17/08/2026
የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ሀገረ ስብከት አቀፍ ሚንስትሪ ፈተና በጅማ ሀገረ ስብከት ተጠሰ።
በ2018 ዓ.ም የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት መሠረት የ8ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ ተማሪዎች ነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓ.ም የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሃይማኖት ያዕቆብ ደምሴ እና የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤት ማደራጃ ክፍል ኃላፊ ላዕከ ወንጌል ባዬ ከድር በተገኙበት በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ የሚንስትሪ ፈተና ተሰጥቷል።
በሀገረ ስብከቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው የ8ኛ ክፍል ሚንስትሪ ፈተና ከሰባት አድባራት ሰንበት ት/ቤቶች የተውጣጡ 131 ተማሪዎች መመዘኛውን መውሰዳቸውን የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ትምህርት ክፍል ኃላፊ መ/ር ያለው ሐሪንጎ ገልጸዋል።
ነሐሴ ፲፩ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
ጅማ ፤ ኢትዮጵያ
የጅማ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት