Sodo Holy Trinity Catholic Cathedral - ሶዶ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • Sodo Holy Trinity Catholic Cathedral - ሶዶ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል

Sodo Holy Trinity Catholic Cathedral - ሶዶ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይህ የሶዶ ቅ/ሥላሴ ካቴድራል መረጃዎች እና ሌሎች ካቶሊካዊ መረጃዎች የሚጋሩበት ገጽ ነው።

🙌 ✝️⛪መልካም እለተ ሰንበት ይሁንልን!⛪✝️🙌‌👉   •  (A2)  #ያመቱ16 | OT :- Sunday 16Ⓖ   መ.ጥበብ 12:13.16-19║ ሮሜ 8:26-27║ ••••••••••••••••••...
02/08/2026

🙌 ✝️⛪መልካም እለተ ሰንበት ይሁንልን!⛪✝️🙌
‌👉 • (A2) #ያመቱ16 | OT
:- Sunday 16Ⓖ መ.ጥበብ 12:13.16-19║ ሮሜ 8:26-27║
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
👉 🕯️✝️🕯️የእለቱ ወንጌል፡- ማቴ 13:24-43
•+•
"24 ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፡— መንግሥተ ሰማያት በእርሻው መልካም ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች።
25 ሰዎቹ ሲተኙ ግን ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ።
26 ስንዴውም በበቀለና በአፈራ ጊዜ እንክርዳዱ ደግሞ ያን ጊዜ ታየ።
27 የባለቤቱም ባሮች ቀርበው፡— ጌታ ሆይ፥ መልካምን ዘር በእርሻህ ዘርተህ አልነበርህምን? እንክርዳዱንስ ከወዴት አገኘ? አሉት።
28 እርሱም፡— ጠላት ይህን አደረገ፡ አላቸው። ባሮቹም፡— እንግዲህ ሄደን ብንለቅመው ትወዳለህን? አሉት።
29 እርሱ ግን፡— እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም።
30 ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን፡— እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ፡ አለ።
31 ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፡— መንግሥተ ሰማያት ሰው ወስዶ በእርሻው የዘራትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤
32 እርስዋም ከዘር ሁሉ ታንሳለች፥ በአደገች ጊዜ ግን፥ ከአታክልቶች ትበልጣለች የሰማይም ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ ትሆናለች።
33 ሌላ ምሳሌ ነገራቸው እንዲህም አለ፡— መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።
34-35 ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም፡— በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ፡ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም።
36 በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው፡— የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን፡ አሉት።
37 እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፡— መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤
38 መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤
39 እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው።
40 እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል።
41 የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥
42 ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
43 በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።"
•+•
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
💐✝️የተባረከ እና የተቀደሰ እለተ ሰንበት ይሁንልን።🙌✝️💐

🙌 ✝️⛪መልካም እለተ ሰንበት ይሁንልን!⛪✝️🙌‌👉   •  (A2)  #ያመቱ15 | OT :- Sunday 15Ⓖ   ኢሳ 55:10-11║ ሮሜ 8:18-23║ ••••••••••••••••••••••••...
26/07/2026

