ማህበረ ናታኒም በኩየራ ደ/ኃ/ቅ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን

  • Home
  • Ethiopia
  • Kuyera
  • ማህበረ ናታኒም በኩየራ ደ/ኃ/ቅ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን

ማህበረ ናታኒም በኩየራ ደ/ኃ/ቅ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ማህበረ ናታኒም በኩየራ ደ/ኃ/ቅ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን, Religious organisation, Kuyera.

ሐምሌ ፭     ☦️አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንኳን ለአእማደ ቤተ ክርስቲያን ለብርሐናተ አለም ቅዱሳን   እና   ለአባታችን ለአቡነ   አመታዊ ክብረ በዓል በሰ...
12/07/2026

ሐምሌ ፭




☦️አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንኳን ለአእማደ ቤተ ክርስቲያን ለብርሐናተ አለም ቅዱሳን እና ለአባታችን ለአቡነ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም እና በጤና እንኳን አብሮ አደረሰን

☦️አንዱ በመስቀል ወደ ታች ተሰቀለ አንዱም የከበረች አንገቱን በሰይፍ ተቆረጠ የዮና ልጅ ጴጥሮስ ደምህ በመስቀል ላይ ፈሰሰ የሐዋርያው ጳውሎስ ደምም በሰማይ መሰከረ የፃድቃን ሞታቸዉ ህይወታቸዉ ነዉ

☦️እንዲሁም በዚህ እለት ፃድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አይናቸዉን ለእርግቧ ዉኃ ጠጭ ብለዉ የሰጡበት እለት ነዉ የፃድቁ ፀሎት ይጠብቀን አሜን

☦️አምላካችን ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ እንዲሁም ከቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት ረድኤትና በረከት ያሣትፈን የአባቶቻችን አምላክ እና ፀሎት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችንን ሀገራችንን ይጠብቅልን

☦️የአባቶቻችንን አሰረ ፍኖት ተከትላችሁ ስትፆሙ የነበራችሁ የተዋህዶ ልጆች ከቅዱሣን ሐዋርያት ረድኤትና በረከት ያሣትፋችሁ እንኳን ፆመ ልጓሙን ፈታላችሁ ለሁላችንም የበረከት በአል ይሁንልን እንኳን አደረሰን "አሜን"

  ግንቦት 16 የአንድ ቀን ልዩ የወንጌል መርሃግብር በኩየራ ደብረ መድኃኒት መስቀለ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን። በዚሀ ታላቅ የወንጌል አገልግሎት ላይ ሁላችውም ተጋብዛችኋል
22/05/2026


ግንቦት 16 የአንድ ቀን ልዩ የወንጌል መርሃግብር በኩየራ ደብረ መድኃኒት መስቀለ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን። በዚሀ ታላቅ የወንጌል አገልግሎት ላይ ሁላችውም ተጋብዛችኋል

06/02/2026

ጥር 27 የማንዘነጋው የማንረሳው ቀን

  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታላቅ አባት የሆኑት እና በቤተክርስቲያኗ የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የቅዱስ ሲ...
26/01/2026



በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታላቅ አባት የሆኑት እና በቤተክርስቲያኗ የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ዛሬ እንዳስታወቀው፣ የብፁዕነታቸው ሥርዓተ ቀብር ነገ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም በተማሩበት፣ በመነኮሱበትና ለረጅም ዓመታት ባገለገሉበት በታላቁ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ይፈጸማል።

ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም በኢትዮጵያ እና በኢየሩሳሌም በሚገኙ የኢትዮጵያ ገዳማት ከፍተኛ መንፈሳዊ አገልግሎት ያበረከቱ ሲሆን፣ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ በመመደብ ተልእኮአቸውን ሲወጡ ቆይተዋል።

ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም (በቀድሞ ስማቸው ጸባቴ ተክለ ሐዋርያት ባሳዝነው) የተወለዱት በሰሜን ሸዋ ዞን፣ በደብረ ብርሃን አውራጃ፣ በነዋሪ ወረዳ ልዩ ስሙ ከያዱር በዓለ ወልድ በሚባል አካባቢ ነው። መንፈሳዊ ትምህርታቸውን በደብረ ብሥራት ዜና ማርቆስ ገዳም የጀመሩ ሲሆን፣ በሰቃ መድኃኔ ዓለም ገዳም ከታላቁ ምሁር መምህር አባ ዘካርያስ ኃይለ ማርያም (የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ) ዘንድ የቅኔና የትርጓሜ መጻሕፍትን፣ እንዲሁም ሥርዓተ ቅዳሴና ሰዓታትን ተምረዋል።

