የጅማ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሚድያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Jimma
  • የጅማ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሚድያ

የጅማ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሚድያ ጅማ ሀገረ ስብከት

በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድንከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች...
05/06/2026

በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ
ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን
ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

ጅማ ፤ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት አንዳንድ ወረዳዎች በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት በኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ሕልፈተ ሕይወትና የቤተ ክርስቲያን መቃጠልን በማስመልከት በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተመራ ቡድን ከሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ፣
ከሚኒስትር ዲኤታው ከዶ/ር ኸይረዲን ተዘራና ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ትናንት ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስሮስ በምሥራቅ አርሲ በአሰኮ፣ በሺርካ፣ በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ላይ በደረሰው የሕይወት ጉዳት እና በጥንታዊው ቤተ ክርስቲያን መቃጠል እጅግ ማዘናቸውን ገልጸው መንግሥት የችግሩን ምንጭ አጣርቶ ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈልግና በአካባቢውም አስተማማኝ ሰላምን እንዲያሰፍን አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

አያይዘውም በአሁኑ ወቅት በችግሩ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው የሚመለሱበትና መልሰው የሚቋቋሙበት ሥራ እንዲሠራ፣ ወንጀሉን የፈጸሙ ሰዎችም ለፍርድ ቀርበው
ቅጣታቸውን እንዲያገኙ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የምሥራቅ አርሲና የጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሀገረ ስብከታቸው የተከሰተውን ችግር በማስመልከት ዝርዝር መረጃዎችን በቊጥራዊ ማስረጃዎች አስደግፈው አቅርበዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው
በተፈጠረው ችግር ማዘናቸውን ገልጸው በመንግሥት በኩል በአስቸኳይ አጣሪ ቡድን ተቋቁም ወደ ስፍራው ተልኳል ካሉ በኋላ የአጣሪ ቡድኑን ሪፖርት መሠረት በማድረግም አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ብፁዓን አባቶቻችን በኦሮሚያ ፕ/ት ጽ/ቤት ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ከብልጽግና ፓርቲ ጽ/ ቤት አመራሮች ጋር ዝርዝር ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ ወቅት የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንደገለጹት የክልሉ መንግሥት በሥፍራው የተከሰተውን ችግር ለመቆጣጠርና ሊከሰት ይችል የነበረውን ተጨማሪ አደጋን ለመከላከል የሚያስችል ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረጉን፣ በአሁኑ ወቅትም ወደ ሥፍራው አጣሪ ቡድን መላኩንና የማጣራት ውጤቱን ተከትሎም አጥፊዎችን ለሕግ የማቅረቡ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመው ቤተክርስቲያኗ ምዕመናንን ለማጽናናትና ድጋፍ ለማድረግ በምታደርገው ጥረት ሁሉ የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደረግላት ገልጸዋል።

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ፣ወደ ቀያቸው ለመመለስ እንዲሁም የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን መልሶ ለመገንባት እና በአካባቢው ዳግመኛ መሰል ችግር እንዳይፈጠር ለማድረግ የሚያስችል ሥራ በተጠናከረ መልኩ እንደሚያከናውኑ ከልዑካን ቡድኑ ጋር ባደረጉት የማጠቃለያ ውይይት ገልጸዋል።

መረጃው የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአርሲ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያናችን እና በኦርቶዶክሳ...
03/06/2026

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአርሲ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያናችን እና በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።

ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት እንደሚከተለው ነው፦

መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

‹‹ወረሰዩ አብድንቲሆሙ ለአግብርቲከ መብልዐ ለአዕዋፈ ሰማይ፣ ወሥጋሆሙኒ ለጻድቃኒከ ለአራዊተ ገዳም፦ የአገልጋዮችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የቅዱሳንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት።››
(መዝሙረ ዳዊት ፸፰፥፪)

በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤ እና በሙኔሳ ወረዳዎች በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ስለደረሰው አሰቃቂ ጥቃት የሰማነው በተሰበረ ልብ ነው።
የእምነት ነፃነት ተደፍሮ መቶ ዓመታት ያስቆጠረው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በተቃጠለበት፣ እንዲሁም የካራ ኩፍቴና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በተዘረፈበት በዚህ ክፉ ቀን፤ በርካታ ምእመናን በግፍ መሰዋታቸውና በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ቤተ ክርስቲያናችንን በእጅጉ ያሳዘነ ክስተት ነው።

