ኤኬላ አፓስትሊክ world wide

ኤኬላ አፓስትሊክ world wide ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ሀይል ለማዳን ነውና ሮሜ 1:16

የአራተኛ ዓመት ክብረ በዓል – የመጨረሻ ቀን ኮንፈረንስ 🔥በእግዚአብሔር ጸጋ የጀመርነውን የአራተኛ ዓመት ክብረ በዓል ዛሬ በድል አጠናቀናል! የመጨረሻው ቀን ኮንፈረንስ ከተጀመረበት ሰዓት ጀ...
03/03/2026

የአራተኛ ዓመት ክብረ በዓል – የመጨረሻ ቀን ኮንፈረንስ 🔥

በእግዚአብሔር ጸጋ የጀመርነውን የአራተኛ ዓመት ክብረ በዓል ዛሬ በድል አጠናቀናል! የመጨረሻው ቀን ኮንፈረንስ ከተጀመረበት ሰዓት ጀምሮ እስከ መዝጊያው ድረስ በክብርና በመንፈስ ኃይል የተሞላ ድንቅ ጊዜ ነበር።🔥

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደነበረ በግልፅ ተመልክተናል፤ ልቦች ተለወጡ፣ እምነት በረታ፣ ተስፋ ለመለመ።

“ይህን ሁሉ በምንወደው በእርሱ እጅግ እንሻላለን” (ሮሜ 8፥37) የሚለው ቃል በእውነት ተፈጸመ፤ በእርሱ ረዳትነት በድል አጠናቀናል።

በዚህም ቀን በቃል በዝማሬ ያገለገሉን

ነብይ ገዳ
ነብይ ንጉሴ
ነብይ እሸቱ
ዘማሪ ለሎ

እንዲሁም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዬች በሙሉ ጌታ አብዝቶ ይባርካቹ ተባረኩ🙏

ከጎናችን ቆማችሁ በጸሎት፣ በመገኘትና በድጋፍ ያበረታችሁን ሁሉ እናመሰግናለን።

በፍቅርና በትጋት ያገለገላችሁ አገልጋዮቻችን እግዚአብሔር አገልግሎታችሁን ይባርክ፣ ድካማችሁን በብዙ በረከት ይተካ።🙏

ከሁሉ በላይ ግን ምስጋናችን ለረዳን አምላክ ይሁን፤ መጀመሪያችንም መጨረሻችንም እርሱ ነው። ክብር ለእርሱ ይሁን🙏

የአራተኛ ዓመት ክብረ በዓል – ሶስተኛ ቀን ኮንፈረንስ 🔥✨ሶስተኛው ቀን ኮንፈረንስ በእውነት የመንፈስ ፍንጭ የተሞላበት ድንቅ ጊዜ ነበር።ከመዝሙር እስከ ቃል ስብከት ድረስ ክብሩ በግልፅ ተገ...
03/03/2026

የአራተኛ ዓመት ክብረ በዓል – ሶስተኛ ቀን ኮንፈረንስ 🔥✨

ሶስተኛው ቀን ኮንፈረንስ በእውነት የመንፈስ ፍንጭ የተሞላበት ድንቅ ጊዜ ነበር።

ከመዝሙር እስከ ቃል ስብከት ድረስ ክብሩ በግልፅ ተገልጧል፣ እምነታችን ተበረቷል፣ ተስፋ እንደገና ቀጥሏል።

“በሚጠብቁት ላይ ኃይል
ይጨምራል” (ኢሳይያስ 40፥31)
የሚለው ቃል በመካከላችን ተፈጽሟል።

ዛሬ በመጠበቅና በእምነት የቆምን ሁሉ አዲስ ኃይል ተሞልተናል።

ይህ ግን ገና አልተጠናቀቀም!

