ኡስታዝ ያሲን ኑሩ Yasin Nuru

ኡስታዝ ያሲን ኑሩ Yasin Nuru Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ኡስታዝ ያሲን ኑሩ Yasin Nuru, Religious organisation, Kembolcha.

ይህን ፎቶ ሁላችንም እውነት መሥሎን ተቀባብለነው ነበር ይህ ፍቶ ከ2አመት በፊት የነበረ ነው አቀናብረውት ነው፡፡ግን የሞቱትን እንርሳ እያልኩ አይደለም በጣም አዝነናል መንግስት አፋጣኝ እርም...
21/06/2022

ይህን ፎቶ ሁላችንም እውነት መሥሎን ተቀባብለነው ነበር ይህ ፍቶ ከ2አመት በፊት የነበረ ነው አቀናብረውት ነው፡፡

ግን የሞቱትን እንርሳ እያልኩ አይደለም በጣም አዝነናል መንግስት አፋጣኝ እርምጃ ወስዶ ማሣየት አለበት

03/05/2022

ትዝብት ነው ትርፉ!! (በኡስታዝ በድሩ ሁሴን)
ሁሉም ሰው እንደሚያውቀው፣ ዘወትር በየዓመቱ በአደባባዮች የሚከናወነው የዒድ ሶላት፣ በእስልምና ነባር ባሕል (ሱንና) መሠረት ጨቅላ ሕጻናትን ጨምሮ፤ ሴት ወንዱ፣ ልጅ ዐዋቂው፣ ወጣት አዛውንቱ፣ መላው የሙስሊም ቤተሰብ አባላት፣ አንድም ሰው ሳይጎድል በምልዓት የሚታደሙበት ታላቅ መንፈሳዊ በዓል ነው።
ዛሬ ዕለተ ሰኞ ሚያዝያ 24 ቀን 2014 አዲስ አበባ ስታዲየምን ማዕከል አድርጎ፣ ረጅም ርቀት እና ስፋትን በሸፈነ አካባቢ፣ በግምት ከ1.5 ሚሊዮን የማያንስ የከተማው ሙስሊም ቤተሰብ ግልብጥ ብሎ በመውጣት "አገር ሰላም" ብሎ ታድሞ እንደነበር ሁሉም ተመልክቶታል።
ይኼ ሁሉ ሕዝብ ጢም ብሎ ሞልቶ በተሳተፈበት፣ በተለይ በዚሁ ሰሞን በጎንደር ከተማ ተከስቶ በነበረው ዘግናኝ ነገር በሕዝቡ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረትና ስጋት ባረበበትና ገና ከድንጋጤው ባልተላቀቀበት እንዲሁም ቆፈን ውስጥ በነበረበት በዚህ ወቅት፣ ኁልቖ መሳፍርት ሕዝብ በፈሰሰበት በዚህ ስፍራ፣ እንደ ዐይን እማኞች ምስክርነት ከሆነ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል "ባርቆብኝ ነው፡፡" ባለው ምክንያት አስለቃሽ ጭስ፣ በተሰበሰበው ሕዝብ መካከል ፈንድቶ ሕዝብን ያሸበረና ያስደነገጠ ነገር በመከሰቱ፣ ሰዉ እርስ በርሱ በመገፋፋትና በመረጋገጥ ሊያደርስ ይችል የነበረውን እልቂት ማሰብ ራሱ እጅግ ይዘገንናል።
"በዚህ ክስተት ስንት ሕጻናት፣ ስንት እናቶች፣ ስንት አረጋውያን፣ ስንት ነዳያን፣ ስንት አካል ጉዳተኞች፣ ስንት ታዳጊዎች፣ ስንት ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተረጋግጠው ሊሞቱ ይችሉ ነበር!!! …
በዛሬው ዕለት፣ አላህ በተዓምሩ እንዳይኾን አደረገው እንጂ፣ ይህን እጅግ ከባድ አደጋ ሊፈጥር የሚችል እሳት ተለኩሶ ነበር።"
ከዚህ ክስተት ጋር ተያይዞ እኔን በጣም ያሳዘነኝ፣ እጅግ አድርጎ ያስገረመኝና አንዳንድ ሰዎችን እንድታዘባቸው ያደረገኝ፤ አንዳንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነኝ፣ ጋዜጠኛ ነኝ፣ አክቲቪስት ነኝ ባዮችና የፖለቲካ ፓርቲ አመራር ነኝ ባዮች ሳይቀሩ፦
ከደረሰው አደጋ ጋር ተያይዞ በጣም አሳስቧቸው የነበረውና ተሽቀዳድመው አስተያየት ሲሰጡ የነበረው፣ በዚህ ክስተት ሕጻናት፣ እናቶች፣ አረጋውያን፣ ነዳያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ ታዳጊዎች፣ ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተረጋግጠው ሊሞቱ ይችሉ ስለነበረበት አስደንጋጭ ሁኔታ ሳይሆን፤ ይልቁንም እነርሱን ያሳሰባቸው ከክስተቱ ጋር ተያይዞ ስለተሰባበሩ የመንግሥትና የሕዝብ መስታወቶች ነበር፡፡
እነርሱን ያሳሰባቸው ከየአቅጣጫው በተተኮሰባቸው አስለቃሽ ጭስ ታፍነውና እራሳቸውን ስተው ስለተጠፋፉት በመቶዎች የሚቆጠሩ ጨቅላ ሕፃናትና እናቶች ሳይሆን፤ የራሳችን ንብረት ስለሆኑትና ስለተሰባበሩት መስታወቶች ነው፡፡
እነዚህን ሰዎች ያስደነገጣቸው፣ ጫፍ ላይ ደርሶ የነበረውና በዐሥር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሊያጭድ ተቃርቦ የነበረው የእልቂት ድግስ ሳይሆን፤ ይልቁንም እኛው እራሳችን በከፈልነው ግብር የተሠሩ መስታወቶች መሰባበራቸው ነው ይበልጥ ያስደነገጣቸው፡፡
እውነቱን ለመናገር እነዚህ ሰዎች በሰው ሕይወት ላይ ሊደርስ ይችል ከነበረው እጅግ ዘግናኝ አደጋ ይልቅ ስለተሰባበሩ መስታወቶች የደነገጡ መስለው ለመታየት ጥረት ያደረጉት፣ የእውነት ከሌላው ሕዝብ ይበልጥ እነርሱ ለአገርና ለሕዝብ ንብረት ተቆርቋሪ ሆነው ሳይሆን፦
ይልቁንም ውስጣቸው በሰረጸው ስውር የሃይማኖት ዘረኛነትና ሥር የሰደደ ጥላቻ ምክንያት፣ እነርሱን ለማይመስልና የእኛ አይደለም ብለው ለፈረጁት የሰው ዘር ሕይወት ቅንጣት ታክል ደንታ የሌላቸው በመሆኑ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያዊውን ሕዝበ-ሙስሊም ገጽታ ተሽቀዳድመው ለማጠልሸት ካላቸው ከፍተኛ ጉጉት በመነሳት እንደሆነ ልገነዘብ ችያለሁ፡፡

