Woyde Chalbe Kale Heywet Church/በኮይሻ አጥቢያዎች ሕብረት የወይዴ ጫልቤ አ/ቃ/ሕ/ቤ/ያን

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • Woyde Chalbe Kale Heywet Church/በኮይሻ አጥቢያዎች ሕብረት የወይዴ ጫልቤ አ/ቃ/ሕ/ቤ/ያን

Woyde Chalbe Kale Heywet Church/በኮይሻ አጥቢያዎች ሕብረት የወይዴ ጫልቤ አ/ቃ/ሕ/ቤ/ያን This is Official page Of Woyde Chalbe Kale Hiwot Local Church.

12/02/2026
01/12/2025

ሐዋርያት 26
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አግሪጳም ጳውሎስን፦ ስለ ራስህ ትናገር ዘንድ ተፈቅዶልሃል አለው። በዚያን ጊዜ ጳውሎስ እጁን ዘርግቶ መለሰ እንዲህ ሲል፦
²-³ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፥ የአይሁድን ሥርዓት ክርክርንም ሁሉ አጥብቀህ አውቀሃልና በአይሁድ በተከሰስሁበት ነገር ሁሉ ዛሬ በፊትህ ስለምመልስ ራሴን እጅግ እንደ ተመረቀ አድርጌ እቈጥረዋለሁ፤ ስለዚህ በትዕግሥት ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።
⁴ ከመጀመሪያ አንሥቶ በሕዝቤ መካከል በኢየሩሳሌም የሆነውን፥ ከታናሽነቴ ጀምሬ የኖርሁትን ኑሮዬን አይሁድ ሁሉ ያውቃሉ፤
⁵ ሊመሰክሩ ይወዱ እንደ ሆነ፥ በአምልኮአችን ከሁሉ ይልቅ ሕግን በመጠንቀቅ እንደሚተጋ ወገን ፈሪሳዊ ሆኜ እንደኖርሁ ከጥንት ጀምረው አውቀውኛልና።
⁶ አሁንም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአባቶቻችን ስለ ተሰጠው ስለ ተስፋ ቃል አለኝታ ልፋረድ ቆሜአለሁ።
⁷ ወደዚህም ወደ ተስፋ ቃል አሥራ ሁለቱ ወገኖቻችን ሌሊትና ቀን በትጋት እያመለኩ ይደርሱ ዘንድ አለኝታ አላቸው፤ ስለዚህም አለኝታ፥ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፥ ከአይሁድ እከሰሳለሁ።
⁸ እግዚአብሔር ሙታንን የሚያስነሣ እንደ ሆነ ስለ ምን በእናንተ ዘንድ የማይታመን ነገር ሆኖ ይቈጠራል?
⁹ እኔም ራሴ የናዝሬቱን የኢየሱስን ስም የሚቃወም እጅግ ነገር አደርግ ዘንድ እንዲገባኝ ይመስለኝ ነበር።
¹⁰ ይህንም ደግሞ በኢየሩሳሌም አደረግሁት፤ ከካህናት አለቆችም ሥልጣን ተቀብዬ እኔ ከቅዱሳን ብዙዎችን በወኅኒ አሳሰርኋቸው፥ ሲገድሉአቸውም አብሬ ተቸሁ።
¹¹ በምኵራብም ሁሉ ብዙ ጊዜ እየቀጣሁ ይሰድቡት ዘንድ ግድ አልኋቸው፤ ያለ ልክ ስቈጣባቸውም እስከ ውጭ አገር ከተማዎች ድረስ እንኳ አሳድድ ነበር።
¹² ስለዚህም ነገ ከካህናት አለቆች ሥልጣንና ትእዛዝ ተቀብዬ ወደ ደማስቆ ስሄድ፥
¹³ ንጉሥ ሆይ፥ በመንገድ ሳለሁ እኩል ቀን ሲሆን በዙሪያዬና ከእኔ ጋር በሄዱት ዙሪያ ከፀሐይ ብሩህነት የበለጠ ብርሃን ከሰማይ ሲበራ አየሁ፤
¹⁴ ሁላችንም በምድር ላይ በወደቅን ጊዜ፦ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል የሚል ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገረኝ ሰማሁ።
¹⁵ እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ ማንነህ? አልሁ። እርሱም አለኝ፦ አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ።
