Shashemene shewa ber kalehiywot church

Shashemene shewa ber kalehiywot church Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Shashemene shewa ber kalehiywot church, Church of Christ, Shashemene.

ይህ የሻሸመኔ ሸዋ በር ቃለ ሕይወት ቤተ-ክርስቲያን የፌስቡክ ገፅ ነው:: 👇👇👇👇👇👇👇👇

Shashemene Shewa Ber Kale Hiwot Church Website: http://www.sskhc.org
Official YouTube :- https://www.youtube.com/
Telegram:- https://t.me/sskhc1954
Facebook :- http

26/08/2026

  !!
26/08/2026

!!

   #ሻሸመኔ የቤተክርስቲያኒቱ የይዲድያ መዘምራን ህብረት የፊታችን እሁድ ነሐሴ 24 - 2018 የተመሰረቱበትን 20ኛ ዓመት የምስረታ በአላቸውን ያከብራሉ።ይህንንም ምክንያት በማድረግ በዚሁ ...
26/08/2026


#ሻሸመኔ

የቤተክርስቲያኒቱ የይዲድያ መዘምራን ህብረት የፊታችን እሁድ ነሐሴ 24 - 2018 የተመሰረቱበትን 20ኛ ዓመት የምስረታ በአላቸውን ያከብራሉ።
ይህንንም ምክንያት በማድረግ በዚሁ ቀን ልዩ መሰናዶ አዘጋጅተው ይጠብቋችኋል።
በዕለቱ:-
🎤 🎼 ልዩ የዝማሬ አምልኮ
📖 የቃል ጊዜ ፤ እንዲሁም
📢 የህብረቱ የመዝሙር ምረቃ ስነስርዓት ይካሄዳል

በሻሸመኔ እና አካባቢዋ የምትገኙ በሙሉ በዕለቱ በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል።


#ሻሸመኔ

  #ሻሸመኔነሐሴ 10/2018 ዓ.ምየሻሸመኔ ሸዋ በር ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን እሁድ ጠዋት መደበኛ የአምልኮ ፕሮግራምበዕለቱም   የምስረታ በአላቸውን ያከበሩ ሲሆን ወ/ዊ   በቃለ-እግዚአብ...
18/08/2026


#ሻሸመኔ

ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም

የሻሸመኔ ሸዋ በር ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን
እሁድ ጠዋት መደበኛ የአምልኮ ፕሮግራም

በዕለቱም የምስረታ በአላቸውን ያከበሩ ሲሆን ወ/ዊ በቃለ-እግዚአብሔር አገልግሏል።

ቃለ እግዚአብሔር:- ወ/ዊ ካሳ
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል:
የዮሐ . ወንጌል 19፥15-16
የሐዋ . ሥራ 12፥1-3
2ኛ ጢሞ 3፥1-5

ርዕስ:- (የማን ባሪያ ነህ)

#መግቢያ:
አይሁዶች ፋሲካ ሲሆን እስረኛን የመልቀቅ ልማድ ነበራቸውና ጲላጦስ ህዝቡን በጠየቀው መሰረት ወንበዴውን በርባን እንዲለቀቅላቸው እና ኢየሱስን እንዲሰቀል አጥብቀው ጮኹ፤

:
❶ ለራሳችን ፍላጎት
አዳምና ሔዋን እግዚአብሔር በገነት ካለው ዛፍ ሁሉ እንዲበሉ ነገር ግን መልካምን እና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ እንዳይበሉ ቢያዛቸውም እነርሱ ግን እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ በሃጢአት ወደቁ፤

❷ ለሰው ደስታ ብቻ ባሪያ የሆነ ሰው
ንጉስ ሄሮድስ አይሁድን ደስ እንዳሰኘ አውቆ ሐዋርያቱን ያስገድል ነበር፤
የሐዋ . ሥራ 12፥1-3

❸ የሰይጣንን ፍላጎት የሚፈፅሙ
ምግባሩን ተቀብለው የሚተገብሩ ናቸው፤

✍️ ኢየሱስ ያልተቆጣጠረው የሕይወት ምዕራፍ አይኑረን!


