27/07/2026
በቤተክርስቲያናችን ለ11ኛ ዙር የሚከበረው ወጣቶች ሳምንት በብዙ መከናወን፤ እግዚአብሔር ጉልበታችን ሆኖ በድል ተጠናቀቀ
ሀ/አ/ቃ/ሕ/ቤ/ያን፣ ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም
የ2018 ወጣቶች ሳምንት "...ታገኙ ዘንድ ሩጡ " በሚል መሪ ቃል ለ11ኛ ዙር ከሐምሌ 13 እስከ 19 ድርስ ሲካሄድ የነበረው፤ ልዩ የወጣቶች ሳምንት በእግዚአብሔር እርዳታ በብዙ መከናወን በሰላም ተጠናቋል።
ልዩ የወጣቶች ሳምንት ማጠቃለያ መድረክ በሁለት ክፍለ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን፤ በመደበኛው አምልኮ ሙሉ የቤተክርስቲያኗ ጉባኤ በተገኙበት ከቤተክርስቲያናችን አምልኮ ሕብረትና ከዘማሪ ማርቆስ ጋር ጌታን በዝማሬ በማወደስ፤ እንዲሁም ከፓ/ር ዮሴፍ በቀለ ጋር በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ውድ የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል እጅግ ደስ በሚል መንገድ ተከፋፍለናል።
➬ የተከፋፈልነው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ምሳሌ 31v10-31
➬ የተካፈልነው ሃሳብ ፦ ልባም ሰው ተፈልገዋል
እግዚአብሔርን መፍራት በምን ተገለጠ?
#1ኛ በመሰጠት (ቁ_12)
#2ኛ በመስጠት (ቁ_20
#3ኛ የሀኬት እንጀራ አትበላም (ቁ_27)
#4ኛ አፏን በጥበብ ትከፍታለች (ቁ_26)
#5ኛ ስራ ወዳድና ታታሪ (ቁ_19)
ከዚህች ሴት ምን እንማራለን?
#1ኛ ትጋት (ቁ-19)
#2ኛ ጥሩ መሪነት (ቁ_15)
#3ኛ ቁርጠኝነት (ቁ_17)
#4ኛ ሥራውን ትገመግማለች (ቁ_18፤27)
የመጡ ውጤቶች
።።።።።።።።።።።።።
✅ዋጋችን እጅግ ውድ መሆን (ቁ_10)
✅ ሰው የሚታመንበት ሰው መሆን
✅ የሚተርፍ መሆን (ቁ_14)
✅ ብርቱና የተከበረ መሆን
✅ በልጆች የሚመሰገን ሰው መሆን
✅ በትዳር አጋር የሚመሰገን መሆን
ከሰዓት በነበረን ማጠቃለያ ፕሮግራም ከዘማሪ ማርቆስ እና ከቤተክርስቲያናችን አምልኮ ህብረት ጋር ጌታን ከፋ ከፍ በማድረግ ድንቅ ጊዜ አሳልፈናል።
እንዲሁም ከፓ/ር ዮሴፍ በቀለ ጋር እንዲህ በሚል ዕርስ፦ በጸሎት፣ በቃሉና በመንፈስ ቅዱስ ሙላት የተለወጠ ህይወትና አገልግሎት።
ክፍል ሁለትን በመቀጠል... ስለ ጸሎት ምንነትና አንድ ክርስቲያን ጸሎትን እንዴት መጸለይ እንዳለበትና የእግዚአብሔር ቃል በምን መንገድ ማጥናት እንዳለበት ለወጣቱ አቅጣጫ በማሳየት።
የማይጸልይ ክርስቲያን ሕይወት ምን እደሚመስል በማስገንዘብ ለወጣቱ ጥልቅ መልዕክት በማስተላለፍ ተጠናቋል።
በዚህ ማጠቃለያ መድረክ ላይ ተገኝቶ በሁሉ የረዳን እግዚአብሔርን በማመስገን፤ በተለያዬ መንገድ ሳምንቱን ሙሉ ያገለገሉ አገልጋዮችን፣ ወጣቶችን እና በየእለቱ እየመጡ የእግዚአብሔር ቃል የተማሩ ወጣቶችንና የቤተክርስቲያን ምዕመናን በሙሉ የቤተክርስቲያናችን ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አስራት ሎሃ አመስግነዋል።
በሌላ በኩል በተለያዬ መንገድ በወጣቶች ሳምንት ላገለገሉ አገልጋዮች ልዩ ስጦታ የተሰጠ ሲሆን፤ በወጣቶች ሳምንት ፕሮግራሙ እንዲሳካ የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጉ ወጣቶች የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰቷቸዋል።
እንዲሁም በ2018 የወጣቶች ሳምንት "ስፖርት ለወንጌል ዓላማ" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የመረብ ኳስ ጫወታ ሻንፒዮን ለሆነው ቤቴል ዞን የዋንጫ እርክብክብም በድምቀት ተካሂዷል።
በዕለቱ ያገለገላችሁ በሙሉ እግዚአብሔር ይባርካችሁ!
ይህን ድንቅ ጊዜ የሰጠን የእግዚአብሔር ስም ይባረክ።
📲በተለያዬ Social ሚዲያ አማራጮች የወጣቶች ሳምንት ፕሮግራም ስትከታታተሉ የነበራችሁ ቅዱሳን በሙሉ እግዚአብሔር ይባርካችሁ።
✍️️በወጣት፡ ብሩክ ሰይፉ
📲የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን ስለሚከታተሉ ከልብ እናመሰግናለን‼️