በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አፋር ሀ/ስብከት ሕዝብ ግንኙነት / Afar Diocese public relation, EOTC

  • Home
  • Ethiopia
  • Logya
  • በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አፋር ሀ/ስብከት ሕዝብ ግንኙነት / Afar Diocese public relation, EOTC

በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አፋር ሀ/ስብከት ሕዝብ ግንኙነት / Afar Diocese public relation, EOTC በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አፋር ሀ/ስብከት ሕዝብ ግንኙነት / Afar Diocese public relation, EOTC� � �

10/09/2026
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ከሐዋርያት፣ ሁለቱን ከነቢያት መርጦ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓለ ደብረ ታቦር፤ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል የአፋር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ...
19/08/2026

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ከሐዋርያት፣ ሁለቱን ከነቢያት መርጦ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓለ ደብረ ታቦር፤ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል የአፋር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት፣ በአዋሽ ደብረ ሳሌም ቅድስተ ማርያም ካቴድራል በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከብሯል።

በዕለቱ የደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት ለዕለቱ የሚሆን ዝማሬ አቅርቧል።

በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ዕለቱን በተመለከተ ቃለ ወንጌል ካስተማሩ በኋላ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ በመስጠት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፤ እንዲሁም የተዘጋጀውን ችቦ ባርከው እንደ አባቶቻችን ሥርዓት የማብራት መርሃ ግብር ተከናውኗል።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአፋር ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት / ሚዲያ

ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም.

«ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም. የጾመ ፍልሰታ ሱባኤ 13ኛ ቀን እና የበዓለ ደብረ ታቦር ሥርዓተ ማኅሌትና ጸሎተ ኪዳን አገልግሎት በብፁዕ አቡነ ዳንኤል (የአፋር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱ...
19/08/2026

«ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም. የጾመ ፍልሰታ ሱባኤ 13ኛ ቀን እና የበዓለ ደብረ ታቦር ሥርዓተ ማኅሌትና ጸሎተ ኪዳን አገልግሎት በብፁዕ አቡነ ዳንኤል (የአፋር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዲስ አባል) በተገኙበት በአዋሽ ደብረ ሳሌም ቅድስተ ማርያም ካቴድራል ተከናወነ።»

የአፋር ሀ/ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ሚዲያ
ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም

08/08/2026

በአፋር ሀገረ ስብከት በአሚባራ ወረዳ በወረር ደ/መ/ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የልደታ ለማርያም ወጣቶች መንፈሳዊ ማህበር ከሐምሌ 24 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ባዘጋጀው ልዩ ዓመታዊ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ተገኝተው ሕዝበ ክርስቲያኑን ባርከዋል።

የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓለ ንግሥ  ብፁዕ አቡነ ዳንኤል የአፋር ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በሳቡሬ ደብረ ቤቴል ቅዱስ ገብርኤል በርካታ ሊቃ...
07/08/2026

የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓለ ንግሥ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል የአፋር ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በሳቡሬ ደብረ ቤቴል ቅዱስ ገብርኤል በርካታ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።
ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም.
ሳቡሬ / አፋር

በአፋር ሀገረ ስብከት በአሚባራ ወረዳ በወረር ደ/መ/ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የልደታ ለማርያም ወጣቶች መንፈሳዊ ማህበር ከሐምሌ 24 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ባዘጋጀው ልዩ ዓመታዊ ...
07/08/2026

በአፋር ሀገረ ስብከት በአሚባራ ወረዳ በወረር ደ/መ/ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የልደታ ለማርያም ወጣቶች መንፈሳዊ ማህበር ከሐምሌ 24 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ባዘጋጀው ልዩ ዓመታዊ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ተገኝተው ሕዝበ ክርስቲያኑን ባርከዋል።

በብፁዕ አባታችን የአቀባበል መርሐ ግብር ላይ የልደታ ለማርያም ወጣቶች ቅንጅት፣ ህብረት እና ያሳዩት አቀባበል እጅግ ያማረና የምዕመናኑም ደስታ የጎላ ነበር። ማህበሩም ለብፁዕ አባታችን አቡነ ዳንኤል ያላቸውን የልጅነት ፍቅር ለመግለጽ የዕጅ መስቀል ስጦታ አበርክቷል።

ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ.ም

መልካ ወረር (አፋር፣ ኢትዮጵያ)

እንኳን ለታላቁ ጻድቅ ለአባታችን ለአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዓመታዊ የእረፍት በዓለ ንግሥ በሰላም አደረሳችሁ።በአፋር ሀገረ ስብከት በአዋሽ 7 ፈለገ ዮርዳኖስ ቅድስት አርሴማ ገዳም የአቡነ እጨጌ ...
06/08/2026