በደብረ ሊባኖስ ገዳም በመግባት ከየኔታ መርዓዊ ሣህለ ሚካኤል ጾመ ድጓን ከነቃል ትምህርቱ የቀሰሙ ሲሆን፣ መንፈሳዊ እውቀታቸውን ለማስፋት ወደ ጎጃም እና ጎንደር በመሄድ የቅኔ ትምህርታቸውን አጠናክረዋል። በደብረ ሊባኖስ ገዳም የዝማሬ መዋሥዕት ትምህርትን የተከታተሉ ሲሆን፣ በገዳሙ የማኅበር አባልነት በመግባትም በአርድእትነት፣ በቅዳሴ እና በተለያዩ አገልግሎቶች ተሳትፈዋል።

ብፁዕነታቸው በደብረ ሊባኖስ ገዳም በነበራቸው ቆይታ የመጻሕፍተ ሐዲሳትን ትርጓሜ ከመምህር ብርሃኑ ወልደ ሥላሴ እና ከመምህር ገብረ ሕይወት ገብረ ኢየሱስ ተምረው አጠናቀዋል። የምንኩስና፣ የቅስና እና የቁምስና ማዕረግን ከተቀበሉ በኋላ፣ በ1994 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ መልካም ፈቃድ የደብረ ሊባኖስ ገዳም አስተዳዳሪ (ጸባቴ) ሆነው ተሾመዋል። በዚህ ኃላፊነት ላይ እያሉ በገዳሙ ውስጥ በርካታ የልማት ስራዎችን አከናውነዋል።

ሐምሌ 9 ቀን 1997 ዓ.ም በተደረገው የጳጳሳት ምርጫ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ሆነው የተመረጡት ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም፣ ቀጥሎም በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ በመሆን አገልግለዋል። ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ።

የብፁዕነታቸው ህልፈት ለቤተክርስቲያኗ እና ለምእመናን ታላቅ ኀዘን መሆኑ ተገልጿል። ሥርዓተ ቀብራቸው ነገ በደብረ ሊባኖስ ገዳም በታላቅ ክብር ይፈጸማል።

የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች በያለንበት ከክፉ ነገር ከድንገተኛ አደጋ ወጥቶ ከመቅረት ይሰውራችሁ ይሰውረን የልባችንን መሻት ይሙላልን በያለንበት ጥበቃው አይለየን አይለያችሁ አሜን!!!የተወደዳችሁ...
09/01/2026

የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች በያለንበት ከክፉ ነገር ከድንገተኛ አደጋ ወጥቶ ከመቅረት ይሰውራችሁ ይሰውረን የልባችንን መሻት ይሙላልን በያለንበት ጥበቃው አይለየን አይለያችሁ አሜን!!!

የተወደዳችሁ ከየትኛውም ዓለም የምትገኙ የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች የ2018 ዓ.ም ጥምቀት በዓል እጅግ በደመቀ ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በላይ በተሻለና በሚያስደስት መልኩ ለማክበር ከታህሳስ መጀመሪያ ጀምሮ እንቅስቃሴ ላይ መሆናችን ይታወቃል፡፡

ሆኖም በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የምተገኙ ውድ የአካባቢው ተወላጆች ከዚህ በፊት ላለፉት ዓመታት በአካባቢው በሚገኙ በጎ አድራጊዎች ድጋፍ የጥምቀት ማውረጃ ቀይ ምንጣፍ፣ሰረገላና ሌሎች ለበዓሉ ድምቀት የሚሆኑ ቁሳቁሶችን በመግዛት በተሻለ አስተምህሮ ስናከብር መቆየታችን ይታወቃል።

ስለሆነም ከዚህ ቀደም ስንጠቀምባቸው የነበሩት ቁሳቁሶች ከጊዜ እርዝማኔ የተነሳ አገልግሎት መስጠት ስላቆሙ አዲስ ግዥ እንዲደረግ ተገደናል።

በመጨረሻም ለዚህ ለተቀደሰ ተግባር ማለትም
👉 ለቀይ ምንጣፍ መግዣ
👉ለማጥመቂያነት የሚያገለግል ወተር ፓምፕ እና ለሌሎች ጥቃቅን ቁሶች መግዣ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የበረከቱ ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ ባላችሁበት ተጋብዛችኋል።

ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇
0916517638
0923890328
0922243759

👉በተጨማሪም በውስጥ መስመር ይፃፉልን።
በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ወረዳ ዳግማዊ ቁልቢ የኩየራ ደ/ሀ/ቅ/ገ/ቤ/ን ህዝብ ግኑኝነት
የኩየራ ፈልቻ ደብር ገነት ቅድሰት ማርያም ቤተክርሰቲያን ሰንበት ት/ ቤት
ZeBete Michael

የአእላፋት ዝማሬ ወደ የአእላፋት ቅዳሴ ሊያድግ ነው:: ጃንደረባው ሚድያ | ታኅሣሥ 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ ኢትዮጵያ* የአእላፋት ዝማሬ በዋዜማው ዋዜማ እንዲካሔድ ተወስኖአል* የአእላፋት...
07/01/2026

