04/01/2025
የአባቶች ወግ (ማር 7÷1-13)
ከዚህ ምንባብ ስለ አይሁድ ወግ ስናጠና የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ፈለገ የሚሽር ነበር፡፡በቃል ሲተላለፍ ከነበረዉ ብዙ የአባቶች ወግ መካከል አንዱ ኮርባን ብለዉ በዕብራይስጥኛ የሚጠሩት ነዉ፡፡ትርጉሙም ለእግዚአብሔር የተለየ ስጦታ ማለት ነዉ፡፡
ከልጁ እርዳታ የሚፈልገዉ ወላጅ ልጁን አግዘኝ ቢለዉ ወላጆቹን መጦር የማይፈልገዉ ልጅ የአባቶችን ወግ ምክንያት በማድረግ በሙሴ በኩል ለወላጆቻችሁ ታዘዙ የሚለዉን የእግዚአብሔርን ቃል ይተላለፋል፡፡በዚህም ምክንያት አንድ ልጅ በተፃፈዉ ህግ መሰረት ለወላጆቹ ማድረግ የሚገባዉን ግዴታ በመሸሽ በእጄ ያለዉ ንብረት ለእግዚአብሔር የተለየ ስጦታ ነዉ በማለት ዉጫዊ ስርአት ብቻ ይፈፅማል፡፡ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ወጋቸዉን በእግዚአብሔር ቃል ሲመዝነዉ ግብዝነት የሞላበት እንደሆነ መስክሯል፡፡
ዛሬም ቢሆን የቤተክርስቲያናችን ወግና ባህል በእግዚአብሔር ቃል ሲመረመር ከልብ በሆነ እዉነተኛ አምልኮ ላይ የተመሰረተ ሆኖ ካልተገኘና በሰዉ ስርአት ላይ ብቻ ከተንጠለጠለ የእግዚአብሔር ቃል የሚለዉን እንስማ፡፡‹‹ጌታም፦ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባልና፥ በከንፈርቹም ያከብረኛልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛልና›› (ኢሳ 29÷13)