#ሻሸመኔ

  #ሻሸመኔ የነሐሴ 03 -2018 ዓ.ም የዕሁድ ማለዳ መደበኛ የአምልኮ ፕሮግራም።በዕለቱ ወ/ም   የእግዚአብሔርን ቃል ያካፈለን ሲሆን ወራዊ   ስነስርዓትም ተከናውኗል።  ክብር ሁሉ ለጌታ ...
14/08/2026


#ሻሸመኔ

የነሐሴ 03 -2018 ዓ.ም የዕሁድ ማለዳ መደበኛ የአምልኮ ፕሮግራም።

በዕለቱ ወ/ም የእግዚአብሔርን ቃል ያካፈለን ሲሆን ወራዊ ስነስርዓትም ተከናውኗል።
ክብር ሁሉ ለጌታ ይሁን!!


#ሻሸመኔ

     ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ መጀመራችንን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው፡፡    ●ፕሮግራሞች🎓  #በሰርተፊኬት 🎓  #በዲፕሎማ እና🎓  #በዲግሪ   ● ትምህርቱ የሚሠጥባቸው ...
11/08/2026


ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ መጀመራችንን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው፡፡
●ፕሮግራሞች
🎓 #በሰርተፊኬት
🎓 #በዲፕሎማ እና
🎓 #በዲግሪ
● ትምህርቱ የሚሠጥባቸው ቋንቋዎች
🗣 በአማርኛ እና 🗣 በአፋን ኦሮሞ
● መርሃ-ግብሮች
👉 ከሰኞ እስከ አርብ ከ 11፡00 – 12፡30 ⌚️
👉 በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት (አርብ እና ቅዳሜ)

❗️ማሳሰቢያ፡- አመልካቾች ካሉበት አጥቢያ ቤተክርስቲያን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡


#ሻሸመኔ

  #ሻሸመኔ እሁድ ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም  የእሁድ ጠዋት መደበኛ የአምልኮ ፕሮግራም ባሳለፍነው እሁድም ቀጥሎ ተከሂዷል፡፡ቃለ እግዚአብሔር:- በወ/ም አዳነ በኩ     📖 የመጽሐፍ ቅዱስ ክ...
05/08/2026


#ሻሸመኔ
እሁድ ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም

የእሁድ ጠዋት መደበኛ የአምልኮ ፕሮግራም ባሳለፍነው እሁድም ቀጥሎ ተከሂዷል፡፡

ቃለ እግዚአብሔር:- በወ/ም አዳነ በኩ
📖 የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል:

👉 ሚክያስ 6
⁶ ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን?
⁷ እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጎች ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? ወይስ የበኵር ልጄን ስለ በደሌ፥ የሆዴንም ፍሬ ስለ ነፍሴ ኃጢአት እሰጣለሁን?
⁸ ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?

ርዕስ:- ወደ እግዚአብሔር ፊት እንዴት እንቅረብ???

● ምህረት በማድረግ፤

● እውነተኛ ፍርድ በመፍረድ፤

● በትህትና ከእግዚአብሔር ጋር በመሄድ፤

● ከሚታይ ነገር ይልቅ ውስጥን በማጥራት፤

እግዚአብሔር ድንቅ እና መልካም ጊዜን ሰጥቶናል፡፡ የረዳን እግዚአብሔር ይመስገን፡፡

እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ይባርክ!!!