አስ ሰላት
20/04/2022

አስ ሰላት

ወንድሜ አላህ አፍያህን ይመልስልህ
20/04/2022

ወንድሜ አላህ አፍያህን ይመልስልህ

የጠሮ መስጅድ ወንድሞች‼====================✍ ትናንት ማታ ጠሮ በሚገኘው ዑሥማን ኢብኑ አፋን መስጅድ ውስጥ ዲናቸውን ለመማማር በገቡ የአካባቢው ንጹሕ ሙስሊም ማኅበረሰቦች ላይ የ...
01/04/2022

የጠሮ መስጅድ ወንድሞች‼
====================
✍ ትናንት ማታ ጠሮ በሚገኘው ዑሥማን ኢብኑ አፋን መስጅድ ውስጥ ዲናቸውን ለመማማር በገቡ የአካባቢው ንጹሕ ሙስሊም ማኅበረሰቦች ላይ የተደራጁ ቡድኖች ድብደባ ፈጽመዋል። የሚገርመው የጸጥታ አካላት ወደ ፖሊስ ጣቢያ የወሰዱት ውስጥ ላይ በሰላም ቁጭ ብለው እየቀሩ ያሉ ወንድሞችን ነው። ምናልባትም ማታ ምሽት ላይ ወደ ቤታቸው ሲያቀኑ ውጭ ላይ እየጠበቋቸው በነበሩት ወንበዴዎች ጥቃት እንዳይደርስባቸው ተብሎ ታስቦ ከሆነ መልካም ነው። አለበለዚያ እንደ ጥፋተኛ ታይተው ከሆነ ግን እነዚህን ያሰረው አካል እነዚያን «ሂዱና ደብድቧቸው፣ አለንላችሁ!» ብሎ የላካቸው ነው ብለን ለማሰብ እንገደዳለን።