¹⁶ ነገር ግን ተነሣና በእግርህ ቁም፤ ስለዚህ እኔን ባየህበት ነገር ለአንተም በምታይበት ነገር አገልጋይና ምስክር ትሆን ዘንድ ልሾምህ ታይቼልሃለሁና።
¹⁷-¹⁸ የኃጢአትንም ስርየት በእኔም በማመን በተቀደሱት መካከል ርስትን ያገኙ ዘንድ፥ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሰይጣንም ሥልጣን ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዲሉ ዓይናቸውን ትከፍት ዘንድ፥ ከሕዝቡና ወደ እነርሱ ከምልክህ ከአሕዛብ አድንሃለሁ።
¹⁹ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፥ ስለዚህ ከሰማይ የታየኝን ራእይ እምቢ አላልሁም።
²⁰ ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ላሉት በኢየሩሳሌምም በይሁዳም አገር ሁሉ ለአሕዛብም ንስሐ ይገቡ ዘንድና ለንስሐ የሚገባ ነገር እያደረጉ ወደ እግዚአብሔር ዘወር ይሉ ዘንድ ተናገርሁ።
²¹ ስለዚህ አይሁድ በመቅደስ ያዙኝ ሊገድሉኝም ሞከሩ።
²²-²³ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ረድኤት ተቀብዬ ለታናሹም ለታላቁም ስመሰክር እስከዚች ቀን ድረስ ቆሜአለሁ፤ ነቢያትና ሙሴ ይሆን ዘንድ ያለውን፥ ክርስቶስ መከራን እንዲቀበል በሙታንም ትንሣኤ ለሕዝብና ለአሕዛብ ብርሃንን በመጀመሪያ ሊሰብክ እንዳለው፥ ከተናገሩት በቀር አንድ ስንኳ የተናገርሁት የለም።
²⁴ እንዲህም ብሎ ስለ ራሱ ሲመልስ ፊስጦስ በታላቅ ድምፅ፦ ጳውሎስ ሆይ፥ አብድሃል እኮ፤ ብዙ ትምህርትህ ወደ እብደት ያዞርሃል አለው።
²⁵ ጳውሎስ ግን እንዲህ አለ፦ ክቡር ፊስጦስ ሆይ፥ የእውነትንና የአእምሮን ነገር እናገራለሁ እንጂ እብደትስ የለብኝም።
²⁶ በእርሱ ፊት ደግሞ በግልጥ የምናገረው ንጉሥ ይህን ነገር ያውቃል፤ ከዚህ ነገር አንዳች እንዳይሰወርበት ተረድቼአለሁና፤ ይህ በስውር የተደረገ አይደለምና።
²⁷ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፥ ነቢያትን ታምናለህን? እንድታምናቸው አውቃለሁ።
²⁸ አግሪጳም ጳውሎስን፦ በጥቂት ክርስቲያን ልታደርገኝ ትወዳለህ አለው።
²⁹ ጳውሎስም፦ በጥቂት ቢሆን ወይም በብዙ አንተ ብቻ አይደለህም ነገር ግን ዛሬ የሚሰሙኝ ሁሉ ደግሞ ከዚህ እስራቴ በቀር እንደ እኔ ይሆኑ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እለምናለሁ አለው።
³⁰ ንጉሡም አገረ ገዡም በርኒቄም ከእነርሱም ጋር ተቀምጠው የነበሩት ተነሡ፥
³¹ ፈቀቅ ብለውም እርስ በርሳቸው፦ ይህ ሰው እንኳንስ ለሞት ለእስራትም የሚገባ ምንም አላደረገ ብለው ተነጋገሩ።
³² አግሪጳም ፈስጦስን፦ ይህ ሰው እኮ ወደ ቄሣር ይግባኝ ባይል ይፈታ ዘንድ ይቻል ነበር አለው።

ኢሳይያስ 52¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¹¹ እናንተ የእግዚአብሔር ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፥ እልፍ በሉ፥ ከዚያ ውጡ፥ ርኩስን ነገር አትንኩ፥ ከመካከልዋ ውጡ፥ ንጽሐን ሁኑ።¹² እግዚአብሔር ይቀ...
11/09/2024

