17/08/2023
ህገወጡ ማነው?።
- - - - - - - - - - - - -
የዠህ ሰሞን ጩሔት ህገወጥ የሚል ጫጫታ ነው። ለመሆኑ ህገወጡ ማነው?። ህጋዊውስ የትኛው ነው?። እውነት ራሷን አትደብቅም ነገርግን ሁሉንም ተሸክማ የመውጫ ቀኗን ትጠባበቅና ቀኑም ስደርስ ትወጣለች። ብፁዕ አቡነ እስጥፋኖስ ወደጅማ ሀገረስብከት ከመጡ ዘንድሮ 23 አመታትን አስቆጥረዋል። በሳቸው የጲጲስና ዘመናት በጉልህ የሚወሳው ልማትነው ገቢላይ ያቶከረ ልማት።
በእነዠህ ጊዜያት የተስፋ ተዋህዶ ት/ቤቶች ተገንብተው አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉ የሚካድ አይደለም። ለሎች የእንዱስትሪ እና የእርሻ ልማት ዶ/ር አቡነ ጴጥሮስ ካደረጉት ሌላ የተሠራ ነገር የለም።
በተለይም ማንም ሠው በሚረደ መልኩ ታቦታት በቆሙበት አውደምህረት ላይ ምዕመናንን ወንጌል በመስበክ ፋንታ የገንዘብ ልመና እና የቁሳቁስ ጥየቃ ትኩረት የሚሠጠው ተግባርና ብዙሃኑን ከቤተክርስቲያን ያራቀ ተግባር ነበር።
በተለይም በየወረዳው ባሉት አቢያተክርስቲያናት መልሰው አብያተ ክርስቲያናቱን የሚረዳ ህንፃ እየሰራነው ገንዘብ አምጡ ተብለው የደብር አስተዳዳሪዎችና የወረዳ ሊቃነካህናት ለብዙ አመታት ከተዘጋችው የገጠር ቤተክርስቲያን ተሰብስቦ ህንፃ ቢሠራም ምንም አይነት ድጎማ አልተደረገም። ይልቁንም ባልታወቀ ምክንያት ህንፃውን በስማቸው እንዲጠራ አድርገዋል። ይህ ደግሞ ነጌ የሆነ ነገር ቢፈጠር ለወገኖቻቸውና ለ________ ለማውረስ ታስቦ የተሰራ ሴራነው እና ምዕመናኑ ልትነቁ ይገባል። ከዠህም ባሻገር:-
1, ለአበልቲ ኪዳነምህረት ሥም የሚሰበሰበው ገንዘብ እና እህል ለዘመዶቻቸውና ለፋኖ ማስታጠቂያ ወደ ሰሜኑ ይላካል።
2,ከመረዋ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳምና ከአበልቲ ክዳነምህረት ገዳማት የሚሠበሠቡት የልማት ቱሩፋቶች ለግለሰቦች ጥቅም ስውሉና ስባክኑ እንጂ እዠህ ግባ የሚባል ነገር ለገዳማቱም አላተረፊም።
3, በሀገረስብከቱ ይህነው የማይባል የኦሮሞ ጥላቻና እንግልት እሳቸው እያዩ ፍትህ እንዲሰጡና በእኩልነት እንዲመለከቱት ተጠይቀው በፌዠ የታለፉ ብዙ ናቸው።
4,በአሁኑ ጊዜ በሀገረስብከቱ ወጣቶችን ገንዘብ በመበተንና ለሁከት በማዘጋጀት ህገወጥ ስራዎች እየተሠሩ ይገኛል።
5,ለ23 አመታት ስለአገለግሉን እናመሠግናለን ያልተገለገልነው ደግሞ የመገልገል እኩል መብት ይኑረን ማለት ህገወጥነት አይደለም ሀዋርያትም ለወንጌል አገልግሎት ስወጡ የየአከባቢውን ቋንቋ ተጎናፅፈው 72 ቋንቋዎችን አውቀው ነውና ቆም ብላችሁ አስታውሉ!።
6, ህገወጥነት ወንጌል በኔ ቋንቋ ቢቻ ከልተሰበከ ዶግማ ይፈርሳል፣በተክርስቲያን ትደፈራለች፣ ቅኖና ተጣሰ ወ,ዘ,ተ,ብሎ የምተርተው ነውና ተውት። ህብረት ይሻለናል። ሰውላይ ሳይሆን የቤተክርስቲያናችን ሙሽራ እና ራስ በሆነው በክርስቶስ ላይ እንጣበቅ። ሰው በሚችለው ቋንቋ ወንጌልን እንዲማር እንፍቀድለት።