Jimma Emmanuel United Church

Jimma Emmanuel United Church የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እን?

የተዓምራትና የተሐድሶ ኮንፍራንስ በጅማ አማኑኤል ቤ/ክጅማ ከተማ።ከመስከረም 20-22አድራሻ፡ መንደራ ባለው ቤ/ክ
28/09/2022

የተዓምራትና የተሐድሶ ኮንፍራንስ በጅማ አማኑኤል ቤ/ክ
ጅማ ከተማ።
ከመስከረም 20-22
አድራሻ፡ መንደራ ባለው ቤ/ክ

18/03/2022
Loding  ....
04/09/2021

Loding ....

የ ገና በዓል  የልጆች አገልግሎት ቆጪ አጥቢያ
10/01/2021

የ ገና በዓል የልጆች አገልግሎት ቆጪ አጥቢያ

የነሐሴ ወር  የፆምና የፀሎት ፕሮግራማችን ዛሬ በታላቅ ምስጋና  እግዚአብሔር እረድቶን አጠናቃናል።የ2013 የዓመቱ መሪ ቃል                      #3፤1-17             ...
05/09/2020

የነሐሴ ወር የፆምና የፀሎት ፕሮግራማችን ዛሬ በታላቅ ምስጋና እግዚአብሔር እረድቶን አጠናቃናል።
የ2013 የዓመቱ መሪ ቃል
#3፤1-17
እንግዲህ ለንሰሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ

መጥመቁ ዮሀንስ ስለ ራሱ የሚውቀው ነገር ቢኖር በነብዩ የተባለለትን በምድረበዳ የሚጮህ ሰው ድምጽ መሆኑን ነው ሲጠይቁትም የሚመልሰው ይህንኑ ነው፡፡ይሄ ስም ለምን እንደተሰጠው የሚያወቅ ማንም ያለ አይመስልም፡፡ ከመንፈሳዊ እውነት እርቀው የአምልኮ ቤትን የንግድ ማዕከል ባደረጉ የሀይማኖት መሪዎች ለሚመሩ ህዝቦች መልእክት ይዞ የመጣ ሰው ስለነበረ የህዝቡ ልብ ለመስማት የራቀ በመሆኑ ሰሚ የሌለው በምድረ በዳ የሚጮህ አይነት ሰው አስመሰሎታል፡፡ይህ ሰው ግን ጩኸቱን አላቆመም ጥዋት ተነስቶ መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንሰሐ ግቡ እያለ ይጮሃል በየመንገዱ ይህንኑ ድምጽ ያሰማል፡፡ጨኸቱ ሰሚ ማግኘት ጀምሮ አገር ሁሉ በሚመስል ሁኔታ ሰወች ወደ እርሱ መምጣትና የንሰሀ ጥምቀት መውሰድ ጀምሩ እልፍ ሲልም እነኛ አንቱ የተባሉት የኃይማኖት አስተማሪዎች ሰዱቃውያንና ፈሪሳውያን ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ አየ በዚህ ጊዜ ነበር ድንገት ትዕዛዝ አዘል ቃል የተናገረው እንግዲህ ለንሰሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ ፡፡ ይህንን ፍሬ እግዚአብሔር ከግለሰብ ከቤተስብ ከቤተክርስቲያን ከአገር ይፈልጋል፡፡
ስለነስሀ የአይሁድ ማህበረሰብ ብዙ ያውቃል ዛሬ ግን የተጠየቁት የንሰሐ ፍሬ ነው ይህንን የሚፈልገው ደግሞ አምላካቸው ነው፡፡ ይህ ፍሬ የሕይወትን አቅጣጫ የሚለውጥ ከሀይማኖታዊ ስርዓት ፈጻሚነት ወደ መለኮታዊ የህይወት ልምምድ የሚስገባ በር ነው ስለዚህም ነው መጥመቁ ዮሀንስ ከእኔ በኃላ የሚመጣው . . . በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኃል ያላቸው፡፡
በህይወታችን መንፈሳዊ ምሪት መንፈሳዊ ጉብኝት የሚገኝበት አልፎም እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት የምንችልበት ብቸኛው መንገድ ንሰሐ ቢሆንም ውጤት ያለው ግን ፍሬ አስከትሎ ሲመጣ ነው፡፡እግዚአብሔርም ሰውም ከኛ ሕይወት ፍሬ ይፈልጋሉ እኛም ፍሬው በእኛ ሕይወት እንዲገኝ ወደ ቃሉን መንፈሱ ጠልቀን መግባት ያስፈልገናል፡፡ አይሁዶች አብረሀም አባት አለን ብለው የሚመኩ ነበሩ ይህ ለንሰሀ ፍሬ እንደማያመጣላቸው አውቀው ሁሉን በሚችል እግዚአብሔር መታመንና መደገፍ እንዳለባቸው ሁሉ እኛም ከራሳንን ብርታትና ኃይል ሳይሆን በጌታ ተደግፈን ፍሬ የምናይበት ጊዜ እነዲሆንልን አይኖቻንን ከብቃታችንና ከድካማችን አንስተን በእርሱ ላይ እናድርግ፡፡
ቃሉና መንፈሱ በሕይወታችን ፍሬ መግኘት የሚቻልበትን ፀጋ ይሰጡናል፡፡ፀጋው አቅም አለው መለኮታዊ ብቃት ነው በክርስቶስ የተሰራልንን ስራ በእኛ የሚገልጥ መለኮታዊ ስጦታችን ነው ስለዚህ ፍሬያማ ሊያርገን የሚችል ከእግዚአብሔር የሆነ የሚረዳን የሚያስችለን ኃይል እኛ ውስጥ አለ፡፡
የንሰሀ ፍሬ ወደ ተከፈተ ሰማይ ይዞን ይሔዳል በዚያ ደግሞ ግንኙነታች ከመለኮታዊው መንፈስ ጋር ይሆናል ያን ጊዜ በምድር የምንኖር በመለኮታዊ አስተዳደርና ምሪት የምንመላስ እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝብን ልጆቹ እንሆናለን፡፡
እግዚአብሔር ይባርካችሁ ፊቱን ያብራላችሁ ሰላሙንም ይስጣችሁ !
ኢየሱስ ጌታ ነው!
አሜን