የሰላም፣ የፍቅርና የታሪክ ማህደር የሆነችው ቤተ ክርስቲያን በምድራዊ መከራ ውስጥ ያሉትን ምእመናን በምታጽናናበት በዚህ ወቅት ራሷ በፈተና ውስጥ ሆና ከመቸገሯም በላይ በአርሲ ምድር በተደጋጋሚ የሚስተዋለው በደልና ግፍ በሁላችንም ልቡና ውስጥ "እስከ መቼ?" የሚል የቁጭት እና የኀዘን ጥያቄን ፈጥሯል።

በመሆኑም ይህ መከራ እያበቃ ሳይሆን እየሰፋ በመምጣቱ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን አደራ የተጣለባችሁ የጸጥታ አካላትና በየመዋቅሩ ያላችሁ ሓላፊዎች ከምንም በላይ ታሪክ የሚጠይቃችሁ በሥልጣን ዘመናችሁ ለዜጎች ደኅንነት በምትከፍሉት ዋጋ ነውና ይህንን የጥቃት ሰንሰለት በማስቆምና ወንጀለኞችን ለሕግ በማቅረብ ከታሪክ ባለዕዳነት ትድኑ ዘንድ በቤተ ክርስቲያናችን ስም አበክረን እናሳስባለን።

በየአካባቢው የምትገኙ ምእመናንና መላው ኢትዮጵያውያንም በወንድማማችነት መንፈስ ተጋግዛችሁ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና በጸሎት ከቤተክርስቲያናችን ጎን እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያናችን ለሰላም፣ ለይቅርታና ለሰው ልጆች ክብር ሁል ጊዜ የምትቆም መሆኑን በመግለጽ ይህንን የኀዘን ሰዓት አምላካችን በምሕረቱ ያሳልፍልን፣ የሞቱትን ነፍሶቻቸውን በመንግሥቱ ይቀበልልን፣ የተጎዱትንም በቸርነቱ ያጽናናልን በማለት አባታዊ የኀዘን መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

© የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ከ10 በላይ ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉየ101 ዓመት እድሜ ያለው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።  የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይም ...
02/06/2026

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ከ10 በላይ ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ
የ101 ዓመት እድሜ ያለው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።

የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይም ዘረፋ የተካሄደ ሲሆን ምእመናን ጽላቱን ይዘው ተሰደዋል፤ መኖሪያ ቤታቸውም ተቃጥሏል።

የጅማ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም

እንደ ወትሮው ሁሉ ዛሬም በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ምድር ላይ ታላቅ ሃዘን ላይ ይገኛል። ማቅ የለበሱ እናቶች፣ እንባቸው ያላለቀ ሕፃናት እና ማደሪያ ያጡ አረጋውያን ጩኸት ሰሚ አጥቷል።

ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት፣ አሰኮ ወረዳ፣ ጠላታ ጨፋ ቀበሌ እና ካራ ኩፍቴና በሚባሉ አካባቢዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠረ አሰቃቂ ግድያ ተፈጽሟል።

ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸውን የማንጠቅሰው የአይን እማኝ እና መረጃ ሰጭያችን እንደገለጹልን ከሆነ፣ ጥቃቱ እጅግ አሳዛኝና አረመኔያዊ እንደነበር ይናገራሉ።

በአሰኮ ወረዳ ጠላታ ጨፋ ቀበሌ ብቻ በታጣቂ ኃይሎች በተፈጸመ ሰብአዊነት በጎደለው ጥቃት ከ10 በላይ ንጹሃን ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል።

ይህ አሰቃቂ ጥቃት በሰዎች ሕይወት ላይ ብቻ አላበቃም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም የሚፈተትበትን መቅደስም ጭምር ኢላማ ያደረገ ነበር። በአካባቢው 101 ዓመታትን ዕድሜ ያስቆጠረው፣ ታላቁ የዕድሜ ባለጸጋ የጠላታ ጨፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወውደሙን መረጃ ሰጭያችን ገልጸውናል።

