Tebela Heywot Kal Church youth minstry

Tebela Heywot Kal Church youth minstry Only spiritual posts

17/05/2025
 dani
04/05/2025

dani

ቅዱሳን እንደምን ቆያችሁ? ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ከእግዚአብሔር እና ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ሆነን የቤተክርስቲያናችን የአምልኮ...
18/12/2024

ቅዱሳን እንደምን ቆያችሁ?
ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

ከእግዚአብሔር እና ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ሆነን የቤተክርስቲያናችን የአምልኮ አዳራሽ ለመገንባት ህዳር 22/2017 ዓ/ም የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በድምቀት የመሠረተ ድንጋይ እንዳስቀመጥን ይታወቃል። ከተገኙ እንግዶች በጥቂቱ፦
1. ፓስተር አስፋው ጡሜቦ: የኢትዮጵያ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ዘርፍ ኃላፊ፣
2. ፓስተር አክሊሉ ሳሙኤል: የኢትዮጵያ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ ዘርፍ ኃላፊ፣
3. ዕጩ ዶ/ር ታረቀኝ ገቸሬ: የጠበላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ፣
4. አቶ ተገኝ ታደመ: የሁምቦ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ እና በዕለቱ የዋና አስተዳዳሪ ተወካይ፣
5. አቶ አሸብር ዘካሪያስ: የጠበላ ከተማ አስተዳደር የፖለቲካና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ።
6. ወ/ሮ ዘነበች ሀጅሶ: የጠበላ ከተማ አስተዳደር ዋና አፈጉባኤ፣
7. የጠበላ ከተማ መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተውካይ፣
8. የጠበላ ከተማ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን ተውካይ፣
9. አቶ ቶማስ ጃርሳ: በጠበላ ከተማ ብሎም በሁምቦ ወረዳ የልማት አርበኛ፣ እና ሌሎችንም ተጋባዥ እንግዶች በቤተክርስቲያናችን ስም ልባዊ ምስጋና እያቀረብን ለሥራው ስኬት የእግዚአብሔር ሕዝቦች እጃችሁን አሁንም እንድትዘረጉ እና የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ እንጋብዛችኋለን። እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካችሁ።

1. ንግድ ባንክ: 1000633505806
2. ብርሃን ባንክ: 1602780097370

የጌታ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን!!

“የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን !  ናህ 2V20የተወደዳችሁ  በጉጉት ስጠበቅ የነበረው መሰረት ድንጋይ  የማኖር ፕሮግራም ዛሬ አድርገናል። ክብር ሁሉ ለ...
01/12/2024

“የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን ! ናህ 2V20

የተወደዳችሁ በጉጉት ስጠበቅ የነበረው መሰረት ድንጋይ የማኖር ፕሮግራም ዛሬ አድርገናል። ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን። የድጋፍ እጃችሁን እንድትዘረጉ በዛዉም የበረከት ተካፋይ እንድትሆኑ አበረታታችኋለዉ😍 ብሩካን ናችሁ 😍
1. ንግድ ባንክ: 1000633505806
2. ብርሃን ባንክ: 1602780097370
ስልክ ቁጥር: 0915398542/0936454478

የጠበላ ከተማ የሕይወት ቃል አጥቢያ ቤተክርስቲያን የህንፃ ግንባታ ጥሪ❗️“የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤” ነህምያ 2፥20እነሆ ከእግዚአብሔር እና ከእግ...
27/11/2024

የጠበላ ከተማ የሕይወት ቃል አጥቢያ ቤተክርስቲያን የህንፃ ግንባታ ጥሪ❗️

“የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤” ነህምያ 2፥20

እነሆ ከእግዚአብሔር እና ከእግዚአብሔር ህዝብ ጋር ሆነን የጠበላ ከተማ የሕይወት ቃል አጥቢያ ቤተክርስቲያን የአምልኮ አዳራሽ ለመገንባት ተነስተናል።

