የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰንበት ት/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Kolfe
  • የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰንበት ት/ቤት

የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰንበት ት/ቤት egziabher hayal new

ማንም እንዳይቀር
03/09/2026

ማንም እንዳይቀር

የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰ/ት/ቤት በ2018 ዓ.ም ባለፉት 10 ወራት ያስተማራቸውን የበገና ተማሪዎች ሊያስመርቅ ነው::የምርቃት መርሐግብሩ የፊታችን ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም...
02/09/2026

የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰ/ት/ቤት በ2018 ዓ.ም ባለፉት 10 ወራት ያስተማራቸውን የበገና ተማሪዎች ሊያስመርቅ ነው::

የምርቃት መርሐግብሩ የፊታችን ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ7:30 በሰንበት ት/ቤቱ አዲሱ አዳራሽ ይከናወናል::

በመርሐግብሩ በሁለት ፈረቃ የተማሩ 59 ተማሪዎች የሚመረቁ ይሆናል

በኘሮግራሙ ተመራቂ ተማሪዎችና ወላጆች,ተጋባዥ መምህራንና ዘማሪያን ይገኛሉ::

ከዚህ በተጨማሪ በዕለቱ በ2019 ዓ.ም የበገና ትምህርት ለመማር የሚፈልጉ ምዕመናን እና የሰንበት ት/ቤቱ አባላት የምዝገባ ኘሮግራም ተይዞል::
የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰንበት ት/ቤት

ከሐምሌ 1- ሐምሌ 30 ሲሰጥ የነበረው የክረምት ሥልጠና ፍፃሜ ትናንትና ሰንበት ትምህርት ቤታችን ይህን በሚመስል መልኩ አክብሯል። ለ1 ወር በቼዝ ፣ በሩቢክስ ኪዩብ አፈታት፣ በአባከስ ስሌት...
26/08/2026

ከሐምሌ 1- ሐምሌ 30 ሲሰጥ የነበረው የክረምት ሥልጠና ፍፃሜ ትናንትና ሰንበት ትምህርት ቤታችን ይህን በሚመስል መልኩ አክብሯል። ለ1 ወር በቼዝ ፣ በሩቢክስ ኪዩብ አፈታት፣ በአባከስ ስሌት እና በሂሳብ ትምህርት ሲሰለጥኑ የቆዩ ህፃናት የተማሩትን እውቀት የሚያሳዩበት ውድድር ተካሂዷል ።

በዚህም ውድድር
መክሊት በሰኔ (Rubik's cube)
ረድኤት ስራኔ (Abacus)
ይስሐቅ ተዘራ (Chess) አንደኛ በመውጣት ተሸልመዋል::

ይህ ፕሮግራም ሙሉ በሙሉ የልጆቹን ስኬት ለማክበር የተዘጋጀ ነበር። ለተወዳዳሪዎቹ በሙሉ የተሰማንን ታላቅ ደስታ እየገለጽን፣ ለዚህ በጎ አላማ መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ አስተማሪዎች እና ቤተሰቦች ምስጋናችንን እናቀርባለን።
የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰንበት ት/ቤት

የሰበካ ጉባኤ አባላት ምርጫየፊታችን እሁድ ነሀሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚደረገው የሰበካ ጉባኤ አባላት ምርጫ እድሜያቸው ከ18 ዓመት እስከ 35 ያሉ የሰንበት ት/ቤታችን አባላት የቀበሌ ወ...
21/08/2026

የሰበካ ጉባኤ አባላት ምርጫ

የፊታችን እሁድ ነሀሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚደረገው የሰበካ ጉባኤ አባላት ምርጫ እድሜያቸው ከ18 ዓመት እስከ 35 ያሉ የሰንበት ት/ቤታችን አባላት የቀበሌ ወይም የት/ቤት መታወቂያ በመያዝ በገዳሙ የዕለት ገንዘብ ያዥ ጋር በመሄድ ካርድ መውሰድና በምርጫው መሳተፉ እንደምንችል ተገልፆልናል

የመመዝገቢያ ሰዓት

ዛሬ አርብ ከ10:00 ሰዓት እስከ 1:30
ቅዳሜ ጠዋት እስከ ቅዳሴ ማብቂያ እንዲሁም ምሽት ከ10 ሰዓት እስከ 1:30

ማሳሰቢያ
ምርጫው እሁድ የሚደረግ በመሆኑ በዕለቱ ካርድ መውሰድ አይቻልም

የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በደብረ ታቦር አገልግሎት ላይ የአመት ሰው ይበለን 13/12/2018 ዓ.ም
20/08/2026

የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በደብረ ታቦር አገልግሎት ላይ
የአመት ሰው ይበለን
13/12/2018 ዓ.ም

