16/05/2026
ቃል ጸሎት
እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤
በክንፎችህም ጥላ ሰውረኝ፤
መዝሙር 17፥8
አቤቱ ጠብቀኝ ! ትድግናህ የሚያሻኝ ድኩም ፣ ጠብቆትህ የሚያስፈልገኝ ፣ ለአውሬ ለሌባ ተጋላጫ የሆንኹ በግ ፣ ከለላህ የሚያኖረኝ ልል ፣ ማዳናህ ሚፈውሰኝ ሕማም ፣ እጅህ የሚመራኝ ተጓዝ ፣ ቃልህ የሚያጸናኝ ወላዋይ ነኝና እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቀኝ ።
የዐይንን ብሌን ከራስ በታች ከሌላው የሰውነት ክፍል ሁሉ ከፍ አድርገህ ፥ በማበጀት ከብዙ ጥፋት እንዲጠበቅ እንዳደረግህ ፤ ከዚህ ዓለም ክፋት እና ነውር በላይ በጽድቅህ ከፍታ እግሮቼን እንድታጸና እማጸንሃለሁ ። የዐይንን ብሌን በተከለለ ሥፍራ እንዳኖርከው አቤቱ ባርያህንም በእቅፍህ እንድታኖረኝ አሻለሁ ።
ንስር ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሰውራ ከውጩ ብርድ ሙቀትን እንደምትቸር ፣ ከፀሓዩም ከልላ ጥላ እንድምትሆነው ፣ ከዝናብ ከውርጭ ሸሽጋ በጉያዋ እንደምታሳርፍ አቤቱ ልጅህ ነኝና ከዚህ ዓለም ዐመጽ እና ነውር እንዲሁም ክፋት ሁሉ በክንፎችህ ሰውረኝ ።
አምላክ ሆይ፤ ስለምትመልስልኝ ስምህን በመጥራት ልመናዬን አቅርቤያለሁና ስማኝ ። በእረኝነትህ እስከፍጻሜው አኑረኝ ፣ ለዘላለሙ አሜን !!
✍️ጌታሁን አያኖ