እንደ እግዚአብሔር ቃል “ወደ ተራራው ውጡ፥ እንጨትንም አምጡ፥ ቤቱንም ሥሩ፤ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፥ እኔም እመሰገናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።” ሐጌ 1፥8 እግዚአብሔር ደስ እንዲሰኝ፣ እንዲመሰገን እና እንዲከበር ኑ አብረን እንጨቱን በማምጣት ቤቱን እንስራ።

ከዚህ በታች በተቀመጡት የባንክ አካውንቶች እግዚአብሔር በሰጣችሁ ገንዘብ እንድታገለግሉና እና የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በማለት ቤተክርስቲያኒቷ በክብር ትጋብዛለች።

ከዚህም በተጨማሪ የመሠረተ ድንጋይ የሚጣልበት ቀን ህዳር 22/2017 ዓ/ም ስለሆነ በጠበላ ከተማ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን ግቢ በእለቱ በሚደረገው ፕሮግራም ተካፋይ እንድትሆኑ ቤተክርስቲያኒቷ በክብር ትጠራችኋለች። የጌታ ጸጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን።

1. ንግድ ባንክ: 1000633505806
2. ብርሃን ባንክ: 1602780097370
ስልክ ቁጥር: 0915398542/0936454478

እጅግ የምንወድህ ፓስተር Aklilu Samuel እንኳን ደስ አለህ ዘመንህ ሁሉ ይባረክ
22/05/2024

እጅግ የምንወድህ ፓስተር Aklilu Samuel እንኳን ደስ አለህ ዘመንህ ሁሉ ይባረክ

እነሆ አደረሰ❗️"ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ" 1ኛ ቆሮ 9:23 *************************************በጉጉት የምንጠብቀውን የኢትዮጵያ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን 32...
12/02/2024

እነሆ አደረሰ❗️

"ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ" 1ኛ ቆሮ 9:23
*************************************
በጉጉት የምንጠብቀውን የኢትዮጵያ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን 32ኛ ዓመታዊ ኮንፈረንስ ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተዋል።

በቦዲቲ ከተማ ረቡዕ የካቲት 6 እስከ 9/2016 ዓ/ም በሚደረገው ታላቅ አመታዊ ኮንፈረንስ የማስጀመሪያ ቀን።
👉 ማለዳ ከ12:00 ጀምሮ የከተማ ፅዳት፣
👉 የሩጫ ውድድር፣
👉 ጸሎትና የወንጌል ስርጭት፣

በዚህ የመክፈቻ ስነ-ስረዓት ሁላችሁም በእግዚአብሔር ፍቅር ተጋብዛችኋል። እግዚአብሔር ድንቅና ተዓምራትን ያደርጋል። ነፍሳት ይድናሉ፤ ወንጌል በኃይል ይሰበካል።

#ከቦዲቲ
#ከሶዶ
#ከበዴሳ
#ከሻንቶ

#ከሁምቦ


!

ቲሸርት ለምትፈልጉ👕👕👕
📞 +251934819848
+251916470904

ኑ አብረን ወ/ሶዶ የሕይወት ቃል ቤ/ክ ጣርያ እናለብስ።Bank Acc: 1000158682471 CBEሶዶ ሕይወት ቃል ቤ/ክ ሕንፃ ግንባታ አካውንት
06/11/2023

ኑ አብረን ወ/ሶዶ የሕይወት ቃል ቤ/ክ ጣርያ እናለብስ።
Bank Acc: 1000158682471 CBE
ሶዶ ሕይወት ቃል ቤ/ክ ሕንፃ ግንባታ አካውንት

ነ ባይዳ ዳሳ❗"ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።" ማቴዎስ 25፥34ከላይ የተጠቀሰው የእግ...
12/10/2023

ነ ባይዳ ዳሳ❗

"ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።" ማቴዎስ 25፥34

ከላይ የተጠቀሰው የእግዚአብሔር ቃል እንደ ቃሉ ለኖሩ ክርስቲያኖች የተሰጠ የበረከት ቃል ነው። ይህን የፍርድ ቃል የሚሰሙት፣ በክርስቶስ መንገድ ተልዕኳቸውን እየፈፀሙ ያሉት ናቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም በሚገለጥበት ጊዜ የእርሱ የሆኑት ከእርሱ ጋር በክብር ይገለጣሉ። ጳውሎስ ለቆላስይስ ሰዎች፣ "ሞታችኋልና ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና፤ ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ" ይላል። ሃሌሉያ!