ለሰንበት ት/ቤታችን አባላትና ምዕመናን በሙሉየሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያንን ባለፍት ሶስት ዓመታት በሰበካ ጉባኤ አመራርነት ሲያገለግሉ የነበሩት አባቶች ወንድሞችና እህቶች የአ...
17/08/2026

ለሰንበት ት/ቤታችን አባላትና ምዕመናን በሙሉ

የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያንን ባለፍት ሶስት ዓመታት በሰበካ ጉባኤ አመራርነት ሲያገለግሉ የነበሩት አባቶች ወንድሞችና እህቶች የአገልግሎት ጊዜያቸውን አጠናቀዋል::

ስለሆነም በቀጣይ ሶስት አመታት ቤተክርስቲያናችንን የሚመሩ በስነ ምግባራቸው,በስራቸው,ለቤተክርስቲያን የሚጠቅሙ አገልጋዮችን ለመምረጥ የፊታችን እሁድ ነሀሴ 17/2018 ዓ.ም ከቅዳሴ በሆላ ምርጫ ለማድረግ መርሐግብር ተይዞል::

ስለሆነም ምርጫው የሚደረገው በካርድ ስለሆነና ዘወትር ጠዋትና ማታ ምዝገባ እየተደረገ በመሆኑ የሰበካ ጉባኤ አባልነታችሁን የሚገልፅ ደብተር በመያዝ እንድትመዘገቡና ለቤተክርስቲያናችን ህልውና የሚጠቅሙ አገልጋዮችን እንድንመርጥ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን::

ችቦዎችን ከሰንበት ት/ቤታችን ይግዙ ይደግፉ !!!እንኳን ለበዓለ ደብረ ታቦር በሰላምና በጤና አደረሰንየሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰ/ት/ቤት የ2018 ዓ.ም የደብረ ታቦር በዓልን ም...
17/08/2026

ችቦዎችን ከሰንበት ት/ቤታችን ይግዙ ይደግፉ !!!

እንኳን ለበዓለ ደብረ ታቦር በሰላምና በጤና አደረሰን

የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰ/ት/ቤት የ2018 ዓ.ም የደብረ ታቦር በዓልን ምክንያት በማድረግ ችቦዎችን በብዛት አዘጋጅቶል::

የአንድ ችቦ ዋጋ 60 ብር ብቻ ሲሆን ከሰንበት ት/ቤታችን በመግዛት ድጋፍ እንድናደርግ እየጠየቅን

ችቦዎቹን የምናገኝባቸው ቦታዎች

1. በሰንበት ት/ቤቱ ሱቅ አጠገብ ከነገ 12/18 ጀምሮ
2. ልኳንዳ 09 ክበብ ፊት ለፊት 13/18
3. የቤተክርስቲን መግቢያ በር ላይ 13/18

ለበለጠ መረጃ
+251913888646
+251913655354
+251916498216

የ2019 ዓ.ም የማጠቃለያ ፈተና ተሰጠየሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰንበት ት/ቤት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከተ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተዘጋጀውን የ4ኛ,8ኛ እና 10 ኛ ክፍል...
03/08/2026

የ2019 ዓ.ም የማጠቃለያ ፈተና ተሰጠ

የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰንበት ት/ቤት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከተ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተዘጋጀውን የ4ኛ,8ኛ እና 10 ኛ ክፍል ምዘና እንዲሁም በመንበረ ፓትርያርክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የተዘጋጀውን የ12 ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና በዛሬው ዕለት ተሰጥቶል::

ለ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች የተሰጠው ፈተና ኮልፌ ላይ ካሉ 36 ሰንበት ት/ቤቶች መካከል ሰዋስወ ብርሃን ብቻ ተማሪዎችን በማስተማር አስፈትኖል::

በዛሬው የፈተና መርሐግብር ሰንበት ት/ቤታችን ለሌሎች ሰንበት ት/ቤቶች የፈተና ማዕከል ሆኖ ያገለገለ ሲሆን በአጠቃላይ
4ኛ ክፍል 54
8ኛ ክፍል 103
10ኛ ክፍል 60
12ኛ ክፍል 34 በድምሩ 251 ተማሪዎችን ተፈትነዋል

በመርሐግብሩ የገዳማችን አባቶች በጸሎተ ወንጌል ፈተናውን ያስጀመሩልን ሲሆን ከክ/ከተማ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተወካዮች ተገኝተዋል::

👂👂👂
02/08/2026

👂👂👂

30/07/2026

Address

Kolfe

Telephone

+251910978168

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰንበት ት/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰንበት ት/ቤት:

Shortcuts

Share