆናል።
ቦታ :- ጦና ህንጻ, ሲቲ ሆል
ሰዓት :- 3:00
ሁላችንም በቦታው በመገኘት ይህን አስደናቂ እውነት : ከቤተክርስትያን አበው ጋር በአንድነት እናውጅ! !
29/01/2013 ዓ.ም
ወላይታ ሶዶ