Ethiopian Catholic Church Vicariate of Jimma Bonga

Ethiopian Catholic Church Vicariate of Jimma Bonga Catholic Church Vicariate of Jimma -Bonga,Ethiopia

የሮማ ሊቃነ ርዕሰ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የ71ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን እያከበሩ ናቸው፡፡ሊዮ 14ተኛ በአመሪካ እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር  በ19 55 በአሜሪካ ቺካጎ ተወለዱ፡፡በላቲን አሜሪካ...
14/09/2026

የሮማ ሊቃነ ርዕሰ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የ71ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን እያከበሩ ናቸው፡፡

ሊዮ 14ተኛ በአመሪካ እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር በ19 55 በአሜሪካ ቺካጎ ተወለዱ፡፡

በላቲን አሜሪካዋ ፔሩ በተለያዩ አከባቢዎች አገልግለዋል፡፡

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፖፕ ፍራንሲስ ከዚህ ዓለም በድካም ማረፍን ተከትሎ በአለም የካቶሊክ ርዕሰ ሊቀቃነ ጳጳሳት በመሆን እያገለገሉ ናቸው፡፡

በዚህም መስከረም 14 የሊዮ 14ኛ ልደት በዓል ይከበራል።

መልካም ልደት ፈጣሪ የአገልግሎት ዘመናቸውን ይባርክ፡፡

12/09/2026

top fans! Betelihem Imito Beyene Balgo Bitre Assefa Teka Tariku Zinaro, Yosef Petros Yohannes Wube Tikur Sew Wolde Yohannes Gebre Selamneh Bahiri Muluken Demissie Gebremichael Buze Ye Kaffa Katolik Belay Gebreyohanis Deneke Zewude Ango Gebreyohannes Mati YE Inatu Agegnehu Alemu Fikire Yohannes Abraham Adisu Beli Ye B Liji ወዳጆ ወርቁ Melaku Yasin Ella Ella Girma Asfaw Éťhíø Ƙāffa Mark Ye Catho Tadele Tekle Gebre Amerku Yeuma Amerku Yeuma Tekalign Ango Ŷè CaTho Lij Asche Jeses Man Asisho Man Shumiye Shumiye Catho Lij Niguse Wly Ejigayehu Gezahagn Mesifn Mengesha

የ2019 አዲስ ዓመት   #በቦንጋ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን በደማቅ ሁነታ ተከብሯል። #በአዲስ ዓመት 28 ታዳጊዎች ቅዱስ ቁርባን ተቀብለዋል። #በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጅማ-ቦን...
11/09/2026

የ2019 አዲስ ዓመት #በቦንጋ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን በደማቅ ሁነታ ተከብሯል።

#በአዲስ ዓመት 28 ታዳጊዎች ቅዱስ ቁርባን ተቀብለዋል።

#በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጅማ-ቦንጋ ሀገረስብከት ቦንጋ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አዲስ ዓመት በዓል በደማቅ ሁነታ ተከብሯል።

ዕለቱን ስርዓተ ቅዳሴ የቁምስናው ቆሞስ ክቡር አባ #ሉቃስ፣ ክቡር አባ #ግሩም ተስፋዬ እና አባ #ጴጥሮስ #ከኢየሱሳዊያን #አሪዮ ካቶሊክ ትምህርት ተቋም በጋራ መርተዋል።

ለበዓሉም የእንኳን አደረሳችሁ አደረሰን መልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

አዲሱ ዓመት የሰላም፣የፍቅር እና ለሀገራችን በጎ የሚሆንበት እንድሆን ጸሎት ተደርጓል።

አዲሱን ዓመት ልዩ የሚያደርገው 28 ታዳጊዎች ምስጢሬ ቁርባን ትምህርት አጠናቀው የተቀበሉበት ቀን በመሆኑ ከጥምቀት ቀጥሎ ትልቅ የቤተክርስቲያን ምስጢር መቀበላቸው በትልቅ የመንፈስ ጥንካሬ እንዳያድጉ ያስችላቸዋል።

ለህጻናት ፣ለወላጆች እና ለቤተክርስቲያን ትልቅ ደስታን የፈጠረ ሁኗል።

አዲሱን ዓመትም የቁምስናው ወጣቶች እና ታዳጊዎች በዝማሬ ዕለቱን አድምቀውታል።

በድጋሚ እንኳን አደረሰን፤እንኳን አደረሳችሁ። መልካም አዲስ ዓመት።

11/09/2026

በ2018 አመተ ምህረት በጎ ተግባራትን በማከናወን አሳልፈናል የሚሉት የእምነቱ ተከታዮች 2019 አመተ ምህ...