#ሻሸመኔ
👇👇👇👇👇👇👇👇

Shashemene Shewa Ber Kale Hiwot Church Website: http://www.sskhc.org
Official YouTube :- https://www.youtube.com/
Telegram:- https://t.me/sskhc1954
Facebook :- https://web.facebook.com/shewaberKHC.1/

   #ሻሸመኔ #ሻሸመኔ:-  ዓመታዊው የልጆች የክረምት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ እና መልስ ውድድር በትናንትናው ዕለት ተጀምሯል፡፡   ዓመታዊው የልጆች   የጥያቄ እና መልስ ውድድር በትናንትናው...
02/08/2026


#ሻሸመኔ

#ሻሸመኔ:- ዓመታዊው የልጆች የክረምት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ እና መልስ ውድድር በትናንትናው ዕለት ተጀምሯል፡፡

ዓመታዊው የልጆች የጥያቄ እና መልስ ውድድር በትናንትናው ዕለት በዕለተ ቅዳሜ በ25-11-2018 ዓ.ም ተጀምሯል፡፡
ወላጆች እና አሳዳጊዎች ልጆቻችሁ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠኑ በቤት ውስጥ ከምታደርጉላቸው ድጋፍ በተጨማሪ ወደ እግዚአብሔር ቤት በመላክ እና ይዛችሁም በመምጣት የእግዚአብሔርን ቃል እንዲማሩ የበኩላችሁን እንድትወጡ ቤተክርስቲያን ታሳስባለች፡፡


#ሻሸመኔ

  #ሻሸመኔ19-11-2018 ዓ.ም. (ዕሁድ ማለዳ)  መደበኛ የዕሁድ የአምልኮ መርሃግብር ተካሂዳል፡፡                    ፡- " የሚገባንን ቀንበር ተሸክመን የማይገባንን ቀንበር ...
28/07/2026


#ሻሸመኔ
19-11-2018 ዓ.ም. (ዕሁድ ማለዳ)
መደበኛ የዕሁድ የአምልኮ መርሃግብር ተካሂዳል፡፡
፡-
" የሚገባንን ቀንበር ተሸክመን የማይገባንን ቀንበር እናውርድ"
( )
📖ማቴ 11፡28
#28 "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
#29 ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤
#30 ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።"
ብዙ ሰዎች ይህንን ክፍል ላላመኑ ሰዎች ወንጌልን በሚመሰክሩበት ጊዜ ብቻ የሚጠቀሙት ቃል አድርገው ልምድ አድርገው ይወስዱታል፡፡ ነገር ግን በጌታ አምነን ድነናል ብለው የሚያምኑ እና እየዘመሩ እያመለኩ ነገር ግን በብዙ ቀንበር ውስጥ ያሉ ሰዎች ጥቂቶች አይደሉም፡፡
ቀንበር እንዲሁ ዝም ብሎ የሚመጣ ሳይሆን የራሱ የሆኑ ምንጮች አሉት
ዋና ዋና የቀንበር ምንጮች
1. #ሠይጣን
- ሰው በክርስቶስ ካልሆነ እና ራሱን በጌታ አምኖ ነጻ ካላወጣ በሰይጣን ቀንበር ውስጥ ይኖራል፡፡
2. #ኃጢአት
- ከኃጢአት ጋር መዛመድ ፤ መታሰር እና መተሳሰር እንዲሁም ድፍረት(ነገሮችን አቅልሎ ማየት) ወደ ኃጢአት ልምምድ ውስጥ ይመራናል፡፡ የኃጢአት ልምምድ በራሱ ክፉ ቀንበር ነው፡፡
3.
- በዚህ ዓለም ስንኖር እንደ እግዚአብሔር ሃሳብ ብቻ መውጣት እና መግባት ካልቻልን ዓለም በራሷ ወጥመድ ውስጥ ታስገባን እና ቀንበር ትጭንብናለች