🙌 ✝️⛪መልካም እለተ ሰንበት ይሁንልን!⛪✝️🙌
‌👉 • (A2) #ያመቱ15 | OT
:- Sunday 15Ⓖ ኢሳ 55:10-11║ ሮሜ 8:18-23║
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
👉 🕯️✝️🕯️የእለቱ ወንጌል፡- ማቴ 13:1-23
•+•
"1 በዚያን ቀን ኢየሱስ ከቤት ወጥቶ በባሕር አጠገብ ተቀመጠ፤
2 እርሱም በታንኳ ገብቶ እስኪቀመጥ ድረስ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፥ ሕዝቡም ሁሉ በወደቡ ቆመው ነበር።
3 በምሳሌም ብዙ ነገራቸው እንዲህም አላቸው፡— እነሆ፥ ዘሪ ሊዘራ ወጣ።
4 እርሱም ሲዘራ አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ፥ ወፎችም መጥተው በሉት።
5 ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀ፤ ጥልቅ መሬትም ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፥
6 ፀሐይ በወጣ ጊዜ ግን ጠወለገ፥ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ።
7 ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾህም ወጣና አነቀው።
8 ሌላውም በመልካም መሬት ወደቀ፤ አንዱም መቶ፥ አንዱም ስድሳ፥ አንዱም ሠላሳ ፍሬ ሰጠ።
9 የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
10 ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፡— ስለ ምን በምሳሌ ትነግራቸዋለህ? አሉት።
11 እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፡— ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፥ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።
12 ላለው ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።
13 ስለዚህ እያዩ ስለማያዩ እየሰሙም ስለማይሰሙ ስለማያስተውሉም በምሳሌ እነግራቸዋለሁ።
14 መስማት ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትም ታያላችሁና አትመለከቱም።
15 በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል።
16 የእናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው።
17 እውነት እላችኋለሁ፥ ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም።
18 እንግዲህ እናንተ የዘሪውን ምሳሌ ስሙ።
19 የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፥ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው።
20 በጭንጫ ላይ የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ ወዲያው በደስታ የሚቀበለው ነው፤
21 ነገር ግን ለጊዜው ነው እንጂ በእርሱ ሥር የለውም፥ በቃሉ ምክንያትም መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላል።
22 በእሾህ መካከል የተዘራውም ይህ ቃሉን የሚሰማ ነው፥ የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት መታለል ቃሉን ያንቃል፥ የማያፈራም ይሆናል።
23 በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፤ እርሱም ፍሬ ያፈራል አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል።"
•+•
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
💐✝️የተባረከ እና የተቀደሰ እለተ ሰንበት ይሁንልን።🙌✝️💐

የሶዶ ቅድስት ሥላሴ አመታዊ ክብረ በዓል በበርካታ ሺዎች የሚቆጠሩ ካቶሊካውያን ምዕመናን፥ በርካታ ካህናት አባቶች፥ በርከት ያሉ ደናግላን እህቶች እንዲሁም ከሩቅም ከቅርብ የመጡ ጥሪ የተደረገ...
14/07/2026

የሶዶ ቅድስት ሥላሴ አመታዊ ክብረ በዓል በበርካታ ሺዎች የሚቆጠሩ ካቶሊካውያን ምዕመናን፥ በርካታ ካህናት አባቶች፥ በርከት ያሉ ደናግላን እህቶች እንዲሁም ከሩቅም ከቅርብ የመጡ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ካቶሊካውያን በተገኙበት - በብጹዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ በተመራ ቅዳሴ - በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከበረ። የቅድስት ሥላሴ በረከት ሬዲኤቱ ዘወትር አይለየን። የአመት ሰው ይበለን።🙌

  እየተከበረ ይገኛል። እንኳን አደረሰን!💐✝️💐
14/07/2026

እየተከበረ ይገኛል። እንኳን አደረሰን!💐✝️💐

14/07/2026

የሶዶ ቅድስት ሥላሴ አመታዊ ክብረ በዓል እለት (በብጹዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ - የሶዶ ሀገረ ስብከት ጳጳስ)

💐🎊   🎊✝️💐 !🎊💐 የሶዶ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አመታዊ ክብረ በዓል ዋዜማ በተለያዩ ዝግጅቶች በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት እየተከናወነ ይገኛል። ! የቅድስት ሥላሴ በረከት ከሁላችንም ጋር ይ...
13/07/2026

💐🎊 🎊✝️💐
!🎊💐 የሶዶ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አመታዊ ክብረ በዓል ዋዜማ በተለያዩ ዝግጅቶች በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት እየተከናወነ ይገኛል።
! የቅድስት ሥላሴ በረከት ከሁላችንም ጋር ይሁን። አሜን።