በዚህም ቀን በቃል በዝማሬ ያገለገሉን
ነብይ ገዳ
ነብይ አክሊሉ
ዘማሪ ይስሀቅ
እንዲሁም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮች ሁሉ ጌታ አብዝቶ ይባርካቹ ተባረኩ🙏

ፕሮግራሙ በተጨማሪ ክብርና ሀይል ይቀጥላል። እንዳትቀሩ — ከዚህ በላይ የሚበልጥ በረከት እየመጣ ነው! 🙏🔥

የአራተኛ ዓመት ክብረ በዓል – ሁለተኛ ቀን ኮንፈረንስ ✨ዛሬ የነበረው ሁለተኛ ቀን ኮንፈረንስ እጅግ ድንቅና በክብር የተሞላ ጊዜ ነበር። የእግዚአብሔር መገኘት በግልፅ ተገለጧል ልባችን ተነክ...
28/02/2026

የአራተኛ ዓመት ክብረ በዓል – ሁለተኛ ቀን ኮንፈረንስ ✨

ዛሬ የነበረው ሁለተኛ ቀን ኮንፈረንስ እጅግ ድንቅና በክብር የተሞላ ጊዜ ነበር። የእግዚአብሔር መገኘት በግልፅ ተገለጧል ልባችን ተነክቶል መንፈሳችን ታድሷል።

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል፦
“ክብሩ ይህን ቤት ይሞላዋል” (ሐጌ 2፥7) —
ቃሉ በመካከላችን ተገልጧል

በዚህም ቀን በቃል በዝማሬ ያገለገሉን
ነብይ ገዳ
አገልጋይ እዮብ
ዘማሪ አዲስ
እንዲሁም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮች ሁሉ ጌታ አብዝቶ ይባርካቹ ተባረኩ🙏

ፕሮግራሙ በኃይልና በክብር እየቀጠለ ነዉ...አብረን እንቀጥላለን

እንዳትቀሩ — ከዚህ በላይ ድንቅ ጊዜ ይኖረናል

የአራተኛ ዓመት ክብረ በዓል – የመጀመሪያ ቀን ኮንፍራንስ“በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ”የመጀመሪያ ቀናችን በእግዚአብሔር ኃይልና በክብሩ መገኘት ውስጥ እጅግ ድንቅ ነበር። ልባችን ተነክቶ፣ ነ...
26/02/2026

የአራተኛ ዓመት ክብረ በዓል – የመጀመሪያ ቀን ኮንፍራንስ

“በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ”

የመጀመሪያ ቀናችን በእግዚአብሔር ኃይልና በክብሩ መገኘት ውስጥ እጅግ ድንቅ ነበር። ልባችን ተነክቶ፣ ነፍሳችን ታድሶ፣ ክብሩን በግልፅ ተመልክተናል።
በመገኘቱ ውስጥ ሰላም፣ ኃይል እና መታደስ ተሞልተን ተመልሰናል።

በዚህ ቀን በቃልና በመዝሙር ያገለገሉን
Prophet GEDA
Prophet BELACHEW
Singer Dawit
እንዲሁም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮች ሁሉ ጌታ አብዝቶ ይባርካችሁ!
አገልግሎታችሁ ፍሬ ያፍራ!

ፕሮግራሙ በክብር እየቀጠለ ነው… አብረን እንቀጥል! 🔥✨

ይቀጥላል.....

ልዩ የምስጋና ኮንፍራንስ በኤኬላ አፖስቶሊክ ሚሽን ቸርች ከየካቲት 19 እስከ  የካቲት 22.2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ አራት ቀናት    የ4ኛ አመት የምስረታ ቀን በዓላችንን በማስመለከት...
18/02/2026

ልዩ የምስጋና ኮንፍራንስ በኤኬላ አፖስቶሊክ ሚሽን ቸርች
ከየካቲት 19 እስከ የካቲት 22.2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ አራት ቀናት
የ4ኛ አመት የምስረታ ቀን በዓላችንን በማስመለከት ምስጋና ለሚገባው በሚል ርዕስ ባዘጋጀነው በዚህ ድንቅ የምስጋና ኮንፍራንስ ላይ ከቤተክርስቲያኒቱ ባለራዕይና መስራች ነቢይ ገዳ እንዲሁም ከተወደዱ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ጋር የእግዚአብሔርን ቃል እንካፈላለን በመዝሙርና በአምልኳችንም አምላካችንን እናመሰግንሀለን እንለዋለን የአምልኮ መስዋዕታችንንም በፊቱ እናቀርባለን።

