ቡኢ ገነት ቤ/ክ Genet Church

ቡኢ ገነት ቤ/ክ Genet Church “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ?

እግዚአብሔር ይመስገን ጌታ ድንቅ ጊዜ አድርጎልናል 🔥🔥🔥
22/06/2026

እግዚአብሔር ይመስገን ጌታ ድንቅ ጊዜ አድርጎልናል 🔥🔥🔥

ዛሬ ይጀምራል ሁላቹም ተጋብዛችኋል 🔥🔥🔥
19/06/2026

ዛሬ ይጀምራል ሁላቹም ተጋብዛችኋል 🔥🔥🔥

2 ቀን ቀረው
17/06/2026

2 ቀን ቀረው

“ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።”  — ኢሳይያስ 1፥18        ውድ የእግዚአብሔር...
15/06/2026

“ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።”
— ኢሳይያስ 1፥18
ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች
ከቀን 12/10--14/10/2018ዓ.ም. ድረስ በቡኢ ገነት ቤተክርስቲያንና በቤተክርስቲያኒቷ ሐ(c) መዘምራን ታለቅ የመነቃቂዬ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል በእነዚህ ሶስት ቀናት የእግዚአብሔር ቃል በኃይል ይሰበካል፣ ለህመምተኞች ይጸለያል፣ በአጋንት እስራት ስር ላሉት ነጻ መውጣት ይሆናል
ስለዚህ፦ አርብ ከሰዓት ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ
ቅዳሜ ከሰአት ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ
እሁድ ጥዋት ከ3--7 እና ከ9--12 ሰዓት ሙሉ ቀን
አይቀርም

ኢቲ 208 ቡኢ ገነት ቤተክርስቲያን ህፃናት  ልማት ፕሮጀክት በስሩ ለሚገኙ ቤተሰቦች የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ።ግንቦት 26 -2018 ዓ.ም """""""""" ቡኢ""""""""""" በምስራቅ ...
03/06/2026

ኢቲ 208 ቡኢ ገነት ቤተክርስቲያን ህፃናት ልማት ፕሮጀክት በስሩ ለሚገኙ ቤተሰቦች የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ።

ግንቦት 26 -2018 ዓ.ም
"""""""""" ቡኢ"""""""""""

በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡኢ ከተማ አስተዳደር ኢቲ 208 ቡኢ ገነት ቤተክርስቲያን ህፃናት ልማት ፕሮጀክት በስሩ ላቀፋቸው ለ216 ቤተሰቦች የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ።

በድጋፍ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የቡኢ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ስመኝ ሻንቆ ፕሮጀክቱ በተለያየ ጊዜ በስሩ ላቀፋቸው ቤተሰቦችና ህፃናት እንዲሁም ነብሰጡርና ወላድ እናቶችን በልዩ ሁኔታ ድጋፋ እያደረገ እንደመጣ ተናግረው ድጋፉ በተይም በኢኮኖሚ አቅማቸው አነስተኛ የሆኑ ቤተሰቦች የተሻለ አቅም ኖሯቸው ቤተሰብ መምራት እንዲችሉ ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል ።

አክለውም በተለይ ህፃናትና ነብሰጡር እናቶች እንዲሁም ወላድ እናቶች የተሻለ ጤንነት የተሰተካከለ አስተዳደግ ኖሯቸው ጤናማ የሀገር ተረካቢ ዜጎችን ማፍራት እንዲችሉ የፕሮጀክቱ ድጋፍ ሚናው የላቀ መሆኑን ገልፀዋል።

የኢቲ 208 ቡኢ ገነት ቤተክርስቲያን ህፃናት ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት አቶ መሀመድ ዋርጋ ፕሮጀክቱ በተለያየ ጊዜ ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ተናግረው በዛሬው እለትም 1 ሚሊየን 97 ሺ 335 ቡር ወጪ በማድረግ የልብስ ፣ የቅባት የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች የእህል እንዲሁም ለሰርቫይቫል እናቶች የሚሆኑ የሩዝ ፣የፓስታ ፣መኮሮኒ፣ የዘይትና የተለያዩ ድጋፎችን 216 ቤተሰቦች ድጋፍ ማድረጉን ገልፀዋል ።

