Wolaita Sodo Mehal Ketema Kale Heywet Church

Wolaita Sodo Mehal Ketema Kale Heywet Church ሠላም ለእናንተ ይሁን !
ይህ ትክክለኛው የወላይታ ሶዶ መሀል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ገጽ ነው። ከእኛ ጋር ስለነበሩ እናመሰግናለን🥰

“አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ” በሚል መሪ ቃል በቤተክርስቲያናችን ለ8ኛ ዙር ከነሐሴ 3-10 ሲከበር የቆየው የልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት ማጠቃለያ ምስጋና እሁድ በአጥቢያዪቱ በመሀል ከተማ ተደ...
18/08/2026

“አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ” በሚል መሪ ቃል በቤተክርስቲያናችን ለ8ኛ ዙር ከነሐሴ 3-10 ሲከበር የቆየው የልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት ማጠቃለያ ምስጋና እሁድ በአጥቢያዪቱ በመሀል ከተማ ተደርጎል።
በኡሪም የWorship team
በህፃናት የኳየር አገልግሎት
የከበረውን የእግዚአብሔርን ቃል በወጣት አሸብር ዘርገነ
እና ሌሎች አስተማሪ እና አዝናኝ ፕሮግራሞችን በልጆች እና በመምህራን ተሰናድቶ የቀረበ ሲሆን በአመቱ ደግሞ በክፍላቸው አማካይ ውጤት ላመጡ የሰንበትና የክትትል ተማሪዎች ሽልማት ተሰጥቷል።

ለበለጠ መረጃ
⭕️Facebook : https://www.facebook.com/wsmkkc
⭕️Instagram : https://www.instagram.com/wsmkkc
⭕️website:https://wesite.to/wolaitasodoMKKC
⭕️Telegram:https://t.me/WSMKKC
⭕️Twitter : https://twitter.com/wsmkkc
⭕️Google+ : https://plus.google.com/wsmkkc

ቀን 6ከነሐሴ 3-10 ሲካሄድ የቆየው የልጆች ሳምንት በቀን 6 ቅዳሜ ስፖርትንም ለወንጌል በሚል በሜዳ በተካሄደው ፕሮገራም ለብዙዎች የኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት ተመስክሯል።እንዲሁም ሌሎች ...
17/08/2026

ቀን 6
ከነሐሴ 3-10 ሲካሄድ የቆየው የልጆች ሳምንት በቀን 6 ቅዳሜ ስፖርትንም ለወንጌል በሚል በሜዳ በተካሄደው ፕሮገራም ለብዙዎች የኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት ተመስክሯል።እንዲሁም ሌሎች ፕሮግራሞች በስፍራው ተካሄዷል።
በነበረው በኳስ ጨዋታ ለመጨረሻው ዙር የበቁ ቡድኖች የተጫወቱ ሲሆን ገሪዛን ዞን ሮሆቦት ዞንን ሲያሸንፍ መምህራንና ተተኪ መመህራን ባደረጉት ግጥሚያ ደግሞ መምህራን በሰፊ የጎል ልዩነት መርታት ችሏል።

16/08/2026

በመሐል ከተማ ቃ/ሕ/ቤ/ያን የሚከበረው 8ኛ ዙር የልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት
መዝጊያ ፕሮግራም ቀጥታ ስርጭት



Wolaita S**o Mehal Ketema Kale Heywet Church

� New to streaming or looking to level up? Check out StreamYard and get $10 discount! �

13/08/2026

DAY #3
የወንጌል ስርጭት ቀን
2018 የልጆች ወንጌል ፌስቲቫል በመሀል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን

DAY  #3የወንጌል ስርጭት ቀን2018 የልጆች ወንጌል ፌስቲቫል በመሀል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን
13/08/2026

DAY #3
የወንጌል ስርጭት ቀን
2018 የልጆች ወንጌል ፌስቲቫል በመሀል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን

DAY  #2የፍቅር ቀን2018 የልጆች ወንጌል ፌስቲቫል በመሀል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን
12/08/2026

DAY #2
የፍቅር ቀን
2018 የልጆች ወንጌል ፌስቲቫል በመሀል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን

12/08/2026

#የመስቀል በዓል አከባበር:-
1. ታሪካዊ መነሻ እና የታሪኩ ተዓማኒነት
* የንግሥት እሌኒ ታሪክ: በታሪካዊ ሰነዶች (እንደ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች ዘገባ) ንግሥት እሌኒ (የቆስጠንጢኖስ እናት) በኢየሩሳሌም እውነተኛው መስቀል እንዲፈልግ ጥረት አድርጋለች።

መስቀሉ መገኘት ዙሪያ የተሰጡት ትርክቶች በክርስቲያናዊ ትውፊት ውስጥ ትልቅ ሥፍራ አላቸው።

* የተነሱት ጥያቄዎችና የቀረበው ሐሳብ መስቀሉ መገኘቱ በእርግጠኛነት ሊረጋገጥ የማይችል መሆኑን እና ኢየሱስ የሞተውና የተቀበረው በመካከለኛው ምስራቅ (ኢየሩሳሌም) እንጂ በኢትዮጵያ ባለመሆኑ ታሪኩ መሠረት የለውም ይላል።

2. መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት እና የጣዖት አምልኮ ውግንና
* የእግዚአብሔር ቃልና ጣዖት አምልኮ:
«ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ። በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድር ውኃም በታች ባለው የትኛውም ነገር ምሳሌ የተቀረጸውን ምስል ለእራስህ አታድርግ፤ አታስገድዳቸውም፥ አትገዛላቸውምም፤ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነኝና...» (ዘጸአት 20፡3-5)

* በባህላዊ መልኩ የሚደረጉ እንደ ዳመራ ማብራት እና ዙሪያውን መዝፈን ያሉ ተግባራት ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ውጪ የጣዖት አምልኮ መገለጫዎች ናቸው የሚል እምነት ያላቸው ወገኖች አሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ በዓሉን የሚያከብሩ አካላት መስቀሉ የድል፣ የሰላም እና የክርስቶስ ፍቅር መገለጫ እንጂ አምልኮ የሚሰጠው ለእንጨቱ ሳይሆን ለተሰቀለበት አዳኝ ነው ብለው ያምናሉ።

3. የመስቀል በዓልን የመቃወሚያ ነጥቦች:-
* 3.1 ከመነሻው የጣዖት አምልኮ ሥርዓት ስለመሆኑ: -
ብዙዎቹ አህጉራዊ ወይም የጥንት አረማዊ ልማዶች ከጊዜ ሂደት ጋር እየተቀላቀሉ መጥተዋል በሚል ከቀደምት የአምልኮ ሥርዓቶች ጋር ዝምድና አለው የሚል ክርክር ይነሳል።

* 3.2 የኢኮኖሚ ቀውስ ማስከተል: -
ትላልቅ በዓላት ሲከበሩ የሚወጣው ወጪ፣ የእርድ እንስሳት ዋጋ ንረት እና ማኅበራዊ ጫናዎች ለዜጎች የኢኮኖሚ ቀውስ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

* 3.3 መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት አለመኖር:-
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክርስቲያኖች የመስቀልን በዓል በየዓመቱ በልዩ ድምቀት እንዲያከብሩ የታዘዘበት ግልጽ ትዕዛዝ ባለመኖሩ, በዓሉ የሰው ሰራሽ ትውፊት እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትእዛዝ አይደለም።

«እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለም መርህ ባለ በእውቀት ማነስና በከንቱ መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠንቀቁ።» (ቆላስይስ 2፡8)

* 3.4 በውስጡ የጣዖት አምልኮ ሥርዓት መያዙ: -
በዳመራ አከባበር ዙሪያ የሚደረጉ አንዳንድ ሥርዓቶች ከክርስቲያናዊ ንጽህና ውጪ ከሆኑ ልማዶች ጋር የተቆራኙ ናቸው የሚል ስጋት ይነሳል።

👉የማቴዎስ ወንጌል 15፥3
«እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦
እናንተስ ስለ ወጋችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለ ምን ትተላለፋላችሁ?»

ዋናው ሐሳብ፦
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰዎችን ሥርዓትና ባህል (ወግ) ከእግዚአብሔር እውነተኛ ቃልና ትእዛዝ አስበልጠው ለሚያከብሩ ፈሪሳውያንና ጻፎች የሰጠው ከባድ ወቀሳ ነው። የሰዎች ወግ የእግዚአብሔርን ሕግ እንዲሽር መደረግ እንደሌለበት ያስተምራል።

👉ወደ ገላትያ ሰዎች 6፥14
«ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።»

ዋናው ሐሳብ፦
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በራሱ ስራ፣ በሃይማኖታዊ ሥርዓት (ለምሳሌ በመገረዝ) ወይም በዓለማዊ ማንነቱ እንደማይመካ የሚገልጽበት ሐሳብ ነው።

DAY  #1የፀሎት ቀን2018 የልጆች ወንጌል ፌስቲቫል በመሀል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን
11/08/2026

DAY #1
የፀሎት ቀን
2018 የልጆች ወንጌል ፌስቲቫል በመሀል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን

8ኛ ዙር የልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት መክፈቻ ፕሮግራም ምስሎችበሳምንቱ የሚደረጉ ፕሮግራሞች●መንፈሳዊ ትምህርቶች🗒●የተለያዩ የስነጽሁፍ ዝግጅቶች📜●የመድረክና የዉጪ ጨዋታዎች🎉●የልጆች መ...
10/08/2026

8ኛ ዙር የልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት
መክፈቻ ፕሮግራም ምስሎች

በሳምንቱ የሚደረጉ ፕሮግራሞች
●መንፈሳዊ ትምህርቶች🗒
●የተለያዩ የስነጽሁፍ ዝግጅቶች📜
●የመድረክና የዉጪ ጨዋታዎች🎉
●የልጆች መንፈሳዊ ፊልም🎥
●የፈጠራ ዉድድር💈
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

06/08/2026

ልዩ የአምልኮ ምሽት

Address

S**o
60021

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Sodo Mehal Ketema Kale Heywet Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Wolaita Sodo Mehal Ketema Kale Heywet Church:

Shortcuts

Share

Category