ለማንኛውም ወንድሞቻችን በአሁኑ ወቅት 18 ድልድይ 10ኛ ወጣት ማዕከል ስለሚገኙ፤ ማታ ሳያስቡት ለቂርኣት እንደመጡ በዛው ነውና ድበደባ የደረሰባቸው ራትም ሆነ ቁርስ ስላላገኙ የምትችሉ ሁሉ ወደ ቦታው በማቅናት ዘይሯቸው። ከተደበደቡ ወንድሞች መካከል አስቸኳይ ሕክምና የሚያስፈልጋቸውም አብረው በዚሁ ማዕከል ውስጥ ይገኛሉ። የያዟቸው የጸጥታ አካላት ከጥቂት ቆይታዎች በኋላ ይለቋቸዋል ብለን እንጠብቃለን። ይህ ካልሆነ ግን ሌላ ሚስጥር አለ ማለት ነው።

ምክንያቱም ወንጀለኛ ማለት መስጅድ ውስጥ ቁጭ ብሎ በሰላም የሚቀራ ሳይሆን ከመስጅድ ውጭ የድብደባ መሳሪያዎችን ይዞ የመስጅድ ውስጥ ሰዎችን የሚደበድብ ቡድን ነው።


✔ በዚሁ አጋጣሚ በነዛ በኩል «ሙኣዚኑን ደበደቡ፣ መስጅድ ውስጥ በፌስታል ድንጋይ ይዘው ገቡ፣ በጫማ ገቡ፣ አስቀድመው አስበውበት ነው…!» ወዘተ በማለት የሚያያዟቸውን ምስሎች በተመለከተ ያለውን እውነታ ላካፍላችሁ።

እንደሚታወቀው ከአሁን በፊትም ከ"ሐጂ" ጦሃ ሃሩን የጥላቻ ሰበካ በኋላ በዚሁ መስጅድ ብጥብጥ መከሰቱ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።
በዚያ የተነሳ ቂርኣት ተቋርጦ ስለነበር ትናንት የአካባቢው ሙስሊሞች የተቋረጠውን ቂርኣታቸውን ቀጠሉ። እነዚህ የተደራጁ የነ ጦሃ ቡድኖች በባዶ እጃቸው ገቡና በጥፊውም በእርግጫውም በመደብደብ ለማስቆም ሞከሩ። ሳይሳካላቸው ቀሩና ተመለሱ። ወንድሞችም ቂርኣታቸውን ቀጠሉ።
ይህ የመጀመሪያው ዙር ድብደባ ወንድሞችን ስላላስቆማቸው የነ ጦሃ ቡድኖች ለመስጅዱ እድሳት የተከማቹ እንጨቶችን በመያዝና ስለታማ ነገር በመጨመር ለሁለተኛ ዙር ድብደባ ገቡ። በርካታ አንጋፋ አባቶችንና ወጣቶችን በያዙት መሳሪያ ደበደቡ። ወንድሞችም የነፍሰ ደማቸውን ከሞት ለማምለጥ ሲፍጨረጨሩ እነዚያ ለመደብደቢያ የያዙትን ቁሳቁስ አቅም ያለው በመቀማት ራሳቸውን ተከላከሉ። በዚህ ወቅት ከሁለቱም ወገኖች የተደበደበ መኖሩ የማይታበል ሐቅ ነው። በዚህ ሁለተኛው ዙርም የተደበደበው ተደብድቦ የተረፈው ቂርኣቱን ቀጠለ። በሚዘዋወሩት ምስሎች ላይ ፌስታልም ይሁን ጫማ የለበሱ ሰዎች የሚታዩት ከዚህ በኋላ ነበር። የሚታዩት ድንጋዮችና እንጨቶችም የነ ጦሃ ቡድኖች ውስጥ ላይ የሚቀሩ ወንድሞችን ለመደብደብ ይዘዋቸው የገቡትና በኋላ እነዚህኞቹ ራሳቸውን ሲከላከሉ ደማቸውን አፍሰው የቀሟቸው ናቸው።

ያለው እውነታ ይህ ነው። እንጂማ ምንም በሌለበት ቦታ ቂርኣት ለመቅራት በጫማ የሚገባ፣ ድንጋይና እንጨት ሰብስቦ የሚገባ ሙስሊም አለ ተብሎ ይታሰባልን?