ኢሳይያስ 52
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ እናንተ የእግዚአብሔር ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፥ እልፍ በሉ፥ ከዚያ ውጡ፥ ርኩስን ነገር አትንኩ፥ ከመካከልዋ ውጡ፥ ንጽሐን ሁኑ።
¹² እግዚአብሔር ይቀድማችኋልና፥ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና በችኰላ አትወጡም በመኰብለልም አትሄዱም።

ኩሪፍቱ ቃለ ህይወት ይዞታ ላይ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር እየተፈጸመ ስላለው ይዞታ ዝርፊያ ዝም አንልም!
22/07/2024

ኩሪፍቱ ቃለ ህይወት ይዞታ ላይ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር እየተፈጸመ ስላለው ይዞታ ዝርፊያ ዝም አንልም!

17/07/2024
31/01/2024
የጉኑኖ ከተማ እናት ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን   በአጥቢያችን ለተከታታይ ሦስት ቀናት ባደረጉት ወንጌል ስርጭትና የምስጋና ኮንፌራንስ በርካታ ነፍሳት ወደ ጌታ መጥቷል። ክብር ለወደደን ከኃ...
15/03/2021

የጉኑኖ ከተማ እናት ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በአጥቢያችን ለተከታታይ ሦስት ቀናት ባደረጉት ወንጌል ስርጭትና የምስጋና ኮንፌራንስ በርካታ ነፍሳት ወደ ጌታ መጥቷል። ክብር ለወደደን ከኃጢአታችን በደሙ ላጠበን ለመድኃኒታችንና ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን ። አሜን!!

CONGRATULATIONS!!.........ሌላ በረከትና ክብር!!(ዘፍጥረት ምዕ. 49)22፤ ዮሴፍ ትንሹ የፍሬ ዛፍ ነው፥ በምንጭ አጠገብ የሚያፈራ የፍሬ ዛፍ፤ አረጎቹ በቅጥር ላይ ያድጋሉ። ...
03/03/2021

CONGRATULATIONS!!.........ሌላ በረከትና ክብር!!
(ዘፍጥረት ምዕ. 49)
22፤ ዮሴፍ ትንሹ የፍሬ ዛፍ ነው፥ በምንጭ አጠገብ የሚያፈራ የፍሬ ዛፍ፤ አረጎቹ በቅጥር ላይ ያድጋሉ። 23፤ ቀስተኞች አስቸገሩት፥ ነደፉትም፥ ተቃወሙትም፤ 24፤ ነገር ግን ቀስቱ እንደ ጸና ቀረ፤ የእጆቹም ክንድ በያዕቆብ አምላክ እጅ በረታ፥ በዚያው በጠባቂው በእስራኤል ዓምድ፥.....

21/02/2021

(መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 5: 12-15)
የደማስቆ ወንዞች አባናና ፋርፋ ከእስራኤል ውኆች ሁሉ አይሻሉምን? በእነርሱስ ውስጥ መታጠብና መንጻት አይቻለኝም ኖሮአልን? ዘወርም ብሎ ተቈጥቶ ሄደ። ባሪያዎቹም ቀርበው አባት ሆይ፥ ነቢዩ ታላቅ ነገርስ እንኳ ቢነግርህ ኖሮ ባደረግኸው ነበር፤ ይልቁንስ። ታጠብና ንጹሕ ሁን ቢልህ እንዴት ነዋ! ብለው ተናገሩት። ወረደም፣ የእግዚአብሔርም ሰው እንደ ተናገረው በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ፤ ሥጋውም እንደ ገና እንደ ትንሽ ብላቴና ሥጋ ሆኖ ተመለሰ፥ ንጹሕም ሆነ። እርሱም ከጭፍራው ሁሉ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመለሰ፥ ወጥቶም በፊቱ ቆመና። እነሆ፥ ከእስራኤል ዘንድ በቀር በምድር ሁሉ አምላክ እንደሌለ አወቅሁ።

በጸሎት የተከፈተ በር!
17/02/2021

በጸሎት የተከፈተ በር!

27/09/2020

የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 28)
----------
18፤ ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።

19-20፤ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።

Address

ወላይታ ባይራ ኮይሻ
S**o

Telephone

+251916568699

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Woyde Chalbe Kale Heywet Church/በኮይሻ አጥቢያዎች ሕብረት የወይዴ ጫልቤ አ/ቃ/ሕ/ቤ/ያን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share