የአእላፋት ዝማሬ ወደ የአእላፋት ቅዳሴ ሊያድግ ነው::

ጃንደረባው ሚድያ | ታኅሣሥ 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

* የአእላፋት ዝማሬ በዋዜማው ዋዜማ እንዲካሔድ ተወስኖአል
* የአእላፋት ዝማሬ ቀን የአእላፋት ቅዳሴ ቀን ይሆናል::
* የቅዳሴ ተሰጥዎ ትምህርት ዐቢይ ጾም ላይ ይጀምራል

3ኛው የአእላፋት ዝማሬ በመስቀል አደባባይ በተሳካ ሁኔታ ተካሔደ:: የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና የሸገር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የማኅበራት ምዝገባና ክትትል መምሪያና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ፣ የአዲስ አበባ የሐዲያና ሥልጤ አህጉረ ስብከቶች ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በተገኙበት በዚህ ዝማሬ ላይ የየመምሪያው ኃላፊዎች ፣ የጉባኤ መምህራን ፣ ሰባኪያንና ዘማርያን እንዲሁም በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ምእመናን ታድመዋል::

የአእላፋት ዝማሬው በጃን እስጢፋኖስ በመሐረነ አብ ጸሎት የተጀመረ ሲሆን ጸሎተ ወንጌል ደርሶ የዕለቱ ወንጌል በብፁዕ ሥራ አስኪያጁ ተነብቦ የሰርክ ኪዳን ደርሶአል:: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥን ዋና ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ ዶ/ር አካለ ወልድ ተሰማ የተመራው ጉባኤው በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ቃለ ምዕዳን ተከፍቶአል::

ብፁዕነታቸው በመልእክታቸው "ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከጥንት ጀምሮ በቅዱስ ያሬድ ዜማ በሊቃውንት ድርሰት በዓለ ልደትን ከዋዜማው በመነሣት ሌሊቱን በቅኔ ማኅሌትና በሥርዓተ ቅዳሴ ሐዋርያዊ ትውፊትን ጠብቃ በዝማሬ ስታከብር ኖራለች ዛሬም እያከበረች ትገኛለች፡፡ ይኽንኑ ፍጹም መንፈሳዊ የሆነ የተቀደሰ ትውፊት መሠረት በማድረግ፣ በጌታችን ልደት በዓልምእመናን በተለይም ወጣቶች ከመንፈሳዊ ሥርዓት ውጭ በአልባሌ ቦታዎች ቀኑንና ሌሊቱን እንዳያሳልፉ፣ መዝሙራትን አጥንተው፣ ከዋክብት ብሩሃንን ሆነው የጌታችንን ልደት በምስጋና ለመቀበል መሰባሰባቸው የሚያስመሰግንና በረከትን የሚያሰጥ የተቀደሰ ተግባር ነው" ብለዋል::

የአእላፋት ዝማሬ መድረክ በጥንታዊው የክብ ቤተ ክርስቲያን ቅርፅ የተሠራ ሲሆን በደመራ ቦታው ላይ ደግሞ የቤተልሔም ግርግምን የልደት የብራና ሥዕል በማድረግ ምእመናን ወደ ተወለደበት ሥፍራ ሕሊናቸውን እንዲመልሱ የሚያደርግ ሆኖአል::

ሦስተኛው የአእላፋት ዝማሬ በብፁዕ ሥራ አስኪያጁ አብሣሪነት በይፋ የተከፈተ ሲሆን በጃን እስጢፋኖስ ዲያቆናት ወረብ ተከፍቶ ዐሥራ አምስት መዝሙራት ተዘምረዋል:: በሁለተኛ ዙር ከዲያቆናት "መድኃኒነ ተወልደ ነዋ" የሚል ወረብ በማስከተል ዐሥራ አምስት መዝሙራት ተዘምረው በበኩረ መዘምራን ኪነ ጥበብ ወልደ ቂርቆስ "እንደ ቸርነትህ" ጸሎት ተደርጎ በሰላም ተጠናቅቆአል:: የአእላፋት ዝማሬው ላይ የታደሙት ምእመናን ቁጥራቸው ከተጠበቀው በላይ ቢሆንም የጸጥታ አካላትን ባስደነቀ ፍጹም ሰላማዊ መንፈስና በእርጋታ ወደየ በአታቸው ሔደዋል:: በዕለቱ የታደሙ ምእመናን የጧፍ መባቸውን ለታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም ሠጥተዋል::