መስከረም 1/2019 በጅማ-ልደታ ማርያም ካቴድራል ምስጢሬ ቁርባን የተቀበሉ ህጻናት በፎቶ📷📷📷📷📷📷
11/09/2026

መስከረም 1/2019 በጅማ-ልደታ ማርያም ካቴድራል ምስጢሬ ቁርባን የተቀበሉ ህጻናት በፎቶ
📷📷📷📷📷📷

የ2019 አዲስ ዓመት ክብረበዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጅማ-ቦንጋ ሀገረስብከት ቦንጋ ጋጫ-ካራ ቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን ተከብሮ ውሏል።የዕለቱን ስርዓተ ቅዳሴ የመሩት የቁምስ...
11/09/2026

የ2019 አዲስ ዓመት ክብረበዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጅማ-ቦንጋ ሀገረስብከት ቦንጋ ጋጫ-ካራ ቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን ተከብሮ ውሏል።

የዕለቱን ስርዓተ ቅዳሴ የመሩት የቁምስናው ቆሞስ ክቡር አባ ብርሃነ ኢየሱስ ታዬ ናቸው።

ለመላው ካቶሊካዊያን ዮ እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል።

በድጋሚ እንኳን አደረሰን፤እንኳን አደረሳችሁ።

የ2019 አዲስ ዓመት ክብረበዓል በኢትዮጰያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ጅማ ቦንጋ ሀገረስብከት  በጅማ ልደታ ማሪያም ካቴድራል በደማቅ ሁነታ ተከብሮ ዋለ።መስከረም 1/2019 ፡-(ጅ ቦ ሀ )...
11/09/2026

የ2019 አዲስ ዓመት ክብረበዓል በኢትዮጰያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ጅማ ቦንጋ ሀገረስብከት በጅማ ልደታ ማሪያም ካቴድራል በደማቅ ሁነታ ተከብሮ ዋለ።

መስከረም 1/2019 ፡-(ጅ ቦ ሀ )

የ2019 አዲስ ዓመት ክብረበዓል በኢትዮጰያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ጅማ ቦንጋ ሀገረስብከት በጅማ ልደታ ማሪያም ካቴድራል በደማቅ ሁነታ ተከብሮ ዋለ።

በዕለቱ 9 ህጻናት ቅዱስ ቁርባን ተቀብለዋል።

ይህም ለህጻናት፣ ለቤተክርስቲያን እና ለወላጆች ትልቅ የቤተክርስቲያን ምስጢር መሆኑ በአዲስ ዓመት ትልቅ ደስታ የፈጠረ ሁኗል፡፡

የዕለቱን ስርዓተ ቅዳሴ የመሩት የጅማ-ቦንጋ ሀገረስብከት አቡኑ እንደራሴ ክቡር አባ ሳሙኤል ዮሐንስ እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አዲሱን ዓመት ስንቀበል መተግበር ስላለን ክርስቲያናዊ ግዴታዎች ላይም በወንጌል ቃል አሰደግፈው አስተምረዋል።

“አዲስ ልብ፣ አዲስ ተስፋ”
ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ በክርስቶስ፣
የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት ስናከበር፣ በሦስት ነገሮች ወደ እግዚአብሔር እንቀርባለን፤ በምስጋና፣ በተስፋ እና በጸሎት።
በመጀመሪያ፣ ባለፈው ዓመት ሁሉ ስለጠበቀንና ስለረዳን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን።
ያለፈው ዓመት ለብዙዎቻችን ቀላል አልነበረም። በአገራችን ግጭት፣ የሰው ሕይወት መጥፋት፣ መፈናቀል፣ ፍርሃት፣ ድህነትና እርግጠኛ ያልሆነ ሁኔታ ችግሮች ነበሩ። ብዙ ቤተሰቦች ተሰቃይተዋል፤ ብዙ ልቦችም ቆስለዋል።
ነገር ግን በእነዚህ ችግሮች መካከል እግዚአብሔር አልተወንም። ምሕረቱ አጽንቶናል፣ ጥበቃው ከእኛ ጋር ሆኗል፣ ፍቅሩም እስከዛሬ አድርሶናል።
ስለዚህ በዚህ አዲስ ዓመት መጀመሪያ ቃላችን፦
“አቤቱ፣ ስለምሕረትህና ስለጥበቃህ እናመሰግንሃለን” ይሁን።