የነሀሴ 21/2012ዓ/ም  የጸሎት  ክፍል ነህምያ  ምዕራፍ  8፤1-18    የቅጥሩን  አጠቃላይ  ስራ  ጨርሶ  በሮችን  ከገጠመ  በኃላ  በህዝቡ  ህይወት  ላይ  መሰራት  ያለበትን ስራ ...
29/08/2020

የነሀሴ 21/2012ዓ/ም የጸሎት ክፍል ነህምያ ምዕራፍ 8፤1-18
የቅጥሩን አጠቃላይ ስራ ጨርሶ በሮችን ከገጠመ በኃላ በህዝቡ ህይወት ላይ መሰራት ያለበትን ስራ ለመስራት ተነሳ በዚህ ምዕራፍ ህዝቡ ወደ ህጉ ቃል የተመለሰበት ክፍል ነው፡፡የረሳውን ቀድሞ የነበረው ህጉን መስማትና ምላሽ መስጠት እንደገና ሲጀመር ለብዙ ዘመን የተቐረጠውን የደስ በዓል በማድረግ ወደ ታላቅ ደስታ መመለሱ ዕለት ዕለት የህጉን ቃል ለመስማት ታላቅ ጉባኤ መሰምሰቡን እናገኛለን፡፡
ስለዚህ እንዲህ እንጸልያለን
1. እግዚአብሔርን ማወቅ እንዲሆንልን የቃሉ ጥማት ለህዝቡ ነፍስ እንዲሰጥ ቃሉን የሚግልጥ የቃሉን ብርሀን የሚሰጥ መንፈስ እንዲሆንልን
2. ቃሉን የሚስተወል ለቃሉ ክብር የሚሰጥ ልብ እንዲሆንልን
3. ቃሉን የሚያደርግ በቃሉ የሚኖር ህይወት እንዲኖረን
4. የተውናቸውን የረሳናቸውን መልካም የሆኑ መንፈሳዊና ወደጌታ የሚያቀርቡንን ለቃሉ ክብር እንድንሰጥ ወደሚያደርጉ የህይወት ልምዳን እንድንለስ እንዲረዳን
5. በምድሪቱ ላይ ለእግዚአብሔር ቃል ክብር እንዲሰጥ የሚያርግ መንፈስ እንዲሰጠን
6. ከቃሉ የተነሳ ወደምገኝ ደስታና እርካታ እንዲያስገባን
እግዚአብሔር የጸሎት መንፈስ ይስጣችሁ
join our telegram channel

