08/08/2022
በጾም እግዚአብሔርን መለመን እንዴት እንደሚጠቅም::
ከዚህም ነገር በኋላ በፋርስ ንጉሥ በአርጤክስስ መንግሥት ዕዝራ.. ከባቢሎን ወጣ፤ ፤ የእስራኤልም አምላክ እግዚአብሔር በሰጠው በሙሴ ሕግ ፈጣን ጸሐፊ ነበረ፤ የአምላኩም የእግዚአብሔር እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና ንጉሡ የሻውን ሁሉ ሰጠው።
ከእስራኤልም ልጆች.. በንጉሡ በአርጤክስስ በሰባተኛው ዓመት አያሌዎች ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ (ዕዝራ 7) ።
ወደ አኅዋም ወደሚፈስስ ወንዝ ሰበሰብኋቸው፥ በዚያም ሦስት ቀን ሰፈርን.. በአምላካችን ፊት ራሳችንን እናዋርድ ዘንድ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅሁ።
ንጉሡንም፡- የአምላካችን እጅ በሚሹት ሁሉ ላይ ለመልካም ነው፤ ኃይሉና ቍጣው ግን እርሱን በሚተዉ ሁሉ ላይ ነው ብለን ተናግረን ነበርና በመንገድ ካለው ጠላት ያድኑን ዘንድ ጭፍራና ፈረሰኞች ከንጉሡ እለምን ዘንድ አፍሬ ነበርና። ስለዚህም ነገር ጾምን፥ ወደ እግዚአብሔርም ለመንን፤ እርሱም ተለመነን።
በመጀመሪያውም ወር በአሥራ ሁለተኛው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም እንሄድ ዘንድ ከአኅዋ ወንዝ ተነሣን የአምላካችንም እጅ በላያችን ነበረ፥ በመንገድም ከጠላትና ከሚሸምቅ ሰው እጅ አዳነን። ስለዚህም ነገር ጾምን፥ ወደ እግዚአብሔርም ለመንን፤ እርሱም ተለመነን። ..በመንገድም ከጠላትና ከሚሸምቅ ሰው እጅ አዳነን። ወደ ኢየሩሳሌም ደረስን ( ዕዝራ 8 ÷ 15 – 32 ) ::
ማብራሪያ
አይሁድ እግዚአብሔርን በመበደላቸው እንዲመለሱና ጣዖት ማምለክ እንዲተዉ ደጋግሞ ቢናገራቸውም ባለመስማታቸው ለ70 ዓመት እንዲማረኩ አደረጋቸው፡፡ ከ70 ዓመት በኋላ የተወሰኑት የመጀመሪያዎቹ ተመላሾች ወደ ሀገራቸው መጡ፡፡ ቆይቶ ደግሞ ሌሎች ተመላሾች ከካህኑ ዕዝራ ጋር ተመልሰዋል፡፡
አይሁድ 70 ዓመት የተማረኩት በባቢሎናውያን ሲሆን ባቢሎን ደግሞ በፋርስና በሜዶን ስር ወደቀች፡፡ በመጨረሻ የፋርስ መንግሥት አይሁድ ያሉበትን የባቢሎንን ግዛት ብቻውን ያዘ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ተመላሾች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ያደረገው የፋርሱ ንጉሥ ቂሮስ ነበር፡፡
የፋርስ ንጉሥ አርጤክስ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ፣ የመጀመሪዎቹ የምርኮ ተመላሾች አገራቸው ከገቡ ከብዙ ዓመት በኋላ ዕዝራና ሌሎች አያሌ ሰዎች ወደ ሀገራቸው ለመሄድ በንጉሡ አርጤክስ ይሁንታ አገኙ፡፡ እነ ዕዝራ በመንገድ ሲጓዙ ከሽፍታ የሚጠቡቁአቸው የንጉሥ ወታደሮችና ፈረሰኞች ያስፈልጓቸው ነበር፡፡
ዕዝራ ዘራፊዎች በመንገድ እንደሚያጋጥሙት ቢያውቅም በዚህ ጉዳይ እግዚአብሔር እንደሚያድናቸው ለንጉሡ አርጤክስ ቀድሞ ነግሮት ነበር ፡፡ የኋላ ኋላ የሚጠብቋቸው የንጉሥ ወታደሮች እንደሚያስፈልገው ቢያምንም ንጉሡን መልሶ መጠየቁ አሳፈረው፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ይጠብቀናል ብሎ ተናግሮ ነበርና፡፡
ዘራፊዎች ቢያጋጥሙአቸው ራሳቸውን ለመከላከል ምንም አቅም አልነበራቸው፡፡ የዘራፊዎች ጉዳይ ዕዝራን ስላሳሰበው ተስፋቸው እግዚአብሔርን ብቻ መለመን እንደ ሆነ ተገንዝቦ በመንገድ ላይ እያሉ ዕዝራ ጾም አወጀ፡፡ የጾሙ ዓላማ
1) በአምላካቸው ፊት ራሳቸውን ለማዋረድ
2) እግዚአብሔር ጉዞአቸውን እንዲያቀናላቸው
3) እግዚአብሔር መላውን ተጓዦችና ልጆቻቸውን ፣ ንብረታቸውንም ከጠላት እንዲጠብቅ ነበር፡፡
በጾምና በጸሎት የለመኑት አምላክ ተለመናቸው፡፡ እንደ ለመኑት ከዘራፊዎች ጠብቆ ወደ ሀገራቸው አስገባቸው፡፡
ዕዝራ ምስክርነቱን ሲሰጥ እንዲህ ነበር ያለው፡-
ስለዚህም ነገር ጾምን፥ ወደ እግዚአብሔርም ለመንን፤ እርሱም ተለመነን ( ቁ 23) ። በመንገድም