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ነጥቦች የቀንበር ዋና ምንጮች ናቸው፡፡
- 👉 ምልክቶቹ ( አንድ ሰው በቀንበር ውስጥ ለመሆኑ ምልክቶቹ ምንድናቸው)
1.
2. (መንፈሳዊ ድካም)
3.
- አንድ በጌታ ያለ ወይም መንፈሳዊ ሕይወት አለኝ ብሎ የሚያምን ሰው ከጸሎት ፤ ከቅዱሳን ኅብረት ፤ ከእግዚአብሔር ቃል ጥናት ራሱን የሚያሸሽ ከሆነ አንዱ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
4. (ውስጣዊ ድካም)
- ለመንበርከክ እና በእግዚአብሔር ፊት ጊዜ ለመውሰድ አቅም ካጣን ይህም አንዱ በቀንበር ውስጥ እየተመላለስን ለመሆኑ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
- 👉ምን እንሸከም
1. የክርስቶስን ስም እንሸከም (ስሙን)
- 📖 ሐዋ 9፡15 15 ጌታም። ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና
ጳውሎስ ከዚህ ቀደም ዘረኝነት አሳዳጅነትን የተሸከመ ሰው ነበር፡፡ ይህንን ቀንበር ከጣለ በኋላ ግን የክርስቶስን ስም ተሸከመ፡፡ ለዚህም ስም መከራን ለመቀበል ራሱን አዘጋጀ፡፡
2. የጸሎት አደራን እንሸከም
- የዚህ ዓለም እና የሠይጣን ቀንበር የተሰበረለት ሰው፡- ላልዳኑ ፤ ለታመሙ ሠዎች ፤ ለሀገር፤ በጦርነት እና ችግር ውስጥ ላሉ ሠዎች ለበንበርከክ የተሠጠ ይሆናል፡፡
3. ቃሉን በዕምነት እንሸከም
- አንዳንድ ሰው በዚህ ዘመን ለእግዚአብሔር ቃል ጊዜ የለውም፡፡ ሰው በችኮላ እና በመቅበዝበዝ ተሞልቷል የእግዚአብሔር ቃል ግን ፡- ምሳ 1፡33 ላይ ፡- የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። .."ይለናል፡፡
- እንዲሁም ኢዮ 22፡22 ላይ ቃሉን በልባችን እንድናር ያዘናል፡፡ ኢዮ 22፡22 22 ፤ ከአፉም ሕጉን ተቀበል፥ በልብህም ቃሉን አኑር፤
4. ፍቅርን ይቅርታን እና ምህረትን እንሸከም
5. አገልግሎትን እንሸከም
ምን እንዳጎበጠው ሳያውቅ ብዙ ሰው ጎባጣ ሆኑ ይኖራል፡፡ የተጫነበትን እና ያጎበጠውን ቀንበር ግን አያውቅም ስለዚህ ሁላችንም ራሳችንን እንመርምር ያጎበጠንን ለይተን እንወቅ እና እንጣለው፡፡ መልካሙን እና ልዝቡን እንዲሁም ጌጣችን የሆነውን የጌታን ሸክም እንሸከም፡፡
ስለነበረን መልካም ጊዜ ሁሉ ክብር ለ እግዚአብሔር ይሁን፡፡

#ሻሸመኔ

   #ሻሸመኔ12-11-2018 ዓ.ም. (ዕሁድ ማለዳ)የሻሸመኔ_ሸዋ_በር_ቃለ_ሕይወት_ቤተ_ክርስቲያ የዕሁድ ማለዳ መደበኛ የአምልኮ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡ በዕለቱ   አምልኮ መሪዎች ዝማሬን በመ...
22/07/2026


#ሻሸመኔ
12-11-2018 ዓ.ም. (ዕሁድ ማለዳ)
የሻሸመኔ_ሸዋ_በር_ቃለ_ሕይወት_ቤተ_ክርስቲያ የዕሁድ ማለዳ መደበኛ የአምልኮ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡
በዕለቱ አምልኮ መሪዎች ዝማሬን በመምራ ያገለገሉ ሲሆን #የቤተክርስቲያኒቱ መጋቢ:- ከመጽሐፍ ቁዱስ #ምሳሌ 6፡16-19 መሰረት በማድረግ የእግዚአብሔር ቃል አገልገሏል፡፡ በተያያዘም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ጨርሰው ለተመረቁ የቤተክርስቲያኒቱ ወጣቶች #የሰርተፊኬት እና #የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡
ስለነበረን መልካም ጊዜ ሁሉ ክብር ለ እግዚአብሔር ይሁን፡፡
የሻሸመኔ_ሸዋ_በር_ቃለ_ሕይወት_ቤተ_ክርስቲያን
#ሻሸመኔ

Address

Shashemene

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shashemene shewa ber kalehiywot church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share