8/12/12   አርብ ምሽት ከመጋቢ ሲሳይ ተፈራ ጋር የቀጥታ ስርጭት
11/08/2020

8/12/12 አርብ ምሽት ከመጋቢ ሲሳይ ተፈራ ጋር የቀጥታ ስርጭት

ሰኔ21/2012ዓ/ም                      የዕለቱ  የመልዕክት  ክፍል  ትንቢተ  አሞጽ 9፤1-15                   ጌታ- የፈረሰውን ያድሳል  የወደቀውንም  ያነሳል  ...
29/06/2020

ሰኔ21/2012ዓ/ም
የዕለቱ የመልዕክት ክፍል ትንቢተ አሞጽ 9፤1-15
ጌታ- የፈረሰውን ያድሳል የወደቀውንም ያነሳል
የከብት እረኛው አሞጽ በሰው ሳይሆን አፍ ሆኖ እንዲናገርለት በእግዚአብሔር ሲጠራ የዳዊት ስሮው መንግስት ለሁለት ከመከፈል አልፎ በከፍተኛ የትዕቢት ተራራ ላይ የተቀመጠበት ዘመን ነበር፡፡የሚያሳዝነው አምላካቸን የሚሉት ያህዌ ከደማስቆ ጡንቻ ስር በድንገት አውጥቶ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ብልጽግና ማውጣቱ ሳያንሰው ብርቱ የሆነ ጠላቶቻው ሊደነግጡበት የሚችል ሰራዊት እንዲገነቡ አድርጉአቸው ነበር ይህንን አስደናቂ ዕድል ግን ከማስተዋል አውጥቶአቸው በሲና ተራራ ከሰጣቸው ኪዳን ጋር ተጋጩ ይህ ደግሞ ለአምላካቸው አይመቸውም ለዚህ ደግሞ ማሻሻያ የለውም መልዕክቱ አንድ ነው በደለኞች ናችሁ ተመለሱ፡፡ ይህንን ጩሀቱን እንዲጮህለትና ከፊታቸው ያለውም ትልቅ ተስፋ እንዲነግራቸው አሞጽ ተጠራ፡፡ ይህ ሰው ብርቱ ነው ካሀናትም ሆኑ ልባቸው እንደ ቡላድ ድንጋይ ተንካራ የሆኑትን የአይሁድ ህዝብን የማይፈራ መናገር ያለበትን የሚናገር ነብይ ነው፡፡በደላቸው በዓይነት እየጨመረ ከእግዚአብሔር ይልቅ በማያድን ጣኦታትን መታመንና መደገፋቸው የሚታየውና የሚታመኑበት የዳዊትን መንግስት እንደሚያፈርስባቸው ከአይናቸው የተሰወረ ይመስላል፡፡እግዚአብሔር ከምድር ሕዝብ ሁሉ ለአይሁድ ህዝብ ልዩ እውቅና ነበረው ለዚህም ቤተመቅደስ ሰጣቸው ኪዳን ሰጣቸው ተስፋ ሰጣቸው እነርሱ ግን ይህንን ሁሉ ወደ ጎን በመተው የማያድኑትን በእርሱ ቦታ መተካትን መረጡ፡፡በማለዳ /በጥፋታቸው መጀመሪያ/ የተላኩት ነብያቶች የመመለስ ጥሪ ቢያድርጉላቸውም የአይሁድ መሪዎችና ህዝብ ምርጫ ግን አልነበረም፡፡የአሞጽ መልዕክት ኪዳኑን በማርከሳቸው ከፊታው የሚገጥማቸውን ፍርድ ያስታውቃቸው ነበር ይህም ፍርድ የመንግስታቸው መፍረስና የእነእርሱ መበተን ነው፡፡ ውገኖቼ አንድ ነገር እንወቅ መቼ እንደሆነ ባናውቅም አንድ ቀን ግን ፍርድ አለ፡፡የእስራኤላውያን መቀማጠልና አልሰማ ባይነት ከፍርድ ቀን አላስጣላቸውም፡፡