ቢያንስ አላህን እንፍራ‼ በተጎዱ ሰዎች ደም አንሳለቅ። ከብጥብጥ ጉዳት እንጂ ቅንጣት ትርፍ የለም። የመንግስት የጸጥታ አካላትም የተያዙትን ንጹሐን ወንድሞች ለቀው በምትኩ ነገሩን በጥልቅ በማጣራት ከላይ እስከ ታች ከዚህ ረብሻ ጀርባ እነማን እንዳሉ ይድረሱበትና ለወደፊቱም የማያዳግም እርምጃ ሊወስዱ ይገባል።

እንድህ አይነት ሰወች ናቸው አሁን መጅሊሱን እየመሩት ያሉት ኢን ሻ አላህ ሁሉም ይስተካከላል
31/03/2022

እንድህ አይነት ሰወች ናቸው አሁን መጅሊሱን እየመሩት ያሉት ኢን ሻ አላህ ሁሉም ይስተካከላል

ዐይኑል ሀያትዐይኑል ሀያት ወይም ምንጨ-ህይወት ስለተሰኘው ውሀ ሚስጥር እንድፅፍ እጅግ በርካታ መልዕክቶች ከረጅም ግዜ ወዲህ በውስጥ መስመር ደርሰውኛል። እነሆ! ተከታተሉት።ዐይኑል ሀያት በታ...
29/03/2022

ዐይኑል ሀያት

ዐይኑል ሀያት ወይም ምንጨ-ህይወት ስለተሰኘው ውሀ ሚስጥር እንድፅፍ እጅግ በርካታ መልዕክቶች ከረጅም ግዜ ወዲህ በውስጥ መስመር ደርሰውኛል። እነሆ! ተከታተሉት።

ዐይኑል ሀያት በታችኛው ምድር ላይ የሚገኝ የውሃ ምንጭ ሲሆን፤ እሷን ምንጭ የቀመሰ ሰው ህይወት እስኪሰለቸው ድረስ የመኖር ቃል ኪዳን ከጌታው ዘንድ እንደተገባለት የታሪክ መዛግብት ያትታሉ።

በሰው ልጅ ታሪክ ይህችን ምንጭ አግኝቶ ለመጠጣት የሞከሩ ሰዎች እልፍ አዕላፍ ቢሆኑም የተስካለት ግን ሰዪዲና ከድር በመባል የሚታወቁት ደግ የአላህ ባርያ ብቻ ናቸው።

እንዴት ሊያገኙት ቻሉ?

ከብዙ ሺህ አመታት በፊት ዚል ቀርነይን የተሰኘ መልካም የአላህ ባርያ እና ምድርን ከምስራቋ እስከ ምዕራቧ የገዛ ንጉስ ነበር። ለዚህ ንጉስ ሩፋኢል የተባለ የመልአክ ወዳጅም ነበረው።

ከእለታት አንድ ቀን ንጉስ ዙል ቀርነይን ከመልአኩ ጋር እያወጉ ሳለ ንጉሱ የሰማይ ጫዋታ ማንሳት ፈለገ'ና፦‹‹በሰማይ አለም አምልኮአችሁ እንዴት ነው›› ሲል መልዐኩን ጠየቀው።

መልዐኩም፦‹‹አወይ! ዙል ቀርነይን! የኛ አምልኮ ከእናንተው ሲነፃፀር እኮ የእናንተው አምልኮ እዚህ ግባ አይባልም።

ይኸውልህ! እኛ ሰማያት አለም ብዙ ጉድ ነው ያለው። ሱጁድ ያደረጉ መላዕክትን ታያለህ፤ ግና ለዘለአለም ቀና አይሉም። ሩኩዕ የደረጉትንም ታያለህ፤ ግና ለዘለአለም ቀና አይሉም። ቁመው የሚያመልኩትንም ታያለህ ፤ ግና ለአፍታ እንኳ አያጎበድዱም።

ከዚህም ጋር እንዲህ ሲሉ አላህን ያወድሱታል "ጌታችን ሆይ! አንተ የቅድስና ንጉስ ስትሆን ጥራት ይገባህ። የመላዕክት እና የመንፈሱ ጌታ ሆይ እሚጋባህን አምልኮ አላመለክንህም ›› ሲል የሰማያት አለም ወግ አጫወተው።

ንጉሱ አለቀሰ።
ወደ መልአኩም ዙሮ፦‹‹እኔ ህይወት ቢረዝምልኝ ና ለጌታዬ እሚገባውን አምልኮ ባደርግለት ምንኛ ደስ ባለኝ›› አለ።