1. እግዚአብሔር እንደገና እንድንጀምር ይጠራናል ኢሳይያስ እንዲህ ይላል፦ «“ማዳኔም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ እንዲደርስ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ።” (ኢሳይያስ 49፥6)»
አዲስ ዓመት ማለት የዘመን ቁጥር ብቻ መቀየር አይደለም። እግዚአብሔር እንደገና እንድንጀምር የሚሰጠን እድል ነው፡፡ ምናልባት ባለፈው ዓመት በልባችን ቁጣ፣ ቅሬታ፣ መከፋት፣ መለያየት ወይም ቁስል ተሸክመን መጥተን ይሆናል። ዛሬ ግን እግዚአብሔር፦ “ተስፋ አትቁረጥ፤ እንደገና ጀምር” ይለናል። ያለፈውን መመለስና ማስተካከል አንችልም፤ ነገር ግን ዛሬንና ነገን በእግዚአብሔር ጸጋ በተሻለ መንገድ መኖር እንችላለን። ስለዚህ ይህ አዲስ ዓመት አዲስ ልብና የታደሰ አስተሳሰብ የምንቀበልበት ዓመት ይሁን።

2. በግጭት ለተጎዳች አገር የሰላም መሣሪያዎች እንሁን፡ ዛሬ አዲስ ዓመትን በደስታ ስናከብር፣ በአገራችን ያለውን መከራ መዘንጋት የለብንም። ብዙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሰላምን ይናፍቃሉ። የጥላቻ እና የበቀል ዑደት መቆም አለበት። ግፍና ጥቃት በሕይወት ላይ የሚያመጣው መከራ መቆም አለበት። ይህን እንበል፦ “ጥላቻ በቃ! በቀል በቃ! ዓመፅ በቃ! ውይይትን እንምረጥ። ዕርቅን እንምረጥ። ሕይወትን እንምረጥ።”
ሰላም የሚጀምረው በመንግሥት ቢሮ ወይም በፖለቲካ ውይይት ብቻ አይደለም። ሰላም የሚጀምረው በሰው ልብ በእኛ በእያንዳችን ልብ ነው።
በቤተሰባችን፣ በሰፈራችን፣ በቁምስናችን፣ በማኅበረሰባችን እና ከተለያዩ ብሔርና ሃይማኖት ወንድሞቻችን ጋር ሰላምን እናስቀድም። ሰላማዊት ኢትዮጵያን ከፈለግን፣ መጀመሪያ ሰላማዊ ልብ እንዲኖረን እግዚአብሔርን እንጠይቅ።

3. ይህ ዓመት የፍቅር ዓመት ይሁን፡ የጥላቻ ትልቁ መልስ ፍቅር ነው። በዚህ አዲስ ዓመት ለድሆች፣ ለተፈናቃዮች፣ ለአረጋውያን፣ ለታመሙ፣ ለመበለቶች፣ ለወላጅ አልባ ልጆች እና በግጭት ሁሉን ላጡ ቤተሰቦች ልዩ ፍቅርና እንክብካቤ እናሳይ። አንዳንድ ጊዜ፦ “አገሬን ለመቀየር እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ?” ብለን እንጠይቃለን። ምናልባት መላዋን አገር መቀየር አንችልም። ነገር ግን የአንድን ሰው ሕይወት በፍቅር ማሻሻል እንችላለን። በጥሩ ቃል፣ በይቅርታ፣ ያለንን ነገር በመካፈል፣ የተሰቃየን በመጠየቅ እና የተቸገረንን በመርዳት የእግዚአብሔርን ፍቅር ልንገልጽ እንችላለን። ትንሽ የፍቅር ሥራ ታላቁ ጌታ እግዚአብሔር ከኛ ጋር የመሆኑ ምልክት ነውና።

4. ደስታችንን እንመልስ በወንጌል ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጃቸው ዮሐንስ ሲወለድ በታላቅ ደስታ ተሞሉ። ዘመዶቻቸውና ጎረቤቶቻቸውም ከእነርሱ ጋር ደስ አላቸው። ዛሬም እኛ ደስታ እንፈልጋለን። ክርስቲያናዊ ደስታ ማለት ምንም ችግር እንደሌለ ማስመሰል አይደለም። በመከራ መካከልም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዳለ ማመን ነው። ጨለማ የመጨረሻው ቃል አይደለም። እግዚአብሔር አሁንም እየሠራ ነው። ከመከራ ሕይወትን፣ ከመለያየት ዕርቅን፣ ከተስፋ መቁረጥ ተስፋን ማምጣት ይችላል። ስለዚህ የአገራችን ችግር እና ፈተና ተስፋችንን እንዲያደበዝዝ እና እንዲያጠፋ አንፍቀድ።

