23/05/2026
ይህን ያውቃሉ?‼️
ከኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን አማኞች አባላት የሚጠበቅ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ግዴታዎች።
✍️አንድ የእግዚአብሔር ሰዎች ወንዶችም ይሁኑ ሴቶች በእግዚአብሔር ፍርሃት ውሳጣዊና ውጫዊ ቅድስናን በመጠበቅ ሥጋና መንፈስን ከሚያረክስ ነገሮች ሁሉ ራሳቸውን ማንጻት ይገባቸዋል ( 2ኛ ቆሮ 6:14, 7:1 1ኛ ዮሐንስ 2:15 1ኛ ተሰሎንቄ 5:22)
✍️ውስጣዊ ስባል:- ነፍስና መንፈስን የሚያረክስ የሥጋ ስራዎች የሚያካትት ነው እነዚህ ደግሞ ክፋት ፤ ተንኮል ፥ ዝሙት ፥ ርኩሰት ፤መለያየት ፤ሐሜት፤ አድመኝነት ወዘተ ናቸው። ገላትያ 5:19_21)
✍️ውጫዊ ስባል:- ደግሞ ማነኛውም የሚያሰክር መጠጥ መጠጣት አደንዛዥ ዕጽ መትከል መንገድና መጠቀም ማነኛውም የሚያረክስ የመዝናኛ ቦታዎች ላይ መገኘት የማይቻል ነው። (1ኛ ተሰሎንቄ 5:22_23)
ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ። የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ። አሜን
1ኛ ተሰሎንቄ 5:22_23
የተወሰደው ከኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን አባላት መመሪያ ኅዳር 2013 ዓ.ም ከታተመው መጽሐፍ ገጽ 3 ላይ
በ ወንድማችሁ ነኝ የተጻፈው ነው።