ነብዩ ጌታን ከመሰዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት ይለናል ክፋታቸውና በደላቸው ቢበዛም የፍርዱ ሰዓት እስኪደርስ ድረስ እርሱ ከመሰዊያው አጠገብ አልጠፋም ጌታ ሁል ጊዜ ከቤተክርስቲያ ጎን አይታጣም ፡፡ነብዩ በምዕራፍ ዘጠኝ ላይ ከእስራኤል አልመለስ ባይነቱው የተነሳ እግዚአብሔር ሊያርግ ያለውን ሁለት ነገር ይነግናል፡፡ እርሱም 1. ጉልላቶቹ ይመታሉ መድረኮቹ ይናወጡ አሞጽ9፤1
2. ምድርን ይዳስሳል እርስዋም ትቀልጣለች አሞጽ9፤5
መንፈሳዊውንም አካላዊውንም ነገር የሚነካ ፍርድ በምድሪቱ ላይ እንደሚያልፍ ግድ የሆነበት ሰዓት ነው፡፡
እነኝን ነገሮችን ለማድረግ እግዚአብሔር ሲነሳ ከውጤቶቹ ለማምለጥ የሚችል ማንም እንደማይኖር ሊሸሹ ከሚፈልጉበት ቦታ እንደሚያወጣቸው በሚደበቁበት ስፍራ ጠላት እንደሚያዘጋጅባቸው ነገራቸው ከእነርሱ የተነሳ በምድሪቱ ላይ ታላቅ መፍረስ እንደሚሆን ገለጸላቸው፡፡ይህ እንጊዲህ አባቶቻቸው እግዚአብሔርን ሲሰሙበት ክብሩንም ሲያዩበት ከነበረው ቤተምቅደስ መፍረስ ጀምሮ ልዩ ኩራት እና በመለኮታዊ ቅባት የተመሰረተው የምንገስታቸው መበተን አልፎ ከምድር አካል ሁሉ በልዩነት የምትታወቀውን ወተትና ማር የምታፈሰውን ምድራቸውን ወደ ሰው አልባ በረሃነት እንደምትለወጥ የሚያመለክት ከባድ ፍርድ ነው፡፡አዎ ይህ ህዝብ ትልቅ ኩራት ነበረው የዳዊት መንግስት የታላቅነታቸው ምክንያት ነበር አሁም ግን እንድ እርግጠኛ የሆነ ነገር አለ መውደቅ መፍረስ መለኮታዊ ትዕዛዝ ሆኖ ወጥትዋል ይህንን ደግሞ ሊያስቆምም ሊከለክልም የሚችል ማንም የለም፡፡ይህ ኃጢያተኞች የሚቀጡበት ዋጋቸውን የሚቀበሉበት በእርሱ የተዘጋጀ መንገድ ነው፡፡
በዚህ ውስጥ ግን እግዚአብሔር ያዘጋጀው ልዩ ስራ ነበር ንጉስ ሰለሞን የጀመረውን የበደል መንገድ በመከተልና የበለጠውንም በማድረግ የዳዊት መንግስት እንድትወድቅ ቢያደርጉም እግዚአብሔር ግን የዳዊትን ድንኩዋን ያነሳል፡፡ይህ ማለት እንደገና በዳዊት ዘመን የነበረው መለኮታዊ የእግዚአብሔርን አመራር በህዝቡ መካከል የነበረው ሞገስ በምድሪቱ ላይ የነበረው ህልውናውን እንደሚመልሰውና እንደሚገልጠው እየነገራቸው ነው፡፡በሚታየው የዳዊት ድንኩዋን ውስጥ የማይታየው እግዚአብሔር በሚታየው የዳዊት መንግስት ውስጥ የማይታየው የእግዚአብሔር መለኮታዊ መንግስት ነበር ይህ መለኮታዊ እውነት እንደገና መገለጥ እንደሚጀምር እግዚአብሔር ታላቅ ተስፋ እየሰጣቸው ነው፡፡ይህንን ያለው የተናገረውን የሚያርገው እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ የዳዊት ድንክዋን መነሳት እስራኤል በምድር ላይ በመለኮታዊ ክብር በመሞላት አምላክዋ ይሄ ነው የሚባልላት ክብርና ብልጽግናዋ የሚታይበት ማስፈራትዋ የሚገለጥበት ዘመን ውስጥ የምትገባበት ጊዜ ከፊትዋ እንደሚኖር እየተነገራ ነው፡፡የማይታየው ያህዌ በእርስዋ ላይ ምድር ትወቀኝ ብሎ የሚገለጥበት ዘመን እንደሚመጣ ያሳየል፡፡
ሰው እራሱን ለክፋ አሰራር አሳልፎ ከመስጠቱ የተነሳ ምድር በክፋት ስትሞላ የእግዚአብሔር ዝምታ ምድርን በጨለማ እንድትናወጥ ቢያርጋትም ቤተክርስቲያን አንገትዋን ዝቅ አድርጋ መልክዋን ብታጣም ልዑል ግን እንደገና ያስባታል፡፡ያለንበት ዘመን የመጨረሻው እንደመሆኑ ቤተክርስቲያን በቀደመ ታላቅ ክብርዋ የምትነሳበት ጊዜ በደጅ ነው፡፡ይህ ደግሞ ያንተ ያንቺ የኔ መነሳት ነው፡፡ትላንትና የወደቅንበት የፈረሰብን ብዙ ነገር ሊኖር ይችላል ዛሬ ግን እግዚአብሔር ዕድል ሰቶናል ዛሬ በሕይወት መኖራችን የእንደገና ዕድል እንድናገኝ አድርጎናል፡፡ስለዚህ በመስቀል በክርስቶስ የተከፈለልንን ታላቅ ዋጋ አሰበን እጀችንን ለእርሱ እናነንሳ ዛሬ እልከኝነት አያዋጣም የቤተክርስያንን ክብርና ውበት ሊመልስ ከጎንዋ ከቆመው ጌታ ጋር መስማማት ውጤቱ ታላቅ ነው፡፡እርገጠኛ ነኝ የተናገረው እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን የፈራረሱ ነገሮችን እንደገና ይሰራል ነገሮች እዳለፈው ዘመን እንዳይቀጥል ሊያስቆም ተነስትዋል ነገር ግን ንፋሱ አንቺን አንተን እኔን ይዞን እንዳይሄድ በመስቀል ላይ በፈሰሰው ወደ ሚናገርልን የኪዳን ደም እንቅረብ፡፡
ጌታ በመስቀል ላይ በቃል ልንገልጸው ከምንችለው በላይ የሆነን ዋጋ ከፍሎልናል ስለዚህ በወደቀብንና በፈረሰብን ነገር ደስተኛ አይደለም ስለሆነም የፈረሰብንን ሊሰራ የወደቀብንን ሊያነሳ ከፊታችን ቆምዋል እንገዲህ እራሳችንን በእውነት ገልጸን በማሳየት የመጨረሻው ዘመን የቤተክርስቲያን ጉብኝት ነገ እንዲያገኘን ዛሬን ከእርሱ ጋር እንስማማ፡፡ከፊታችን ያለው ጊዜ እንዲህ ነው በምድሪቱ የሚያቀልጥ ነገር እያለፈ ጌታ- የወደቀውን የሚያነሳበት የፈረሰውን የሚያድስበት በኪዳኑ ላሉት የመታደሻ የመሰሪያ ወቅት ይሆናል፡፡ስለዚህ በኪዳኑ ያለን እኛ አንፍራ አይኖቻንን ቀና አድርገን # ይህን የሚደርግ እግዚአብሔር ; የተባለውን እንመልከት፡፡
እግዚአብሔር ይባርካችሁ ሰላሙንም ይስጣችሁ ፊቱንም ያብራላችሁ!
ኢየሱ ክርስቶስ ጌታ ነው!
አሜን