በተመሳሳይ ጥቃት በካራ ኩፍቴና መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት የተሰነዘረ ሲሆን፣ የቤተክርስቲያኑ ንብረት የሆኑ ቤቶች በመቃጠላቸው ምእመናን የመድኃኔዓለምን ቅዱስ ጽላት ይዘው በእግራቸው ወደሌላ አካባቢ መሸሻቸው ታውቋል።

ኦርቶዶክሳውያኑ ተወልደው ካደጉበት፣ ወልደው ከሳሙበት ቀያቸው በሃይማኖታቸው ብቻ ቤታቸው እየተለየ ተቃጥሏል፤ ንብረታቸውና ከብቶቻቸው ተዘርፈዋል። ከጥቃቱ የተረፉት ነዋሪዎችም ይዘውት የሸሹት እምነታቸውንና ማንነታቸውን ብቻ በመሆኑ አሁን ላይ ሜዳ ላይ ወድቀው ይገኛሉ ሲሉ ነበር በሃዘን ተውጠው የነገሩን።

በተያያዘ ዜና

በዚሁ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሺርካ ወረዳ በሁለት ወጣት ኦርቶዶክሳውያን ላይ ዘግናኝ ግድያ መፈጸሙ ተሰምቷል።

ድርጊቱ የተፈጸመው ሚታና ዋጂ ቀበሌ ሲሆን፣ ታጣቂዎች ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ወጣቶቹ መኖሪያ ቤት በመግባት በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸውና በመቀጠልም ወጣቶቹን ወደ ሚታና ጋዶ ቀበሌ በመውሰድ፣ አንደኛውን በስለት አርደው፣ ሁለተኛውን ደግሞ በጥይት በመምታት በጭካኔ ሕይወታቸውን እንዳጠፉት ተገልጿል።

ሕይወታቸውን ያጡት የእነዚህ ወጣቶች ሥርዓተ ቀብር ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በጋዶ ማሕደረ ስብሐት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን፣ ምዕመናንና በቤተሰብ በተገኘበት በአንድ መቃብር ተፈጽሟል።

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በአገልጋዮችና ምእመናን ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት እንደሚፈጸምበት ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ለዓመታት መረጃ እያደረሰ ቢሆንም ዛሬም ድረስ ዘላቂ መፍትሔ አልተገኘም።

መረጃው የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቭዥን ነው።

ለቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ጅማ ቅርንጫፍ ተማሪዎች የተላለፈ መልእክት።በጅማ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የርቀት ተማሪዎቻችን በሙሉ :- የአንደኛ ዓመት አንደኛ መንፈቅ ዓመት (1st Semest...
01/06/2026

ለቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ጅማ ቅርንጫፍ ተማሪዎች የተላለፈ መልእክት።

በጅማ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የርቀት ተማሪዎቻችን በሙሉ :- የአንደኛ ዓመት አንደኛ መንፈቅ ዓመት (1st Semester) የፈተና ቀን ዓርብ ሰኔ 26/10/2018 ዓ.ም ሲሆን ፤ የአንደኛ ዓመት ሁለተኛ መንፈቅ ዓመት (2nd Semester) የገጽ ለገጽ (Tutorial) የሚሰጠው ቅዳሜና እሁድ ማለትም ሰኔ 27 እና ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም መሆኑን የርቀትና በይነ መረብ ትምህርት ኮሌጅ በአክብሮት ያሳውቃል።

‹‹ዕለት ዕለት የሚያሳስበኝ የቤተ ክርስቲያን ነገር ነው›› (፪ኛ ቆሮ.፲፩፥፳፰)
08/05/2026

‹‹ዕለት ዕለት የሚያሳስበኝ የቤተ ክርስቲያን ነገር ነው›› (፪ኛ ቆሮ.፲፩፥፳፰)

"... ተሰቅለ እንከ በትስብእቱ ወሐይወ በመለኮቱ ወንሕነ ነአምን በትንሣኤሁ ከመ ውእቱ እግዚአብሔር ወልደ እግዚአብሔር ዘበአማን። "" እንግዲህ ሰው በመሆኑ ተሰቀለ ፤ አምላክ በመሆኑ ተነሣ...
12/04/2026

"... ተሰቅለ እንከ በትስብእቱ ወሐይወ በመለኮቱ ወንሕነ ነአምን በትንሣኤሁ ከመ ውእቱ እግዚአብሔር ወልደ እግዚአብሔር ዘበአማን። "

" እንግዲህ ሰው በመሆኑ ተሰቀለ ፤ አምላክ በመሆኑ ተነሣ ፤ እኛም በመነሣቱ እግዚአብሔር የእግዚአብሔርም የባሕርይ ልጅ በእውነት እንደሆነ እናምናለን። " (ሃይማኖተ አበው ዘቅ. ቄርሎስ)

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሠላም አደረሳችሁ!!!