5. እያንዳንዳችን እግዚአብሔር የሚሰጠን ተልእኮ አለ፡ ዮሐንስ መጥምቁ ለራሱ ብቻ አልኖረም። እግዚአብሔር ለእርሱ ልዩ ተልእኮ ነበረው። ኢሳይያስም የእግዚአብሔር ባሪያ ለአሕዛብ ብርሃን እንዲሆን ተጠርቶ እንደነበር ይነግረናል። እኛም እንዲሁ ተጠርተናል። ተስፋን፣ ሰላምን፣ ፍቅርንና ደስታን ወደ ሌሎች ሰዎች ለማምጣት ተጠርተናል። በዚህ አዲስ ዓመት እያንዳንዳችን ራሳችንን እንጠይቅ፦ እግዚአብሔር ሰላምን ወዴት እንዳመጣ ይፈልጋል? ይቅር ማለት የሚገባኝ ማን ነው? መርዳት የሚገባኝ ማን ነው? ተስፋ ለሌለው ሰው ተስፋ እንዴት ልሆን እችላለሁ? ለአንድ ሰው ብርሃን እንዴት ልሆን እችላለሁ? የአዲሱ ዓመት ጸሎታችን ወድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ይህንን አዲስ ዓመት አገራችንን፣ ቤተሰቦቻችንንና የወደፊታችንን በምሕረቱ እጅ እናስገባ። ባለፈው ዓመት ስለጠበቀን እግዚአብሔርን እናመስግን። የሕዝባችንን ቁስል እንዲፈውስ እንጸልይ።
ጦርነት ባለበት ሰላም፣
መለያየት ባለበት ዕርቅ፣
ጥላቻ ባለበት ፍቅር፣
ተስፋ መቁረጥ ባለበት ተስፋ፣
ሐዘን ባለበት ደስታ እንዲሰጥ እንለምነው።
ለመሪዎቻችን ጥበብና ድፍረት ስጥ፤ ለሕዝባችን ሰላምና አንድነት ስጥ። ልጆቻችንንና ወጣቶቻችንን ጠብቅ፤ ተስፋ ያለው የወደፊት ሕይወትም ስጣቸው። ከሁሉም በላይ አዲስ ልብና የታደሰ አስተሳሰብ ስጠን። የሰላምህ፣ የፍቅርህና የብርሃንህ መሣሪያዎች እንድንሆን እርዳን። “አቤቱ፣ ባለፈው ዓመት ስለምሕረትህና ስለጥበቃህ እናመሰግንሃለን። በአዲሱ ዓመት ከእኛ ጋር ሁን።ልባችንን አድስ። አስተሳሰባችንን አድስ።ቤተሰቦቻችንን አድስ።አገራችንን አድስ። የሰላምህም መሣሪያዎች አድርገን።”
እግዚአብሔር አዲሱን ዓመት ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቿ የተስፋ፣ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ ዓመት ያድርግልን።
መልካም አዲስ ዓመት!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ። አሜን።

መልካም አዲስ ዓመት ይሁንል፡፡

የአዲስ ዓመት መልእክት ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን  #ጅማ-ቦንጋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት“እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤ ፊቱንም ያብራልህ፥ ይማርህም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አ...
10/09/2026

የአዲስ ዓመት መልእክት ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን #ጅማ-ቦንጋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት

“እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤ ፊቱንም ያብራልህ፥ ይማርህም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጥህ።”
— ዘኁልቍ 6፥24–26

በጅማ-ቦንጋ ሀገረ ስብከት የምታገለግሉ ክቡራን ካህናት፣ የተወደዳችሁ ምእመናንና የተለያዩ አገልግሎቶች ተሳታፊዎች፤

እንኳን #ለ2019 አዲሱ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!

አዲሱ ዓመት ለሀገረ ስብከታችን ካህናትና ምእመናን፣ ለቤተሰቦቻችሁና ለምትወዷቸው ሁሉ የእምነት፣ የተስፋ፣ የፍቅርና የበረከት ዓመት ይሁን።

በመላው ዓለምና በአገራችን ላይ ሰላምና ስምምነት፣ እርቅና ወንድማማችነት እንዲሰፍን፤ ልዩነቶቻችንን በፍቅርና በመቻቻል በማስተናገድ በሰላም አብረን የምንኖርበት ዓመት እንዲሆን እንመኛለን።

እግዚአብሔር ካህናቱን በጸጋው ያጽና፣ ምእመናኑን በእምነት ያበርታ፣ ሀገራችንን በሰላሙ ይጠብቅ፣ ለመላው ዓለምም ሰላምን ያድል።

መልካም፣ የተባረከና የሰላም አዲስ ዓመት!

#ጳጉሜ 5/2018

ጅማ-ቦንጋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት

Address

Jimma

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Catholic Church Vicariate of Jimma Bonga posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Ethiopian Catholic Church Vicariate of Jimma Bonga:

Shortcuts

Share