አስተባባሪው እንደሁልጊዜው ሁሉ ፕሮጀክቱ በቀጣይም ከከተማው መንግስት ጋር በጋር በመሆን ሰፊ ስራዎችን እየሰራ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የቡኢ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ስመኝ ሻንቆ ፣የቡኢ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መኮንን ወልደገብርኤል ፣የኢቲ 208 ቡኢ ገነት ቤተክርስቲያን ህፃናት ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ መሀመድ ዋርጋ እንዲሁም ፕሮጀክቱ ሰራቶኞችና ሌሎችም ተገኝተዋል።

ዘገባው ምንጭ የቡኢ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን የሴቶች አገልግሎት የመጋቢት ወር አመታዊ የምስጋና ፕሮግራም በግንቦት 20/2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል፡፡ የፕሮግራሙ ዋና ይዘት የጸሎት እና የዝማሬ...
31/05/2026

የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን የሴቶች አገልግሎት የመጋቢት ወር አመታዊ የምስጋና ፕሮግራም በግንቦት 20/2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል፡፡ የፕሮግራሙ ዋና ይዘት የጸሎት እና የዝማሬ እንዲሁም የኢገቤ ፕረዚዳንት እና የኢገቤ ምክትል ፕረዚዳንት እንዲሁም ከተቋማት እና ከመምሪያ ኃላፊዎች ጋር የሴቶችን አገልግሎት በተመለከተ የተደረገ ጥልቅ ውይይትን ያካተተ ነበር፡፡ ይህ የምስጋና እና የውይይት ፕሮግራም በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ የሴቶችን የአገልግሎት እና የአመራር ሚና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ መነቃቃትን የፈጠረ ነበር፡፡

እግዚአነብሔር የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያንን እና ቅዱሳንን ሁሉ ይባርክ!

20/05/2026
04/02/2026

በኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን የጥር ወርን የሚሽን ወር በማለት የሰየመች ሲሆን በዚህ ወር በብሔራዊ ደረጃ ሚሽንን በተመለከተ ግንዛቤ የሚፈጠርበት፣ የተለያዩ ትምህርቶች እና ስልጠና...

ውድ  ቤተሰቦቻችን እንደ ሚታወቀው ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚሆን ሚክሰር/ ማይክ/ እንዲሁም ኪቦርድ ለመግዛት የተጀመረ ቻሌንጅ እንዳለ ይታወቃል በእናንተ ብረታት ለጌታ ቤት ባላቹ ቅንሀት...
18/12/2025

ውድ ቤተሰቦቻችን እንደ ሚታወቀው ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚሆን ሚክሰር/ ማይክ/ እንዲሁም ኪቦርድ ለመግዛት የተጀመረ ቻሌንጅ እንዳለ ይታወቃል በእናንተ ብረታት ለጌታ ቤት
ባላቹ ቅንሀት ሚክሰር እና ማይክ ማሳካት ችለናል በእናንተ እግዛ ጌታ ይባረካቹ🙏 ማለት እንፈልጋለን አሁንም ትልቁ ስራ ይቀጥላል ኪቦርድ የመግዛት ቻሌንጅ እንቀጥላለን እስካሁን ያልተሳተፍቹ እንድትሳተፍ እየተሳተፍቹ ያላቹ ደግሞ አሁንም ከቤተክርስቲያን ጎን እንድትቆሙ በጌታ ፍቅር🥰 እንጠይቃለን ጌታ ዘመናቹን ይባረክ 🙏

ኪቦርድ እንገዛለን 🎹

1000711687417
Muluken and Solomon and kufa sisay

በቡኢ ገነት ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኘው  ኢቲ 208 ፕሮጀክት ለታቃፊ ህፃናትና ቤተሰቦች  ከ7 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት የእህል እና የአልባሳት  ድጋፍ አደረገ።ታህሳስ 8/2018 ዓ....
17/12/2025