መልአኩም፦‹‹እውነት ይህን ትሻለህን?›› ሲል ጠየቀው።
ንጉስም፦‹‹አዎን›› አለው።
መልአኩም፦‹‹ምድር ላይ እኮ አንዲት ምንጭ አለች፤ የህይወት ምንጭ በመባል የምትታወቅ ስትሆን አላህም እሷን ለቀመሰ ሰው ህይወትን እስካሻው ሊቸረው ቃል ገብቷል›› አለው።

ዙል ቀርነይን በጉጉት ስሜት ሁኖ፦‹‹ቦታውን ታውቀዋለህን?›› ሲል መልዐኩን ጠየቀው።
መልዐኩም፦‹‹ቦታውን እንኳ አላውቅም ግና በሰማያት አለም ሲወራ እንደሰማሁት ምድር ላይ አንድ ፅልመት አለ፤ ያችን ፅልመት የሰው ልጅም ሆነ የጂን ኮቴ አልደረሰባትም። ምናልባት የህይወት ምንጯ መገኛዋ እዝያ ፅልመት ውስጥ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ›› ብሎ ነገረው።

ንጉስ ጉጉቱ እጅግ ጨመረ። ስለዚህ ምንጭ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማደራጀት ፈልጎ በአለም ላይ ያሉ የሀይማኖት ምሁራንን እና የታሪክ አዋቂዎችን ሰበሰበ።

‹‹ጌታችሁ ባወረደው መፃህፍት እና ነብያቶች ከተናገሯቸው ትውፊቶች ውስጥ ዐይኑል ሀያት የተሰኘ ነገር አይታችሁ ታውቃላችሁ?›› ሲል ጠየቃቸው።

የሁሉም ምላሽ፦‹‹አናውቅም›› የሚል ነበር።

አንድ ሰው ፈንጠር ብሎ፦‹‹እኔ አውቃለሁ። አደም ይህን ስፍራ ለልጆቹ ተናዟል። አላህ ምድርን በፈጠረ ግዜ ጂንም ሆነ ሰው ያልረገጠውን ፅልመት ፈጠረ። በዝያ ፅልመት ውስጥም ዐይኑል ሀያት/የህይወት ምንጭን አመነጨ›› ሲል ትናገረ።

‹‹ታድያ ምንጯ የት እንደሆነች አልተናዘዘም?›› ሲል ንጉስ ጠየቀ።
‹‹ተናዟል። ፅልመቱ በፀሀይ መጥለቅያ ቀንድ ላይ ይገኛል›› ብሎ መለሰለት።

ንጉስ ከየክፍላተ አለሙ ያሉ ንጉሶችን እና ምሁራንን አስከትሎ ጉዞ ወደ ፀሀይ መጥለቅያ ቀንድ ጀመረ።

ያለማቋረጠ ለ12 አመታት ከተጓዙ በኋላ ይፈልጓት የነበረችውን ፅልመት ከፀሀይ መጥለቅያ ቀንዱ ዘንድ

⚈ በመንግሥት አይዞህ ባይነት በሙስሊሙ ድርጅት ላይ ያሻቸውን የሚያደርጉት ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ለምንም ዓይነት ሕግ ተገዢ አለመሆናቸውን ካስመሠከሩበት ክስተት አንዱ ቦርዱ እንዲባረር ማድረጋቸው ...
28/03/2022

⚈ በመንግሥት አይዞህ ባይነት በሙስሊሙ ድርጅት ላይ ያሻቸውን የሚያደርጉት ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ለምንም ዓይነት ሕግ ተገዢ አለመሆናቸውን ካስመሠከሩበት ክስተት አንዱ ቦርዱ እንዲባረር ማድረጋቸው ሲሆን ቦርዱን ካስጠመዱት ተግባራት አንዱ ደግሞ ለዘመናት በሙስና ሲጨማለቅ የኖረው መጅሊስ በግልጽ ጨረታ በውጭ ኦዲተር ኦዲት እንዲደረግ ጥረት ማድረጉ ነበር!
በወቅቱ ሐጂ ዑመር በሰርቲፋይድ ኦዲተሮች ብዙ ተለፍቶበት የተሠራውን የኦዲት ሪፖርት ❝ጅብሪልም ቢመጣ የኦዲት ሪፓርት አልቀበልም❞ ብለው መዛታቸውን ቦርዱ በደብዳቤ አሳውቆ ነበር። እንደፈለጉትም ኦዲቱን ከማስቀረት አልፈው ጠቅላላ ጉባዔ እንዳይደረግ ለዓመታት አግደው ቆዩ። የቀድሞ መጅሊሱን ሙሰኛ የፋይናንስ አሥተዳደር በድጋሚ አምጥተው ሾሙ።
ከጀርባ የዶ/ር ዐቢይ መንግሥት በሚሰጣቸው ማደፋፈሪያ እስካሁንም ቦርዱን በጉልበት እና በማናለብኝነት ያገዱ ሲሆን በትናንትናው ዕለትም ጠቅላላ ጉባዔው ይህንኑ ሕገ ወጥነት ለመቀልበስ ያደረገውን ሙከራ ❝ተጠሪነቴ ለእናንተ አይደለም❞ ብለው አግደዋል። የመንግሥት ተወካዩዋም ይህንኑ አስፈጽመዋል።
ሙፍቲው አይዞህ የሚላቸውን መንግሥት ተማምነው ❝ምን ታመጣላችሁ❞ እያሉ ነው! በሕዝበ ሙስሊሙ ላይ እየቀለዱ ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ራሳቸው መሆናቸው በሁሉም ዘንድ ሊታወቅ ይገባል!
#እስልምናጉዳዮች #መጅሊስ #ባለቁልፉ #ዐቢይአሕመድ