መልካም የፋሲካ በዓል!!!

"ዓይ አፍ ፣ ወዓይ ከናፍር ፣ ወዓይ ልሳን ዘይትናገር ሕማማቲሁ ለወልድ። ልብ ይትከፈል ወሕሊና ይዘበጥ ፣ ነፍስ ትርዕድ ፣ ወሥጋ ይደክም ሶበ ይትናገር ሕማማቲሁ ለፍቁር""...የጌታን ሕማማ...
10/04/2026

"ዓይ አፍ ፣ ወዓይ ከናፍር ፣ ወዓይ ልሳን ዘይትናገር ሕማማቲሁ ለወልድ። ልብ ይትከፈል ወሕሊና ይዘበጥ ፣ ነፍስ ትርዕድ ፣ ወሥጋ ይደክም ሶበ ይትናገር ሕማማቲሁ ለፍቁር"

"...የጌታን ሕማማተ መስቀሉን የሚናገር ምን አፍ ነው ፣ ምን ከንፈር ነው ፣ ምንስ አንደበት ነው?

የጌታን ሕማማተ መስቀሉን በሚናገርበት ጊዜ ልብ በኃዘን ይለያያል ፤ ሕሊና በኃዘን ይሰባበራል ፣ ነፍስ ትርዳለች ትንቀጠቀጣለች ፣ ሥጋም በኃዘን ይደክማል"
ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ

እንኳን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ላዳነባት ዕለተ ስቅለት በሠላም አደረሳችሁ!!!

የ2018 ዓ.ም 1ኛ መንፈቅ ዓመት አጋማሽ ፈተና ቅዳሜና እሑድ በሁሉም ሰንበት ት/ቤቶች ይሰጣል።የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ወጥ በሆነ መልኩ በሁሉም አድባራት በተጠናከረ ሁኔታ እየተ...
27/03/2026

የ2018 ዓ.ም 1ኛ መንፈቅ ዓመት አጋማሽ ፈተና ቅዳሜና እሑድ በሁሉም ሰንበት ት/ቤቶች ይሰጣል።

የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ወጥ በሆነ መልኩ በሁሉም አድባራት በተጠናከረ ሁኔታ እየተሰጠ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት አጋማሽ (MID EXAM) መጋቢት 19 እና 20 ቀን 2018 ዓ.ም በጅማ ሀገረ ስብከት በሁሉም አጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች ይሰጣል።

@የጅማ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሚድያ

በጅማ ሀገረ ስብከት እየተሰጠ የሚገኘው የካህናት ስልጠና ዛሬ መጋቢት 21 በሁለተኛ ቀኑም እንደቀጠለ ነው።⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜⚜መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓ...
30/03/2025

በጅማ ሀገረ ስብከት እየተሰጠ የሚገኘው የካህናት ስልጠና ዛሬ መጋቢት 21 በሁለተኛ ቀኑም እንደቀጠለ ነው።

⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜⚜

መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓ.ም (ጅማ፤ ኢትዮጵያ)
@የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን!!

የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን
አማራጭ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤ/ክ ድምፅ

✍️ የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/jimmadiocese

✍️ የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን የፌስቡክ ገጽ፦ https://www.facebook.com/jimmadiocese

✍️ ትክክለኛውን የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን የማኅበራዊ ድኅረ ገጽ ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ያጋሩ!

በጅማ ሀገረ ስብከት የካህናት ስልጠና ውሎ በፎቶ !
29/03/2025

በጅማ ሀገረ ስብከት የካህናት ስልጠና ውሎ በፎቶ !

Address

Jimma

Telephone

+251993931940

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጅማ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሚድያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share