25/06/2020
ሰኔ14/2012ዓ.ም          የመልዕክት  ክፍል የሉቃስ  ወንጌል 18፤1-43                            እንጩህ - የሚፈርድ አለ    በምድር  የሚኖር  ሰው  ዓይነቱ ...
21/06/2020

ሰኔ14/2012ዓ.ም
የመልዕክት ክፍል የሉቃስ ወንጌል 18፤1-43
እንጩህ - የሚፈርድ አለ
በምድር የሚኖር ሰው ዓይነቱ ይለያይ እንጂ በግል ህይወቱ በቤተሰብ ጉዳዩ በመህበረሰቡ መካከል አልፎም በአገሩ ጉዳይ ላይ ፍትህ መለስ የሚፈልግበት ነገር ይኖረዋል፡፡ የዛሬዋ ባለታሪካችን መበልት ናት ማለትም ባልዋ የሞተባት ወይንም በዕድሜ የገፋች ያለበለዚያም ሁኔታዎች ተጭነዋት የተጎሳቀለችና የደከመች ሴት፡፡ይህች ሴት አዘውትራ ፍርሀትና እፍረት ወደሌለው የከተማው ህዝብ ሁሉ ወደሚያውቀው ዳኛ ትሄዳለች፡፡ፍርድ ፍለጋ ፡፡ድካምና መታከትን አታውቅም ሁል ጊዜ ያለማቐረጥ በዳኛው መውጫና መግቢያ በር ላይ ትገኛለች አትሰለችም ተስፋ አትቆርጥም አንድ ድምጽ ታሰማለች ከባላጋራዬ ፍረድልኝ፡፡ ፍርድ አጣምልኝ ለኔ አዳላልኝ አይደለም የሚገባኝን ትክክለኛ ውሳኔ ስጠኝ ነው፡፡ሰውየው ጨካኝ ነው ልቡ የማይሸነፍ ብዙዎች ተሰላችተው የተዉት ጉዳይ ሳይኖራቸው አይቀርም ይህቺ መበልት ግን እንደሌሎች አይደለችም ሁል ጊዜ ያለማቐረጥ ትጮሀለች ፍድልኝ፡፡አንድ ቀን ግን ጨካኙ ዳኛ ተሸነፈ ፍርድን በእውነት ለሚገባት መበልት ሰጠ፡፡ኢየሱስ እንዲህ አለ #እግዚአብሔር እንኪያ ቀንና ለሊት ወደ እርሱ ለሚኞሁ ለሚታገሳቸው ምርጦችቹ አይፈርድላውምን?; ሉቃ18፤7
እግዚአብሔር የሚፈርድልን / መልስ የሚሰጠን/ አባታችን ነው፡፡ክርስትና ሳይታክቱ የሚፀለይበት ህይወት ነው ፀሎት በባንክ እንደሚቆጠብ የቁጠባ ሒሳብ ለነገ የምናስቀምጠው ሳይሆን በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ጋር የምናደርገው ግንኙነት ነው፡፡ፀሎት ቆይታን ይጠይቃል እግዚአብሔርም ቆይታውን ይፈላጋል፡፡ ቆይታው አማኙ እንዲታይ ያደርገዋል ምክንያቱም ቆይታ ልብ ያስጥላል ተስፋ ያስቆርጣል ይህንን ማለፍ የሚቻለው ደግሞ በትዕግስትና በእምነት ነው፡፡ብዙ ጊዜ በፍትህ ቦታ መብልቶች ፍርድ ይጣመምባቸዋል ይበደላሉ ምክንያቱም ብቸኞች ናቸው የሚረዳቸው አይኖርም ስዚህም ብዙ ስፍራ ላይ ይገፋሉ፡፡ለዚህም ነው መፅሀፍ ቅዱስ ባልቴቶችን እንድንረዳ የሚመክረን፡፡በዚህ ምዕራፍ ያየናት ባልቴት ግን ከጎንዋ ማንም ባይኖር ያለማቐረጥ ትጮህ ነበር ፍርድ ፍለጋ፡፡
በፀሎት መቆየት ልዩነት የሚያመጣ በመሆኑ ሕይወታችንን ልንመራበት የሚገባ አቅጣጫ ልናረጋው ይገባል፡፡ በእግዚአብሔር ፊት የምናጠፋው ጊዜ ለህይወታችን እንድንጠነቀቅና ተግባራዊ የሕይወትን ልምምድ የሚያሲዘን ሲሆን የመናፍስትን እቅድ በማወቅ ከጠላት ዕቅድ ያስመልጠናል፡፡ስለዚህ ያለመታከት የጩሀት ድምጽ የሚያሰሙ አማኞች እንደ ኢያሪኮ የተቀጠረባቸውን ቅጥር በቅን ፈራጁ ጌታ እየፈረሰላቸው የበረከት ህይወት መግባት የሚችሉበትን መንገድ ያገኛሉ፡፡ኤርሚያስን #ወደ እኔ ጩህ እኔም እመልስልሀለሁ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሀለሁ ; ኤር33፤3 ሲለው ኤርምያስም ከሌሎች ነብያአቶች በላይ በጠለቀ ነገር ውስጥ ሆኖ ታላቅ ጩኸት ይጮህ ነበር ለዚህም የሰቆቃው ኤርምያስ መጻሀፍ ማበብ በቂያችን ነው የሚያስደንቀው ግን በእርግጥም ጩሀቱ ፍሬ ያለው ነበር እያንዳንዱ የእሰራኤልና የይሁዳ ህዝብ መንገድና ፍፃሜው አልፎም ትልቁ ተስፋ ቅን ፈራጁ ለኤርምያስ ግልጽ አርጎለት ነበር፡፡ዛሬም የሚገፋ ነገር የበዛባችሁ ቅን ፍርድ ያጣችሁ ከተከበበ ጠንካራ አጥር ጀርባ ያለውን የበረከት ስፍራ ውስጥ እራስን ለማግኘት እንዲሁም ግራ ገብቶአቸው ግራ የሚጋቡ በበዙበት ዘመን ውስጥ ትክለኛውን የእግዚአብሔርን ሀሳብ ለማግኘትና የማናውቀው ግን በእርሱ በታወቀልን ቦታ ላይ ለመገኘት ወደ እውተኛው ፈራጅ እንጩህ/እንፀልይ/፡፡ያኔ የልዩነት ሕይወት መገለጥ ይጀምራል አስታውሱ የጮሁት የኢያሱ ሰራዊቶች ናቸው የኢያሪኮ ግንብ እንዲወድቅ ምክንያት የሆኑት፡፡በዚህ ዘመንም ሁሉን አልሰማ ያለ በየስፍራው ተቀምጦ ፍርድ የሚያጣምመውን የታሪክን አቅጣጫ ለማሳት የሚተጋውን አልፎም የፍጥረት ማንነት ላይ ተፅእኖ ለመፍጠር የሚሰራውን የሚJገት ፍረድልኝ የሚል ትውልድ ሊነሳ ይገባል ቅን ፈራጅ በሰማይ አለ፡፡
በቅን ፈራጁ ፊት ስንቆም በህይወታችን ከሚፈለጉ ነገሮች አራቱን እንመልከት
1. በራስ ጽድቅ ላይ አለመቆም ሉቃ 18፤9-12
ፈሪሳዊውም ቀራጩም የቆሙት በቅን ፈራጁ ፊት ነው ፈሪሳዊው እራሱን ከመመልከት ይልቅ ቀራጩን መመልከቱ የራሱን ፅድቅ ቆጣሪ አደረገውለ፡፡ የሌሎችን ድካም መመልከትና መቁጠር እራሳችንን በራሳችን የጽድቅ ማማ ላይ ማስቀመጥ ይሆናል ስለዚህ ስለ ወንድማችን ድካም ተንታኞች ሳንሆን እራሳችንን በጌታ ጽድቅ ላይ በመስቀመጥ እንደ አማኝ እራሳችንን ልናስለምደው ያስፈልጋል፡፡አንሳት ፈሪሳዊውን የጣለው የቀራጩን ድካም መቁጠሩ ነው፡፡
2. እንደ ሕፃን መሆን ሉቃ 18፤15-17
ኢየሱስ ሕፃናትን በእርሱ ፊት እንዳይቆሙ የሚከለክላቸው ምንም ነገር እንደሌለ ተናገረ፡፡ ይህ በጊዜው የነበሩትን የሀይማኖት አባቶች የሚስደነግጥ ነው፡፡ኢየሱስ የሕፃናትን ልብ ያያል በዙሪያው የነበሩት አባቶች ህፃንነታቸውን ያያሉ፡፡ ሕፃናት ልባቸው ንጽሁ ነው በደልን አይቆጥሩም ሁሉን ይወዳሉ ትሁት ናቸው፡፡ ፍረድልኝ ብለን ስንጮህ /ስንፀልይ/ ትሁት ልንሆን ይገባል ማለትም እራሳችንን ልናውቅ ራሳችንን ልንቀበል እራሳችንን ልንሆን ያስፈልጋል፡፡እውነተኛ ትህትና ለራስ ሳይሆን ቅድሚያ ስለሌሎች ያስባልና፡፡ሕፃናት በደልን አይቆጥሩም ዛሬ በደልን እየቆጠርን የተደረገብንን እያሰብን በፀሎት እንተጋለን ብንል ቅን ፈራጁ #አስቀድመህ ከወንድምህ ጋር ታረቅ; ይላል ስለዚህ ይቅርታን የሚያውቅ የሚተገብር ትሁት ልብ ያለን አማኝ እንሁን ይህ በሰማይ ያለውን ቅን ፈራጅ ደስ ያሰኛል፡፡
3. ሁሉን መተው ሉቃ 18፤18-30
ወደ መሲሁ የመጣው አለቆች ተብለው ከተደረደሩት መካከል አንዱ ነው በሰው ዓይን ስለህግ የተመሰከረለት ነው ስለ መምህሩ ቸርነትም ያውቃል በመሲሁ ፊት ቆሞ ጥያቄ ጠየቀ ወደ መንግስቱ የሚገባበትን፡፡የተሰጠው መልስ ግን ጥያቄ ነበር እንዲተው፡፡ይህ ወደ መሲሁ የመጣ አለቃ ፍርድ ሳያገኝ ተመለሰ ምክንያቱም መተው አልቻለም፡፡በቅም ፈራጅ ፊት ስንቆም የፍረድልኝ ፀሎት ስናሰማ የተበደልነውን ልንተው የኔ የምንለውን ልንተው ብቻ ሁሉን ልንተው ይገባል ይህ ነው በቅን ፈራጁ እየተፈረደልን በዚህ አለም ብዙ እጥፍ በሚመጣው አለም የዘላለም ህይወት እንድናገኝ የሚያርገን፡፡ስለሆነም በሰው ዘንድ ብዙ ምስክርነት ቢኖረንም በቅን ፈራጁ ፊት ሁሉን መተዋችንን ሊመሰከርልን ይገባል፡፡