ወንጌልም ልንኖርበት የተሰጠን ህይወት ሆኖ ለእግዚአብሔር ክብር መልካም ስራ ሁሉ ሰርተን እንድናልፍ የተሰጠን ትዕዛዝ ነው። "መልካሙን ስራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን" ኤፌ 2፥10 ተብሎ እንደተፃፈ ወንጌልን የተቀበልነው ለመስራት ነው። ይህን ስራ የምንሰራው ደግሞ በነፃ የተነገረንን የምስራቹን ወንጌል በቃልም ሆነ በመዝሙር ለሰው ልጆች በማድረስ ነው።

የጥንት አባቶቻችንና ሐዋርያት ክርስቶስ ያስተማራቸው ቃል በህይወታቸው በመፈፀሙና ከመከራውም በመካፈላቸው ደስ ብሏቸው አልፈዋል። አሁን በእኛ ዘመንም ዋጋ እየከፈሉ ያሉ የእምነት አባቶች የሚመጣውን ክብር በማየት በእምነታቸው ፀንተዋል። ይሄ ለወንጌል የተከፈለ ያለ ዋጋ ነው። እሱም ትውልዱ በዙሪያው እንደ ደመና ያሉ ምስክሮችን በማየት የወንጌልን ችቦ በማቀጣጠል እንጂ ባለማጥፋት፣ የወንጌልን አደራ በሚገባ በመወጣት እንጂ ከውስጡ ባለማውጣት፣ ለብቻው ሳይሆን ወንጌልን ይዞ ወደ አለም እንዲሄድ ትልቅ መልዕክት ነው።

በሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን ዝማሬና የወንጌል አገልግሎት ጉዞ ትልቅ ዋጋ ከከፈሉ አባቶቻችን መካከል አንዱ የሆኑት ዘማሪ ፓስተር ዮናስ ጋትሶ ከ80 በላይ የወላይትኛና አልፎ አልፎም የአማርኛ መዝሙሮቹንም በመዘመር ይታወቃሉ። እኛም በያለንበት የአጥቢያ ቤተክርስቲያናት እና አካባቢዎች የምንዘምራቸው የወላይትኛና አማርኛ መዝሙሮች የዘማሪ ዮናስ ጋትሶ ዜማና ድርሰቶች ናቸው ሲባል በጣም እንገረማለን። ዛሬ ደግሞ "ነ ባይዳ ዳሳ" ይሉናል።

ወንጌልን በመስበክ፣ በመሪነት፣ ቤተክርስቲያንን በመትከል፣ መዝሙርን በመዘመር፣ በኳየር አግልግሎት፣ ለዘማሪያን ድርሰትና ዜማን በመስጠት ለረዥም ጊዜ በእግዚአብሔር መንግስት ስራ ውስጥ የተጉ አባታችን ዘማሪ ፓስተር ዮናስ ጋትሶ በውስጣቸው ከተቀመጡ ብዙ ዝማሬዎቹ መካከል ጥቂቶችን በቁጥር አንድ አልበማቸው በኩል እንካችሁ ይሉናል። እኛም ቅርብ ጊዜ የሚለቀቁ ዝማሬዎቹን ሰምተን እንደገና ለመባረክ እየተዘጋጀን ሌሎችም የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ በእግዚአብሔር ፍቅር እንጋብዛለን።

እናመሰግናለን ፓስተር🙏🙏

@followersuMuluken Yonas BoltanaoMuluken Yonas BoltanaoMuluken Yonas Boltana

እግዚአብሔር ኃይል ይሁንላችሁ።እንወዳችኋለን💜
16/09/2023

እግዚአብሔር ኃይል ይሁንላችሁ።
እንወዳችኋለን💜

Address

S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tebela Heywot Kal Church youth minstry posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share