በቡኢ ገነት ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኘው ኢቲ 208 ፕሮጀክት ለታቃፊ ህፃናትና ቤተሰቦች ከ7 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት የእህል እና የአልባሳት ድጋፍ አደረገ።

ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም

በቡኢ ገነት ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኘው ኢቲ 208 ፕሮጀክት 2 መቶ 20 ለሚሆኑ የታቃፊ ህፃናት ከ7 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት የእህል፣የልብስ ፣የዘይት ፣የሳሙና እና የቅባት ድጋፍ አደረገ።

በድጋፉ ወቅት የተገኙት የቡኢ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ በቀለ ፕሮጀክቱ ለረጅም ጊዜ አቅም የለሌላቸው ህፃናትና ቤተሰቦች እና ለእርጉዝ እናቶች በብዙ መልኩ እየደገፈ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለትም መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ ያደረገው የእህልና የህፃናት አልባሳት ድጋፍ ለተደረገላቸው ቤተሰቦች ጭንቀት የሚቀንስ ትልቅ ድጋፍ እንደሆነ አንስተዋል።

ድጋፉ ለእርጉዝ ሆነ ወላድ እናቶች እና ህፃናት ሥርዓተ ምግብን ለማስተካከል ተጨማሪ ዕድልና አቅም የሚሰጥ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ለዚህም ድጋፍ በተደረገላቸው ህፃናትና በከተማው አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር የሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ስመኝ ሻንቆ በበኩላቸው የአቅም ውስንነት ላለባቸው እና እርጉዝ እናቶች ጋር በተያያዘ በተለያዩ መስኮች በጋራ ተቀናጅተው የሚሰሩ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ፕሮጀክቱ በርካታ ህፃናትን ከስሩ አቅፎ በተለያየ መልኩ እየደገፈ እንደሚገኝ ገልፀው ከህፃናቱ በተጨማሪ ለእርጉዝ እናቶችም የተለያየ ድጋፍ ሲያደርግ እንደቆየ ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለትም መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ ለህፃናቱና ለቤተሰቦቻቸው ያደረገው የእህልና የአልባሳት ድጋፍ እጅግ የሚያስደስት እንደሆነ ጠቁመዋል።

ፕሮጀክቱ እያደረገ ለሚገኘው ድጋፍ በተቋማቸው ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የሆኑት አቶ መሀመድ ዋርጋ የቡኢ ገነት ቤተ ክርስቲያን በትምህርት፣በጤና፣በኢኮኖሚያዊ እና በሌሎች ማህበራዊ ዘርፎች የሚሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለትም መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ በፕሮጀክቱ ለታቀፉ 2 መቶ 20 ለሚሆኑ ህፃናት የእህል፣የዘይት ፣ልብስ፣የሳሙና እና የቅባት ድጋፍ ማድረጉን ገልፀዋል።

በዛሬው ዕለትም የተደረገው ድጋፍ ፕሮጀክቱ በማህበራዊ ዘርፍ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ እንደሆነ ተናግረዋል።

በዚህ ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን በአጠቃላይ ከ 7 መቶ 50 ሺህ በላይ የሚገመት እንደሆነ አመላክተዋል።

ፕሮጀክቱ ስራዎቹን ሲሰራ ከመንግስት ጋር ተቀናጅቶ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን መንግስት ለሚያደርግላቸው አስፈላጊውን ትብብር በድርጅቱ ስም አመስግነዋል።

በመጨረሻም ለህፃናቱና ለቤተሰቦቻቸው እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክቶቻቸው አቅርበዋል።

የዘገባው ምንጭ የቡኢ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት

Address

Ho
S**o
00

Telephone

+251975757528

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቡኢ ገነት ቤ/ክ Genet Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share