እንኳን ለታላቁ ጻድቅ ለአባታችን ለአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዓመታዊ የእረፍት በዓለ ንግሥ በሰላም አደረሳችሁ።
በአፋር ሀገረ ስብከት በአዋሽ 7 ፈለገ ዮርዳኖስ ቅድስት አርሴማ ገዳም የአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዓመታዊ የእረፍት በዓለ ንግሥ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል የአፋር ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ውሏል።
የአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዓመታዊ የእረፍት በዓለ ንግሥ
አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ጨረቃንና ፀሐይን በእጃቸው እየያዙ ይጸልዩ የነበሩ፣ በመንዝ እና በይፋት ያሉ ክርስቲያኖች ውርጩን በስማቸው የሚገዝቱባቸው ታላቅ የበረከት አባት ናቸው።
በኢየሩሳሌም ለ50 ዓመት፣ በሀገራችን ኢትዮጵያ ለ450 ዓመታት ኑረዋል። እጨጌ ዮሐንስ በአንድ በዓት ተወስነው የሚቆዩት ለ50 ዓመት ነበር። በሀገራችን 5 የተለያዩ በዓቶች ነበሯቸው። በደብረ ሊባኖስ፣ በጠገሮ፣ በአዘሎ፣ በፍርኩታና በሌሎቹም ታላላቅ ቦታዎች ላይ በእያንዳንዱ ገዳም ሃምሳ ሃምሳ ዓመት በጸሎት ኖረው በአጠቃላይ በ500 ዓመታቸው ነው በዛሬዋ ዕለት ያረፉት።
ዐፅማቸው መንዝ ከአርባ ሐራ መድኃኔዓለም አጠገብ ፍርኩታ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ውስጥ ይገኛል።
አቡነ ዮሐንስ ዘጠገሮ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፤ በጸሎታቸው ይማረን!
ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም.

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫየእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክ...
14/05/2026

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶሳዊ በመሆኗ አበው ቅዱሳን በፍትሕ መንፈሳዊና በጉባኤ አድያም ዘአንጾኪያ “ወይኩን ሲኖዶስ ዘጳጳሳት ፪ተ ጊዜያተ በበዓመት - የጳጳሳት ጉባኤም በዓመት ሁለት ጊዜ ይሁን” ብለው በደነገጉት ቀኖና መሠረት፤ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሚመራው፣ የሐዋርያት መንበር ወራሽ የሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤውን በኅብረተ መንፈስ ቅዱስ ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ አካሄዷል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት፤ ስለ ሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነትና ክብር፣ በአጠቃላይ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ሰፊ ውይይቶችን በማድረግ ዘመኑን የዋጁ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ ከውሳኔዎቹም መካከል፡-

የቤተ ክርስቲያናችንን አንድነት መጠበቅና ማስጠበቅ የቅዱስ ሲኖዶስ ተግባር በመሆኑ ጥንታዊትና ሐዋርያዊት የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን በአንድነቷና በሉዓላዊነቷ እንደተረከብናት ለወደፊቱም ሉዓላዊ ክብሯ ተጠብቆ እንድትቀጥል በምልዓተ ጉባኤው የተሠየመው በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራው “የሀገራዊ ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት” ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ በተረጋጋ መንገድ እንዲካሄድ፣ ለሀገር ሰላምና ለሕዝብ አንድነት በሚጠቅም ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምትጸልይ ሲሆን ምርጫው በሁሉም ወገን ለኢትዮጵውያን ዘላቂ ሰላምንና መረጋጋትን የሚያስገኝ ሆኖ እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንዖት ያሳስባል፡፡

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የአርሲ ሀገረ ስብከትን በሊቀ ጵጵስና በቋሚነት እንዲመሩ፣ ሕዝቡን እንዲያጽናኑ እየደረሰ ያለውን ችግር ከቋሚ ሲኖዶስና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከሚመራው የሰላም ኮሚቴ ጋር በመሆን የሚመለከተውን የመንግሥት አካል በማነጋገር ዘላቂ መፍትሔ እንዲያፈላልጉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወስኗል፡፡

ከጥንት ጀምሮ “ቅዱስ ሲኖዶስ” በሚል ርእስ እየተዘጋጀ ይታተም የነበረው ታሪካዊ መጽሔት የቅዱስ ሲኖዶስ ቀኖናዊ ውሳኔዎችን በማካተት በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አስፈጻሚነት ሕትመቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

የቤተ ክርስቲያናችንን ደንቦች መመሪያዎች መርምሮ ማጽደቅ የቅዱስ ሲኖዶስ ሉዓላዊ ሥልጣን በመሆኑ፡-

የስብከተ ወንጌል ሐዋርያዊ ተልእኮ ማስፈጸሚያ ደንብ በብፁዕ አቡነ ማርቆስ ሰብሳቢነት

የአንድነት ገዳማት ኅብረት መተዳደሪያ ደንብ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስና ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ባሉበት በድጋሚ እንዲታይና ሌሎቹም ለውሳኔ የቀረቡ ደንቦች በሊቃውንትና በሕግ ባለሙያዎች ታርመው ለጥቅምት 2019 ዓ/ም ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል