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ዘንድሮ በመስቀል አደባባይ ያካሔደውን የአእላፋት ዝማሬ በድኅረ ሁነት ውይይቱ በጥንቃቄ የገመገመ ሲሆን እግዚአብሔር ቢፈቅድ የአእላፋት ዝማሬን ወደ አእላፋት ማሕሌትና የአእላፋት ቅዳሴ ለማሳደግ ሲያወርግ የነበረውን ጥረት በ2019 ዓ.ም. የአእላፋት ዝማሬ ላይ ዕውን ለማድረግ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና ብፁዓን አባቶችን በማማከር ድምዳሜ ላይ ደርሶአል::

የአእላፋት ዝማሬ በመስቀል አደባባይ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ መካሔዱ የታየው አዲስ ነገር የአደባባዩ ጠባይ ፣ የተሳታፊው ብዛት ፣ ሰልፍና ፍተሻው የሚወስደው ታሳቢ ሆኖ ጸሎትና ዝማሬው ብቻ አምስት ሰዓታትን የሚወስድ መሆኑ ፣ ሕዝቡ ከአደባባዩ ለመውጣት የሚፈጅበት ጊዜ ከአክፍሎትና ወደየአጥቢያው ለመድረስ ከሚደረግ ጉዞ ጋር አዳጋች እንደሚሆን ተስተውሎአል::

በዚህ ምክንያት ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ የአእላፋት ዝማሬ አንድ ቀን ቀድሞ በዋዜማው ዋዜማ እንዲደረግና በዋዜማው ዕለት ደግሞ የአእላፋት ቅዳሴ ዘመቻ እንዲጀመር ተወስኖአል:: ይህ መደረጉም ማሕሌት የሚቆሙ ምእመናን ከአእላፋት ማግሥት ዕረፍት አድርገው እንዲቆሙ ፣ ወደ ቅዱስ ላሊበላና ወደ ሌሎች ቅዱሳት መካናት ጉዞ የሚያደርጉም ተሳትፈው በማግሥቱ በረራዎች እንዲሔዱ እንዲሁም ልደትን በቅዳሴ አሳልፈው የማያውቁም በዋዜማው ዝማሬ መንፈሳቸው ለቅዳሴ እንዲዘጋጅ ያበረታታል::

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ጃን ቅዳሴ በተሰኘው ፕሮጀክቱ አማካኝነት ቅዳሴ ለማስተማር ትምህርታዊ ቪድዮ ከመማሪያ ሞጁል ጋር ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን የአእላፋት ሳምንት ዐውደ ርእይ ላይ በ3D Model የቅዳሴ ትዕይንት ለብዙኃን ማስጎብኘቱም ይታወቃል:: ከመጪው ዐቢይ ጾም ጀምሮ ይህንን የቅዳሴ ተሰጥኦ ትምህርት ለምእመናን በይፋ የሚጀምር ሲሆን በ2019 ዓ.ም. በአእላፋት ዝማሬ ላይ የታደመውን ሕዝብ ያህል በየአጥቢያው በቅዳሴ ላይ ተገኝቶ የዝማሬውን ድምፅ በተሰጥዎ ድምፅ እንዲደግም ለማድረግ ዕቅድ ተይዞአል:: ጃን ቅዳሴ ከ፳፬ቱ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ፕሮጀክቶች አንዱ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ ሦስት ዙር የቅዳሴ ተሰጥዎ ተማሪዎችን አስተምሮ አስመርቆአል:: በተቋማት ደረጃ የቅዳሴ ተሰጥዎ ለመማር ጥያቄ ላቀረቡ የሙያ ማኅበራትም እንዲሁ ከሥራ ሰዓታቸው ጋር የተስማማ የመማሪያ መርሐ ግብር ነድፎ በማስተማር ላይ እንደሚገኝ የጃን ቅዳሴ ሰብሳቢ ዲያቆን ኃይለ ኢየሱስ ተሻለ ገልጸዋል::

በመስቀል አደባባይ የተካሔደውን ሦስተኛውን የአእላፋት ዝማሬ ከቀደሙት ሁለት የአእላፋት ዝማሬዎች እጅግ የሚበልጥ ቁጥር ያላቸው ምእመናን የታደሙበት ሲሆን በኦንላይን ደግሞ ሚልዮኖች ተመልክተውታል:: የEOTC TV ፣ ሀገሬ ቲቪ ፣ አርትስ ቲቪ ፣ ቃና ቲቪ ፣ ፋና ቲቪ ፣ ኢቢሲ ፣ አሶሽየትድ ፕሬስ ፣ BBC ፣ ሮይተርስ ፣ ዶቼቬሌ ፣ ቪዮሪ ቲቪ ፣ ስፖትኔክ ሬድዮ ለሦስተኛው የአእላፋት ዝማሬ ሽፋን የሠጡ ሚድያዎች ናቸው::



አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ!...የአእላፋት ዝማሬ
06/01/2026

አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ!...
የአእላፋት ዝማሬ

Address

Kuyera

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ማህበረ ናታኒም በኩየራ ደ/ኃ/ቅ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share