 ፡||•   ✝️በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አንድ አምላክ አሜን፡፡🌟ክብር ለአብ ይሁን፡-🙌በራሱ መልክና አምሳያ ለፈጠረኝ፡፡🌟ክብር ለወልድ ይሁን፡-🙌በሕማማቱና በመስቀሉ ገሃነምን ድል...
13/07/2026

፡||• ✝️በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አንድ አምላክ አሜን፡፡
🌟ክብር ለአብ ይሁን፡-🙌
በራሱ መልክና አምሳያ ለፈጠረኝ፡፡
🌟ክብር ለወልድ ይሁን፡-🙌
በሕማማቱና በመስቀሉ ገሃነምን ድል ነሰቶ፤
የመንግሥተ ሰማይን በር ለከፈተልኝ፡፡
🌟ክብር ለመንፈስ ስቅዱስ ይሁን፡-🙌
በምስጢረ ጥምቀት ላነጻኝ እና
በየቀኑ በጸጋዎች ለሚባርከኝ፡፡
🌟ክብር ለቅድስት ሥላሴ ይሁን፡-🙌
ኦ ቅድስት ሥላሴ ሆይ !
በመንፈስ ቅዱስ ሥጦታዎች ባርከኝ፤
ቅድስት ስላሴ ሆይ !
እባክህን የባልንጀሮቼን አስፈላጊነት እና፤ አንተን በሕይወቴ ውስጥ ማዕከላዊ እንዳደርግ ጥበብህን ስጠኝ፡፡
እንዲሁም ለእኔና ለሀገሬ (.... የጸሎት ሀሳባችንን እዚህ ጋር መግለጽ....) ጸጋዎች፤ ምላሾችን እና በረከቶችን እንዳገኝ እርዳኝ፡፡
አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ሆይ !
በአፌ ምስጋና እና በልቤ አክብሮት ይገባሃል፤
አንተ ታላቅና ድንቅ ነገሮችን የምታደርግ ነህ፤
አንተ ብቻ አምላክ ነህ፤
ቅድስት ሥላሴ ሆይ ! ክብርና ምስጋና ሁሉ አሁንም ለዘለአለም ያንተ ነው፡፡ ለአብ ለወልድ እና ለመንፈስ ቅዱስ ክብርና ምስጋና ይሁን፡፡አሁንም ዘወትርም ለዘለዓለሙ። አሜን፡፡
በሰማይ የምትኖር...
ፀጋ የሞላሽ......
ለአብና ለወልድ....
✝️ በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ....
(ከሰዶ ቅድስት ሥላሴ ቁምስና )

👉ሁሉ ዝግጁ ሆኗል!  ✝️⛪✝️😍💐🎊 እንኳን ለ ታላቁ የ   ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!🎊💐 ዛሬ ከዋዜማው ዕለት ጀምሮ የሚኖሩን የታላቁ ክብረ በዓል ዝግጅቶች የሚከተሉ...
13/07/2026

👉ሁሉ ዝግጁ ሆኗል!
✝️⛪✝️😍
💐🎊 እንኳን ለ ታላቁ የ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!🎊💐 ዛሬ ከዋዜማው ዕለት ጀምሮ የሚኖሩን የታላቁ ክብረ በዓል ዝግጅቶች የሚከተሉት ይሆናሉ፡-
👉 ዛሬ (ሰኞ - ሐምሌ 6) - በጧፍ መብራት የታጀበ የመቁጠሪያ ጸሎት ኡደት፥ ልዩ የዋዜማ እለት አስተምሕሮ፥ ዝማሬዎች እና ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ምሽት ከ12:00 ጀምሮ ይኖራሉ።