የቀድሞው የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ “የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ”ና “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ” በሚሉ አርእስት አዘጋጅተው ያሳተሟቸው መጻሕፍትን የማሳተምና የማሰራጨት የባለቤትነት መብት ከሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

ከተለያዩ አህጉረ ስብከት በቀረቡ ጥናቶችና የማጣራት ውጤቶች መሠረት፡-

የደቡብ ሱዳን ሀገረ ስብከት ከምሥራቅ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ጋር ተደርቦ በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ሊቀ ጳጳስ እንዲመራ፤
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ሊቀ ጳጳስ የጋምቤላንና የቤንሻንጉል ጉምዝ አህጉረ ስብከትን ብቻ እንዲመሩ፤
ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጰስ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከትን እንደያዙ እንዲቀጥሉ፤
ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከትን ደርበው በአባትነት እንዲመሩ፣
የኮንታ ዞን ሀገረ ስብከት እንዲሆን የቀረበው ጥያቄ የጸደቀ በመሆኑ ሀገረ ስብከቱ ራሱን ችሎ እንዲደራጅና በብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ እንዲመራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የልማት ተግባራትን ምልዓተ ጉባኤው በከፍተኛ ደረጃ በማድነቅ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ/ ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ሲቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ በአባታዊ አመራር የፈጸሙት አስደናቂ የሥራ አፈጻጸም በጉልህ የሚታይ ለውጥ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የሚጠቅም፣ ሉዓላዊ ክብሯን የሚያስጠበቅ፣ ለሁሉም አበው ምሳሌነት ያለው በመሆኑ ምልዓተ ጉባኤው እጅግ ከፍ ባለ ክብር አመስግኗል፡፡

በዚህም መሠረት በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጁ አባታዊ መሪነት እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት ማለትም፡-

የቤተ ክርስቲያንን ቀደምት ሠነዶች በዲጂታል ቴክኖሎጅ እንዲደራጁ የተደረገበት ሥልት ተጠናክሮ እንዲቀጥል፤

ከ1970 ዓ/ም ጀምሮ በመጋዝን ተከማችተው የቆዩ በርካታ ልዩ ልዩ መጻሕፍትን የማሠራጨት ሂደት በተጀመረው መንገድ እንዲጠናቀቅ፤

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የኢንፎርሜሽንና ኮምኒኬሽን ተጠቃሚ እንድትሆን የተጀመረው ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ በሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን መዋቅር በየደረጃው ተጠናክሮ ተግባራዊ እንዲሆን፤

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥር የተጀመሩ የሕንፃ ግንባታዎችና አጠቃላይ የልማት ሥራዎች በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ሁሉም አህጉረ ስብከትና ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦና ትብብር እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንዖት ያሳስባል፡፡

በሰሜን አሜሪካ የሰሜን ካሊፎርኒያ፣ ኔቫዳና አሪዞና ሀገረ ስብከት ኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና ቅድስት አርሴማ ገዳም የመንፈሳዊ ኮሌጅ፣ የአብነት ት/ቤት ሥርዓተ ትምህርት የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ታሪክና ትውፊት በጠበቀ መልኩ ተጠናክሮ መዋቅራዊ ተጠሪነቱም በአግባቡ ተጠብቆ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ያቀረበውን የ2019 ዓ/ም በጀት በማጽደቅ በተገቢው መንገድ ሥራ ላይ እንዲውል ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡

በመጨረሻም ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በተነጋገረባቸው ጉዳዮች በትኩረት የተወያየው የቤተ ክርስቲያናችንን ሁለንተናዊ ዕድገትና ተቋማዊ ሕልውና ስለማስጠበቅ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ሀገራችንን ጨምሮ በመላው ዓለም እየታየ ያለው ግጭትና የሰላም መታጣት በእጅጉ አሳስቦታል፡፡

በመሆኑም ስለ ዓለምና ስለ ሀገራችን ሰላም፣ ስለ ሰው ልጆች ደኅንነት፣ በየቦታው በሃማኖታቸው ምክንያት መከራ የሚደርስባቸውን በየቦታው የሚገኙና ግጭት ባለባቸው ቦታዎች ያሉ ኦርቶዶክሳውያንን በማሰብ በመጪው የ2018 ዓ/ም ጾመ ሐዋርያት በመላው ዓለም ባሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት፣ አድባራትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎተ ምሕላ እንዲደርስ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

በመላው ዓለም፣ በደቡብ አፍሪካና በሳውዲ ዐረቢያ የሚኖሩ ዜጎቻችን ሰብዓዊ መብት እንዲከበር፣ የርኅራኄ ምሕረትና ፍትሕ እንዲያገኙ የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ክትትል እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ጥሪውን በማቅረብ ለሰባት ቀናት ሲያካሂድ የሰነበተውን ቀኖናዊ ጉባኤ ዛሬ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም. በጸሎት አጠናቋል፡፡

“እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ”

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ/ም

Address

Semera
Logya

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አፋር ሀ/ስብከት ሕዝብ ግንኙነት / Afar Diocese public relation, EOTC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share