18/05/2024
መንፈሳዊ ነገር ከእኛ አይጀምርም። ከእኛ ከጀመረ አንድ ቀን መብረድና መቆሙ አይቀርም። በመንፈስ ያልተጀመረ በሥጋ አይገለጥም። የሚታየው ከማይታየው ነው። ሥር አይታይም ነገር ግን የሚታይ ፍሬ እንዲያፈራ ያደርጋል። ክርስቶስ የቤተክርስቲያን ሥርና መሠረት እንጂ ስምና መታወቂያ አይደለም። የአንድን ዛፍ ፍሬ ሁኔታ የሚወስነው ሥሩ ነው። ብዙ ሰዎች ግን የሚጨነቁት ስለ ፍሬው እንጂ ስለ ተተከሉበት ሥር አይደለም። ክፉ ዛፍ ክፉ ፍሬ፣ መልካም ዛፍ መልካም ፍሬ እንደሚያፈራ እኛም መልካም ፍሬ እንድናፈራ እግዚአብሔር ክርስቶስ ላይ ተክሎናል። የምናፈራው ፍሬ የክርስቶስ አይነት ነው። ክርስቶስ ላይ ስለ ተተከልን እርግጠኛና የተማመነ የሕይወት ምስክርነት (ፍሬ) አለን።