4. ሞቱና ተንሰኤው ማስተዋል ሉቃ 18፤31-348ደቀ መዛሙርች ይህንን ጥልቅ ሚስጢር ሲነግራቸው አላስተዋሉም የአማኝ ጅማሬውም ፍጻሜውም በሞቱና በተንሳኤው ውስጥ ነው ስለዚህ ሁል ጊዜ ቅን ፈራጁ ፊት እንዳለን አወቀን ሞቱንና ተንሳኤውን ማሰብ መሰላሰል ማስተዋል ይገባናል፡፡መጽሀፍ አንደሚል #ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን; ሮሜ6፤5 # የኢየሱስን መሞት በስጋችን ተሸክመን እንዞራለን ;2ቆሮ4፤10 እነደሚል ለዓለም ለሰይጣን ሀሳብ ለስጋችን ፍቃድ የሞተ ማንነት ይዘን በፊቱ ልንገኝ ያስፈልጋል፡፡ ጳውሎስ #እርሱንና የትንሳኤውን ኃይል እንዳውቅ; ፊል3፤10 እንዳለው የትንሳኤውን ኃይል በማሰብ በፊቱ ልንቆም ያስፈላጋል የትኛውም ነገር በትንሳኤው ኃይል ተሸንፎአል፡፡ ስለሆነም ሞቱንና ተንሳኤውን እናስተውል ያን ጊዜ የተንሳኤው ጌታ ቅን ፈራጅ ዘንበል ይላል፡፡
ኢየሱስ ለሚጮሁት ምርጦቹ እግዚአብሔር እንደሚፈርድላቸው በማስረገጥ ሳይታክቱ እንዲጸልዩ ማስተማር የጀመረበትን ምዕራፍ ሲያጠናቅቅ በኢያሪኮ ከተማ በር መንገድ ዳር ላይ በገኘው Åሂ ሰው ነው፡፡ይህ ሰው ስለ ናዝሬቱ ኢየሱስ የሰማው ነገር ሳይኖር አይቀርም የሚያልፈው እሱ ነው ሲባል አብዝቶ መጮሁን ቀጠለ የከልካዮቹን ድምጽ አልሰማም ነገር ግን በቅን ለሚፈርደው አብዝቶ መጮሁን ቀጠለ #በቀንና በለሊት ወደ እርሱ ለሚጮሁ . . . አይፈርድላቸውምን; ሉቃ 18፤7 ያለው ጌታ ይህንን ጩሀት ማለፍ አልቻለም ቆመ መቆም ብቻ አይደለም ለነፍሱ ጥያቄ የሆነውን ለዘመናት ጥገኛ ሆኖ አንዲኖር ያደረገው ጉዳይ ላይ ፈረደለት አይኖቹን ከፈተ፡፡ ይህ የህይወታችን መርህ ነው መፀለይ ፤ መጮህ ፤ የቅን ፈራጁን ፊት መፈለግ እርሱ ደግሞ አይጨክንም ምን አልባት በዙሪያችን ያሉት ሰወችና ሁኔታዎች ዝም ለማሰኘት ይፈልጉ ይሆናል እኛ አማኞች ግን አብዝተን ከጮህን ፈራጁ ስለእኛ ይነሳል፡፡አዎ እንጮሀለን ስለ አንተ ስለ አንቺ ይነሳል ስለ ቤተክርስቲያን ስለ አገራችን ምድርን ስላስጨነቀው ነገር ይነሳል፡፡እንጊዲህ ለምርጦቹ የሚፈርድ ጌታ ካለ በልዩነት ህይወት ለመኖር አብዝተን እንጩህ ትዝ ይላችኃል በምድረበዳ የሚጮህ ሰው ድምጽ መሲሁ በደጅ እንዳለ የሚናገር የሚጮህ፡፡ ቀን ፈራጁ መሲሁ ጌታ ሊመጣ በደጅ ነው አብዝተን እንጩህ፡፡

እግዚአብሔር ይባርካችሁ ፀጋውንም ይስጣችሁ ፊቱንም ያብራላችሁ!
ኢየሱስ ጌታ ነው!
አሜን

Address

Jimma

Telephone

+251471112669

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jimma Emmanuel United Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Jimma Emmanuel United Church:

Share

Category