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑንInnaa lillaahi wa innaa ilayhi Raaji'un. ✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿ኢማም ሙሳ ያሲን ወደ አኼራ ሄደዋል።  አላህ ይዘንላቸው፣ ቀብራቸውን ኑር ...
24/03/2022

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን
Innaa lillaahi wa innaa ilayhi Raaji'un.
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿

ኢማም ሙሳ ያሲን ወደ አኼራ ሄደዋል። አላህ ይዘንላቸው፣ ቀብራቸውን ኑር ፣ ማረፊያቸውንም በጀነተል ፊርዶስ ያድርግላቸው::
Imaam Muusaan gara Aakhira adeemaniru. Allaahin isaanif haraaramufi. Rabbin Qabri isaani nuura jannatal firdawus bakka qubannaa isaani taasisinfi.

22/03/2022
በጦርነቱ ምክኒያት እልፍ መሳጅዶች ወደሙ : አያሌ ዑለማዎች ተፈናቀሉ : በድርቅ ምክኒያት እልፍ ሙስሊሞች ተራቡ ታረዙ :: እልፍ የሚሽነሪ ድርጅቶች በቢሊየን በጀት መድበው ወደ "ስራ " ገቡ...
22/03/2022

በጦርነቱ ምክኒያት እልፍ መሳጅዶች ወደሙ : አያሌ ዑለማዎች ተፈናቀሉ : በድርቅ ምክኒያት እልፍ ሙስሊሞች ተራቡ ታረዙ :: እልፍ የሚሽነሪ ድርጅቶች በቢሊየን በጀት መድበው ወደ "ስራ " ገቡ :: የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መሪ የሆነው መጅሊስ ምን አደረገ ? ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የሚያስተባብራቸው የሚያቀናጃቸው ካገኙ ታሪክ እንደሚሰሩ አሳይተዋል ::
በዚህ ሁሉ መካከል የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መሪ ድርጅት የሆነው መጅሊስ የት ነው ያለው ??

ለኔ መጅሊስን የምፈልገው ህዝበ ሙስሊሙን አስተባብሮ የተጎዱ ሰዎችን እምባ እንዲያብስ ነው:: ህዝብን አስተባብሮ ኸይር ስራ እንዲያሰራ ነው:: ማንም ይምጣ ማንም ይሂድ ለኔ ከግለሰቦች ጉዳይ የለኝም :: ነገር ግን ይህን ህዝብ የሚመጥን ተቋም ሊኖረን ይገባል ::

እርስዎ ምን ይጠብቃሉ?የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤወን የዛሬ ሳምንት መጋቢት 17፣ 2014 በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ቅጥር ግቢ ይካሄዳል:...
22/03/2022

እርስዎ ምን ይጠብቃሉ?
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤወን የዛሬ ሳምንት መጋቢት 17፣ 2014 በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ቅጥር ግቢ ይካሄዳል::

ጠቅላላ ጉባኤው በአብዛሃኛዎቹ የክልል ምክር ቤቶች እና በፌዴራል መጅሊስ 2/3ኛ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ጥያቄ መሰረት መሆኑ ታውቋል::
ከዚህ በጉጉት ሲጠበቅ ከነበረ ጉባዔ እርስዎ ምን ይጠብቃሉ?

Address

Kembolcha

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኡስታዝ ያሲን ኑሩ Yasin Nuru posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share