ስለሆነም እርስዎም በእነዚህ ቀናት ማለትም የካቲት 19 ሐሙስ ሙሉ ቀን, የካቲት 20 ና 21 ዓርብና ቅዳሜ ከ11:00 ጀምሮ እስከ ምሽት 2:00 ድረስ እንዲሁም እሁድ የካቲት 22 ሙሉ ቀን በሚኖረን ፕሮግራም ላይ በመገኘት አብረውን እንዲያመልኩ ምስጋና ለሚገባው የምስጋናን መስዋዕት እንዲሰዉ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ፀጋ እንዲካፈሉ በክብር ጋብዘንዎታል
አድራሻ:- ወለቴ ስላሴ መውጫ 500 ሜትር ገባ ብሎ ከነማ መድሀኒት መሸጫ በስተቀኝ በኩል
ለበለጠ መረጃ 0929006726 / 0910842157
ኤኬላ አፖስቶሊክ ሚሽን ቸርች

ሚያሳድዳቹ ጠላታቹ ትቶአቹ ይመለሳል28 ሳኦልም ዳዊትን ማሳደድ ትቶ ተመለሰ፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ሊዋጋ ሄደ። ስለዚህ የዚህ ስፍራ ስም የማምለጥ ዓለት ተባለ።
18/01/2026

ሚያሳድዳቹ ጠላታቹ ትቶአቹ ይመለሳል
28 ሳኦልም ዳዊትን ማሳደድ ትቶ ተመለሰ፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ሊዋጋ ሄደ። ስለዚህ የዚህ ስፍራ ስም የማምለጥ ዓለት ተባለ።

“እግዚአብሔርም መጥቶ ቆመ፥ እንደ ቀድሞውም፦ ሳሙኤል ሳሙኤል ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም፦ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር አለው።”  — 1ኛ ሳሙኤል 3፥10
28/12/2025

“እግዚአብሔርም መጥቶ ቆመ፥ እንደ ቀድሞውም፦ ሳሙኤል ሳሙኤል ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም፦ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር አለው።”
— 1ኛ ሳሙኤል 3፥10

ኢሳይያስ 41¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯⁸ ባሪያዬ እስራኤል፥ የመረጥሁህ ያዕቆብ፥ የወዳጄ የአብርሃም ዘር ሆይ፥⁹ አንተ ከምድር ዳርቻ የያዝሁህ ከማዕዘንዋም የጠራሁህና፦ አንተ ባሪያዬ ነህ፥ መርጬሃለሁ ...
21/12/2025

ኢሳይያስ 41
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ ባሪያዬ እስራኤል፥ የመረጥሁህ ያዕቆብ፥ የወዳጄ የአብርሃም ዘር ሆይ፥
⁹ አንተ ከምድር ዳርቻ የያዝሁህ ከማዕዘንዋም የጠራሁህና፦ አንተ ባሪያዬ ነህ፥ መርጬሃለሁ አልጥልህም ያልሁህ ሆይ፥
ኢሳይያስ 41
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
¹¹ እነሆ የሚቆጡህ ሁሉ ያፍራሉ፥ ይዋረዱማል፤ የሚከራከሩህም እንዳልነበሩ ይሆናሉ፥ ይጠፉማል።
¹² የሚያጣሉህንም ትሻቸዋለህ አታገኛቸውምም፥ የሚዋጉህም እንዳልነበሩና እንደ ምናምን ይሆናሉ።
1.የሚቆጡህ
ሁሉ ያፍራሉ
ይዋረዳሉም
2.የሚከራከሩህም
እንዳለነበሩ ይሆናሉ
ይጠፉማል
3.የሚያጣሉህንም
ትሻቸዋለህ አታገኛቸውም
4.የሚዋጉህንም
እንዳልነበሩና
እንደምናምን ይሆናሉ

20/12/2025
“እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።”  — 1ኛ ዮሐንስ 1፥3
15/12/2025

“እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።”
— 1ኛ ዮሐንስ 1፥3

Address

Welete
Sebeta

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኤኬላ አፓስትሊክ world wide posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share