👉ነገ( ማክሰኞ - ሐምሌ 7) በታላቁ የቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል ዕለት በርካታ ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን እና ጥሪ የተደረገላቸው የቅድስት ሥላሴ ወዳጆች ካህናት፥ ደናግላን እና ከሩቅም ከቅርብም የሚመጡ ካቶሊካውያን እና ሌሎች በጎ ፈቃድ ያላቸው እንግዶች በተገኘበት በሀገረ ስብከታችን ጳጳስ በብጹዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ የሚመራ የክብረ በዓል ቅዳሴ ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ ይጀመራል።

🌟እነዚህን እና ሌሎች የቅድስት ሥላሴ በዓል ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን ተገኝታችሁ በመካፈል የበረከቱ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ በታላቅ ትህትና በእግዚአብሔር ፍቅር የግብዣ ጥሪያችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን።
[ የሶዶ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቆሞስ - አባ ማቴዎስ ተገኝ - እና የሶዶ ቅድስት ሥላሴ ቁምስና ሐዋሪያዊ ተግባር ምክር ቤት ]

✝️ የቅድስት ሥላሴ በረከት ዘወትር አይለየን። አሜን።

 ፡||•  ✝️በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አንድ አምላክ አሜን፡፡🌟ክብር ለአብ ይሁን፡-🙌በራሱ መልክና አምሳያ ለፈጠረኝ፡፡🌟ክብር ለወልድ ይሁን፡-🙌በሕማማቱና በመስቀሉ ገሃነምን ድል ...
12/07/2026

፡||•
✝️በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አንድ አምላክ አሜን፡፡
🌟ክብር ለአብ ይሁን፡-🙌
በራሱ መልክና አምሳያ ለፈጠረኝ፡፡
🌟ክብር ለወልድ ይሁን፡-🙌
በሕማማቱና በመስቀሉ ገሃነምን ድል ነሰቶ፤
የመንግሥተ ሰማይን በር ለከፈተልኝ፡፡
🌟ክብር ለመንፈስ ስቅዱስ ይሁን፡-🙌
በምስጢረ ጥምቀት ላነጻኝ እና
በየቀኑ በጸጋዎች ለሚባርከኝ፡፡
🌟ክብር ለቅድስት ሥላሴ ይሁን፡-🙌
ኦ ቅድስት ሥላሴ ሆይ !
በመንፈስ ቅዱስ ሥጦታዎች ባርከኝ፤
ቅድስት ስላሴ ሆይ !
እባክህን የባልንጀሮቼን አስፈላጊነት እና፤ አንተን በሕይወቴ ውስጥ ማዕከላዊ እንዳደርግ ጥበብህን ስጠኝ፡፡
እንዲሁም ለእኔና ለሀገሬ (.... የጸሎት ሀሳባችንን እዚህ ጋር መግለጽ....) ጸጋዎች፤ ምላሾችን እና በረከቶችን እንዳገኝ እርዳኝ፡፡
አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ሆይ !
በአፌ ምስጋና እና በልቤ አክብሮት ይገባሃል፤
አንተ ታላቅና ድንቅ ነገሮችን የምታደርግ ነህ፤
አንተ ብቻ አምላክ ነህ፤
ቅድስት ሥላሴ ሆይ ! ክብርና ምስጋና ሁሉ አሁንም ለዘለአለም ያንተ ነው፡፡ ለአብ ለወልድ እና ለመንፈስ ቅዱስ ክብርና ምስጋና ይሁን፡፡አሁንም ዘወትርም ለዘለዓለሙ። አሜን፡፡
በሰማይ የምትኖር...
ፀጋ የሞላሽ......
ለአብና ለወልድ....
✝️ በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ....
(ከሰዶ ቅድስት ሥላሴ ቁምስና )

12/07/2026

እንኳን ለ #50ኛው የ #ክህነት አመት መታሰቢያ እለት በሰላም አደረሳችሁ ብጹአን አባቶች! ❤️

Address

S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sodo Holy Trinity Catholic Cathedral - ሶዶ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share